Ethiopian Lottery Service/የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት/


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Букмекерство


To have alternative communication channel

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Букмекерство
Статистика
Фильтр публикаций


እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አድማስ ዲጅታል ሎተሪ 27ኛ ዙር ዕጣ ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በእድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል


የባህርዳር ነዋሪው 1,000,000 /አንድ ሚሊየን/ ብር ተሸለሙ !
አቶ አዳነ ካሳሁን የባህርዳር ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የዕለተለት ስራቸውን ሲከውኑ ሎተሪ የመቁረጥ ልማድ አላቸው ፡፡ እንደ ተለመደው የትንሳኤ ሎተሪ በገበያ ላይ ነበርና ቀኑን በደምብ ባላስታወሱት ጠዋት ወደስራ ሲሄዱ ፊትለፊታቸው የሎተሪ አዟሪ ያገኙና የትንሳኤ ሎተሪ ቲኬትን በመቁረጥ ምንም እንዳልተፈጠረ ኪሳቸው ውስጥ ከተው ይሄዳሉ ፡፡ አቶ አዳነ ገንዘቤን አውጥቸ እስከገዛሁት ድረስ የተወሰነ ጊዜ ሰጥቸ የገዛሁትን ሎተሪ የማስተያየት ልምዱ አለኝ ይላሉ ፡፡ ታዲያ የገዙትን የትንሳኤ የሎተሪ ቲኬት ሰያስተያዩት የ1ሚሊየን ብር መኖሩን በማረጋገጥ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ድረስ በመምጣት ሽልማታቸውን ተረክበዋል ፡፡


ሁለት ሚሊየን ብር ለጡረተኛው !
የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጥለሁን ረታ ጡረተኛ ሲሆኑ የረጅም ዓመታት የሎተሪ ደንበኛ ናቸው ፡፡ ታዲያ ሎተሪ እና እድል የሚገናኙት ተስፋ ባለመቁረጥ ቲኬቱን በመግዛት ነውና አቶ ጥላሁንም በቆረጡት የ2016 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በ4ኛው ዕጣ የ2ሚሊየን ብር ዕድለኛ አድርጓቸዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ በጅምር ላይ ያለውና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ቆሞ የነበረውን የመኖሪያ ቤታቸው እንደሚያጠናቁቁበት ገልጸዋል ፡፡


ህገ-ወጥ ሎተሪ የሚያጫውቱ ተቀጡ
አዲስ አበባ ውስጥ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የህገ-ወጥ ሎተሪ ሲያጫውቱ በተገኙ ግለሰቦች ላይ የእስረትና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነባቸው፡፡
የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አዲስ ከተማ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም፣ መስከረም 3 እና 5 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሶስቱ ግለሰቦች ላይ በእያንዳንዳቸው ላይ በሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ፣ የአንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ከ2,500 እስከ 18,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ የፀና ፈቃድ ሳይኖር የሎተሪ ጨዋታ ማጫወት የሚከለክሉትን አንቀጾች በመጣሳቸው በፈፀሙት ወንጀል አቶ ዘውዱ ውባለም ወረታ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 18,000 ብር፣ አቶ ሽኩር ወርቁ ደረጀ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 2,500 ብር እንዲሁም አቶ ማሙሽ ደሬሎ ጫላ አንድ ዓመት ከስምንት ወር እስራትና ብር 2,500 ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ በህገወጥ የሎተሪ አጫዋቾች ላይ የሚተላለፉ የፍርድቤት ውሳኔዎችን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡


ኦሞራቴ
አቻው ቶቶሊክ ‘የኦሞራቴ ከተማ ስለኔ እያወራ ነው’ አለን በዚህ ሳምንት ቢሯችን ተገኝቶ
‘በምን ጉዳይ?’ ጠየቅነው
‘አድማስ ሎተሪ ስለደረሰኝ’ መለሰልን
አሞራቴ የት አካባቢ የምትገኝ ናት? ከአዲስ አበባ 720 ኪሎ ሜትር፤ ከጂንካ 150 ኪሎ ሜትር፤ ከቱርሚ ከተማ ደግሞ 72 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለች፤ ረጃጅም ጥቅጥቅ ያሉ የሳቫና ሳሮችን አልፈው በኦሞ ወንዝ ምስራቃዊ ዳርቻ ኬንያ ደንበር ሊደርሱ ሲሉ የአሞራቴ ከተማን ያገኟታል፡፡
የአሞራቴ ከተማ ነዋሪው ወጣት አቻው ቶቶሊክ በአድማስ ዲጂታል ሎተሪ 26ኛው ዙር በ9ኛ እጣ 75ሺህ ብር ዕድለኛ ሆኗል፡፡
በከተማዋ ግብርና መስሪያ ቤት የግብርና ባለሙያ ሆኖ የሚሰራወ የ25 አመቱ አቻው ስለዕድሉ ስንጠይቀው ‘የኦሞራቴ ከተማ ነዋሪ እድለኛ መሆኔን ከሰማ ዕለት ጀምሮ የአድማስ ሎተሪን በብዛት እየቆረጠ ነው፤ዕድለኛ በመሆኔ ብቻ ሳይሆን አድማስ ሎተሪን ለኦሞራቴ ከተማ ነዋሪዎች በማስተዋወቄ ደስተኛ ነኝ’ ብሎናል
የአድማስ ዕድለኞች ከአድማስ ጥግ እስከ አድማስ ጥግ ከሚገኙ ከተሞችና ገጠሮች የሚመጡ ናቸው፡፡ ሞባይል ባለበት ቦታ ሁሉ ከትላልቅ ከተሞች ብቻ ሳይሆን ከትናንሽ ከተሞችም ዕድለኛ ሆነው ይመጣሉ፡፡ የራያ ቆቦ፣ የወናጎ፣ የአለታ ወንዶ፣ የእንጅባራ፣ የስማዳ፣ የታች አርማጭሆና ሌሎች እድለኞች ከሃገራችን ራቅ ያለ ከተማ እና ገጠር ዕድለኛ የሆኑ ናቸው፡፡


አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 27 ዛሬ ከለሊቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል፡፡ ምንም ጊዜ ሳያጠፉ ዕድልዎን ይሞክሩ፡፡ የ4 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ሽልማቶችን ለማግኘት 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር በመቁረጥ ዕድለኛ ይሁኑ፡፡የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል !


መደበኛ ሎተሪ 1721ኛ ዕጣ ዛሬ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።


አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 27ን ይቁረጡ የእጅ ስልክዎን አንስተው አሁኑኑ በመቁረጥ በቀሩት ጥቂት ቀናት ዕድልዎን ይሞክሩ፡፡ የ4 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ሽልማቶችን ለማግኘት 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር ይቁረጡ፡፡የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


አቶ ተመስገን ማርቆስ ይባላሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ በ26ኛው ዙር በአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ350ሺ ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡
አቶ ተመስገን በራይድ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚያገኙት ገቢ ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ ፡፡


አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 27 ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት፡፡ በቀሩት ጊዜዎች ዕድልዎን ደጋግመው ይሞክሩ፡፡ የ4 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ሽልማቶችን ለማግኘት አሁኑኑ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር ይቁረጡ፡፡የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር


የሀዋሳ ነዋሪው ወጣት ታምራት በቀለ በአነስተኛ የሻይቡና ንግድ የተሰማራ ሲሆን በቆረጠው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ700ሺህ ብር ዕድለኛ በመሆን ሽልማቱ ተረክበዋል ፡፡ በደረሰውም ገንዘብ ንግዱን እንደምያስፋፋበት ተናግረዋል ፡፡


አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 27 ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት፡፡ በቀሩት ጊዜዎች ዕድልዎን ደጋግመው ይሞክሩ፡፡ የ4 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች ሽልማቶችን ለማግኘት አሁኑኑ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር ይቁረጡ፡፡የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ https://t.me/lottery_service1


ወጣት ሷሊህ ማሬ ይባላል ነዋሪነቱ መተማ ሲሆን በልብስ ስፌት ይተዳደራል ፡፡ ታዲያ ወጣቱ የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የመቁረጥ ልምዱ ነበረውና ከ26ኛው ዙር አድማስ ሎተሪ የ2 ሚሊየን ብር ዕድለኛ በመሆን ሽልማቱን ተረክበዋል ፡፡


የ26ኛው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕድለኞች ሽልማታቸውን እየወሰዱ ነው ፡፡
ወጣት በለጠ ታመነ ይባላል የድሬዳዋ ነዋሪ ሲሆን በአድማስ ዲጂታል ሎተሪ 1ኛ ዕጣ የ4ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡
ወጣት በለጠ የተገኘውን የቀን ስራ በመስራት ቤተሰቡን የሚመራ ሲሆን ሁሌም በሎተሪ ተስፋ ባለመቁረጥ ሎተሪ የመሞከር ልምድ አለው ፡፡ በደረሰውም ገንዘብ ቤት እንደሚገዛበት ገልጸዋል ፡፡


ህልምዎን ዕውን ያድርጉ የ4ሚሊዮን ብር አሸናፊ ይሁኑ፣ 605 ላይ ማንኛውንም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር በ10 ብር የ4 ሚሊዮን ብር እና የሌሎችም ዕድሎች አሸናፊ ይሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ https://t.me/lottery_service1


እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የነብዩ መሀመድ የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የ27ኛ ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ በገበያ ላይ ነው ፡፡ በ605 ላይ ማንኛውም ምልክት በማድረግ ወይም በቴሌብር የ4 ሚሊዮን እና የሌሎች ዕድሎች ተሸላሚ ይሁኑ፡፡
መልካም ዕድል! መልካም በዓል !
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር

Показано 20 последних публикаций.