H̲a̲l̲a̲l̲ ̲l̲i̲v̲i̲n̲g̲ ̲ᶠᵒʰᵃᵐ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Психология


...................꧁﷽꧂.....................

ኢስላማዊ_መረጃዎች
ኢስላማዊ_ታሪኮች
አጫጭር_ዳዕዋዎች እና
የተለያዩ_ሀዲሶችን_ያገኛሉ
አዝናኝ ቀልዶች ☺️
owner 👉 #HAMZA (FOHAM)
ለማንኛውም አስታየት @foham2 አናግሩኝ
ከተሳሳትኩም አርሙኝ✌️ @foham2

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Психология
Статистика
Фильтр публикаций


.
“እጁ አመድ አፋሽ ይሁን ረመዳንን አገኝቶ ወንጀሉ ሳይማርለት ያለፈው።”

ረሱል (ﷺ)😍


﴿وَاعفُ عَنّا وَاغفِر لَنا وَارحَمنا أَنتَ مَولانا﴾


በቁመት ዱአ ወቅት

إنه لا يذل من واليت , ولا يعز من عاديت تباركت ربنا و تعاليت.

ሲባል ዝም ይባላል፡ ካልሆነም  ሱብሃነሏህ ይባላል እንጂ አሚን አይባልም

ምክነያቱም አሏህ ወዳጁን ያደረገው የበታች እንዳይሆን|እንዳይዋረድ፡ ጠላት ያደረገውን ደግሞ የበላይ እንዳይሆን| ልቅና እንዳያገኝ፡

ለአሏህ ዱዓእ እንደ ማድረግ ስለሆነ!

  ሸይኽ ሷሊህ ዑሰይሚይ አሏህ ይጠብቃቸውና።


ለምንድን ነው ከዙህር ጀምሮ የምታኮርፉትና የምትኮሳተሩት¿
ኧረ! ተው እናንተ ፈገግና ነቃ በሉ። አታስፎግሯ¡


.
የፆመኞች ይሄ ሁሉ ኢባዳ ጌታዬ አንተኑ ፍራቻ ነዉና ባሮችህን ተቀበላቸው፣
እዘንላቸው፣ማራቸው
ጀነትህንም ወፍቃቸው 🥰

@Islamisthis


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሱሁር ተነስቶ መብላት ሚከብደው 😭😁

@Islamisthis


{  رَبِّ إِنِّی لِمَاۤ أَنزَلۡتَ إِلَیَّ مِنۡ خَیۡرࣲ فَقِیرࣱ }

ላጤያንስ ይቺን ዱዓ አብዙ ፈጣን ነበረች አሉ ለነቢ ሙሳ 😁


members በቻልኩት መጠን ላግዛቹ እየሞከርኩ ነው 😭🍿


@Islamisthis || 𝕗𝕠𝕙𝕒𝕞♡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


القران الكريم،،،،،،،،،،🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አንድ ሰው ሲያፈጥር የሚያደርገው ዱዓእ‼


ﻋﻨﺪ ﺍﻹﻓﻄﺎﺭ ﺗﻘﻮﻝ ﻣﺎ ﻛﺎﻥ ﻳﻘﻮﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﷺ ، ﻓﺈﻥ ﻣﻦ ﺳﻨﺘﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺃﻧﻪ ﻛﺎﻥ ﺇﺫﺍ ﺃﻓﻄﺮ ﻗﺎل ( ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ )
📚[ ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678)

👉በአማርኛ ሲነበብ፦
"ዘሃበ'ዝ-ዘመኡ ወብተለቲ-ል-ዑሩቁ ወሠ'ብ-በተል አጅሩ ኢንሻ አሏህ"
ትርጉሙም፦" ጥም ተወገደ፣ ጎሮሮዎችም ረጠቡ፣ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።" ማለት ነው።


•••እናስተውል

ኢብኑ አል ጀውዚይ رحمه الله

በአላህ ይሁንብኝ ቀብር ውስጥ ያሉ
ሙታኖች ተመኙ እስቲ ቢባሉ

የረመዳን አንዲትን ቀን በተመኙ ነበር
ይላሉ።🌷 "


በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️
========================
1) አንድ ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16  መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20  ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20  ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

አላህ ያግዘን።
||
Murad Tadesse
May 4, 2019 G.C


የዕለት ዱዓ

ረመዳን 1

(ربنا اغفر لي ولوالدي وللمؤمنين يوم يقوم الحساب
)

(ጌታችን ሆይ : ለእኔም ለወላጆችም ለምዕመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት ቀን ማር)


የረመዿን የመጀመርያ ቀን ሱሁር ስጋ መብላት ግዴታ ነዋ😌


تسحروا فإن في السحور بركة😊


«ሰሑርን» በተመለከተ ጥቂት ጥቆማዎች‼️
===============================
✍️ ሰሑር ማለት በጾም ወቅት ትክክለኛው ጎህ ከመውጣቱ በስተፊት በሌሊቱ ክፍለ ግዜ ወደ ፈጅር አቅራቢያ የሚበላ ምግብ ነው።
ሰሑር ሱንና ነው። የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግብረውታል።
1️⃣ጥቅል ነጥቦች፥
✔️ አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«تسحروا فإن في السحور بركة!»
"ሰሑርን ተመገቡ፣ ሰሑር በመመገብ ውስጥ በረከት አለ።"

[ቡኻሪ፥ 1921
ሙስሊም፥ 1095]
✔️ በሌላ ሐዲሥም ከዐምር ኢብኒል ዓስ በተገኘ ዘገባ ላይ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፥
«فصل ما بين صيامنا وصيام أهل الكتاب أكلة السحر!»
"በኛ ጾምና በኪታብ ባለቤቶች ጾም መካከል ያለው ልዩነት፤ ሰሑርን መመገብ ነው።"

[ሙስሊም: 1096]
እኛ ስንጾም ሰሑር እንመገባለን፣ አህለል ኪታቦች (የሁዳዎችና ነሷራዎች) ግን አይመገቡም።
✔️ አነስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ እንዳለ አስተላልፈዋል፥
«تَسَحَّرْنَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ثُمَّ قَامَ إِلَى الصَّلاةِ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَ الأَذَانِ وَالسَّحُورِ قَالَ قَدْرُ خَمْسِينَ آيَةً!»
«ከነብዩ ﷺ ጋር ሰሑር ተመገብን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ!" አለ።
"በአዛንና በሰሑር መካከል ያለው ግዜ ስንት ይሆናል?" አልኩት! (አነስ ለዘይድ ነው የሚጠይቀው!)
(ዘይድም) ሃምሳ አንቀጽ (የሚያስቀራ ግዜ) ያክል! (ብሎ መለሰለት)»
[ቡኻሪ፥ 1821]
ይህ የሚያሳየው ሰሑርን ወደ ፈጅር ማዘግየቱ የሚወደድ መሆኑን ነው።
✔️ ዐብዱልሏህ ኢብኑል ሐሪሥ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
"ከነብዩ ﷺ ባልደረቦች መካከል አንዱ እንዲህ አለ፦
መልዕክተኛው ﷺ ሰሑር እየተመገቡ ሳለ ገብቼ ፥

«إنها بركة أعطاكم الله إياها؛ فلا تدعوه»
"እርሷ (ሰሑር) በረካ ናት (አለባት)። እርሷን አላህ ሰጥቷችኋል፣ እንዳትተውት።" አሉኝ አለ።

[ነሳኢይ ዘግበውታል።]
✔️ ሰልማነል ፋሪስ ረዲየልሏሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፥
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«البركة في ثلاثة: في الجماعة، والثريد، والسَّحور»
"በሶስት ነገሮች ውስጥ በረካ አለ፥ በጀመዓ፣ በሠርድ (የምግብ አይነት [ስጋና ዳቦ ቅይጥ])፣ በሰሑር።"

[ጦበራኒይ ዘግበውታል።]
✔️ አቢ ሰዒዲኒል ኹድሪይ ረዲየልሏሁ ዐንሱ ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
«السَّحور بركة؛ فلا تدعوه..!»
"ሰሑር በረካ ነው፣ እንዳትተውት።"
[አሕመድ ዘግበውታል።]
እንዲህም ብለዋል፥
«إن الله وملائكتة يصلون على المتسحّرين»
"አላህና መላእክቱ በሰሑር ተመጋቢዎች ላይ አክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ!" ]
[አሕመድ ዘግበውታል።]
*
2️⃣ሰሑርን ማዘግየት ይወደዳል!!
`````````````````````````````
ሰሑር ያልተመገበ ሰው ጾሙ ትክክል ነው አይበላሽም፣ ግን ሱንናው አምልጦታል።
✔️ ስለዚህ ጉዳይ አቡበከር ኺሷስ "አሕካሙል ቁርኣን፥ 1/265" ላይ አስፍረዋል።
*
«فالسنة السحور، ولكن ليس بواجب، من لم يتسحر فلا إثم عليه، لكن ترك السنة، فينبغي أن يتسحر ولو بقليل، ليس من اللازم أن يكون كثيراً، يتسحر بما تيسر ولو تمرات أو ما تيسر من أنواع الطعام في آخر الليل»
"ሱንናው ሰሑር መመገብ ነው። ነገር ግን ግደታ አይደለም። ሰሑር ያልተመገበ በርሱ ላይ ወንጀል የለበትም። ነገር ግን ሱንናን ትቷል። በትንሽ ነገርም ቢሆን ሰሑር ሊመገብ ይገባል። ብዙ መሆኑ ግድ የሚል አይደለም። በሌሊቱ መጨረሻ ላይ በገራለት ነገር በተምሮችም ሆነ በገራለት የምግብ አይነት ሰሑር ሊመገብ ይገባል።..."

[ኢብኑ ባዝ፥ ኑሩን ዓለ ደርብ]"
✔️ እናታችን ዓኢሻእ ረዲየልሏሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፥
«عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهَا أَنَّ بِلالا كَانَ يُؤَذِّنُ بِلَيْلٍ ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( كُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّى يُؤَذِّنَ ابْنُ أُمِّ مَكْتُومٍ ، فَإِنَّهُ لا يُؤَذِّنُ حَتَّى يَطْلُعَ الْفَجْرُ ) »
"ቢላል በሌሊት አዛን ያደርግ ነበር። ረሱልሏህ ﷺ እንዲህ አሉ፥ «ኢብኑ መክቱም (ዐብዱልሏህ) አዛን እስከሚል ድረስ ብሉ፣ ጠጡ፤ እርሱ ፈጅር ሳይወጣ አዛን አይልም።»"

[ቡኻሪ፥ 1919
ሙስሊም፥ 1092"
✔️ ኢማመ ነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፥
«اتَّفَقَ أَصْحَابُنَا وَغَيْرُهُمْ مِنْ الْعُلَمَاءِ عَلَى أَنَّ السَّحُورَ سُنَّةٌ , وَأَنَّ تَأْخِيرَهُ أَفْضَلُ ، وَدَلِيلُ ذَلِكَ كُلُّهُ الأَحَادِيثُ الصَّحِيحَةُ , وَلأَنَّ فِيهِمَا (يعني السحور وتأخيره) إعَانَةً عَلَى الصَّوْمِ , وَلأَنَّ فِيهِمَا مُخَالَفَةً لِلْكُفَّارِ...»
"ሰሑር ሱንና መሆኑንና እርሱን ማዘግየቱም በላጭ መሆኑን የኛ ባልደረቦቻችን (ሻፊዒይያዎች) እና ከዑለማዎች ሌሎችም ተስማምተዋል።
ይህንንም ሁሉም ትክክለኛ ሐዲሦች ያመላክታሉ።
በነርሱም ውስጥ (ሰሑር በመገብና በማዘግየቱ) ለጾሙ ይረዳል፣ በነርሱም ውስጥ ከሃዲያንን መቃረን አለበት።..."
[አል-መጅሙዕ፥ 6/406]
✔️ ለጂነቲ ዳኢማም ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቃ፣ በ10/284 ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልስ አስፍራለች።

ሸይኽ ኢብኑ ባዝም ተጠይቀው የመለሱት በመጅሙዐቱል ፈታዋ ኢብኑ ባዝ፥ 15/281 ላይ ይገኛል።
*
ጽሁፉ እንዳይረዝም ነው።
ዐብዱልሏህ ኢብኑ ጀብሪንም ተጠይቀው የመለሱት አለ።
አስፈላጊ ከሆነ ኮሜንት ላይ ከነ ትርጉሙ አሰፍረዋለሁ።

||
ወንድማችሁ፥ ሙራድ ታደሰ
==========

ረመዳን 1, 1440 ዓ.ሂ
|


ከፆም አርካኖች አንዱ ኒያ ነው። ነገ ለመፆም ዛሬ ለሊት ነይቶ ያላደረ ሰው ፆሙ ተቀባይነት የለውም።

ኒያ ማለት እፆማለሁ ብሎ በልብ ቁርጠኛ ውሳኔ መያዝ እንጂ በንግግር የሚደረግ ነገር አይደለም።
ለየትኛውም ዒባዳ ነወይቱ... ብሎ መናገር ቢድዓ ነውና።


የዛሬ የረመዿን የተራዊሕ ኢማሞች በሐረም!



Показано 20 последних публикаций.