ኬንያ አሰልጣኝ በይፋ ሾመች !
የኬንያ ብሔራዊ ቡድን በኤሪክ ቴን ሀግ ስር የነበረውን የማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኞች ቡድን አባል ቤኒ ማካርቲን ዋና አሰልጣኝ አድርጋ እንደሾመች አስታውቃለች፡፡
የ47 አመቱ አሰልጣኝ ማካርቲ ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝነት ህይወቱ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙትን ክለቦች ኬፕታውን ሲቲን እና አማዙሉን ማሰልጠኑ ይታወሳል፡፡
በፊፋ የዓለም የደረጃ ሰንጠረዥ 108ኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኬንያ በአሁኑ ወቅት በአለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድቡ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
አዲሱ የሀራምቤ ኮከቦቹ አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲ የመጀመሪያ ጨዋታውን የፊታችን መጋቢት ሰባት ወደ ጋምቢያ በማቅናት ከጋምቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚጫወት ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ በሜዳው የሚጫወት ይሆናል፡፡
ቤኒ ማካርቲ እ.ኤ.አ ከ1997 እስከ 2012 ድረስ 79 ጨዋታዎችን ለደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን በማድረግ 31 ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ይህም እስካሁን የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን ክብረ ወሰን በእጁ ይዟል፡፡
የቀድሞው አፍሪካዊ ኮከብ በአያክስ፤ ሴልታ ቪጎ፤ ፖርቶ፤ ብላክበርን ሮቨርስ እና ዌስተሀም ዩናይትድ በመጫወት ድንቅ ጊዜን ማሳለፉ ይታወሳል፡፡
SHARE
@MULESPORT