በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እየተናደ ያለው የብልፅግና ስርዓት በአስከሬን ፖለቲካ እና የፋኖ ቤተሰቦችን በማገት ታጅቦ የቁልቁለት ጉዞውን ቀጥሎበታል ። ያልተገራ በቅሎን ስራ ለማሠራት እጅግ አስቸጋሪ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ከባድ ከመሆኑም በላይ ቃጭል ከተጨመረበት ደግሞ በራሱ ጊዜ መሞቻውን ያፋጥናል ይህ ስርዓት ደንበራ በቅሎነቱ ሲያስገርመን ቃጭል ጨምሮበት ብቅ ብሎላ ።
ደንባራነቱ እመራዋለሁ ብሎ ሚያስበውን ህዝብ ከዘር ተኮር ጭፍጨፋ እስከ ዘር ተኮር መፈናቀል፣ አግቶ ብር ከመቀበል እስከ አግቶ እስከ መድፈር ፣ ነፍሰ ጡር ሴት ከመግደል እስከ ፅንስ አውጦ እስከ መጣል ፣ ባንክ ከመዝረፍ እስከ ዘርፎ እስከ መታጠቅ ፣ ቅርስ አጥፍቶ አዲስ የኗሪነት መታወቂያ እስከ መስጠት ፣ የአፄ ሚኒሊክን ፎቶ አንስቶ የራሱን ፎቶ እስከ መስቀል ፣ ከቤተክርስቲያን እስከ መስጊድ ማቃጠል ፣ ከሸሆቹ ግድየ እስከ ቀሳውስት እና መነኮሳት ግድያ ፣ የሠውን ልጅ በህይወት ከማቃጠል ዘቅዝቆ እስከ መስቀል ፣ ከፓርለማ ተወካዮች እስከ ሙሕራን እና አንቂዎች የአዋሽ አርባ እና የቃሊት የግዞት እስር ፣ ከፓለቲከኛ እሰከ ተዋቂ ድምፃዊያን ማለትም ከሐጫሉ ሆንዴሳ (ኦሮሞ) እስከ ማዲንጎ አፈወርቅ(አማራ) ፣ ከዳዊት ነጋ (ትግራይ ) እስከ ታምራት ደስታ (ደቡብ) በዋዛ ሞቶች ይቺን አለም ተሰናብዋል ።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለይ አማራ ሚባል ማንነት ላለው ህዝብ ደግሞ የገሐነብ እሳት ያክል እጅግ መራራ የግፍ እና የግዞት ጊዜን እንዳሣለፈ አሁናዊ ሁኔታዎችም ምስክር ጭምር ናቸው ።
ይሄን ሁሉ ግፍ የሰራን የአሸባሪዎች ፊት አውራሪ የምንኖርባት አለም የሠላም ሎሬት መሸለሟን ስተረዳ አለም ለተበዳዮች እንደማትቆም ከመረዳት ባለፈ ለነፃነትህ ይሄን ስርዓት ጨርሶ ለመጣል የሚያቋምህ ምክንያት እና ቤትህ እንድትቀመጥ የሚያስገድድህ አዕምሮ በፍፁም አይኖርኸም ።
ይሄን ስርዓት የተሸከመች ሀገር ዛሬ በአማራ ፋኖ ክንድ እና ከሌሎች ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያን ጋር ነፃነቷን ልታመጣ የጀመረችው የነፃነትን ጉዞ ፍለጋ የቤተ-መንግስቱን አምባገነን እስከ ግብረ አበሮቹ ከላይ እና ከታች እንደ ገና ዳቦ ማቃጠሉን ቀጥሎበታል ።
ትላንት እና ዛሬ የሐገሪቱ ምርኮኛ ጄነራሎች ኮሜዲ አዘል ስለ ፋኖ በጊዜ ልዩነት የተሰጡ የጀግና ምስክርነት እና የክህደት ገለፃዎች ፣ እንደ ህዳር አህያ የመጣ የሄደው ሲጫነው በማጨብጨብ ወደር ማይገኝለት የሮቦት ጥርቅሙ የፓርላማ አባላት ትላንትና ስለ ፋኖ ጀግንነት ያጨበጨቡበት እጅ መልሶ ስለ ፋኖ ፅንፈኝነት ሲያጨበጭቡ ፣ መሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴን ለመከረኛው ክልል ምክር ቤት ላይ ገድለነዋል ብለው መሣቂያ የሆኑት የታሪክ አተላዎች እየታዛበ ጊዚያቶቹን አሳልፏል ።
ፋኖ ከነበረው ውስን ሀይል የውስጥ ችግሮቹን እየፈታ ዛሬ ላይ ከዚህ ግዙፍ ሀይል ግንባታ ላይ ደርሷል ። ለማጥፋት የአንድ ሳምንት ቀጠሮ ብቻ ይዞ የተነሳው ወፈፌ በሶስት ኮማንድ ፖስት አራዝሞ ዛሬ 14 ወራቶችን አሳልፎ በሁሉም ዘርፍ እያስታጠቀን ይገኛል ። ለአንድ አማራ አራት ወንበር ጠባቂ ሰራዊት ቢመድብ እንኳን አማራን ማሸንፍ እንደማይችል ያውቀዋል ። ከ ደንባራነቱን ላይ ቃጭል ሲይደርብ የመውደቂያውን የመጨረሻ ፊሽካ እራሱ ነፍቶ የፋኖ ቤተሰቦችን ማገት እና ንብረት መውረስ ጀምሯል ።
አሁን ላይ ተስፋ ቢሆናቸው የመሪያችን የአርበኛ ዘመነ ካሴን የወንድም ልጅ እና ከብቶቻቸውን ጃሪ፣ ኮሎን እና ትሙላን እየነዱ መሄዳቸውን ስንሰማ ስርዓቱ መሞቱ እና የቀብር ስነ-ስረዓቱን ለመፈፀም የተዘጋጁ ቀብር አስፈፃሚዎች መሆናቸውን እንጅ የሀገር መከላከያ ናቸው ብንል ማን ሊሰማን እና ሊያምነን ይችላል ።
ያ የአማራን ህዝብን እልቆ ቢስ መከራ ያሣየው እና ጀግኖች ልጆቹን በልቶ ያለፈው ብልፅግና ወለዱ የጨለማው ስርዓት ዛሬ የነፃነት ጎህ ሊቀድ አጥቢያ ላይ ይገኛል ። የብልፅግና መገረፊያም መወገጃም የራሱ ዱላ መሆኑን ስናስረዳችሁ በኩራትም በጀግንነትም ጭምር ነው ።
የራሳችሁ ዱላ ስንል ከእናንተው ውስጥ ያሉ የመረጃ ምንጮቻችን ፣ የራሣችሁ የሠው ሐይል ፣ የእናንተው መሣሪያ ፣ የእናንተው ተተኳሽ ፣ የእናንተው መረህ አልባ እውቀት የለለው የቁልቁለት ጉዞ እና እኛ ይዘነው ከተነሳነው ምክንያታዊ እውነት ከአማራዊ ጀግንነታች ጋር ተጨምረው ማለታችን ነው ።
'መልሳት ገንዘቤን በልተሐታል በእጅህ ፣
የእርሳስ ሽማግሌ ሳይላክ በደጅህ ። ' የሚለውን አማራዊ ብሂል ለናንተም ቤተሰቦች እና ንብረትም እንደ ሚሰራ ትረዱ ዘንድ ማስገንዘብ እወዳለሁ ።
አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !
ፋኖ ግሩም ምሳሌ
ድል አለማራ ፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
ንሥር ብሮድካስት መረጃ
ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም
=====================
ቤተሰብ ይሁኑ! ትግላችን በጋራ!
ትዊተር:
twitter.com/NISIRInternati1 ዮቱብ፣
https://youtube.com/@nibcnewsethiopia?si=oM5AASTB3fSDK53Fቴሌግራም:
https://t.me/nisirbroadcasting ቲክታክ:-
tiktok.com/@nisirbroadcas…
ዌብሳይት :
https://nisirbroadcasting.com/WhatsApp: +1 (252) 574‑6084
Telegram: +1 (252) 574‑6084