መዝሙረ ዳዊት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🔔🔔🔔 መዝሙረ-ዳዊት 🔔🔔🔔

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ወረቦችን ትምህርቶችን ከነዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉ
@mezmurochh
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@Estifo_17 ላይ ያገኙናል

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔
         
      ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው

ገብርኤል ነው አምላክ የሾመው(2)
አናንያን አዛሪያን ሚሳኤልን ከእሳት ያዳነው

ናቡከደነፆር አንተን በግልፅ አይቶ
ለእግዚአብሔር ሰገደ ያንን ምስል ትቶ
ሃሰት እንደሆን ይመስክሩ ሶስቱ
ከዚያች ከባቢሎን(2) የወጡ ከእሳቱ

አዝ----------------

ከአለም በላይ ከቅዱሱ ቦታ
የሰውን ልጅ መረጥክ ልትረዳ ጠዋት ማታ
አንጌቤናይቷ ቅድስትዬን ይዤ ልውጣ
ትመስክር ስላንተ (2) ከነልጇ ትምጣ

አዝ----------------

ልመስክር ስላንተ ነህና ህይወቴ
ገብርኤል (2) ሰመረ ስለቴ
ያአናብስትን አፍ የዘገሀው መላክት
ገብርኤል አንተ ነህ(2) በኛ ሁሉ የታመንክ

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  💚 @mezmurochh 💚 ✥
   ✥  💛 @mezmurochh 💛 ✥
   ✥  ❤ @mezmurochh ❤ ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✞ጥር 18 ” ዝርዎተ አጽሙ ” ቅዱስ ጊዮርጊስ

✞ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉስ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኃላ እንደመጭመቂያ ሆኖ ከተሰራ የስቃይ መሳሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤

✞አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከስጋው ተለየች የሰማእቱን ሰጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን  ፈጽመው  ተመለሱ።

   ✞ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማእቱን ስጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤

  ✞ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤

  ✞ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤ በኃላም በሰማእትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን ” ዝርዎተ አጽሙ ” ስትል ቤተክርስቲያን ሰማእቱን አዘክራ ትውላለች፤

  ✞በስሙ በታነጹለት አብያተክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ህጉ ውጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል።

  ✞ አራዳ ጊዮርጊስን የተከሉት ደጉ ንጉስ እምዬ ምኒሊክ ናቸው ታዲያ የዚህን ታላቅ ደብር መሰረቱን ሲጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ከሚገኝበት ቦታ አፈሩን በመርከብ አጓጉዘው በበቀሎ በፈረስ አስጭነው መሰረት አድርገውታል፤ይህንን ከአባቶቻችን የሰማነው ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

  ✞ ✞ ✞
ለእግዚያብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ሰማዕት ፀሎት ይማረን በረከቱን ያሳድርብን አማላጅነቱ አይለየን ሰማዕት በረከት ያሳትፈን።

የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                         ✍     ✔
❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ለመቀላቀል   👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
     💚@mezmurochh💚
     💛@mezmurochh💛
     ❤@mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

        ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
         
        ቅዱስ ጊዮርጊስ አማለደን

  ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ቅዱስ ጊዮርጊስ አማለደን

ቅዱስ ጊዮርጊስ አማለደን አማለደን ከመድኃኔዓለም አስታረቀን
ማረን ይቅር አለን ማረን ይቅር አለን
አማኑኤል ታረቀን

ሹመት ለመፈለግ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ነገሥታት ዘንድ ሄዶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጣዖት ሲያመልኩ አየ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
አምላኩ ተክዶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
      
አዝ----------------

ክርስቲያን ነኝ የሚል - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዓለም ሁሉ ጠፍቶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እኔ አምናለሁ አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
የአምላኩን ስም ጠርቶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
    
አዝ----------------

የዓለም ግሳንግሷ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጸባይዋ ሳይገዛህ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለ ጌታ ፍቅር - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከእናትህ ተለየህ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
   
አዝ----------------

የመቅጫው መሳሪያ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዓይነት ተደቅኖ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እኔ አልፈራም አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በአምላኩ ተማምኖ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዝ----------------

ተፈጭቶ ተደቅቆ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደብረ ይድራስ ሳለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እጽዋቱ ሁሉ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ

       
                መላከ ሰላም
        ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  💚 @mezmurochh 💚 ✥
   ✥  💛 @mezmurochh 💛 ✥
   ✥  ❤ @mezmurochh ❤ ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


➤ ሖረ ኢየሱስ በትፍሥሕት ውስተ ከብካብ እንዘ ይገብር ተአምረ ወመንክረ በውስተ አሕዛብ ➣

ኢየሱስ በደስታ በአህዛብ መሐል ተአምራትን እያደረገ ወደ ሠርግ ሄደ

  ቅዱስ ያሬድ

✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✝️

፫ - መዝሙር ሖረ ኢየሱስ

✝️ የቅዳሴ ምንባባት ✝️

ዕብ ም ፪ ቁ ፩ - ፫
፩ ዮሐ ም ፭ ቁ ፩ - ፲፫
ግብ.ሐዋ ም ፲ ቁ ፴፬ - ፴፱

✝️ ምስባክ ✝️

እስመ መምህር ህግ ይሁብ በረከተ
ወየሐውር እምኃይል ውስተ ኃይል
ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን 

     መዝ ፹፫ - ፭

✝️ ወንጌል ✝️

ዮሐ ም ፪ ቁ ፩ - ፲፪

✝️ ቅዳሴ ✝️

ዲዮስቆሮስ

በዓሉን በዓለ በረከት ያድርግልነ ቸሩ መድኃኔዓለም ኹላችንም ይማረነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጇዋ አይለየነ በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረነ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚
@mezmurochh 💚   
           💛
@mezmurochh 💛   
           ❤
@mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

ኪዳነ_ምህረት ለኔ መመኪያዬ

 ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
            💚@mezmurochh💚   
            💛@mezmurochh💛   
            ❤@mezmurochh❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ኪዳነምህረት ለኔ

ኪዳነምህረት ለኔ መመኪያዬ
ለችግሬ ደራሽ ነሽ መጠለያዬ
ህይወቴ ጎስቁሎ በነብሴ ብዝልም
በምልጃሽ ታምኜ በኪዳንሽ ልቁም/2/

እጅግ ምስኪን ሆኜ ለሰዎች ብታይም
ሞልቶ የተረፈ ጥሪት ባይኖረኝም
አንቺ ካለሽልኝ ጓዳዬ ሙሉ ነው
አፍሮ አያውቅምና የተማፀነሽ ሰው

አዝ----------------

ዳቢሎስ እቅዱን በልቤ ቢያገባ
ተገፍቼ ባጊጥ በሰናዖር ካባ
የሐጥያን ደሞዙ እንዳይከፈለኝ
በሞት እንዳልጠፋ ድንግል ተለመኚኝ

አዝ----------------

ወገን የለኝ ዘመድ ፍፁም ካንቺ በቀር
እኔን የሚረዳ በዓለም ስቸገር
አይዞ በዪኝና ደግፊኝ እናቴ
የጸጋ ልብስ ሁኚኝ ሲራቆት ህይወቴ

አዝ----------------

ነብሴ እንድትቀደስ ከርኩሰት አምልጣ
ከሴኬም ልሰደድ ወደ ቤቴ ልውጣ
ገሪዛን ልበልሽ ድንግል መሸሻዬ
እዮአታም ልጅሽ መጣሁ አንቺን ብዬ

                        መዝሙር
                  ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥     💚 @mezmurochh 💚    ✥
   ✥     💛 @mezmurochh 💛    ✥
   ✥     ❤ @mezmurochh ❤    ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
@teksochina_meslochi
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

🕊  † አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ †  🕊

† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ [ ተስዓቱ ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-

፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ:
፪. ዓላማ [ የእግዚአብሔር መንግስት ] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አቡነ አረጋዊን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬፻፸ [470] ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች:: አቡነ አረጋዊና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አቡነ አረጋዊ እንደገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አቡነ አረጋዊ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አቡነ አረጋዊ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

- ዸንጠሌዎን በጾማዕት :
- ገሪማ በመደራ :
- ሊቃኖስ በቆናጽል :
- አባ ይምዓታ በገርዓልታ :
- ጽሕማ በጸድያ :
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
- አባ አረጋዊ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ዳሞ [እዛው ትግራይ] ሆነ::

በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ፭ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::

ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው " ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::

በዚያም በገዳመ ዳውናስ [ግብጽ] የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በሁዋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ፯ ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::

"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ፰ ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ፰ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::

በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ፬፻፸ [470]ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን [አክሱም] ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::

ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን [ደብረ ሃሌ ሉያን] አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ ፷ [60] ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::

እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በሁዋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::

ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ - የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::

ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::

ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በገዳሙ በስተ ምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም ፲፭ [15] ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::

ዛሬ ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው::

የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                         ✍     ✔
❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን


ለመቀላቀል   👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
    💚 @mezmurochh 💚
    💛 @mezmurochh 💛
    ❤ @mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛


🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት🔔🔔🔔

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

     ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሀኑ

           ቃና ዘገሊላ

  ✥ መዝሙረ ዳዊት በ ቴሌግራም ✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
   ✥ 💚 @mezmurochh 💚   ✥
   ✥ 💛 @mezmurochh 💛   ✥
   ✥ ❤ @mezmurochh ❤   ✥
   ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ቃና ዘገሊላ

ቃና ዘገሊላ /2/ በዛ በሠርግ ቤት
ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ
ተግኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ

እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ እልቆበት     
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም     
አንቺ ደረሽለት ሆንሽው አማላጅ

አዝ----------------

አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው      
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላችው     
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ      
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ

አዝ----------------

የጌታ አምላክነት የተገለፀበት      
ምንኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት      
ዛሬም ይኸው በዚህ በሠርገኞቹ ቤት     
በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት

አዝ----------------

ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን     
በቃና ገሊላ ሁላችን አየን     
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን     
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን

                መዝሙር
      ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
   ✥ 💚 @mezmurochh 💚   ✥
   ✥ 💛 @mezmurochh 💛   ✥
   ✥ ❤ @mezmurochh ❤   ✥
   ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ​​​​ቃና ዘገሊላ

በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው።

ሰርግ ደግሶ የነበረው ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።

አምላካችን ጋብቻ ክቡር መሆኑን ዓለም እንዲረዳ ያደረገበት፣ ሰዎች ያዘጋጁት ነገር ተንጠፍጥፎ አልቆ በተጨነቁ ጊዜ እመቤታችን ለልጇ አሳስባ ጎደሏቸው እንዲሞላ ፣ጭንቀታቸው እንዲወገድ የምታደርግበት በዓል ነው።

ጥንተ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ  ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።

ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው።

እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው። በዓሉን ማክበር የሚገባንም ይህን እያሰብን ነው። አምላካችን ከበዓሉ በረከት ይክፈለን።

የተሣተውን ✍ ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት     
                         ✍     ✔
❤️ስለ  ማይነገር ስጦታው   እግዚአብሔር ይመስገን ❤️

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን


ለመቀላቀል   👇
      ┏━━° •❈• ° ━━┓
    💚 @mezmurochh 💚
    💛 @mezmurochh 💛
    ❤ @mezmurochh
      ┗━━° •❈• ° ━━┛


✤ ቅዱስ ዳዊት ✤

ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙር ውስተ ጽርሐ ቤትከ

✥ ቅዱስ ያሬድ ✥

ከብካብ ኮነ ወኮነ እሙነ ወለማይኒ ረሰዮ ወይነ ዘገብረ እግዚእየ ጥዒመ አንከረ ሊቀ ምርፉቅ ማየ ረሰየ ወይነ

✟ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ✟

ገብረ ተአምራት እስከ ረሰየ ማየ ወይነ

ውኃን ጠጅ እስከ ማድረግ ድረስ ተአምራት አደረገ

✞ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ✞

ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ እግዚእ ኢየሱስ በቃና ዘገሊላ ወአርአየ ስብሐቲሁ ወአምኑ ቦቱ አርዳኢሁ

ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መዠመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ ክብሩንም ገለጠ ደቀመዛሙርቱም በርሱ አመኑ

ጥር ፲፪ በዓለ ቃና ዘገሊላ

ኀብስተ መና ፍቅሩን ወይነ ቃና ፍቅሩ ያሳድርብን ቸሩ መድኃኔዓለም ወላዲተ አምላክ ምልጃዋ ቃልኪዳኗ ይጠብቅን

ዮስጦስ ወልደ ዮሴፍ
ጵርስቅላ ወለተ ዶኪማስ ትዳር የባረካች ወላዲተ አምላክ የኹላችንም ሕይወት ትባርክልን

ደገኛ በዓል

✍️ ምኑን በኀበ ሰብእ ✍️ ፳፻፲፮ ዓ.ም


📎 ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ ' ከበበ ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር ፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ ( ይገድባሉ ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ ( ለጥር 11 ) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
   ✥ 💚 @mezmurochh 💚   ✥
   ✥ 💛 @mezmurochh 💛   ✥
   ✥ ❤ @mezmurochh ❤   ✥
   ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


👉 ስለጥምቀት በሊቃውንት ልሳን 👈

✥ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴው ✥

አንሶሰው ገሃደ ወአሰተርአየ ከመ ሰብእ በበሕቅ ልሕቀ በ፴ ክረምተ ዮርዳኖስ ተጠመቀ

በግልጥ ተመላለሰ እንደሰውም ታየ በየጥቂቱ አደገ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ

# ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በቅዳሴው #

በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠመቀ ከመ ያንጽሐነ እምኃጢአት በሕፁበት ዳግም ልደት

በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ በሁለተኛ ልደት መታጠብ ከኃጢአት ያነጻን ዘንድ

✟ ቅዱስ ሄሬኔዎስ በሃይማኖተ አበው ላይ ✟

ወአግሐዶ ዮሐንስ ወአጥመቆ በውስተ ዮርዳኖስ ተመከረ

ዮሐንስም ገለጠው በዮርዳኖስም አጠመቀው

ለጥምቀት አዲስ ልብስ የምታሰፉ አድቡ ወይ የዓምናውን ለተቸገረ ሰው እንስጥ

በዓለ ጥምቀት ክርስቶስ

☞እስኪ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተዋል የምንሔድበትን : እርሱን የምናስደስትበትን ጊዜ ይስጠን!!

መልካም በዓል!!

ከስሜት የነፃ በዓለ ጥምቀትን እናክብር

✍️ መነ ትብል ርእስከ ✍️ ፳፻፲፯ ዓ.ም


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  🔔🔔🔔 መዝሙረ ዳዊት 🔔🔔🔔

       ✧ ጥምቀተ_ባህር ✧

 ✥ መዝሙረ ዳዊት / በ ቴሌግራም/ ✥

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           💚 @mezmurochh 💚   
           💛 @mezmurochh 💛   
           ❤ @mezmurochh ❤   
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

Показано 20 последних публикаций.