Фильтр публикаций


የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የበጎ-ፈቃድ ስራ ተሳትፎ
-------
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት መኖ ሳር አጨዳ በጎ ፈቃድ ሥራ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በበጎ ፈቃድ ሥራው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም የአውት ሶርስ ሠራተኞች ከታኅሳስ 9 እስከ 18/2017 ዓ.ም ድረስ በወጣው ፕሮግራም መሰረት የሳር አጫዳ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ የታጨደው ሳር በዩኒቨርሲቲው እየተካሄደ ላለው ዘመናዊ የወተት እርባታ ላሞች የእንስሳት መኖ ግብዓትነት እንደሚያገለግልም ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከወዲሁ በበጎ ፈቃድ ሥራው እየተሳተፉ ላሉ ሠራተኞች ምስጋና ያቀርባል፡፡

ታኅሳስ 10/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ


የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ አጀንዳዎችን አጸደቀ፡፡
--------
ታኅሳስ 8/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ አጀንዳዎችን ገምግሞ አጽድቋል።
ለሴኔቱ የቀረቡ አጀንዳዎች
1. የተሻሻለውን ሴኔት ሌጅሽሌሽን ማጽደቅ
2. PhD in Applied linguistic ስርዓተ ትምህርት (curriculum) ማጽደቅ የሚሉ ሲሆን ሴኔቱ በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ የቀረቡትን አጀንዳዎች አጽድቋል፡፡
ቀደም ሲል ተግባራዊ ሲደረግ የነበረው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሌጅሽሌሽን በአዲሱ መዋቅር መሰረት አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ማድረግ በማስፈለጉ እና እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ አንጻር የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችን ልምድ መነሻ በማድረግ የተሻሻለ ሴኔት ሌጅሽሌሽን ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡ ሰኔቱም ተሻሽሎ በቀረበው ሌጅስሌሽን ላይ በሰፊው በመወያየት እና ግብዓቶችን በመጨመር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ሁለተኛው አጀኝዳ የ3ኛ ዲግሪ ስርዓተ ትምህርት (Curriculum ) ማጽደቅ ሲሆን ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው ከሚሰጡ ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች (PhD in Developmental psychology and Teaching English as a foreign language) በተጨማሪ PhD in Applied linguistics ለመጀመር የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ሂደቱም አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች የሚባሉት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንዲሁም የውስጥ እና የውጭ ግምገማዎች የተካሄዱበት መሆኑም ተገልጿል። ሴኔቱም የቀረበውን ስርዓተ ትምህርት አግባብነት በመገምገም PhD in Applied Linguistics ትምህርት እንዲጀመር በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡


በእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ጉብኝት እና የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እና ሆስፒታሉ ያለበትን ሁኔታ በመጎብኘት የምክክር መድረክ አካሂደዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የጉብኝቱ ዓላማ እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል እየሰጠ ያለውን አጠቃላይ አገልግሎት እና የስራ እንቅስቃሴ፣ የመሰረተ ልማት፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች ግብዓቶችን ለማሟላት እንዲሁም ያሉበትን ሁኔታ ለመለየት እና በቀጣይ መፍትሄ ለማስቀመጥ የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና ዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሁሉንም ህክምናዎች እንዲሰጥ ለማድረግ ከ19 በላይ ስፔሻሊቲ እና ጠቅላለ ሀኪሞችን በመቅጠር በማህበረሰብ አቀፍ ጤና ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል የዩኒቨርሲቲው አንድ አካል እንደሆነ አውስተው ሆስፒታሉ ያለበትን የግብዓት፣ የህክምና ቁሳቁስ (ሲቲ ስካንን ጨምሮ)፣ የመድሃኒት አቅርቦች ችግር ደረጃ በደረጃ እንዲፈታ ለማድረግ ከአጋር አካላት እና ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ችግሩን መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡   
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0yj6xYToNHM3D8Mg227JzWGLueKNeRgp5hLJz8fD1Nhn1L7sbcjzxT98uQf64oZ4Xl/?app=fbl


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተልዕኮዎች ላይ ተመስርቶ የተላለፈ ዘጋቢ ፊልም
ለተጨማሪ መረጃዎች
Telegram-https://t.me/injiuniversity
Website- https://www.inu.edu.et/
Facebook-https://www.facebook. Com/injibaruni
Email- injibarau@gmail.com
linkedin.com/in injibara-university-12b279166/
Institution Email -injibarauniversity@inu.edu.et
Twitter- (https://twitter.com/injibara_Inu/)
YouTube-https://www.youtube.com/c/injibarauniversity
Explore Your Creative Potential.


የሀዘን መግለጫ
------
ተማሪ ሌሊሳ ጌታቸው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የ3ኛ አመት በ lifelong learning and community development ትምህርት ክፍል በመማር የነበረ ሲሆን ባጋጠመው ህመም ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ሄዶ ህክምና ቢያደርግም በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተማሪ ሌሊሳ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።

ኅዳር 26/2017 ዓ.ም



Показано 6 последних публикаций.