©Legal details center© :የህግ ማብራሪያ ማዕከል©


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ይህ channel ለማንኛውም የፌደራል ና የክልል ህጎችን ማወቅ ና ማሳወቅ ለሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አገልግሎት ይሰጣል ።በዚህ ቻናል ውስ የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኙበታል። ለበለጠ መረጃ የ ዩቲዩብ ገጻችንን ይቀላቀላሉ 👇👇
youtube:https://www.youtube.com/@legaledetailscenter
Tik Tok:tiktok.com/@user2867965117502

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞🔞
ከ 18 አመት በታች ለሆናችሁ የተከለከለ ነው!

https://t.me/+loL_-JUohKhmZjJk
https://t.me/+loL_-JUohKhmZjJk
https://t.me/+loL_-JUohKhmZjJk


በቀን ከ 5000 ብር እና ከዚያ በላይ ስልክን 📱📱📱 በመጠቀም ብቻ ያለምን ክፍያ በ online ስራ መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ!!! የምትከፈሉት በ dollar 💸💸💸💸 ነው ስለ ስራው ማወቅና መስራት የምትፈልጉ @Abusha1945 በዚህ username አዋሩኝ

ያለው ቦታ ሊሞላ ስለሆነ አፍጥኑት 🔥!!!!!!!💸💸💸💸💸💸


እነዚህ ቻናሎች ከ18 አመት በላይ ለሆናችሁ ብቻ ነው 🔞

if you like watching 18+ videos #Join የሚለውን ይጫኑ 🫦❤️🔞

» https://t.me/TVerse?startapp=galaxy-00019956570003baee8e0000d5975e

» https://t.me/TVerse?startapp=galaxy-00019956570003baee8e0000d5975e


ለሀይማኖት ድምጽ እንሰጥ!

እነንቴስ ሚን ቲለላቹ?

👇👇👇👇

https://t.me/addlist/Zcae6t2LlkQyMDhk




እስኪ በዚህ ፍርድ ላይ አስተያየት ስጡበት

✔️
ከቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ጫማዎችን የሰረቀው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ


ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝ የተባለው ግለሰብ በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣው የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 669(3)ለ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ  የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡ በጉራጌ ዞን በምኁር አክሊል ወረዳ ሀዋርያት ከተማ ውስጥ ሰላም መንደር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኘው ሀዋርያት ፅርሀ ፅዮን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምቱ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ወንጀል ለመፈፀም እንደሚያመቸው በከተማው የተወሰነ  ማብራት ቆጣሪ ሄዶ ካጠፋ በኋላ የዘጠኝ ሰዎችን ጫማ ሰርቋል፡፡

ህዳር 21 ለሚከበረዉ ክብረ በዓል መጥተው ቤተ-መቅደስ በራፍ ጫማቸውን አውልቀው ቤተመቅደስ ከገቡ በኋላ ተከሳሽ በለበሰው ጃኬት ዘጠኝ ጫማ ሰርቆ ከቤተክርሰቲያኑ ሲወጣ በክትትል በቤተ-ክርስቲያን በር ላይ በፖሊስ የተያዘ በመሆኑ አስቦ በፈፀመዉ በከባድ ስርቆት በወረዳው የመጀመረያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሷል።ተከሳሽ የተከሰሰበት ተደራራቢ ክስ ከደረሰው በኋላ የእምነት ክህደት ቃሉ ሲጠየቅ ክሱ እንደማይቃወም ወንጀሉ መፈፀሙን በዝርዝር ያስረዳ በመሆኑ ባመነው መሰረት ጥፋተኛ መባሉን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በዚህም በመሰረት ችሎቱ ግራ ቀኙ ከተመለከተ በኋላ በቀን ታህሳስ 15 ቀን በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሹ ያርማል ሌላውንም ማህበረሰብ ይህን መሰል ወንጀል ከመፈፀም ያስተምራል በሚል በ18 ዓመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ኤልያስ ሰብለጋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
****


አንድ comment በአንድ ጫማ ሁለት አመት እስራት (9*2=18) ታስቦ ይሆናል😂😂 የሚል አይቻለሁ እስኪ እናንተ ሳትቀልዱ ያላችሁሂ አስተያየት ከ ተጠቀሰው አንቀፅ ጋር እያነፃፀራችሁ ፃፊ ።ተመሳሳይ አስተያዬት ከተፃፈ መልስ እንሰጥበታለን ።



አስተያየት ለመፃፍ ይሄን ግሩፕ ይጠሙ👇👇👇👇

http://t.me/Judge1234


መንግስት የግለሰብ መሬት ለሕዝብ ጥቅም የሚፈልግ ከሆነ ቀድሞ ተገቢውን ካሳ የመክፈልና ተተኪ መሬት
የመስጠት ግዴታ ያለበት ስለመሆኑ
የሕ/መ/ጉ/አ/ጉባኤ መዝገብ ቁጥር 1151/06እና የፌ/ም/ቤት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም (አመልካች......)
አመልካቾች የዳኝነት ጥያቄ ከቤተሰቦቻችን በውርስ ያገኘነው የገጠር መሬት የመንገዶች ባለስልጣን ለልማት ወስዶ ድንጋይ ሲያወጣ ቆይቶ ሲለቅ በእጃችን ገብቷል፡፡ ከዚህ በኃላ 1ኛ ተጠሪ የነበረው  ድርጅት ማዕድን ለማውጣት ፍቃድ  ወስጄበታለሁ በማለት ሁከት ስለፈጠረ ይዞታውን ይልቀቅልን የሚል ነበር፡፡ ክርክሩን የተመለከቱት በየደረጃው ያሉት ፍርድ ቤቶች አመልካቾች ክሱን ለማቅረብ መብት የላቸውም በማለት ወስነዋል፡፡ ጉባኤውም ሆነ ምክር ቤቱ የመሬት ይዞታው ባለቤትነት መብትን ከሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ካጣሩ በኃላ መሬቱ የአመልካቾች መሆኑን ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ መሬቱ የአመልካቾች እስከሆነ ድረስ መንግስት መሬቱን ለልማት የሚፈልግ ከሆነ በቅድሚያ ተገቢውን ካሳ የመክፈል እና ተተኪ መሬት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ሳይደረግ የአመልካቾች መሬት መውስድ ስለማይቻል አመልካቾች በመሬቱ ላይ ያላቸው ሕገ መንግስታዊ ያለመፈናቀል መብታቸው ሊከበርላቸው ይገባል ሲል በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 40 ንኡስ አንቀፅ 4 እና 8 መሰረት ወስኗል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግስት ትርጉም ውሳኔዎች ማጠቃለያ እና ማብራሪያ ከሚል መጽሐፍ የተወሰደ በያደታ ግዛው ( 2016 ዓ.ም )


ለበለጠ መረጃ ግሩፓችንን ይቀላቀሉ👇

http://t.me/Judge1234


አዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ ያካተታቸው ተጨማሪ ድንጋጌዎች የትኞቹ ናቸው?
****

ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 8፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የባንክ ስራ አዋጅ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው ይዘት የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበታል። በሶስት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ በረቅቁ ላይ ተካትተው በነበሩ ትርጓሜዎች እና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል። 
ማሻሻያ ከተደረገባቸው ድንጋጌዎች መካከል የባንክ ቅርንጫፎች እና የውጭ ባንኮችን የተመለከቱት ይገኙበታል። የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ የሚሳተፉበትን አካሄድ በሚዘረዝረው የአዋጅ ክፍል ላይ አዲስ አንቀጽ እንዲካተት ተደርጓል። በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ በረቂቁ ላይ ከተቀመጠው በተጨማሪም አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ተካትቷል። 
ከማሻሻያዎቹ እና ከአዳዲስ አንቀጾች ውስጥ በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀሩትን፤ ከዚህ በታች አቅርበናቸዋል፦

ትርጓሜዎች
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት፦ ባለፈው ሰኔ ወር ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ረቂቅ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ትርጓሜ ሲያብራራ “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት ነው” በሚል ነበር ያስቀመጠው። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንደ አዲስ እንዲሻሻል ተደርጓል።
በአዲሱ ድንጋጌ “ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት” ማለት “ወለድ ያለመቀበልን ጨምሮ ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ እንደሆነ” ተቀምጧል። ይህ ማሻሻያ የተደረገው፤ አገልግሎቱ በወለድ ነጻ ባንኮች እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት መስኮት በሚሰጡ ባንኮች የሚሰጥ መሆኑን “በማያሻማ መልኩ” መደንገግ አስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተብራርቷል።  
ቋሚ ንብረቶች፦ የአዋጅ ረቂቁ የትርጓሜ ክፍል፤ ቋሚ ንብረቶች “የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶች ሆነው በመመሪያ ይወሰናሉ” በማለት የተሰጠው ትርጓሜም እንደዚሁ ተሻሽሏል። ዛሬ በጸደቀው አዋጅ “ቋሚ ንብረት” ማለት “ግዙፋዊ ሀልዎት ያለው እና ገቢ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ከአንድ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ንብረት እና ዝርዝሩ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ የሚወሰን ነው” የሚል ትርጓሜ ተሰጥቶታል። 
ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ፦ የአንድ ባንክን የባንክ ስራ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተሰማራ ሌላ ባንክ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ማስተላለፍ የሚመለከተው የ“ሀብት እና እዳ ማስተላለፍ” ትርጓሜ፤ ፋይናንስ ነክ የሆኑ እና ያልሆኑ ሀብቶችን የሚጨምር እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል። በጸደቀው አዋጅ ላይ “ዕዳዎች” በተመሳሳይ መልኩ እንደሚተላለፉ ተደንግጓል።

የባንኮችን ቅርንጫፍ በተመለከተ
የባንክ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ ለመክፈት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች በብሔራዊ ባንክ መመሪያ” እንደሚወሰኑ በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተቀምጦ ነበር። በጸደቀው አዋጅ ከዚህ በተጨማሪ የባንክ ቅርንጫፎችን ለመዝጋት መሟላት ያለባቸው “ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች” በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንዲወሰን ተደርጓል።   
የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ በተመለከተ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም የውጭ ባንክ እንደራሴ ቢሮ ፈቃድ ለማግኘት ሊያሟላቸው የሚገቡ ዝቅተኛ ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን በተመለከተ በመመሪያ እንደሚወስን በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት ነበር። በጸደቀው አዋጅ ላይ ባንኩ ከዚህ ስልጣን በተጨማሪ “ቁጥጥር የማድረግ” ኃላፊነትም ተደርቦለታል።   
በአዋጅ ረቂቁ ላይ “ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ ወይም ንዑስ ቅርንጫፍ መክፈት አይችልም” የሚል ድንጋጌ ሰፍሮ ነበር። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ማንኛውም ባንክ ከብሔራዊ ባንክ አስቀድሞ የጽሁፍ ፈቃድ ሳያገኝ  “የተከፈተ ቅርንጫፍ መዝጋት አይችልም” የሚል ተጨማሪ ድንጋጌ ታክሎበታል።   

የውጭ ባንኮችን በተመለከተ
የአዋጅ ረቂቁ “ማንኛውም ተቀማጭ ገንዘብ የሚቀበል ወይም የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላ፤ ተቆጣጣሪው ያወጣቸውን ማንኛውም የጤናማነት መለኪያ መስፈርቶች እንደአግባብነቱ ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል ማክበር አለበት” ይላል። የውጭ ባንክ ቅርንጫፉ ወይም የውጭ ባንክ ተቀጥላው ከዚህ በተጨማሪ “ሌሎች አግባብነት ያላቸው ተቆጣጣሪ አካላት ያወጡትን ህጎች ማክበር” እንደሚጠበቅበት በጸደቀው አዋጅ ላይ ሰፍሯል። 
ይህ ማሻሻያ የተደረገው “የውጭ ባንኮች የብሔራዊ ባንክን ብቻ ሳይሆን የሌሎች አግባብነት ያላቸውን ተቆጣጣሪ አካላት ህጎችን ከሀገር ውስጥ ባንኮች እኩል አክብረው መስራት እንዳለባቸው ለማመላከት” እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።
የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ ስለሚሳተፉበት ሁኔታ
አዲስ ድንጋጌ፦ የውጭ ዜጎች በተለያዩ ዘዴዎች የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት በባንክ ስራ አዋጅ የተደነገገውን ገደብ በጠበቀ መልኩ መሆኑን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ፤ በረቂቅ አዋጁ ላይ ያልነበረ አዲስ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲካተት ተደርጓል። ይህ ድንጋጌ “በውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያዊያን ወይም እንደ አገር ውስጥ ባለሀብት በሚቆጠር የውጭ ሀገር ዜግነት ባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ በጋራ ባለቤትነት የተያዘ ድርጅት፤ አንድ ባንክ ላይ አክስዮን ሲይዝ፤ ባንኩ ላይ የተደረገው የውጭ ኢንቨስትመንት መጠን የሚሰላው፤ አክስዮን በገዛው ደርጅት ላይ የውጭ ዜጎች ያላቸውን የባለቤትነት ድርሻ መጠን መሰረት በማድረግ ይሆናል” ይላል። 
የተሰረዘ ድንጋጌ፦ “ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍን” በተመለከተ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተካትቶ የነበረው ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ እንዲሰረዝ ተደርጓል። የተሰረዘው ድንጋጌ “ማንኛውም ተቀማጭ የማይቀበል የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ መሰማራት የሚፈቀድለት፤ በማበደር፣ የብድር ክፍያዎችን በመቀበል እና ብድር የመስጠት ሂደቱን ለማቀላጠፍ የተከፈቱ የተበዳሪዎች የተቀማጭ ሂሳቦችን በማስተዳደር ላይ ብቻ ነው” የሚል ነበር። 
የውጭ ባንኩ “ብድሮችን እና ሌሎች ፋይናንሶችን ከውጭ ሀገር ምንጮች ሊያገኝ እና በብሔራዊ ባንክ መመሪያ እና አግባብነት ባላቸው ሌሎች ሕጎች መሰረት መጀመሪያ ላይ በተመዘገበው አግባብ መልሶ ሊከፍል” እንደሚችልም በዚህ ድንጋጌ ላይ ተካትቶ ነበር። ይህ ድንጋጌ በጸደቀው አዋጅ ላይ ሳይካተት የቀረው“ ማንኛውም የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት የሚፈቀዱለትን እንቅስቃሴዎች በግልጽ የሚያስቀምጥ መመሪያ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያወጣ የተደነገገ” በመሆኑ ምክንያት እንደሆነ ለፓርላማ አባላት የተሰራጨው ማብራሪያ ያስረዳል። 

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ ስለሚሰማራበት ሁኔታ
በፓርላማ የጸደቀው አዋጅ በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋ በባንክ ስራ የሚሰማራበትን ሁኔታ የተመለከተ አዲስ አንቀጽ፤ በረቂቁ ከተቀመጡ ድንጋጌዎች በተጨማሪነት እንዲያካትት ተደርጓል። አዲሱ አንቀጽ የተካተተው “በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ዜጎች በባንክ ሥራ ላይ ስለሚኖራቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ስርዓት በግልጽ በሕግ መደንገግ በማስፈለጉ” ምክንያት እንደሆነ በማብራሪያው ላይ ተቀምጧል።ይህ አንቀጽ “አግባብነት ባለው ሕግ የውጭ ሀገር ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ሰው ወይም በእነዚህ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተያዘ እና የተቋቋመ


"ራሴን ለማጥፉት ሞክሬያለሁ " እና ህግ!!!

በዳንኤል ፍቃዱ / ጠበቃና የህግ አማካሪ/

አንድ በሚዲያ እና በሶሻል ሚዲያ  ላይ በሰፊው በተራገበ  ጉዳይ  አንደኛው ባለ ታሪክ ራስን ለማጥፉት ሙከራ ማድረጉን እና ሆስፒታል መግባቱን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሌላኛው ባለ ታሪክ ሦስት ጊዜ የራስ ማጥፉት ሙከራ እንዳደረገ በአደባባይ በባለጉዳዮቹ ሲወራ ታዝበናል።
ለመሆኑ ራስን ማጥፉት ይቻላል? ሙከራውስ? 
አለም ላይ ያሉ ሃገራት ራስን ማጥፉትና ሙከራውን ከመፍቀድና ከመከልከል አንፃር በሶስት ፈርጅ የተከፈለ ህግ አላቸው።
• ራስን ማጥፉትንም ሆነ ሙከራውን የሚፈቅዱ / ወንጀል ነው ብለው ያልደነገጉ ሃገራት/
• ራስን ማጥፉትንም ሆነ ሙከራውን ወንጀል ያደረጉ ሃገራት
• ራስን ማጥፉትን ወንጀል ያላደረጉ ሙከራውን ግን ወንጀል አድርገው የሚቀጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ ከነዚህ በሦስተኛው ክፍል ውስጥ ትመደባለች ጎረቤት ኬንያ ደግሞ በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ ተመድባ ራስን ማጥፉትንም ሆነ ሙከራውን ወንጀል አድርጋለች ፣ እንዴት ራሱን ያጠፉ ይቀጣል ካላችሁ የኬኒያን የወንጀል ህግ ፈልጋችሁ አንቀፅ 209ን አንብቡት።
ወደተነሳው ጉዳይና ወደ ሃገራችን ህግ ስንመለስ የወንጀል ህግ ቁጥር 542 እንዲህ ይነበባል፡
እራስን የመግደል ሙከራ በተደረገ ጊዜ ፡ በቀላል እስራት ፡ እራስን መግደል ተግባር በተፈፀመ ጊዜ ከአምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እሰራት ይቀጣል፡፡ ይላል፤
ስለዚህ 
ራስን የመገደል ሙከራ በህግ የሚስጠይቅ በመሆኑ በአደባባይ ደረት ተነፍቶ አሚወራ እንዳልሆነ ፣ ህግ አስከባሪውም ይህን ተረድቶ ህግ ማስከበር እንዳለበት ሊረዳ ይገባል!!!

ሀሳብ አስተያየት ወይም ማንኛውም ህግ ነክ ጥያቄካለዎት ግሩፓችንን ይጠቀሙ


http://t.me/Judge1234


🇪🇹🇪🇹🇪🇹አጭር ሥነሥርዓት🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🟰🟰 (summary Procedures)
🟰
ከፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ህጋችን ላይ አቤቱታ ለማቅረብ የምንጠቀምባቸው ሶስት መንገዶች አሉ፡፡

እነዚህም🟰 👇👇👇
✅1ኛ/ በመደበኛ ሥነ-ሥርዓት   
✅2ኛ/ አጭር ሥነ-ሥርዓት 
✅3ኛ/ የተፋጠነ ሥነ-ሥርዓት ሲሆኑ

ከእነዚህ ውስጥ🟰👇👇👇
✅2ኛውን የክስ አቀራረብ እንመለከታለን፡፡

1. ከፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ/ 284 እስከ 292 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡
2. በዚህ ሥርዓት መሠረት ክስ ሊቀርብ የሚችለው በቁ. 284 ሥር በተዘረዘሩ ጉዳዮች ብቻ ነው፡፡ ምንጩ ግልፅ ውል፣ የሃዋላ ሰነድ፣ ቼክ፣ የተስፋ ሰነድ ወይም ቀላል ውል የሆነ ልኩ የታወቀ ገንዘብን የሚመለከት ክስ በሆነ ጊዜ ነው።
3. ማመልከቻው በመኃላ ቃል ተደግፎ መቅረብ አለበት (284(ለ))፡፡ የመኃላ ቃለ ተከሳሹ ለነገሩ ምንም ዓይነት መከላከያ እንደሌለው ከሳሽ የሚያምን መሆኑን መግለፅ አለበት
4. ፍ/ቤቱ ማመልከቻውን ከተቀበለ በኃላ ለተከሳሹ መጥሪያ እንድደርሰው ያዛል (ቁ. 285(1))
5. ተከሳሹ ቀርቦ ለመከላከል እንድፈቀድለት ፍ/ቤቱን ጠይቆ ካላስፈቀደ በቀር መከላከያ ሊያቀርብ አይችልም (ቁ. 285(1))፡፡
6. ተከሳሹ ቀርቦ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ለፍ/ቤቱ ካላመለከተ ወዲያው ፍርድ ይሰጣል(ቁ. 285(2))፡፡
7. ለመከላከል ፈቃድ እንዲሰጥ የሚቀርበው ማመልከቻ በቁ. 286 መሠረት በመኃላ ቃል ተደግፎ መቅረብ አለበት፡፡
8. ተከሳሹ ለመከላከል እንዲፈቀድለት ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ካጣ ወዲያው ለከሳሹ ይፈረዳል (ቁ. 287)፡፡
9. ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ ግን ተከሳሹ መከላከያ እንድያቀርብ ይፈቀድለታል፡፡ ክርክሩም የሚመራው ፍ/ቤቱ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ወይም እንደመደበኛው ክስ በቀጥታ ሊሆን ይችላል(ቁ. 290 እና 291)፡፡
10. ፍርድ ከተሰጠ በኃላ ለተከሳሹ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው ከሆነ ፍ/ቤቱ ፍርድ ከመፈፀም እንዲቆይ በማድረግ ተከሳሹ ቀርቦ እንዲከላከልና ስለ ጉዳዩም አፈፃፀም ተገቢ መስሎ የታየውን ትዕዛዝ ለመስጠት ይችላል(ቁ.292
ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ሲኖርዎት ግሩፓችንን ተቀላቀሉ 👇👇👇👇


https://t.me/Judge1234


የህግ ባለሙያው የፍቅር ደብዳቤ

(ደሳለኝ የኔአካል - ፍቅርኤል)
ይድረስ የልቤ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤት ለሆንሽው ለምወድሽና ለማፈቅርሽ!
ባንቺ ይሁንታ ብቻ የምኖረው የህግ ባለሙያው አፍቃሪሽ ነኝ፡፡ ደጋግሜ ልገልፅልሽ እንደሞከርኩት ልቤን በsingular title ከወረስሽው ይሄው ግንቦት ሀያ ሲመጣ አመት ሊሞላኝ ነው፡፡ መጀመሪያ ልተዋወቅሽ ስሞክር ግልምጫ በምትይው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ (preliminary objection) የትውውቅ ሙከራየን ውድቅ ልታደርጊብኝ ከሞከርሽበት ቀን ጀምሮ ፍቅርሽ በልቤ ንውፅውፅታ ፈጥሮብኛል፡፡ እንደ civil procedure code ሸንቀጥ ያለው ቁመናሽ፣ እንደ employment proclamation አንቀፆች በጥንቃቄ የተሞላው ሰበር ሰካ አረማመድሽ፣ እንደ civil code የነጡ በረዶ ጥርሶችሽ፣ ቀዩን ህገ-መንግሥት የመሠለው ሮማን ከንፈርሽ፣ የዳኞችን ጥቁር ጋዎን የመሠለው ሀር ፀጉርሽ፣ እንደመዶሻ እጀታ የተመዘዘው መቃ አንገትሽ ተባብረው እንደ አልሸባብ ሰላሜን አሣጡኝ፡፡ የመበርበርያ ትዕዛዝ (search warrant) ሳይኖርሽ የልቤን በር ከፍተሽ ገባሽ (ያውም 12:00 ካለፈ በሗላ)፡፡ ባንቺ ምክንያት እንደ land proclamation ክፍተቴ በዝቶ በቀላሉ ሆድ ይብሰኛል፡፡ በየቀኑ እየከሳሁና እየኮሰመንኩ የcriminal procedure code መስየልሻለሁ፡፡ ለፍቅርሽ ስል የት ልሂድ? የትም ብሄድ ፍቅርሽ extradite አድርጎ እንደሚመልሰኝ አልጠራጠርም፡፡ ውዴ! ባለፈው ቅዳሜ ባደረግነው oral litigation ላንቺ ያለኝን ልባዊ ፍቅር ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ (beyond reasonable doubt) ላስረዳሽ ሞክሬአለሁ፡፡ አንቺ ግን እንደ አስጠቂ ምስክር ያወቅሽውን ሁሉ ካድሽኝ፡፡ በዚህም በጣም ስለተበሳጨሁ በቸልተኝነት የሚፈፀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ልፈፅምብሽ ነበር፡፡ ያ ነገር በቸልተኝነት እንደማይፈፀም ትዝ ሲለኝ ተውኩት፡፡ the right to be heard የሚለው ህገ-መንግሥታዊ መርህ ባንቺ ዘንድ ቦታ እንደሌለው አስተውያለሁ፡፡ እንደ 1931ዱ ህገ-መንግስት ራስሽን የመካብ አባዜ ተጠናውቶሻል፡፡ የሆድ የሆዴን ሳወራሽ appeal to pitty fallacy ነው እያልሽ ታሸማቅቂኛለሽ፡፡ ነገር ግን ሴቶችን ስሜታቸውን በሚቀሰቅሰው appeal to pitty እና appeal to people (ad hominium fallacy) ካልሆነ በስተቀር በinductive እና deductive reasoning ማሳመን የማይሞከር እንደሆነ አልተሰወረብኝም፡፡ ውዴ! ምነው እንደ ፍትሐ-ብሄር ሕጉ አቋምሽን ማሻሻል ተሳነሽ? ከሕገ-መንግስቱ የማሻሻያ አንቀፆች (አንቀፅ 104 እና 105) የበለጠ ግትር ሆንሽብኝ፡፡ አንዳንዴ ሕገ-መንግስቱን መቀበልሽ እንኳ ያጠራጥረኛል፡፡ ምነው እንደ ሰበር ችሎት (cassation bench) ገደብሽን አለፍሽ?? ሴቶች እኔንና ፖለቲካን ለምን እንደምትጠሉን አይገባኝም፡፡ ተስፋ የጣልኩብሽ አንቺ እንኳን ለፍቅር አቤቱታዬ የሰጠሽኝ መልስ ሁከት ይወገድልኝ ብቻ ሆነ፡፡ የኔ ቆንጆ! ጥያቄየ እንደ ስልጤ ህዝበሸ ጥያቄ ውስብስብ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ ምነው እንደወ/ሮ ከዲጃ በሽር አንዴ እምቢ አንዴ እሺ እያልሽ አስቸገርሽኝ? በነገራችን ላይ ውዴ....... ሴቶች ግን እንደ tax proclam ወሬያችሁ ሁሉ ስለገንዘብ የሆነው ለምንድነው? ሁልጊዜ ገቢ መሰብሰብ ብቻ? አንዳንዴማ ከinsurance እነ ጡረታ አዋጆችም ስለመስጠት ትንሽ ተማሩ እንጅ፡፡ ኤጭ! አንዳንዶቻችሁማ እንደወንጀል ሕጉ አሸማቃቂ፣ እንደ tax authority ሆዳሞች፣ እንደ civil code ወሬኞችና ነገር አራዛሚዎች፣ እንደ ፀረ-ሽብር ሕጉ ቁጡና ግልፍተኞች ናችሁ፡፡ በዚያ ላይ እንደ ሊዝ አዋጁ የከፈለ ሁሉ የሚከራያቸው ብዙ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ  ፀባያቸው እንደ commercial code ይደብራል፡፡ በእርግጥ አንቺ በፍቅር ላይ እንደ immoviable property ሽያጭ ጥብቅና የተለየ መርህ እንደምትከተይ አውቃለሁ፡፡ የሆነ ሆኖ ህይዎቴን እንደ united nations charter አንቀፆች በምትፈልጊው መንገድ እያጣመምሽ እየመራሻት ነው፡፡ ከአፍሪካ human rights charter ጋር ያላቹህን ግንኙነት ባላውቅም አንድ ነገር ግን ያመሣሥላቹሃል፡፡ ሁለታችሁም አሳይቶ መንሳት (claw back) ታበዛላችሁ፡፡ መጀመሪያ ላይ ጥሩ ተስፋ ትሰጡና ቀጥላችሁ ደግሞ ሆኖም ግን፡ ቢሆንም እንኳ፡ ነገር ግን፡ ምናምን እያላችሁ የሰጣችሁትን ተስፋ መልሳችሁ አፈር ታስግጡታላችሁ፡፡ ውዴ........ ፍቅሬን renounce ካደረግሽው ሌላ ወራሽ ስለሌለኝ በ escheat መርህ መሠረት ፍቅሬ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡ ማለትም ላንቺ የነበረኝን ፍቅር ወደ ሀገር ፍቅር እቀይረዋለሁ፡፡ ይሄ ከመሆኑ በፊት ግን ፍቅራችን እነደ evidence ህጋችን በ draft እንዳይቀር ወይም እንደ ደርግ ህገ-መንግስት እድሜው እንዳያጥር የበኩልሽን አድርጊ፡፡ እኔ እንደሆንኩ እነደ gap filling provision ሳይሆን እንደ mandatory rule አክብሬ እይዝሻለሁ፡፡ ከሃሳብሽ intentionallyም ይሁን neglligently አላፈነግጥም፡፡ pacta sunt servanda!
ልዩነታችን እንደ common law እና civil law legal system የሰፋ ቢሆንም በ convergence እንደሚጠብ ተስፋ አለኝ፡፡ እስከዚያው የሲቪል ኮዱን ዝና፡ የክሪሚናል ኮዱን ግርማ ሞገስ፡ የህገመንግስቱን የበላይነት፡ የፋሚሊ ኮዱን ቁንጅና እመኝልሻለሁ፡፡
የፍቅር መዝገቡም ለጊዜው ተዘግቷል!
(የማይነበብ የአፍቃሪው ፊርማ አለበት)
Join 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ ያናግሩን

https://t.me/Judge1234
http://t.me/Judge1234


የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች ከተመረጡ የሰበር ውሳኔዎች ጋር በማጠቃስ የቀረበ!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹1
♨️በቴሌግራም ያግኙ👍👇 https://t.me/HenokTayeLawoffice
ኑዛዜን ለመቃወም የተቀመጠ ጊዜ ገደብ
///////
ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቁጥር 973 ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ሚሆነው ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚለውን ክስ ኑዛዜው ሲነገር በነበሩ ሰዎች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973/1/ ላይ እንደተገለጸው “ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረው ቃል አይጸናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸውን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሂሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የአስራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው”፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች መቃወሚያቸውን መቼ ሊቀርቡ ይችላሉ ለሚለው በፍ/ሕ/ቁ 974/1/ እና 2 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት “ በኑዛዜ ንባብ ሥነ-ሥርዓት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ-ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎች እንዲሁም ኑዛዜው በሌሉበት የተነበበ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተገለጸው የጊዜ ገደብ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነው ሥለ ክፍያው ድልድልና አመዳደብ ሀሳቡን ከተነገራቸው ቀን አንስቶ ነው”፡፡
በፍ/በ/ህ/ቁ 973/2/ ላይ በተገለጸው መሰረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟች ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትና ስለክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
ከዚህ በላይ ከተገለጹት የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 82585 በቅጽ 15 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በትርጓሜውም “በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅርቢው ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ ወይም የተወከለ የመሆን አለመሆን መስፈርት መሰረት በማድረግ ይርጋው መቁጠር የሚጀምርበትን ጊዜ እና ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ በቁጥር 974/2/ ከመደንገጋቸው በስተቀር ሁለቱም ድንጋጌዎች ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን ስርዓት የሚደነግጉ በመሆቸው ተያያዥነት አላቸው በማለት ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና የኑዛዜውን ሙሉ ይዘት ማወቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ሲል በፍ/ብ/ህ/ቁ 973/1/ የተመለከተው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይሆን የመግለጫ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ኑዛዜ መኖር እንጂ ስለድልድሉ የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ስለማይኖርበት ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው በኑዛዜው የተደረገውን ድልድል ካወቁበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በሟች የተደረገ ኑዛዜ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሊፍርስ ይገባል በማለት ኑዛዜው ሲነበብ በነበረ አመልካች የሚቀርብ የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 መሰረት በተገለጠው የጊዜ ገደብ ነው ወይስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው? የሚለው አከራካሪ ጉዳይ በመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 152134 በቅጽ 23 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዲሁም ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዲፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓትና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል /ነቅሎናል/ በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት አይይለም፡፡ በመሆኑም ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ሊታይ የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነውእንጂ በአንቀጽ 973 መሰረት አይደለም በማለት አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሕግ ትርጓሜ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና እንዲሁም መግለጫው እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባው የጊዜ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ተፈጻሚነት የሚኖረው ኑዛዜ ሲነበብ በነበሩ ወይም በተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ሲሆን በአንቀጽ 974 ድንጋጌ ደግሞ ተፈጻሚነቱ በኑዛዜ ሥነ-ሥርዓት ባልነበሩ ወይም ባልተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነው፡፡
//////
የወራሽነት ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ
የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሚመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 ላይ የተመለከተ ሲሆን ወደዚህ ነጥብ ከመግባቴ በፊት ወራሽነት ጥያቄ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እደሚከተለው ለመዳሰስ እሞክራለሁ÷
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 996(1) ላይ በተገለጸው መሰረት ወራሽ የሆነ ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል በማለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ማለት ፍ/ቤቱ የወራሽነት ምስክር እንዲሰጠው ወራሹ ሲፈልግ የሚጠይቀው እንጂ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍ/ቤቱ የወራሽነት ማስረጃ ማምጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እንደሚስተዋለው ስመ ንብረቱ ለማዛወር እና ከሌሎች የሟች መብቶች ለመጠቀምና ለመስራት በፍ/ቤቱ የተረጋገጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መጠየቁ የተለመደ አሰራር ሆኗል፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱን እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀብበት ይችላል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 999 ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ይህን መሰል የክስ አቤቱታ አቤቱታ መቼ ሊቀርብ ይገናል ለሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ላይ የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡
በዚሁ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርሱን ንብረት በተከሳሽ መያዛቸውን ካወቅ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 1000(2) ላይ እንደተገለጸው “ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት አመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም የሚለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡



For any question join our chat
t.me/Judge1234


የውርስ ጉዳይን የተመለከቱ የይርጋ ገደቦች ከተመረጡ የሰበር ውሳኔዎች ጋር በማጠቃስ የቀረበ!

ኑዛዜን ለመቃወም የተቀመጠ ጊዜ ገደብ
///////
ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ በተመለከተ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በቁጥር 973 ላይ የተመለከተው ተፈጻሚ ሚሆነው ኑዛዜ ፈራሽ ነው የሚለውን ክስ ኑዛዜው ሲነገር በነበሩ ሰዎች የቀረበ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973/1/ ላይ እንደተገለጸው “ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ሰዎች ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረው ቃል አይጸናም በማለት ክስ ለማቅረብ ያላቸውን ሀሳብ መግለጫ ወይም ስለ ክፍያው በሂሳብ አጣሪው የቀረበውን የድልድል አመዳደብ ሀሳብ ለመቃወም ኑዛዜው ከተነበበት አንስቶ በሚቆጠር የአስራ አምስት ቀን ጊዜ አላቸው”፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ ሰዎች መቃወሚያቸውን መቼ ሊቀርቡ ይችላሉ ለሚለው በፍ/ሕ/ቁ 974/1/ እና 2 ላይ የተገለጸ ሲሆን በዚህም መሰረት “ በኑዛዜ ንባብ ሥነ-ሥርዓት ላልነበሩ ወይም በኑዛዜው ንባብ ሥነ-ሥርዓት በወኪልነት ላልሰሙ ሰዎች እንዲሁም ኑዛዜው በሌሉበት የተነበበ እንደሆነ ከዚህ በላይ የተገለጸው የጊዜ ገደብ ለመቁጠር መነሻ የሚሆነው ሥለ ክፍያው ድልድልና አመዳደብ ሀሳቡን ከተነገራቸው ቀን አንስቶ ነው”፡፡
በፍ/በ/ህ/ቁ 973/2/ ላይ በተገለጸው መሰረት ኑዛዜ ከፈሰሰበት ጊዜ ከአምስት ዓመት በኋላ ወይም ኑዛዜ የሌለ እንደሆነ ሟች ከሞተ ከአምስት ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትና ስለክፍያው አመዳደብ አጣሪው ያቀረበውን የድልድል ሀሳብ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን መቃወሚያ ሊቀርብበት አይችልም፡፡
ከዚህ በላይ ከተገለጹት የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በተያያዘ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 82585 በቅጽ 15 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የሰጠ ሲሆን በትርጓሜውም “በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅርቢው ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ ወይም የተወከለ የመሆን አለመሆን መስፈርት መሰረት በማድረግ ይርጋው መቁጠር የሚጀምርበትን ጊዜ እና ፍጹም የሆነ የይርጋ ጊዜ በቁጥር 974/2/ ከመደንገጋቸው በስተቀር ሁለቱም ድንጋጌዎች ኑዛዜው ፈራሽ ነው የሚል ክስ የሚቀርብበትን ስርዓት የሚደነግጉ በመሆቸው ተያያዥነት አላቸው በማለት ኑዛዜ መኖሩን ማወቅ እና የኑዛዜውን ሙሉ ይዘት ማወቅ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው ሲል በፍ/ብ/ህ/ቁ 973/1/ የተመለከተው የ15 ቀን ጊዜ ገደብ የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይሆን የመግለጫ ማቅረቢያ ጊዜ ነው፡፡ በመሆኑም ስለ ኑዛዜ መኖር እንጂ ስለድልድሉ የማያውቅ ወራሽ መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ስለማይኖርበት ጊዜው መቁጠር የሚጀምረው በኑዛዜው የተደረገውን ድልድል ካወቁበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በሟች የተደረገ ኑዛዜ ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሊፍርስ ይገባል በማለት ኑዛዜው ሲነበብ በነበረ አመልካች የሚቀርብ የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 መሰረት በተገለጠው የጊዜ ገደብ ነው ወይስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ነው? የሚለው አከራካሪ ጉዳይ በመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት በሰ/መ/ቁ 152134 በቅጽ 23 ላይ አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ስለ ኑዛዜ መነበብ እንዲሁም ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ሰዎች ኑዛዜው እንዲፈርስ አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ሥርዓትና ጊዜውን በሚመለከት የሚደነግግ ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል /ነቅሎናል/ በማለት ኑዛዜው እንዲፈርስ የሚቀርብን ወይም የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት አይይለም፡፡ በመሆኑም ኑዛዜው ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ ሊታይ የሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነውእንጂ በአንቀጽ 973 መሰረት አይደለም በማለት አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቷል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሰው የሕግ ትርጓሜ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ አንድ ኑዛዜ ፈራሽ ነው በሚል ስለሚቀርብ መግለጫ እና እንዲሁም መግለጫው እና ክሱ ሊቀርብ ስለሚገባው የጊዜ ገደብ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 እና 974 ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 973 ተፈጻሚነት የሚኖረው ኑዛዜ ሲነበብ በነበሩ ወይም በተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ሲሆን በአንቀጽ 974 ድንጋጌ ደግሞ ተፈጻሚነቱ በኑዛዜ ሥነ-ሥርዓት ባልነበሩ ወይም ባልተወከሉ ሰዎች ጉዳይ ነው፡፡ ኑዛዜ ሲነበብ የነበረ አመልካች ኑዛዜው ከውርስ ነቅሎኛል በማለት የሚያቀርበው የክስ አቤቱታ ሊቀርብ ሚገባው በፍ/ህ/ቁ 973 መሰረት ሳይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት ነው፡፡
//////
የወራሽነት ጥያቄ ለማቅረብ የተቀመጠ ጊዜ ገደብ🇪🇹

የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ የሚመለከቱ የሕግ ድንጋጌዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000 ላይ የተመለከተ ሲሆን ወደዚህ ነጥብ ከመግባቴ በፊት ወራሽነት ጥያቄ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እደሚከተለው ለመዳሰስ እሞክራለሁ÷
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 996(1) ላይ በተገለጸው መሰረት ወራሽ የሆነ ሰው የሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል በማለት የተገለጸ ሲሆን ይህ ማለት ፍ/ቤቱ የወራሽነት ምስክር እንዲሰጠው ወራሹ ሲፈልግ የሚጠይቀው እንጂ ሟችን ለመውረስ የግድ ከፍ/ቤቱ የወራሽነት ማስረጃ ማምጣት እንዳለበት የሚያስገድድ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እንደሚስተዋለው ስመ ንብረቱ ለማዛወር እና ከሌሎች የሟች መብቶች ለመጠቀምና ለመስራት በፍ/ቤቱ የተረጋገጠ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መጠየቁ የተለመደ አሰራር ሆኗል፡፡
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን መሰረት በማድረግ አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱን እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት በዚህ ሰው ላይ የወራሽነት ጥያቄ ክስ ሊያቀብበት ይችላል በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 999 ላይ ተደንግጓል፡፡ ስለዚህ ይህን መሰል የክስ አቤቱታ አቤቱታ መቼ ሊቀርብ ይገናል ለሚለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000/1/ ላይ የጊዜ ገደብ ተቀምጧል፡፡
በዚሁ መሰረት ከሳሽ መብቱንና የውርሱን ንብረት በተከሳሽ መያዛቸውን ካወቅ ሶስት ዓመት ካለፈ በኋላ ስለ ወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፡፡ በሌላ መልኩ በአንቀጽ 1000(2) ላይ እንደተገለጸው “ሟቹ ከሞተበት ወይም ከሳሹ በመብቱ ለመስራት ከቻለበት ቀን አንስቶ አስራ አምስት አመት ካለፈ በኋላ ከዘር የወረደ ርስት ካልሆነ በቀር የውርስ ጥያቄ ክስ በማናቸውም አስተያየት ቢሆን ተቀባይነት አያገኝም የሚለው ተደንግጎ ይገኛል፡፡


❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥❤️‍🔥

ጅንጀና ስታይል ❤️‍🩹


Репост из: የኔ ቻነል
📢ኑ ቻናላችሁን አሳድጉ🎤

📢መግባት የምትፈልጉ


🌠 wave 🌌  መግባት የምትፈልጉ 
 
Above ➡ 1k+ subscribers
Above ➡ 3k+subscribers
Above ➡ 5k+subscribers
Above  ➡  10k+ subscribers
Above  ➡  20k+ subscribers
Above  ➡  30k+ subscribers
Above  ➡  40k+ subscribers
Above  ➡  50k+ subscribers
Above  ➡  80k+ subscribers
Above  ➡  100k+ subscribers

👉የቻናል ባለቤቶች እና አድሚኖች !!
Inbox me

👉@gofx19


አክስዮን ማህበር (share company ) ምንነት ከአዲሱ የንግድ ህግ አንፃር ምን ይመስላል

አክስዮን ምንድን ነው ?
አክስዮን ማህበር ማለት ዋና ገንዘቡ ወይም ካፒታሉ አስቀድሞ ተወስኖ በአክስዮን የተከፋፈለና ኃላፊነቱም በማህበር ሀብት ብቻ የተወሰነ የማህበር አይነት ነው። ይህም ማለት ማህበሩ ለሚደርስበት እዳም ይሁን ለሚያገኘው ተርፍ ክፍፍል ተጠቃሚ የሚሆነው በገባው አክስዮን መጠን ሲሆን ከገባው የአክሲዮን መጠን በላይ አይጠየቅም
የአክሲዮን ባህሪያት ምንድን ናቸው
1, አክሲዮን ማህበር በመሃበሩ አባል ሞት ወይም የህግ ችሎታ ማጣት ሊፈርስ አለመቻሉ
2, ድርሻ በአባሉ ፍቃድ ማስተላለፍ መቻሉ ይህም ማለት የአክስዮን  አባሉ በፈለገ ግዜ
የአክሲዮን ድርሻውን መሸጥ፣ በስጦታ ወይም በውርስ ማስተላለፍ ይችላል
3, የአክስዬን ድርሻ አባላት ከአምስት ማነስ እና በሌላ ሁኔታ በህግ ካልተደነገገ በስተቀር የአክሲዮን መመስረቻ ካፒታል ከ50,000 ማነስ የለበትም
አክስዮን ማህበር ለመመሰረት የሚያስፈልጉ ጠቅላላ ቅድመ ሁኔታዎች
. የአክሲዮን ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልገው ካፒታል ለመከፈል መፈረም እና
. ቢያንስ ¼ የአክሲዮን ማህበር ድርሻ መክፈል እና
በአክስዮን ማህበሩ አካውንት በዝግ መቀመጥ ይኖርበታል
. አክሲዮን ማህበሩ በአዲሱ የንግድ ህግ አንቀፃ 259 መሰረት አምስት አመት ሳያልፍ መመዝገብ ይኖርበታል ይህ ሳይሆን ቢቀር ገንዘባቸውን ከፍለው የተመዘገቡ አባላት አክሲዮን ምስረታውን መቀጠል ካልፈለጉ ገንዘባቸውን ከተቀመጠበት ጊዜ አንስቶ በሚሰላ የባን የወለድ ምጣኔ ተጨምሮበት እንዲመለስለቸው መጠየቅ ይችላሉ

ጥያቄ ለመጠየቅ ሲፈልጉ

share/join👇👇👇
http://t.me/Judge1234


ለተበዳይ ቤተሰቦች ስለመካስ
👉በወንጀል ሕግ ቁጥር 197 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ እንደተመለከተው ለአንድ ሰው ቅጣቱን ለመገደብ ከሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮች መካከል አንደኛው “በሚቻለው መንገድ ሁሉ በጥፋቱ ያደረሰውን ጉዳት እንደሚክስ ወይም ለተበዳዩ እንደሚከፍል” ማረጋገጫ ማቅረብ አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ነው።
👉ጥፋቱን ያደረሰው ግለሰብ ካሳ ሲክስ በሁለት ዓይነት መንገድ ሊክስ እንደሚችል ይታወቃል።
☝️ተበዳዩን መካስ
👉በዚህ ረገድ የሚደረገው ካሳ ምንም አሻሚነት የለም፤ በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የተጎዳውን ሰው በእርቅ ስምምነት ለደረሰበት ጉዳት ከበዳይ ወገን የሚሰጥና የሚከፈለው ካሳ ነው።
✌️የተበዳዩን ቤተሰቦች መካስ
👉ለተበዳይ ቤተሰቦች የሚሰጠው ካሳ በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት ለደረሰባቸው በደል የሚከፈላቸው ካሳ ሲሆን ካሳው ለባለቤት፣ ለልጆች፣ ለወላጆች ወይም በሟች ገቢ ጥገኛ ሆነው ይኖሩ ለነበሩ የሚከፈል ካሳ ነው።
⚠️⚠️⚠️ይህ ካሳ ሲከፈል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦⚠️⚠️⚠️
1️⃣ካሳ ከመክፈልዎት በፊት ካስ የሚከፍሏቸው ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ ያላቸው መሆኑን ያረጋግጡ። ምክንያቱም ካሳውን ለመቀበል ብቁ ካልሆነ ላልተገባ ሰው ካሳ መክፈልዎት ቅጣቱን አያስገድብልዎትም።
2️⃣የእርቅ ውል ስምምነት ሳይፈጽሙ የካሳ ክፍያ ገንዘብ ክፍያ አይፈጽሙ።
3️⃣የእርቅ ውል ስምምነትዎን ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ እንደሆነ ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲሁም በክስ ሂደት ላይ ያለ እንደሆነ ከፍርድ ቤት መዝገብ ጋር እንዲያያዝልዎት ያድርጉ።
ይግባኝ መብት ነው
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ

ለበለጠ መረጃ👇👇👇
rel='nofollow'>Http://t.me/judgeoffed


ሰ.መ.ቁ 248877 ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ . ም-   የወራሽነት ማስረጃ የወሰደ ሰው በሕግ በታወቀ ጋብቻ ውስጥ ወይም እንደ ባልና ሚስት ግንኙነት ወይም ከሁለቱ በአንዱ በሕግ በሚታወቅ ግንኙነት ውስጥ እንዳልተወለደ ከተረጋገጠ የሟች ልጅ እንደሆነ በመግለጽ ከአዲስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ነው ተብሎ የተሰጠ ማስረጃ ጸንቶ ሊቀጥል የሚችለው ሟች ልጄ ነው በማለት የተቀበሉት ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 131 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሠረት እና በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 143 እና ተከታዮቹ መሠረት አባትነት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚታወቅባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን በመግለጽ በማስረጃ የተደገፈ ክርክር ሲቀርብ መሆኑን: ሰዎች የወራሽነት ማስረጃ የሚወስዱት መብት ለማቋቋም በማሰብ እንደመሆኑ ይህን ማስረጃ በመጠቀም በሚደረግ ተግባራት የሶስተኛ ወገኖች መብቶች ሊነካ የሚችልበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከግምት በማስገባት ማስረጃውን የሚሰጠው ፍርድ ቤትም የወራሽነት ማስረጃ ሲሰጥ ጠያቂዎቹ ከሟች ጋር አለን የሚሉትን ግንኙነት በተገቢው ማስረጃ እንዲያረጋግጡ ማድረግ እንደሚኖርበት: በዚሕ አግባብ ተረጋግጦ የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ መሆኑን ማስረጃው የተሰጠው ሰው ባላስረዳበት ሁኔታ ማስረጃውን በመቃወም ክስ ያቀረበ ሰዉ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ የታገደ ነው የመካድ ክስ እንዲያቀርብም ሊፈቀድለት አይገባም በሚል የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆኑን በመግለጽ አስገዳጅ የሆነ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡


ይወዳጁን👇👇👇
http://t.me/judgeoffed


የውል ህግ ክፍል 5
ክፍል 6 በቅርቡ ይጠብቁን


ውልን ስላለመፈጸም/…
- ባለመብቱ ማስጠንቀቂያውን ሲሰጥ አያይዞ ባለእዳው ግዴታውን
በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መፈጸም እንዳለበት በመግለጽ ጊዜውን
መጥቀስ ይችላል፤ የሚሰጠው ጊዜ እንደግዴታው አይነት የሚለያይ
ሲሆን በህሊናዊ ግምት በቂ የሚባል ጊዜ መሆን ይጠበቅበታል (ፍ/ብ/ህ
1774)፡፡
- አንድ ባለመብት ለባለእዳው ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እንደውሉ
አልተፈጸመልኝምና ይፈጸምልኝ ወይም ውሉ ይፍረስልኝ በሚል ክስ
ቢመሰርት ምንድነው ውጤቱ ?
- ባለመብቱ ለባለእዳው ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ቀጥታ ወደክስ እንዲሄድ
የሚፈቀድበት ሁኔታስ አለ ?
በፍ/ብ/ህ/ቁ 1775 መሰረት በሚከተሉት ሁኔታዎች ጊዜ ባለመብት
ለባለእዳው ማስጠንቀቂያ መስጠት አይጠበቅበትም
- ግዴታው አንድን ነገር ያለማድረግ ግዴታ ሲሆን፤
- ባለእዳው ግዴታውን የሚፈጽምበት ጊዜ በውሉ ላይ ተመልክቶ ከሆነና
ይህ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ፤
- ባለእዳው ግዴታውን የማይፈጽም መሆኑን በጽሁፍ የገለጸ እንደሆነ፤
እና
- በውሉ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠ ይቆጠራል
የሚል ስምምነት በውሉ ላይ ከተጠቀሰ
እንደ ዉሉ ስለማስፈጸም
 እንደ ውሉ ማሰፈጸምን በሁለት ከፍለን ማየት እነችላለን
ሀ. ውልን በግድ ማስፈጸም -- ፍ/ብ/ህ 1776
- ውሉ በግድ ይፈጸምልኝ ብሎ መጠየቅ የሚቻለው 2 ነገሮች ከተሟሉ ብቻ ነው፤
 እንደውሉ መፈጸሙ ለባለመብቱ ልዩ ጥቅም ሲኖረው
 ባለእዳው እንደውሉ መፈጸሙ በነጻነቱ ላይ ምንም አይነት መሰናክል የማያደርስ ሲሆን
ለ.ዉልን በትክ ስለማሰፈፀም
 ባለመብቱ፡ ፍ/ብ/ህ 1777 እና 1778
o የማደረግ እና ያለማድረግ ግዴታ ሲሆን
o በአይነቱ የታወቀ ነገር ሲሆነ (FUNGIBLE THINGS)
 ባለዕዳዉ፡ ፍ/ብ/ህ 1779-1783
o ባለመብቱ የተሰጠዉን ነገር አልቀበልም ካለ
o ባለመብቱ ማን እንደሆነ ማወቅ ካልተቻለ
ውልን መሰረዝ
ዉል በሁለት መልኩ ሊሰረዝ ይችላል
1. ውልን በፍ/ቤት ማሰረዝ-ፍ/ብ/ህ 1784
- በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተፈጸመ ውል እንዲሰረዝ ከተፈለገ
የይሰረዝልኝ ጥያቄ ለፍ/ቤት መቅረብ አለበት፡፡
- ይህ ጥያቄ በአንዱ ወገን ሊቀርብ የሚችለውም ሌላኛው ወገን
ግዴታውን በሙሉ ወይም በከፊል ወይም በበቂ ሁኔታ ሳይወጣ
የቀረ እንደሆነ ነው፡፡
ውልን በገዛ ፈቃድ ማፍረስ
2. ውልን በገዛ ፈቃድ መሰረዝ
ሀ. በውሉ ውስጥ አንዱ ወገን ብቻውን ውሉን ሊሰረዝ የሚችልበት ምክንያት
ተጠቅሶ ከሆነ (ፍ/ብ/ህ 1786)
ለ. በአስገዳጅ የጊዜ ገደብ መፈጸም ያለባችዉ ዉሎች ከሆኑ እና ያንም ጊዜ ካለፈ
 በዳኛ በተሰጠ የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም ከቀረ (ፍ/ብ/ህ 1770)
 ባለመብቱ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ላይ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይወጣ
ከቀረ (ፍ/ብ/ህ 1774)፤
 በውሉ ላይ ባለእዳው ግዴታውን የሚፈጽምበት ጊዜ ተቀምጦ ከሆነና ግዴታውን
ሳይደጽም ይህ ጊዜ ካለፈ (ፍ/ብ/ህ 1775(ለ))
ሐ. ባለዕዳዉ ግዴታዉን መፈጸም የማይችል ከሆነ (ፍ/ብ/ህ 1788)
መ. ባለዕዳዉ ዉሉን እነደማይፈጸም በጽሁፍ ያሳወቀ ከሆነ (ፍ/ብ/ህ 1789)
እንደውሉ ባለመፈጸሙ ካሳ ስለመጠየቅ
እንደውሉ ባለመፈጸሙ ካሳ ስለመጠየቅ
ፍ/ብ/ህ 1790 እና 1791
-ካሳ ዉል ይሰረዝልኝ አልያም እንደዉሉ ይፈጸምልኝ ከሚለዉ በተጨማሪ
ወይም እንደአማራጭ ሊጠየቅ የሚችል ነዉ፡፡
-ግዴታውን ያልተወጣው ወገን ጥፋት ባይኖርበትም እንኳ
በባለመብቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት ካሳ የመክፈል ሃለፊነት አለበት፡፡
-ባለእዳው ከዚህ ሃላፊነት ሊድን የሚችለው ግዴታውን መወጣት
ያልቻለው ከአቅም በላይ በሆነ ሃይል ምክንያት መሆኑን ማስረዳት
ከቻለ ብቻ ነው፡፡
ከአቅም በላይ የሆነ ሃይል
ከአቅም በላይ የሆነ ሃይል
ፍ/ብ/ህ 1792
-አንድ ሃይል ከአቅም በላይ የሆነ ሃይል ሊባል የሚችለው
- ባለእዳው ሊከሰት ይችላል ብሎ ያልገመተው ወይም ሊገምተው የማይችል
ሃይል ሲሆን (UNFORESEEN )፤ እና
- ይህም ሃይል ግዴታውን እንዳይወጣ ፍጹም መሰናክል ሲሆንበት ነው
(ABSOLUTE)፡፡
-በመሆኑም የተከሰተው ድንገተኛ ሃይል ሊከሰት እንደሚችል ባለእዳው
ቀድሞውኑ ሊያስበው የሚችል ሆኖ ከተገኘ ሃይሉ ድንገተኛ ቢሆንም
ግዴታውን ባለመወጣቱ ለደረሰው ጉዳት ሃላፊ ይሆናል
የጉዳት ካሳ መጠን
የጉዳት ካሳ መጠን
-የጉዳት ካሳው መጠን እንደውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ሊደርስ ይችላል ተብሎ
ከሚገመተው ኪሳራ ጋር እኩል መሆን አለበት (ፍ/ብ/ህ 1799)
-ነገር ግን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ተሰልቶ የመጣው የካሳ መጠን በባለመብቱ ላይ
በርግጥ ከደረሰው ጉዳት የበለጠ መሆኑን ባለእዳው ማሳየት ከቻለ ፍ/ቤቱ መጠኑን
በዚያው ልክ መቀነስ ይችላል (ፍ/ብ/ህ 1800)
-በተቃራኒው ባለመብቱ ውሉ በተፈጸመ ጊዜ ከውሉ ልዩ ባህሪ የተነሳ እንደውሉ
ባይፈጸምለት የሚደርስበት ጉዳት ሊደርስ ይችላል ተብሎ ከሚገመተው ኪሳራ በላይ
መሆኑን ለባለእዳው አሳውቆት የነበረ ከሆነ ባለእዳው ግዴታውን ባለመፈጸሙ
ምክንያት በባለመብቱ ላይ በደረሰው ኪሳራ ልክ (ከተለመደው በላይ የሆነ)ካሳ
እንዲከፍል ሊደረግ ይችላል (ፍ/ብ/ህ 1801)
የጉዳት ኪሳራን የመቀነስ ግዴታ
የጉዳት ኪሳራን የመቀነስ ግዴታ
ፍ/ብ/ህ 1802
-አንድ ባለመብት እንደውሉ ያልተፈጸመለት በመሆኑ ምክንያት ኪሳራ
ሊደርስበት እንደሚችል ሲያውቅ የጉዳቱን መጠን በተቻለው አቅም
ለመቀነስ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል (የሚያደርገው ጥረት አስቸጋሪና
ብዙ ወጪ የሚያስወጣው እስካልሆነ ድረስ ማለት ነው)
-ባለመብቱ ይህን ማድረግ እየቻለ ሳያደርግ የቀረ እንደሆነና ባለእዳውም
ይህን ማስረዳት ከቻለ የኪሳራ መጠኑ እንዲቀነስለት ባለእዳው ፍ/ቤቱን
መጠየቅ ይችላል
VI. የውል ግዴታዎች ቀሪ መሆን

ይቀጥላል ....

ማስታወቂያ :ለቻናል ና ግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ
#ትልቅ_የቻናል_ማስታወቂያ_ወይም_Wave_ጀምረናል በ አንድ ጊዜ 100 ቻናሎች ላይ እናስተዋውቅሎታለን ኑ አብረን እንስራ💥💥💥 #የቻናል እና የግሩፕ _ባለቤት_ለሆናችሁ _ብቻ ያለ ምንም ክፍያ 👨‍⚖👩‍⚖
#ለሕግ_ነክ_ ቻናሎች  እና ግሩፖች_ብቻ

✅100+subscribers or members
✅300+subscribers or members
✅500+subscribers or members
✅1k+ Subscribers or members
✅3k+ Subscribers or members
✅5k+ Subscribers or members
✅7k+ Subscribers or members
✅10k+ Subscribers or member
✅15k+ Subscribers or member
✅20k+ Subscribers or member
✅30k+ Subscribers or member
      
ኑ ቻናላችንን አብረን እናሳድግ


መግባት የምትፈልጉ Inbox Me and send your channels link via
         
@gofx19
         @Theothokos21
Join us 💫
rel='nofollow'>Http://t.me/judgeoffed
http://t.me/judgeoffed


የመንደር ውሎች በሕግ ፊት ተቀባይነታቸው ምን ያህል ነው❓ውል የሚጸናው ምን ሲሟላ ነው❓

አራት ነገር ካልተሟላ ውል አይጸናም ።

1ኛ• ፈቃድ (Consent) ነው። ተዋዋዩ ፈቃዱን የሰጠው ወዶና ፈቅዶ በማያሻማ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል። ምን ማለት ነው ይሄ፣ በመታለል/በማታለል የተፈጸመ ውል ዋጋ አይሰጠውም።

2ኛ• ተዋዋዮቹ በሕግ 'ችሎታ ያላቸው' መሆን አለባቸው። 'ችሎታ' የሕግ ትርጉሙ ሁለት ነው። የተዋዋዮች ዕድሜ ከ18 ዓመት በላይ መሆን እና የአእምሮ ጤና ነው።

3ኛ• የውሉ ዋና ጉዳይ በሕግ የሚፈጸም መሆን አለበት። ለምሳሌ ባዶ መሬት መሸጥ አይቻልም። ስለዚህ የባዶ መሬት ሽያጭ ውል ቢደረግም በፍርድ ቤት ውድቅ ነው።

4ኛ• የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ነው። ይህም ማለት ለምሳሌ ለማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ 2 ምስክሮች መኖራቸው፣ በውል አዋዋይ ፊት መረጋገጥ፣ ሕጉ ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች ሟሟላት።

የመንደር ውል ሕጋዊ ነው❓

የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች፣ ማለትም ቤትና መሬት በርካታ ሰዎች በመንደር ውል የሚሻሻጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች ተግባሩን ስላደረጉት ግን ሕጋዊ አያሰኘውም። ይህ የመንደር ውል በሕግ ተቀባይነት የማይኖረው የሰነድ ማረጋገጥ ዋና ዓላማን የሚጥስ መሆኑ ነው ።

ሰነድ ለምን ይረጋገጣል? ባይረጋገጥስ ምን ችግር አለው ❓

አንደኛ በተዋዋዮቹ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግዛት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሦስተኛ ወገን ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። ሦስተኛ ወገን የሚባሉት እነማን ናቸው ያልን እንደሁ፣ ከገዥና ሻጭ ውጪ ያሉ የትኛውንም ወገኖችን ያካትታል። ለምሳሌ የመንግሥት አካል፣ የክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር፣ ባንክ፣ ለምሳሌ ሽያጩ ይፍረስልኝ የምትል/የሚል ሚስት/ባል . . . ወዘተ እነዚህ ሁሉ 3ኛ ወገን ይባላሉ።

ከእነዚህ አካላት አንዱ፣ እንበልና በመንደር ውል በተፈጸመ ንብረት ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ሙግቱን ያለምንም እሰጥ አገባ አሸነፉ ማለት ነው። በመንደር ውል ቤት የገዛ ሰው ቀለጠ ማለት ነው። በአጭሩ ውል የሚረጋገጥበት ዋንኛ ዓላማ ሦስተኛ ወገኖች ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው። "የመንደር ውል ችግሩም ይሄ ነው።

እርግጥ ውል በሰነዶች ሲረጋገጥ መንግሥት ቴምብር ያሳርፍበታል። ገቢ ያገኛል። ገዥና ሻጭ ሰነዱን ይዘው ክፍለ ከተማ ሲሄዱ የመንግሥት አካል ቀረጥ ይጥላል። ከዚያም ገቢ ይገኛል። ተዋዋዮች ሕጋዊ ሰነድ ይዘው ስለቀረቡ፣ ሕጋዊ አገልግሎት አግኝተው የስም ማዞርያ አሹራ ይከፍላሉ። ይህም ሌላ ገቢ ነው። ለዚህም ነው ውሉ በሕጉ ላይ የተቀመጠውን ፎርም ስላሟላ እንደ ሕጋዊ ውል ተቆጥሮ ተፈጻሚነት የሚኖረው።

ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ግን ምን ማለት ነው❓

በአጭሩ ለምሳሌ ሻጭ ለገዢ ስም አላዞርልህም ቢል ፍርድ ቤት ከሶ በግዴታ ስም እንዲያዞር፣ ገዥ ላይ ለደረሰው ኪሳራም ካሳ እንዲያገኝ ይሆናል ማለት ነው። ይህን ዕድል ግን በመንደር ውሎች ላይ ለማሳካት አስቸጋሪ ይሆናል።

በመንደር ውል የተሸጠ ንብረት እጣ ፈንታው ምንድነው❓

በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልተመዘገበ ውል፣ ወይም በውል አዋዋዮች ፊት ያልተረጋገጠ የመንደር ውል እንደ ሕጋዊ ተቆጥሮ አፈጻጸም ሊቀርብበት አይችልም። በዚህ ላይ ምንም ብዥታ መኖር የለበትም። የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆን አለበት፣ በሁለት ምስክሮች ፊት መሆን አለበት። በአዋዋይ ፊት መሆን አለበት።

ወደ ጥያቄው ውሉ በመንደር ቢደረግ እጣ ፈንታው ምንድነው የሚሆነው❓

እውነት ለመናገር በዚህ ረገድ ሕጉ የተረጋጋ አይደለም :: የአገሪቱ የመጨረሻ ፍርድ ቤት የሆነው ሰበርም ቢሆን ከውል አዋዋይ (ውልና ማስረጃ) ውጪ የተደረጉ የመንደር ውሎች ይፀናሉ ወይስ አይፀኑም በሚለው ላይ በተለያየ ጊዜ የተለያየ ውሳኔ ሰጥቷል።

በአንድ በኩል፣ ሰዎች በመንደር ከተዋዋሉና ነገር ግን ፊርማቸውን ካልተካካዱ ውሉ በተዋዋዮቹ መካከል ብቻ ይጸናል ብሎ የወሰነበት ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቍ 21448)

በሌላ በኩል ደግሞ የመንደር ውል በውል አዋዋይ ፊት እስካልተመዘገበ ድረስ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ፍርድ አለ። (ሰበር መዝገብ ቁ 83674)

ይህ ማለት ውሉ የሚጸናው በእነሱ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሆኖ ሊቀርብ ግን አይችልም። ምን ማለት ነው፣ አንድ ሰው ቤቱን በመንደር ውል ቢሸጥና ውል ለማፍረስ ፍርድ ቤት ቢሄድ ገዥ ገንዘቡን ለመክፈል ይገደዳል። ሻጭም ቤቱን ለመስጠት ይገደዳል። ሆኖም ግን፣ ለምሳሌ ባንክ በቤቱ ላይ ጥያቄ ቢኖረው የመንደር ውሉ አይጸናበትም። ወይም ደግሞ ሻጭ ላይ ባለ ዕዳ የሆነ ሰው ዕዳዬ ቤቱ ተሸጦ ይከፈለኝ ቢል ቤቱ ተሸጧልና አይከፈልህም ሊባል አይችልም። ምክንያቱም በመንደር ውል ስለተሸጠ። አደጋውም እዚህ ላይ ነው። ገዢው የመንደር ውሉን ይዞ "እኔ እኮ ይሄን ቤት ገዝቼዋለሁ" ብሎ ጥያቄ ያነሱ ሦስተኛ ወገኖችን ዝም ሊያሰኛቸው አይችልም። ስለዚህ ገዢ በመንደር ውል መፈራረሙ ወዶና ፈቅዶ በራሱ ላይ አደገኛ አደጋን ጋብዟል::

ተዋዋዮች የመንደር ውልን ለምን ተመራጭ ያደርጋሉ❓

አሁን አሁን የተለመደው አሰራር ገዥና ሻጭ ውል የሚፈጽሙት በሁለት ዙር ነው። መጀመሪያ በመንደር ውል ይፈጣጠሙና ነው ወደ ሁለተኛ ውል አዋዋይ ዘንድ የሚመጡት። ብዙውን ጊዜ አንድ ቤት ስንት እንደተሸጠ በትክክል የሚታወቀውም በመንደር ውል ላይ እንጂ በትክክለኛው ውል ላይ አይደለም።

ተዋዋዮች ወደ መንግሥት ተቋማት ሄደው የሚዋውሉት በ2ኛ ደረጃ ነው። ይህን ሲያደርጉም ብዙውን ጊዜ ዋጋ ቀንሰው ነው። ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ትክክለኛ ዋጋ ተናግረው የሚዋዋሉት። መንግሥት ቢቸግረው ተመን አውጥቶ ያስክፍላል። 6 በመቶ አሹራ ትከፍላለህ። የተዋዋልከው ከተመኑ ከፍ ካለ በተዋዋልከው ያስከፍላል። ዝቅ ካለ ደግሞ በተመኑ ያስከፍላል።

በሁለት ዓይነት ዋጋ መፈራረም የሚያመጣው አደጋ ስምምነት ሲፈርስ ነው። አንድ ሰው ለምሳሌ ውል ይፍረስልኝ ብሎ ፍርድ ቤት ሲሄድ ውል ይፈርሳል። ውል ሲፈርስ ደግሞ ወደነበረበት ነው የሚመለሰው። ሻጭ ገንዘብ ይመልሳል፣ ገዥ ንብረቱን ይመልሳል።

በአሥር ሚሊዮን ብር የተሸጠ ቤት ውልና ማስረጃ ባረጋገጠው ውል፣ ፍርድ ቤት ተሂዶ ውል ቢፈርስ ተዋዋዮቹ ዋጋ ዝቅ አድርገው ስለሚዋዋሉ [ለምሳሌ 6ሚሊዮን ብር] ሻጭ ገንዘብ መልስ ይባላል። ይህን ጊዜ እንዲመልስ የሚገደደው በውልና ማስረጃ በገዛበትን ገንዘብ ነው። ይህ ማለት ገዥ 4 ሚሊዮን ብር ከሰረ ማለት አይደል?

በመሆኑም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረጉ የሽያጭ ውሎች በጽሑፍ ብቻ ሳይሆን  በአዋዋይ ወይም ፍርድ ቤት ፊት መከናወን ይገባቸዋል፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ; የማረጋገጥ መስፈርት ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት እንዲኖረው ብቻ መከናወን ያለበት ሳይሆን ውሉ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ውጤት እንዲኖረውም ጭምር መከናወን ያለበት ነው፡፡
rel='nofollow'>Http://t.me/judgeoffed

Показано 20 последних публикаций.