➾ጾመ ነነዌ
ጾመ ነነዌ በስብከተ ዮናስ የተጾመ ጾም ነው። ዮና. ፫፥፩። ሰዎችም ጉዳዩም አልፏል ብለው ለምን አልተውትም ቢሉ፥ ሐዋርያት የቀኖና ጾም ነውና ይጾም፤ ሰዎቹም የተነሳሕያን ምሳሌዎች ስለሆኑ ንስሓ ለሚገቡ ሰዎች አብነት ይሆናሉ ብለው እንዲጾም አዝዘዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ ነነዌ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ምስክር ናትና በሐዲስ ኪዳን ላሉ ሰዎች እነሱ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተው ከዳኑ፥ እኛ ከዮናስ የሚበልጥ ነቢይ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶልን ንስሓ ገብተን ባንድን ፍዳ የሚጠብቀን አይደለምን? እያሉ ራሳቸውን እንዲገሥጹበት፤ በደጅ ያለ ምስክር እንዲሆንልን ነው - ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብሎ በቀኖናችን የተቀመጠው። ማቴ. ፲፪፥፵፩። ታላቁን የጌታን ጾም ከመቀበላችን አስቀድመን መጾማችንም ስለዚህ ነው፡፡ የጾም ሰዓቱ ፱ ሰዓት ነው።
የነነዌ ከተማ በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ዳርቻ ከባግዳድ ከተማ ሰሜን ምዕራብ ፫፻፶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በናምሩድ የተቆረቆረች ታላቅ ከተማ ነበረች፡፡ ዘፍ. ፲፥፲፩-፲፪። ከተማዋ ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚረዝም ቅጥር ነበራት። የሦስት ቀን መንገድ ያህል ሰፊ ከተማ ነበረች፡፡ ዮና ፫፥፫። ሕዝቧ ጣዖት ያመልኩ ነበር። ነቢዩ ሶፎንያስ ነነዌ ጠፍታ ባድማ፣ እንደ በረሃም ደረቅ እንደምትሆን የተናገረው ትንቢት ከ፫፻ ዓመታት በኋላ ተፈጽሟል። ሶፎ. ፪፥፲፫።
ምንጭ፡- (ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን በሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ፤ ጾምና ምጽዋት በቃኘው ወልዴ)
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam #ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊