#የቤተሰብ ዛር
ከቤተሰብ ወርዶ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ የባዕድ አምልኮ የዛር መንፈስ ቁርኝት!
#የዛር መንፈስ ማለት በአብዛኛው ጊዜ ፈቅደን ወደን ከ ፈጠረን አምላካችን ይልቅ ክፉ የዛር መንፈስ ያዘዝከኝን አደርግልሃለሁ ያዘዝኩህን አድርግልኝ ብለን ቃል በመገባባት ከራሳችን ጋር እንደንጉስ አክብረን የምናዋሃደው መንፈስ ሲሆን።
#የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ማህበራዊ ኑሮ በመቆራኘት የሰው ልጅ ስጋውን ለብሰው ከደሙ ጋር ተዋህደው ህይወታቸውን የሚመሩ ረቂቃን መናፍስት ናቸው።
#የዛር መናፍስ ከአያት እንዲሁም ከአባት እናቶቻችን ዘንድ በደም ሐረጋችን በመውረድ ልጅን እንዲሁም የልጅ ልጅን ትልቅ ፈተና ውስጥ የሚጥሉ የከፉ መናፍስት ናቸው።
#የዛር መናፍስት ከሰው ልጅ ጋር ከመላመዳቸው የተነሳ የየእለቱ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ አብረው ስያከናውኑ ወዳልሆነ መንገድ ሲመሩ ሃገርንም ስያተራምሱ የሚኖሩ መናፍስት ናቸው።
#የዛር መናፍስቶ የተለያየ ነገድ ሲኖራቸው በየአከባቢው እና በየሀገሩ የተለያዩ ስሞችን እራሳቸውን በሚገልጽ መንገድ በመጠራት ሲመለኩ ይኖራሉ።
#የዛር መናፍስት የዓይነጥላ እና የመተት ምልክትን በመላበስ ራሳቸውን ደብቀው የሰው ልጅን በጥርጣሬ ከወዳጅ ዘመዶቹ እንዲጋጭ የማድረግ ብቃትም አላቸው።
#የዛር መናፍስት በተለያዩ የጥበብ ሰዎች በተለያዩ አባዎራዎች በተለያዩ ባልቴቶች እንዲሁም በተለያዩ ህጻናቶች በመቆራኘት ስራቸውን ስያከናውኑ ይኖራሉ።
#የዛር መናፍስት በ ተለያዩ መንገዶች ካልተገሰጹ እንዲሁም ካልተወገዱ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የመውረድ አቅም እንዳላቸው ሊቃውንት ያትታሉ።
#የዛር መናፍስት ወደው ፈቅደው ላመለክዋቸው ሰዎች እና ልጆቻቸውን ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸውን በማመዘን ለተለያዩ አካላዊ እና ስነልቦናዊ ችግር የሚዳርጉ መናፍስት ናቸው።
#የዛር መናፍስት በሰዎች ዘንድ በመላክም ሌሎች ሰዎችን የማጥቃት ክህሎትም አላቸው። ይህ ማለት ጉዳዩ አድርግልኝ ላድርግልህ ነውና!በገቡት ቃል መሰረት የተለያዩ እንስሳት በመስዋዕትነት በማቅረብ ጠላታቸውን እንድያጠቃላቸው በታዘዙበት ቅጽበት የተላከበት ሰው በጸሎት እና በሕገ እግዚአብሔር ያልጸና እንደሆነ በዛር መናፍስት የመጠቃት እድሉ እጅግ ሰፊ ነው።
#የዛር መናፍስት የሚፈጥሩት ችግር፦
፦ትዳር እንዳትይዙ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥራሉ።
፦በሰዎች ዘንድ መጠላትን ይፈጥራሉ።
፦የሰውነት ጠረን ፣የአፍ ጠረን፣- ሆድ ውስጥ መንፋት የመንቀሳቀሰ ምልክት ጨጒራን በመመሰል ትልቅ ሁከት ይፈጥራሉ።
፦ሴቶች ላይ የማህጸን ህመም፣የወገብ ህመም፣ ህልመ ሌሊት፣ፍራቻን በመጫር የህይወት ስጋት ይሆናሉ።
፦ወንዶች ላይ ህለመ ሌሊት፣ድክመተ ወሲብ እና ትዳር ማጣትን ያስከትላሉ።
፦ትልቅ የስራ ዕድል መዝጋት፣ብር አለመበርከት፣ማዛጋት ፣ማንጠራራት፣እጅ እና እግር ፓራላይዝድ አልያም ሸምቅቆ በመያዝ ችግር ይፈጥራሉ።
፦በስኳር፣በደም ግፊት ፣በሪህ በመመሰል የክኒን ሱሰኛ አድርገው ሲጫወቱብን ይኖራሉ።
፦ራስ ህመም፣በአስም፣በመካንነት ችግር ይፈጥራሉ።
፦በጣም የባሰ እንደሆነ ደግሞ ማስጎራት ፣አመድ ማስቃም ፣ጫት ፣ቡና ማሰኘት ፣የአልጋ ቁራኛ አድርገው ማሰቀመጥ የመሳሰሉት ችግሮች የመፍጠር ኃይል አላቸው።
#የዛር መናፍስት እንዴት ከእኛ ዘንስ ማራቅ እንችላለን?
#በመጀመርያ ወደ ቤተ አምልኳችን በመሔድ የተለያዩ መፍትሔዎች በታላላቅ አባቶቻችን የ እግዚአብሔር መፍትሔ መሻት።
#በመቀጠል በራስ ጊዜ ሳንሰለች በጸሎት በጾም በስግደት ስጋችንን በማድከም ያ ክፉ ያለውድ ከቤተሰብ የወረደቅ መንፈስ ማስወገድ እንችላለን።
#ይህ ሁሉ አድርገው አማራጭ እና መፍትሔ ያጡ እንደሆነ በየአከባብያችሁ ወደሚኖሩ ከ እግዚአብሔር ዘንድ ጥበብ እና ፀጋ ወደተሰጣቸው አባቶች ጎራ በማለት የ እግዚአብሔር ቃልን በመጥራት የእጽዋቶችንም ኃይል በመጠቀም አስቸጋሪ እና አሰልቺ የሆነ የዛር መንፈስን እንገስጸው እናስወግደውም።
1ኛ መፍትሔ ጧት ጧት
#ከበተሰብ የወረደ ዛርን እንዴት እናስወግደው?
#የምድር እንቧይ ሥር ቀጠል
#የደድሆ ሥር ቅጠል
#የጭቁኝ ሥር ቅጠል
#የፌጦ ፍሬ
#የደማካሴ ሥር ቅጠል
እነዚህ እጽዋቶች ሮብ እና ዓርብ በመቁረጥ አንድ ላይ በመጨቅጨቅ ጧት ጧት በአዲስ እቃ በመዘፍዘፍ ለ ፯ ቀን ያክል ሙሉ ሰውነትን መታጠብ የዛር መንፈስ ያስወግዳል።እንዲሁም ሙሉ ግቢውን ጧት ጧት ለ ፯ ቀን መርጨት።ከራስ አልፎ ጎረቤት ላይ ቢኖርም ይወገዳል።
2ኛ መፍትሔ ማታ ማታ
#ጤና አዳም ሥር ቅጠል
#ቀጠጥና (የአህያ ጀሮ) ሥር ቅጠል
#የጊዜዋ ሥር ቅጠል
#የእንቧጮ ተቀጽላ ሥር ቅጠል
እነዚህን በማድረቅ ከደረቁ በኃላ አንድ ላይ በማቀላቀል ማታ ማታ ሊተኙ ሲሉ ከተቀላቀለው በሾርባ ማንኪያ አንድ በመለካት በፍም እሳት ለ ፯ ቀን ሙሉ ሰውነትዎን እየታጠኑ መተኛት።
ቤተሰብ ሙሉውን ይህ ድርጊት በየእምነቱ እጽዋቱ ላይ በመጸለይ ቢጠቀም ከፈጣሪው ዘንድ ሙሉ መፍትሔ ያገኛል።
የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት ጠልሰም እና ጥቅማቸው በዚህ ጥበባዊ ድህረ ገጽ ይዳሰሳል።
#አምደብርሃን ይትባረክ !!!
#አድራሻችን_ቁ/1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከ አደባባይ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መሄጃ...
#አድራሻችን_ቁ/2 አ/አ ከ አየር ጤና ወደ አለም ባንክ መሄጃ በ ቤተል መገንጠያ በኩል ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት እንገኛለን
👉 የስራ ሰአት ከሰኞ -ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 11:00 ሰአት ለበለጠ መረጃ (ለሐሳብ አስተያየተዎ )
📞#0918487073
📞#0920253444
📞#0918834904 ይደውሉልን
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@mergetaamedeberhane✅ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100076378898155✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
https://t.me/mergeta_amdebrhan✅የቴሌ ግራም ቻናላችን
t.me/mergeta_amdebrhane✳️የቲክቶክ ቻናላችን
http://tiktok.com/@mergetaamdebrhan👉 ❗️❗️እውቀቱ ሳይኖራቸው በተመሳሳይ ፅሁፍ ኮፒ እያደረጉ ከሚያጭበረብሩ ሌቦች ተጠንቀቁ ሌባው በዝቷል ❗️❗️