🕋 አስር ቁም ነገሮች ስለ ዙል ሒጃ አስር ቀናቶች
=========================
// የተለየ ደረጃ እንዳላቸው ሚጠቁሙ ማስረጃዎች//
❶ በነዚህ አስር ለሊቶች አላህ ቁርአን ላይ ምሎባቸዋል።
{ﻭَﺍﻟْﻔَﺠْﺮِ . ﻭَﻟَﻴَﺎﻝٍ ﻋَﺸْﺮٍ } [ ﺍﻟﻔﺠﺮ 2-1: ]
(( በንጋት እምላለ ⓵ በአስሩም ለሊቶች ⓶))
{ሱረት ፈጅር 1-2}
ኢብን ከሲር በዚህ የቁርአን አየቀፅ የተፈለገው አስሩ የዙል ሒጃ እንደሆነ ይጠቅሳል። ይህንን ደግሞ ኢብን አባስ: ኢብን ዙበይር: ሙጃሒድ እና ሌሎችም ብለውታል።
❷ በሀዲስም እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
« ﻣﺎ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻲ ﺃﻳّﺎﻡ ﺃﻓﻀﻞ ﻓﻲ ﻫﺬﻩ ﺍﻟﻌﺸﺮﺓ »
>
ጅሀድም ቢሆን? ብለው ሰሀቦች ጠየቋቸው።
አሏቸው። {ቡኻሪ ዘግቦታል}
❸ አላህ እንዲህ ማለቱ
ﻭَﻳَﺬْﻛُﺮُﻭﺍ ﺍﺳْﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓِﻲ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﻣَّﻌْﻠُﻮﻣَﺎﺕٍ { [ ﺍﻟﺤﺞ 28: ]
(( አላህንም በታወቁት ግዜያቶች ሊያወሱ)) {ሀጅ 28}
ኢብን አባስ አሱሩ ቀናቶች ብሎ ፈስሮታል
❹ በሌላ ሀዲስም እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
« ﻣﺎﻣﻦ ﺃﻳّﺎﻡ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ ﻭﻻ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻴﻪ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﻫﺬﻩ ﺍﻷﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﺘﻬﻠﻴﻞ ﻭﺍﻟﺘﻜﺒﻴﺮ ﻭﺍﻟﺘﺤﻤﻴﺪ » . ( ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻄﺒﺮﺍﻧﻲ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﻌﺠﻢ ﺍﻟﻜﺒﻴﺮ )
> {ኢማሙ ጠበራኒ ዘግበውታል}
➠ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል
"ያ ግልፅ የሚሆነው አስሩ የዙልሒጃ ቀናቶች ከሌሎች የተለዩበት ምክንያት የኢባዳ እናቶች ስለ ተሰበሰቡበት ነው እነሱም #ሰላት_ፆም_ሰደቃ_ሀጅ ይህ በሌላ ግዜ አይመጣም።
========================
// በነዚህ አስር ቀናቶች የሚወደድ ተግባር//
--------- ❺ ሰላት
_ዋጅብ ሰላት ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ መልኩ ይበልጥ መጠናከር ሱና ሰላትንም ማብዛት ይወደዳል።
_ምክንያቱም ሰላት ከትልልቆቹ መልካም ስራዎች መሐከል ነው በነዚህ ቀናቶች ደግሞ መልካም ስራ አብዙ ተብሏል
-------- ❻ ፆም
____ መልካም ስራ ከሚለው ውስጥ ፆምም ስለሚገባ። የአላህ መልእክተኛም ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች ይፆሙ እንደነበር የመጣ ሐዲስ ስላለ
_ኢማመ ነወዊ ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች መፆም የጠነከረ ሱና መሆኑን ይገልፃሉ
---------- ❼ ተክቢራን ማብዛት
____ ከላይ ተራ ቁጥር ❹ ላይ የጠቀስነው ሀዲስ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው። ኢብን ኡመርና አቡ ሑረይራ ወደ ሱቅ ወጥተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር ሰዎችም የነሱን ተክቢራ ሰምተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።
ተክቢራውን ጮክ ብሎ ማለቱ ይወደዳል
------------ ❽ ከሰሀቦች እና ታብእዮች የመጡ የተክቢራ አይነቶች
◅ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ ﻛﺒﻴﺮًﺍ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .
---------❾ የአረፍ ፆም
____የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያስምር ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ መጥቷል
ﻗﺎﻝ ﻋﻦ ﺻﻮﻡ ﻳﻮﻡ ﻋﺮﻓﺔ : « ﺃﺣﺘﺴﺐ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻥ ﻳﻜﻔﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﻗﺒﻠﻪ ﻭﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﺑﻌﺪﻩ » ( ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ) .
---------❿ ሰደቃ
_ መልካም ስራ በነዚህ ቀናቶች የተወደደ ነው ተብሏል። ሰደቃም ደግሞ ከመልካም ስራዎች ውስጥ ነው።
@heppymuslim29