እናስተነትን ዘንድ
ክፍል ሶስት
እነሆ አላህ በስሟ ቁርአንን ምእራፍ የተሰየመላትን ሌላኘዋን በራሪ ነፍሳት የሆነችውን ንብን በዛሬው 'እናስተነን ዘንድ' ፕሮግራማችን ልናነሳ ወደድን።
ብዙወቻችን ስለ ንቦች እናውቃለን። ማራቸውን ማን ያልበላ አለ☺️።
ንቦች ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸው ናቸው። ከነዛ ውስጥ ግን የማር ንቦች ዝርያ ሰባት ወይም ከዛ በላይ ናቸው። እንዲህ ያልኳችሁ 'ጢንዚዛ' በመባል እሚታወቁትም የንብ ዝርያ ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ነው።
ንቦች ሶስት አይነት መደብ አላቸው። ሰራተኛ፣ ንግስቷ እና ድሮን ተብለው እሚታወቁት ናቸው።
እስኪ አሪፍ ጥያቄወችን እናንሳ
ንቦች ለምንድን ነው ማር እሚያመርቱት?!
እኔ ልንገራችሁ ንቦች የክረምት ጊዜ ወይም አበቦች እማይገኙበት ጊዜ ሲመጣ እሚመገቡት እንዳያጡ ነው እሚያከማቹት። ማር ለንቦች ምርጥ የምግብ ምንጭ ይሆንላቸዋል። ማር በ nutreient የበለፀገ ከመሆኑ በተጨማሪ ብዙ ስኳር ስለሚኖረው ሀይል ሰጭ ምግብ ሁኖ እንዲያገለግላቸው ነው።
ሰራተኛ ንቦች በጠቅላላ ሴቶች ናቸው። ደሮን ተብለው እሚታወቁት ደግሞ ወንድ ናቸው። ስራቸው ንግስቲቱን መገናኘት ብቻ ነው። ግን ንግስቲቱም ከሀዲ ናትና ከግንኙነት በኋላ ልትገድላቸው ትችላለች።
እነዚህ ወንድ ንቦች አይናደፉም። ሰራተኛ ንቦች ደግሞ ሴት ቢሆንም መራባት አይችሉም። መራባት እምትችለው ንግስቲቱ ብቻ ናት። ንግስቲቱ ለቀናት ማየት የተሳናት ሁና ልታሳልፍ ትችላለች።ሰራተኛ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ይሞታሉ።
አሁንም እንጠይቅዎ ንቦች ከተናደፉ በኋላ ለምን ትሞታሉ?!
መልሱ ቀላል ነው እሚናደፉበት ሰንኮፋቸው በመቀመጫቸው አካባቢ ነው ያለ። በሚናደፉበት ጊዜ ሰንኮፉ ሆዳቸው ውስጥ ያለውንም ነገር ይዞባቸው ይወጣል። ያ ማለት እሚናደፉበት ሰንኮፍ ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ለማዋሀድ እሚጠቅማቸው እና ሆዳቸው ውስጥ ያለውን ነገር አብሮ ስለሚያወጣው መትረፍ አይችሉም።
ንቦች እሚያዘጋጁት ማር ብዙ የጤና ጥቅሞች አሉ። ከነዛ ውስጥ health line ያስቀመጣቸውን እንንገራችሁ አንቲኦክሲዳንት፣ባክተሪያን እና ፈንገስን ለማጥፋት፣ ቁስልን ለማከም፣ በሽታን የመከላከል አቅም ማሳደግ፣ ለአንጀት ጤንነት እና ለውህደት ፣ እንዲሁም የተዘጋ ጉሮሮን ለመጥረግ ይጠቅማል።
ግን በቅርብ ደግሞ የ አውስትራሊያ ዶክተሮች ከንብ መርዝ አዲስ ግኝት አግኝተናል ይላሉ።
BBC እንደዘገበው ከሆነ ተመራማሪወች ከንብ ሰንኮፍ የጡት ካንሰር ሴሎችን እንደሚገድል አስታውቀዋል። ምን ይሄ ብቻ ሜላኖዋ ተብሎ እሚታወቀውን ካንሰርም እንደሚከላከል አስታውቀዋል።
ሰራተኛ ንቦች በሚናደፉብት ጊዜ ሰውነታችን ላይ ያብጣል። ግን ሊገለን ይችል ይሆን?!
አንድ የንብ መርዝ ሊገለን አይችልም ግን እስከ አንድ ሽህ የሚደርሱ ንቦች ከተነደፍን ግን መሞታችን አይቀሬ ነው።
@ibnuhasent.me/ibnuhasen