⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Право


ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Право
Статистика
Фильтр публикаций








ዕድር ዉስጥ ያለዉን ማህበራዊ መስተጋብር በህግና በአሰራር መሸርሸር እንደማይገባ ተጠቆመ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማይቱ የሚገኙ ዕድሮች እና የዕድር ምክር ቤቶች ተመዝግበው “ሕጋዊ እውቅና” እንዲያገኙ የሚያስገድድ መመሪያ ባሳለፍነዉ ወር ማዉጣቱ ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያዊያን  ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠዉ እና የማህበራዊ መስተጋብር ዉጤት የሆነዉን እድር  በህግና በስረአት ማስቀጠል የሚበረታታ ቢሆንም ለአሰራር ተብለዉ የሚወጡ ህጎች እና ደንቦች  ማህበራዊ መስተጋብሩን የሚያጠፉ ቢሮክራሲ የሚታይባቸዉ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

ህጋዊ አካሄድን መከተላቸዉ የሚበረታታ ቢሆንም በህጋዊነት ስም ማህበራዊ መስተጋብሮችን ሊያደበዝዙ የሚችሉ አተገባበሮች ላይ ግን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ያስገነዘቡት የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዉ አቶ ቴዎድሮስ አዱኛ ናቸዉ፡፡

ከተማዋ የሴቶች፣ የህጻናት እና የማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ያወጣው ይህ መመሪያ የጸደቀው ባለፈው የካቲት ወር ሲሆን፣መመሪያው ከዚህ በፊት የነበረውን የሰርኩላር የፈቃድ አሰጣጥ እንደሚሻር መግቢያው ላይ ሰፍሯል።

የመመሪያዉ መዉጣት ለምን አስፈለlገ ስንል የሴቶች ህጻናትና የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮን ጠይቀናል፡፡ በነበረዉ አሰራር ቅሬታ የሚያቀርቡና ከማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ይልቅ የግለሰቦች ተጠቃሚነት የጎላ እንደሆነ የሚጠቁሙ ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ለቢሮ ሲደርሱት እንደነበርና ችግሩ እንዲቀረፍ ለማድረግ  መመሪያ ማዉጣት አስገላገጊ ሆነ ስለተገኘ ያንን ተግባራዊ ማድረጋቸዉን የቢሮዉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሃደጉ ጸሃዬ ተናግረዋል፡፡

መመርያው ተፈጻሚ የሚሆነው በአዲስ አበባ ከተማ ሥር በሚገኙ ዕድሮችና የዕድር ምክር ቤቶች ላይ ሲሆን፣ የማስፈጸም ሥራውን የሚያከናውነው ቢሮው የምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት፣ ችግሮችን መፍታት፣ መረጃዎችን መሰብሰብ፣ የፋይናንስ አስተዳደር አደረጃጀትን ማጠናከርና ማገዝ፣ እንዲሁም ወደ ልማት የሚገቡበት መንገድ የማመቻቸት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይህ አሰራር የእድሮችን ማህበራዊ መስተጋብር የሚያደበዝ ነዉ በሚል  ከብዙዎች ተቃዉሞ ገጥሞታል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ
👇👇👇
የመመሪያው እንግሊዝኛ ቅጂ ተያይዟል




Репост из: ⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖
ሰበር መ/ቁ/201427 /7 ዳኛ በአብላጫ ድመጽ የተወሰነ-3/4/ -(ያልታተመ)

Daniel Fikadu

በመሰረቱ ይርጋ መብትን እና መብት ለማስከበር የሚቀርብ ክስ/limitation of action/ ቀሪ የማድረግ ዉጤት ያለዉ የህግ ጽንሰ ሃሳብ ነዉ፡፡የይርጋ ደንብ /period of limitation/ ዓይነተኛ ዓላማ እና ዝርዝር አፈጻጸሙ የተለያየ ቢሆንም በጥቅለ ሲታይ አንድ ባለመብት በህጉ በተገለጸ ጊዜ ገደብ ዉስጥ በመብቱ ባለመስራቱ የመብት ጥያቄዉ በጊዜ ማለፍ ምክንያት ቀሪ የሚሆንበት ሲሆን በሌላ በኩል ሌላዉን ወገን ባለመብት የማድረግ ወይም ግዴታዉን ቀሪ የማድረግ ዉጤት ያለዉ ነዉ፡፡በሌላ አገላለጽ የይርጋ ደንብ ጽንሰ ሃሳብ በሶስት ተከፍል ሊታይ ይችላል፡፡አንደኛዉ ዓይነት የይርጋ ደንብ በህግ የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላ የፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ (ዳኝነት) ተቀባይነት እንዳይኖረዉ የሚያደርግ (የሚከለክል) ወይም ዳኝነት ጥያቄ በጊዜዉ ባለመቅረቡ ምክንያት ብቻ ክሱ ቀሪ ነዉ /limitation of action/ የሚባለዉ ሲሆን በፍትሃብሐር ህግ ቁጥር 1845 የተደነገገዉ ዓይነት ነዉ፡፡ይህ ማለት ባለመብቱ ወይም ባለገንዘቡ በህግ በተመለከተዉ ጊዜ ዉስጥ መብቱን ባለመጠየቁ ጥያቄ የማቅረብ መብቱን የሚያሣጣዉ ሲሆን በሌላ በኩል ከባለ ግዴታዉ አንጻር ሲታይ ግዴታ አስቀሪ (liberative prescrption) ተብሎ የሚገለጸዉ ነዉ፡፡ደንቡ የሚያገለግለዉ አንድ ግዴታ ከዉል ይሁን ከዉል ዉጭ የመነጨም ቢሆን ግዴታዉ መጠየቅ ባለበት ጊዜ ዉስጥ ባለመጠየቁ ግዴታ ያለበት ወገን ዝንተ ዓለም እያሰበ እንዳይኖር የሚከለከል ነዉ፡፡ሁለተኛዉ የይርጋ ደንብ አንድ ሰዉ ያልነበረዉን መብት የሚያጎናጽፍ ወይም የሚያሥገኝ (acquisitive prescription) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ደንብ መሰረት ያለማንም ከልካይ ወይም ጠያቂ አንድን ንብረት በህግ ለተወሰነ ጊዜ ይዞታዉ ስር አድርጎ ሌሎች የህግ መስፈርቶችን እያሟላ በመጠቀም በንብረቱ ላይ የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት መብት የሚያገኝበት ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1168 ድንጋጌ ተጠቃሽ ነዉ፡፡ሶስተኛዉ ዓይነት የይርጋ ደንብ ተብሎ የሚወሰደዉ ባለ ንብረቱ በንብረቱ ለተወሰነ ጊዜ ባለመጠቀዉ ወይም ንብረቱን ይዞ ባለመገኘቱ የባለቤትነት ወይም የባለይዞታነት መብት የሚያሣጣ (extinictive perscription) መሆኑን የሚያመለከት ደንብ ነዉ፡፡በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1192 ድንጋጌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ባጠቃላይ የይርጋ ደንብ ዓይነተኛ ዓላማ ባለመብቱ ዳተኛ እንዳይሆን ማስጠንቀቅ ሲሆን በሌላ በኩሌ ከዉል ወይም ከህግ የመነጨ ግዴታ ያለበት ወገን በህግ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በህግ እንደማይገደድ ብሎም መብት ላልነበረዉ ሰዉ መብት የሚሰጥ ተብል የሚወሰድ የህግ ጽንሰ ሀሳብ የያዘ ነዉ፡፡
በተሻሻለው የአማራ ብ/ክ/መ/ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 252/09 ስለ ይርጋ የሚደነግገዉ አንቀጽ 55 ላይ የገጠር መሬትን በወረራ /invasion/ ወይም በሌላ በማናቸውም ህገወጥ መንገድ /in any illegal means/ ይዞ በመገልገል ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው መሬቱን እንዲለቅ በማንኛውም ሰው ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አስተዳደር አካል ሲጠየቅ ወይም በመደበኛ ፍርድ ቤት ሲከሰስ የይርጋ ጊዜ ገደብን በመቃወሚያነት ሊያነሳ እንደማይችል ይደነግጋል። በተያዘው ጉዳይም ክሱ በይርጋ እንደማይታገድ በአብላጫው ድምጽ አቋም ተይዞበታል።
አነስተኛው ድምጽ የተለዩት ዳኞች በሰ/መ/ቁ 178927 ቅጽ 24 የተሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም በገጠር መሬት ይዞታ ይገባኛል ክርክር ተከሳሽ የሆነ ወገን የይርጋ መቃወሚያ ለማንሳት መሬቱን በሕግ መሠረት በሚመለከተው የአስተዳደር አካል ተፈቅዶለት በሕጋዊ መንገድ ወይም በከሳሽ ፈቃድ የያዘው ስለመሆኑ አስቀድሞ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት ተብሏል።ተከራካሪ ወገኖች መብታቸውን በተዘረጋው ሥርዓት አግባብ ካልተጠቀሙ መብታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ ሥነ-ሥርዓታዊ ፍትሕ /procedural justice/ በተመሳሳይ በመሠረታዊ ሕግ እንደተመለከተው መብትና ፍትሕ /substantive justice/ መከበርና መተግበር አለበት፡፡ አንደን ከአንደ ማበላለጥ ሆነ አንደኛውን የፍትሕ ዘንግ ለማስከበር ሌላኛውን መጣስ ተገቢ አይደለም፡፡
አነስተኛው ድምጽ ይህ የህግ ትርጉም መቀየር እንዳለበት አቋም የያዘ ሲሆን አብላጫው ድምጽ ግን ትርጉሙ ይጣጣማል እንጂ አይጋጭም የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል።
// በተጨማሪ የተነሱ ህጎችና የሰበር ውሳኔዎች የፌዴራሌ የገጠር መሬት አዋጅ ቁጥር 456/1997 አንቀጽ 59(2)፣ የፍ/ብ/ህግ/1853 ፣1854 እና 1856፣ሰበር መ/ቁ 69302//
ሙሉ ውሳኔውን
👇👇👇
https://t.me/c/1417001658/3312


🙏🙏ትክክለኛ እይታ 🙏🙏


የሰነድ ማስረጃ በማይመሳከርበት አቤቱታና ፍርድ ብቻ ተያይዞ በሚቀርብበት ሰበር ችሎት መዝገብ ለመክፈት ከግማሽ ቀን በላይ ይወስዳል።
አጣሪ ሦስት ዳኞች ጋር ለመቅረብ 3 ወር ቀጠሮ ይሰጣል።በሦስት ዳኞች ያስቀርባል ከተባለ በኃላ ደግሞ አምስት ዳኞች ጋር ቀርቦ በድጋሚ ለማስረዳት 4 ወር ከ15 ቀን ይቀጠራል። በጥቅሉ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም ለማለት ብቻ ሰባት ወር ከ15 ቀን እየወሰደ ይገኛል።
ወደ ኃላ የተመለስንበት ምክንያት ምንድን ነው?


በግብር እፎይታ ላይ ያለ ድርጅት
*
በግብ
ር እፎይታ ላይ ያለ ድርጅት ያገኘውን የተጣራ ትርፍ ለባለአክሲዮኖች ካከፋፈለ ወይም የተጣራ ትርፉን ለካፒታል ማሳደጊያነት ካላዋለው ወይም ለባለእክሲዮኖች ካላከፋፈለው በአዋጁ መሠረት ሊከፈል የሚገባውን ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡

ስለህብረት ስራ ማህበራት የግብር አከፋፋል ሁኔታ
****
1. የህብረት ስራ ማህበር ካገኘው ትርፍ ላይ 30 በመቶውን ለካፒታል ማሳደጊያ ካዋለው በኃላ የተረፈውን ትርፍ ግለሰብ ላልሆኑ አባላት የሚያከፋፍል ሲሆን ግለሰብ ላልሆኑ አባላት የሚያከፋፍለው ትርፍ ከትርፍ ድርሻ ግብር ነፃ ነው፡፡ ሆኖም ግለሰብ ለሆኑ አባላት የሚከፋፈለው የትርፍ ድርሻ ግብር ይከፈልበታል። 

2. የሕብረት ስራ ማህበር አባላት ያገኙትን ትርፍ ለካፒታል ማሳደጊያ የሚያውሉት ከሆነ ይህን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከህብረት ስራ ኤጀንሲ ወይም አግባብነት ካለው አካል በማቅረብ ካልተከፋፋለ ትርፍ ግብር ነጻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

3. የኅብረት ሥራ ማህበራት ግለሰብ ለሆኑ አባላት ባልተከፋፈለ የትርፍ ድርሻ ላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁት የኅብረት ሥራ ማህበሩ ሂሳብ ኦዲት ከተደረገ በኋላ ባለው የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ለታክስ ባለሥልጣኑ ካላቀረቡ ነው፡፡
#MOR




ሚሊተሪ ለብሶ ቪዲዮ መስራት ያስቀጣል‼️
የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከተሰጣቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ ቪዲዮ በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ‼️
የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከሰጠኋቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ በማህበራዊ ትሥሥር ገጾች ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ።

አሁን ላይ በስፋት በተለይም ቲክቶክ የተሰኘ መተግበሪያን በመጠቀም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እውቅና እና ፍቃድ ውጭ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያጋሩ የፖሊስ አባላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ተቋሙ ገልጿል።

ተቋሙ ወጣቱን ተደራሽ ለማድረግ በተለይ ቲክቶክን ተጠቅሞ አስተማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያሰራቸው አባላት እንዳሉት ገልፆ ከእነሱ ውጭ ባሉት ላይ ግን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።

ድርጊቱ ከደመወዝ ቅጣት እስከ ሥራ መባረር የደረሰ ቅጣት እንደሚያስከትልና እስከአሁንም ቅጣት የተጣለባቸው እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዱ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል::

አንዳንድ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተቋሙን እና የአባላቱን ክብር የማይመጥንና በማህበረሰቡም ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ በመሆኑ ይህን ለማስተካከል ይሰራልም ነው ያሉት።

የማህበረሰቡን ሞራል የማይነኩ እንዲሁም ሃይማኖትና ፖለቲካ ውስጥ የማይገቡ ቪዲዮዎችን የሰሩና ከተቋሙ የማረጋገጫ ፍቃድ ያገኙት ግን ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማጋራት ይችላሉ ብለዋል።


የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ ፮፻፳፪ (622) በንፅህና ክብር ላይ የሚፈፀም የኃይል ድርጊት ማንም ሰው ተቃራኒ ጾታ ያለውን ሰው በኃይል፣ በብርቱ ዛቻ ወይም በማናቸውም ሌላ
መንገድ መቃወም እንዳይችል ካደረገው በኋላ ግብረ ሥጋ ግንኙነት የመሰለን ተግባር ወይም ማናቸውንም ሌላ ዓይነት ለንጽሕና ክብር ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዲፈጽም ወይም ለመፈጸም እሺ እንዲል ያስገደደ እንደሆነ፤ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ወይም ከአንድ ዓመት በማያንስ ቀላል እሥራት ይቀጣል፡፡!


#update

" ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ይግባኝ በመጠየቅ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተደርጓል" - የወምበራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

" ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና ጉዳዩ በኮሚቴ ተጣርቶ እንዲቀርብ ትእዛዝ ተሰጥቷል " - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

በወምበራ ወረዳ ፍ/ቤት ከዚህ ቀደም ስሙ ያልተጠቀሰው ' ተክለአብ ገለታ ' የተባለው ተከሳሽ የ5 አመት ህጻን ልጅ በመድፈር ወንጀል ተከስሶ #በ6ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ አግባብ አለመሆኑንና አስተማሪነቱን ባለመቀበል ዓቃቢ ህግ በፍርድ ቤቱ በኩል ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ #ይግባኝ መጠየቁን የወምበራ ወረዳ ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ አመንቴ ገልፀዋል።

ጉዳዩን አስመልክተው ለወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ማብራሪያ የሰጡት የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ የወረዳው ፍርድ ቤት ባስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተመጣጣኝና አስተማሪ ባለመሆኑ ይግባኝ ተጠይቆ ክሱ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እየታየ መሆኑን  አስረድተዋል።

ይህንን ተከትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመዝገቡን የክስ ሂደት ማጣራትና ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ወደ መተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ኮሚቴ በመላክ ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ኮሚቴ መላኩን አሳውቋል።

ጠቅላይ ፍ/ቤቱ " ይህንን የፍርድ ዉሳኔ የሰጠዉ ዳኛ ከስራና ከደመወዝ ታግዶ እንዲቆይና በኮሚቴዉ ጉዳዩ  ተጣርቶ ሲቀርብ ቀጣይ በዲስፕሊን ታይቶ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወሰዳል " ብሏል።

የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ቅጣት ማነስ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በመተከል ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እየታየ መሆኑን ያረጋገጠው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጠውን ዉሳኔ በቀጣይ መረጃዉን ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከወምበራ ኮሚኒኬሽን እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዳገኘው ያሳውቃል።

@TikvahethMagazine


የአደገኛ ቦዘኔ መቆጣጠሪያ አዋጅ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ቀረበበት

መንግሥት አደገኛ ቦዘኔነት ‹‹እየጨመረና እየተስፋፋ›› በመሄድ ላይ ነው በማለት ከ20 ዓመታት በፊት ባወጣው የአደገኛ ቦዘኔ መቆጣጠሪያ አዋጅ ውስጥ፣ የዋስትና መብትን የሚነፍገው ድንጋጌ ሕገ መንግሥቱን የሚሰጥ ነው ተብሎ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ቀረበበት፡፡

አደገኛ ቦዘኔነትን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ 384/96 አንቀጽ ስድስት ንዑስ አንቀጽ ሦስት በአደገኛ ቦዘኔነት ተጠርጥሮ የተያዘ ሰው በዋስትና አይለቀቅም ተብሎ ተደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ ሕገ መንግሥቱን ይቃረናል የሚል አቤቱታ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የቀረበ ሲሆን፣ ጉባዔው ከሰሞኑ ከሕግ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዶበታል፡፡

የአዋጁ አንቀጽ ሕገ ወንግሥቱን ይቃረናል በሚል የሕገ መንግሥት ትርጉም ይሰጥልን በሚል ያቀረበው ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ችሎት ነው፡፡

በውይይቱ የተሳተፉ የሕግ ባለሙዎች የተጠቀሰው አዋጅ የዋስትና መብትን መከልከሉ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 6 ላይ የተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት አላቸው የሚለውንና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 ሥር የተዘረዘሩትን መብቶች ይቃረናል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ባለሙያዎቹ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 መሠረት ዜጎች በፖለቲካ በማኅበራዊ አመጣጣቸው፣ በሀብት፣ በትውልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳይደረግባቸው ሰዎች ሁሉ እኩልና ተጨባጭ የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት አላቸው የሚለውን ድንጋጌ በማንሳት ተከራክረዋል፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህሩ አቶ ሙሴ መዝገቡ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ አንድን መብት ለመገደብ ቅቡልነት ያለው ዓላማ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ በአዋጁ መግቢያ ላይ የቀረበው ዓላማ የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ የሚለው ቅቡልነት ቢኖረውም ከዕርምጃ ጋር በተገናኘ ግን የወንጀል ዓይነትና ክብደትን መሠረት አድርጎ ዋስትናን መከልከል እንደ ቅቡልነት የሚታይ አይደለም ብለዋል፡፡

የሕጋዊነት መርህ በሚል ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ አንድ ሕግ ግልጽና ተደራሽ መሆን እንዳለበት ቢደነገግም፣ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ስድስት ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ በአደገኛ ቦዘኔነት በሚገባ የተጠረጠረ በሚል የቀረበው አሻሚ የሆነ ጉዳይ ስለመሆኑ ያብራራሉ፡፡

ከሕግ ባለሙያ ለሰብዓዊ መብቶች ድርጅት የመጡ ተወካይ በበኩላቸው ዋስትናን የሚከለክለው ሕግ ፍትሐዊነቱ፣ ምክንያታዊነቱና ተገቢነቱን ትክክለኛነቱ ተፈትሾ በተገቢው መለኪያ ተገምግሞ፣ በተለይም በሕገ መንግሥቱ ከተቀመጡት ድንጎጌዎች አንፃር ታይቶ በሕጉ እንዲሳኩ ከሚፈለጉ ትልሞች አንፃር ሊፈተሽ ይገባል ብለዋል፡፡ በማብራሪያቸው በዋስ የመፈታት መብት በአገሪቱ ሕገ መንግሥትም ይሁን ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ተገቢነት ባላቸው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች ሕጎች አንፃር በመርህ ደረጃ የተቀመጠ ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ማንኛውም የፌዴራልም ይሁን የክልል አካል ሕገ መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ግዴታ እንዳለበት መደንገጉን ገልጸዋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን የዋስትና መርህና የተያዙ ሰዎች መብት ሕግ አውጪው አካል በቀላሉ ሕግ አውጥቶ የሚነፍገውና የሚከለክለው የሚችለው አይደለም ብለዋል፡፡ ለፍርድ ቤቶች ሥልጣን የማይሰጥ ከሆነ ሕግ አውጪው ሕጎችን በቀላሉ እያወጣ መብቶች እንዲጥሱ የሚያደርግ መሆኑን፣ ሕግ አውጪው በሕገ መንግሥቱ የተሰጡ መብቶችን ሊነፍግ አይገባም የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ይህ ሁኔታ ከቀጠለና በአደገኛ ቦዘኔነት የሚጠረጠሩ ሰዎች ዋስትና የሚከለከሉ ከሆነ፣ በተመሳሳይ አሠራር ነገም በስርቆትና በመሰል ጉዳዮች ላይ የዋስትና መብት እንዲነፈግ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ከኦሮሚያ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የመጡ ተሳታፊ በተመሳሳይ ሕገ መንግሥቱ የግል ሕይወት የመከበርና የመጠበቅ መብት፣ እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9 ንዑስ አንድ ላይ ሕገ መንግሥቱ የአገሪቱ የበላይ ሕግ ስለመሆኑ የተደነገገውን የሚጥስና አዋጁ ዜጎችን ለይቶ የመብት ክልከላ የሚያደርግ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡

የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ተወካዮች በበኩላቸው ሕገ መንግሥቱ የዋስትና መብት ሊከለክል እንደሚችል፣ ነገር ግን በዘፈቀደ እንዳይሆን ደግሞ የአዋጁ ዓላማ የተቀመጠ በመሆኑ የዋስትና መብትን የሚጥስ ነው የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

አደገኛ ቦዘኔን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ላይ የቀረበው የዋስትና መብትን የሚከለክለው ድንጋጌ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብት ይጥሳል የሚል እምነት እንደሌላቸው፣ አዋጁ ሕገ መንግሥታዊ ነው በሚል መልስ የሰጡት ደግሞ የፍትሕ ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ተወካይ አቶ ሙሉቀን ካሳው ናቸው፡፡

በቀጣይ አጣሪ ጉባዔው የቀረቡትን ሐሳቦችና አስተያየቶች ተመልክቶ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ከሆነ ውሳኔውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚልከው ሲሆን፣ የትርጉም ችግር የለበትም ተብሎ ከተወሰነ ደግሞ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ችሎት መልስ እንደሚሰጥበት ተገልጿል፡፡ #reporter




Репост из: ቀለሜ
LAW COC Dilla keleme_2013.pdf
231.2Кб
📖 Law Coc Exam.

🏢 University :- Dilla.

━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @Keleme_2013
                       @Keleme_2013


University of Luxembourg 🇱🇺 Scholarship 2024-25 (Apply Now)

Admissions and Scholarship open for Academic Year 2024-25. Open to all Nationals.

No IELTS | Easy Access | Low Tuition Fee | Part Time Jobs.

Deadline: 29th March

Visit: https://opportunitiescorners.com/university-of-luxembourg-scholarships/

#Study #OpportunitiesCorners




994_የቅመማ_ቅመም_ምርት_ጥራት_ቁጥጥር_እና_ግብይት_መመሪያ_ቁጥር_994_2016_1_Stamped.pdf
1.2Мб
https://t.me/lawethiopiacomment ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of Law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com
Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel


Репост из: Ethiopian Law
የደቡብ_ምእራብ_ክልል_የተጠቃለሉ_አዋጆች.pdf
4.3Мб
የክልሉን አዋጆች ማግኘት ለተቸገራችሁ በሙሉ፤ አዲስ ስራ ይዘንላችሁ መጥተናል

በደቡብ ምእራብ ክልል በ2014 እና 2015 የወጡ አዋጆችን በአንድ ጥራዝ በማጠቃለል በዚህ መልኩ ለአጠቃቀም ምቹ አድርገን አዘጋጅተንላችኋል፤ እያወረዳችሁ እንድትጠቀሙና ለሌሎችም እንድታጋሩ አደራ እንላለን፡፡ ቀጣይ የሚወጡትንም በማሰባሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን፡፡

#ደቡብምእራብ #ክልል #ሕገመንግስት #SouthWest #Ethiopia #Constitution
#Abdurahman #አብዱራህማን #law #አዋጅ #የተጠቃለሉ #አዋጆች

https://t.me/abdurahmanlawinfocenter19792015

We believe knowledge is power. Here you will find updated laws, legal informations, articles and books on various legal topics.

Join our channel and find out how we can help you stay up-to-date on the law.

Показано 20 последних публикаций.