ኖኅ Book Delivery


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram


The first and only book delivery service in Ethiopia. Order books from around the world at fair prices with fast delivery. Free delivery
ለአስተያየትና መፅሐፎችን ለማዘዝ ከታች ባሉት አድራሻ መልዕክት ያስቀምጡልን 👇
@Noahbook7

"ማንበብ ፋሽን ነው"
Join us @noahbookdelivery

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


መክሊቱን በአጋጣሚ ያገኘው ቦክሰኛው መሀመድ አሊ የተሰረቀችበት ብስክሌት የሞያ መነሻው እንደሆነች ያውቃሉ?
**** 

ወቅቱ በአውሮፓውያኑ 1954 ነው። መሀመድ አሊ እድሜው ገና የ12 ዓመት ታዳጊ ነው። የቦክስ ሻምፒዮናው መሀመድ አሊ ተጋጣሚዎችን በመዘረር ዓለምን ያስደነቀ፣ የወርቅ ሜዳሊያንም ለሀገሩ በማስገኘት የምንጊዜም አይረሴ ጀግና አሜርካዊ ቦክሰኛ ነው። 

ለዚህ ክብር እና መደነቅ የበቃው መሀምድ አሊ ብዙዎች የዛሬ ማንነቱን እና የዓለም የቦክስ ሻምፒዮና መሆኑን እንጂ እንዴት ለዚህ ክብር እንደበቃ የሚያውቁ መኖራቸው ያጠራጥራል። ለዚህም ይመስላል ሰዎች አንዳንድ አጋጣሚዎችን አለመግፋት የእድላቸው በር እንደመክፈት ይቆጠራል የሚሉት።

መሀመድ አሊ ገና የ12 ዓመት ታዳጊ እያለ የአጎቱ ልጅ የሚያደርገውን የቦክስ ግጥሚያ ውድድር ለማየት ወደ ኮሎሚቢያ ትእይንት በ60 ዶላር የተገዛች ሳይክሉን እየነዳ የሄደው። በዚህ ውድድር ላይ የአጎቱ ልጅ ውጤታማ ሳይሆን መቅረቱን መሀመድ አሊ በአንድ ወቅት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ አስታውሶ ተናግሯል። 

ይህ የውድድር እለት ለመሀመድ አሊ ጥሩ የሚባል አጋጣሚ አልነበረም። ምክንያቱም የአጎቱ ልጅ በውድድሩ አላሸነፈም እና ደግሞ መሀመድ ከውድድሩ ሲወጣ በ60 ዶላር የገዛት ሳይክሉ በሌቦች ተሰርቃበት ነበር። እና በወቅቱ መሀመድ አሊ በንዴት ሁኔታውን ጆ ማርቲን ለተባለ ፖሊስ ሪፖርት ያደርጋል። ሳይክሉን የሰረቀው ሌባ ቢያገኘው በቦክስ ዋጋውን እንደሚሰጠውም መሀመድ ለፖሊሱ ይነግረዋል። የፖሊስ አባሉም የቦክስ አሰልጣኝ ስለነበረ “ቦክስ ዝምብሎ መሰንዘርና ማሸነፍ ማለት አይደለም ይልቁንም የቦክስ ስልጠና መውሰድ ብትችል ብዙ ትማርበታለህ” በማለት ለመሀመድ አሊ ምክር ይለግሰዋል። መሀመድም በዚህች አጋጣሚ የጠፋች ሳይክሉን ለመፈለግ ብሎ ጊዜውን ሳያባክን የፖሊሱን ምክር ተቀብሎ የቦክስ ስልጠናውን ጀመረ። በዚህች ቅጽበትም መሀመድ አሊ የህይወት እጣ ፈንታው የሆነውን የቦክስ ስፖረት ሀ ብሎ ጀመረ። 

ስለመሆነም ዝነኛውና ዓለም አቀፍ ቦክሰኛው መሀመድ ዓሊ የጠፋችበትን ሳይክሉን የማስታወስ እድል አላገኘም ። ይልቁንም የወደፊት ህይወቱን ለማቅናትና ህልሙን ለመኖር የሚረዳውን የጆ ማርቲንን ምክር ተከትሎ በጠንካራ መንፈስ የቦክስ ልምምድ ስራውን ጀመረ። 

መሀመድ ዓሊ ከ6 ሳምንታት ስልጠና በኋላ ለውድድር ብቁ ሆኖ በመገኘቱ የ12 ዓመት ቦክሰኛ ጋር የቦክስ ግጥሚያውን አደረገ። በዚህ ውድድርም መሀመድ ተጋጣሚውን 5 ዙር በማሸነፍ ዘርሮ በመጣል የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ።

ከዚህ በኋላ መሀመድ የሚወስደውን የቦክስ ስልጠና በተከታታይነት ስራዬ ብሎ ያዘው። መሀመድ ዓሊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኞች የሆኑትን እነ ጆ ፍሬዘር፣ ሳኒሊስተር፣ ጆርጅ ፍርማን የተባሉ ተዋቂ ቦክሰኛ ተጋጣሚዎቹን በመፋለም ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል። 

በ18 ዓመቱ በጠንካራ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተጋጣሚዎቹን በከፍተኛ ልዩነት በመርታት ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል። ይህ ክስተት ደግሞ የመሀመድ ሌላ አስደናቂ አጋጣሚ ሆነ።  የዓለም ሻምፒዮናው መሀመድ አሊ ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳሊያ ባገኘ ጊዜ ሜዳሊያውን በአንገቱ አንጠልጥሎ ነጮች ከሚዝናኑበት አንድ ሬስቶራንት ጎራ ይላል። መሀመድ አሊ ወርቁን በአንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ሬስቶራቱ ውስጥ አንደኛው ወንበር ለይ ቁጭ ብሎ አስተናገጇን አንድ ሲኒ ቡና እንድታመጣለት ያዛታል። አስተናጋጇም ጥቁሮች በዚህ ሬስቶራንት መስተናገድ እንደማይችሉ ለመሀመድ ትነግረዋለች። በዚህ ጊዜ መሀመድ ተናደደ። 

በዚህም ምክንያት እንደውም 2 ሲኒ ቡና ካልሰጠሽኝ አልጠጣም ማለቱን አሊ አስታውሶ ተናግሯል። ለሀገሬ የወርቅ ሜዳሊያ አምጥቼ እንዴት በዜጎች አልከበርም የሚለው ጥያቄ የተፈጠረበት መሀመድ ይህ ሁኔታ ስሜቱን እንደጎዳውና በወቅቱ እንደተበሳጨም ገልጿል። እናም ብስጭቱ ለውሳኔ ያደረሰው መሀመድ ኦሀዮ ወንዞ በመውረድ ያገኘውን የወርቅ ሜዳሊያ ከወንዙ ላይ መጣሉን በግለ ታሪኩ ላይ ተጽፏል። 

ይህ ሁኔታ ከተፈጸመ ከ36 ዓመታት በኋላ በአትላንታ በተካሄደ የኦሎምፒክ ውድድር ላይ መሀመድ አሊ ለሀገሬ ያመጣሁት የወርቅ ሜዳሊያ እንዴት አያስከብረኝም ብሎ ወንዝ ውስጥ የጣለውን ምትክ ሜዳሊያ ተሰጥቶታል። መሀመድ አሊ የዓለም ከባድ ሚዛን የቦክስ ውድድሮችን በማሸነፍ የ3 ጊዜ ሸምፒዮና በመሆን ሪከርዱን ማስጠበቅ የቻለ ጀግና ነው። 

በ2024 ዓለም አቀፉ የቦክስ ፌዴሬሽን ማህበር ጉባዔ በዱባይ ሲካሄድ ለመሀመድ አሊ ቤተሰቦች ክብር እና እውቅና ተሰጥቷል። በዚሁ ጊዜም ልጁ ረሺዳ አሊ የአባቷ ስራዎች ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፉ ለማድረግ መሰራት እንዳለበት ተናግራለች።

በርግጥ መሀመድ አሊ ከፕሮፌሽናል ቦክሰኛነቱ ባሻገር ለሰው ልጅ እኩልነት የታገለ እና የሚታገል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንደሆነ የሚመሰክሩለት ብዙዎች ናቸው። መሀመድ አሊ የነበረበት ወቅት የጥቁሮች እና ነጮች እኩልነት ያልተረጋገጥበት ጊዜ በመሆኑ ይህን በብዙ መንገድ ታግሏል።

የዓለም የምን ጊዜም ታላቅ ሰው የሚባለው መሀመድ ከዘመናት የስኬት ጉዞ በኋላ በ74 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። በአጋጣሚ የብስክሌቱ መጥፋት የፈጠረበትን ብስጭት ለማስታገስ እሰነዝረዋለሁ ያለው ቦክስ በህይወቱ ትልቅ ለውጥ ያመጣበት እሱም እንደኮኮብ የሚያበራበት አጋጣሚ የሆነለት ታላቅ ሰው ከዝናው ባለፈ ህይወቱም ለብዙዎች አስተማሪ ሆኖ ተመዝግቧል። 

በመሀመድ ፊጣሞ
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


House at Riverton - Kate Morton

Price 750 birr

The Best of Me - Nicholas Spark

Price 750 birr

The Last song - Nicholas Spark

Price 850 birr
✅✅✅
መጽሐፎቹን ለማዘዝ
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


The Design of Childhood by Alexandera Lange

How the material world shapes independent kids

📚Hardcover

💰1250 birr

✅✅✅
መጽሐፎቹን ለማዘዝ
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ይህቺ ከላይ ያለችው ሴት ባንተ ፍቅር ክንፍ ብላለች ልታገባህ ትፈልጋለች ብትባልና ፎቶዋን እንድትታይ 5 ሴኮንዶች ቢሰጡህ ምን ታደርጋለህ? 1 2 3 4 5 ምን ወሰንክ? መልስ አይ ከነበረ መልካም ልታገባት ተስማምተህ ከነበረ ግን ይህ ፅሁፍ ላንተ ነው።

ሊሊ ፊሊፕስ ትባላለች በዚህ ሰአት አለምአቀፍ የምእራቡ ሚዲያዎች ሽፋናቸውን ከገዛች ብትሰነባብትም ይሄን ሳምንት ግን በተለየ ሁኔታ ተቆጣጥራዋለች። ያለፈው ወር ጥቅምት ላይ . . .

አንዴ መዝገበ ቃላት እንጠቀም

1) Body Count ይህ ቃል ቀጥተኛ የአማርኛ ፍቺ የለውም ትርጓሜው ግን አንድ ሰው ያለው የወሲብ ጓደኛ ቁጥር ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ጋር ብቻ ወሲብ ሚፈፅም ሰው Body Count 1 ይባላል።

2) OnlyFans ይህ የካፒታሊዝም እና የነፃነት ልቅነት የት እንደደረሰ ማሳያ ድህረገፅ ሲሆን በዚህ ድረገፅ ሰዎች የሚደሰቱበት የሰው ልጅ የሚተካበት ሂደት ወሲብ ለንግድ ይቀርባል ፕላትፎርሙ ለሁለቱም ፆታ የቀረበ ቢሆንም ከ80% በላይ ሽያጭ የሚያከናውኑት ሴቶች ናቸው።

አሁን ወደ ሊሊ ጉዳይ እንመለስ ሊሊ ያለፈውን ጥቅምት ወር 100 Body count በ24 ሰአታት ወይንም 100 የተለያዩ ወንዶች ጋር በአንድ ቀን ውስጥ ወሲብ በመፈፀም በOnlyfans የመታየት  ታሪክ ሪከርድ ሰብራ ነበር። ያ ደግሞ ዝም ብሎ አልታየላትም በየፖድካስቶቹ መጋበዝ እና መምጣት ጀመረች።

ታዲያ ሊሊ ሰሞኑን የሚዲያዎች ጋቢ መቋጫ ያደረጋት ጉዳይ ምን መሰላቹ የ100 Body Count ሪከርዷ ቅድመ እይታ ( Trailer ) አሊያም ልምምድ ነው ስትል ተናገረች ይህም በፈረንጆቹ አዲስ አመት 2025 የጥር ወር ላይ ቁጥሩን ወደ 1000 ከፍ አድርጋ ለመምጣት ዝግጅቶች እያደረገች መሆኗን መግለጿ ነበር። እንደውም በተናገረችበት ቃለመጠይቅ ላይ በጣምምምምም ያሳሰባትን ጉዳይ ስትጠቅስ "Logistics" ነው ትላለች።

ኧኧኧ. . . ስታብራ Pump in pump out ብላ በቀላል ቋንቋ ከገለፀችው በውሃላ 1000 ሰው የሚይዝ ከጊዜው ጋ የሚሄድልኝ ፍጥነት እንዴት እንደማመቻች አላቅም ነው የምትለው። እንግዴህ አንድ ሰው ( ወንድ ማለት ይከብደኛል) አንድ ሰው አንድ ደቂቃ ብትሰጥ 1000 ሰዎችን ለመገናኘት በትንሹ 17 ሰአታት ይፈጅበታል ይህ እንግዴ ያለምንም እረፍት እና ማቋረጥ ማሽኑ ከሰራ ነው ሃሃሃ...

ሊሊን አንዴ እንያዛት እና ወደ ሃገራችን እንመለስ አሁን አሁን ሴቶቻችን በየቦታው የምንሰማው ነገር ገና በ19 20 አመታቸው ሁለት ዲጂት የገባ Body count ያላቸው ሴቶች ከተማውን መቆጣጠራቸው ነው በዚህ የሚቀርም አይደለም እንደ ጀብድ እየታየ አንድ Body Count ያላት ሴት እንደ ፋራ የምትታይ ሲሆን (በዛ እድሜ ራሱ ስለወሲብ ማሰብ አይከብድም?) ጭራሽ ምንም የሌላት ድንግል የሆነች ሴትማ ከጀማቸው ከተገኘች እርሷ በነሱ አገላለፅ "እርጥብ" ነች።

( "እርጥብ" ምንም የማታውቅ ፣ ያልሰለጠነች ፣ ዘመኑን ያልዋጀች )

አሁን ላይ ያሉ በተለይ በግል ኮሌጅ የሚገኙ ሴቶች Body Count ዙሪያ ጥናት ቢሰራ ከ80% በላይ ሴቶች ሁለት አሃዝ የገቡ ሲሆን 15% ከዛ በታች 5% ዜሮ የሆኑ ያልተነካኩ ሴቶችን የምናገኝ ይመስለኛል ይህ ግላዊ እይታ ነው።

እስኪ ሴት ልጅ ያላቹ ወላጆች? እህት ያላቹ ወንድሞች ቁጭ ብላቹ ተወያዩ ጠይቋት እስኪ ለምላሿ ግን ከወዲሁ ልባቹን አዘጋጅታቹ ይሁን። ወደሊሊ ታሪክ እንመለስ የሊሊ አመለካከት ያስገርመኛል

የGBNews ጋዜጠኛ እና ዜና አንባቢው ወንዶቹ ምን አይነት ናቸው እንደው ለሚሉ ሰዎች የተጠቀመው ገለፃ እንዲህ ነበር

"Men being men, if something like that is offered on a plate, its likely to be taken"

ትርጓሜውም ወንዶች ወንዶች ናቸው መሰል ነገር ተቀምጦ እንደሚበላ ግልፅ ነው ሲሆን እንዲሁ ሳስበው ግን 100ኛ ላይ የነበረው ወንድ ምን አይነት ጭንቅላት ቢኖረው ነው 99 Body Count ያላትን ሴት ጋር ጭራሽ ከደቂቃዎች በፊት እንደፈፀመች አውቆ ራሱን ለመቶኛነት ሸጠ?

ብቻ ነገሩን ስጠቀልለው ወላጅ የላትም እንዴ ሚያስብል ነገር የሰራችው ይህች ሴት እናት ያሉት ነገር በጣም ያስቃል "ልጄ አንድ ወንድ ላይ ረግታ የፍቅር ህይወቷን ብትመራ ደስ ይለኛል" ያሉ ሲሆን ሊሊ አንቺስ ምታገቢ ይመስልሻል ወይ ተብላ ለጠየቀችው ጥያቄ

"አንድ የቸገረው ወንድ ይመርጠኛል ከሱጋ ህይወት መሰርታለው" ትላለች።

የGBnews ጋዜጠኛውን ንግግር ተውሼ ፅሁፌን ልጨርሰው

"ይህ ጀግንነት አይደለም ፣ ይህ የፈጠራ ስራ አይደለም ፣ ይህ ቴክኖሎጂ አይደለም ፣ ይህ የምእራቡ አለም እብደት ፣ ሞራል ውድቀት ፣ የሀይማኖቶች መናጋት ፣ የማህበረሰብ መፍረስ ነው። መሰል ነገሮች አደባባይ በወጡ ቁጥር ሴት ልጅ እንደ እቃ በቀላሉ የምትገኝ እና የምትገዛ እንዲመስል ሆኗል" ሲል በዚህ ሁሉ መሀል ግን የቲክቶክ እና የኢንስታግራም ገጿ በአንድ አይነት ኮመንቶች የተሞላ ነው

"ሊሊ ሚያስፈልግሽ 1000 ሺህ ሳይሆን አንድ ወንድ ነው እሱም ሳይካትሪስ የሆነ"

ፕሮፌሰር ሄኖክ አራጋ ✍✍✍

⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery




ስፍራችሁ ካልሆነ . . . ውጡ!

ስፍራ ማለት፣ ያላችሁበት ስራ፣ የምትኖሩበትን ቤት፣ ጓደኝነታችሁን ወይም ሌሎችን የወደፊታችሁ የሚወስኑ ሁታዎችን የሚወክል ጉዳይ ነው፡፡ ከተጠቀሱትና ከመሰል ሁኔታዎች አንጻር ውስጣችሁ ያመነበትን፣ ለእናንተ ተስማሚና ትክክለኛ የሆነውን “ስፍራችሁን” ማግኘት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

ስፍራችሁን ለይታችሁ ያለማወቃችሁ ቀንደኛው አጉል ውጤት ያላችሁበትን ስፍራ ተቀብላችሁ እዚያው የመክረማችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሲሆን፣ እድሜያችሁን እንዲሁ ታባክናላችሁ፣ በአንድ ስፍራ ተተክላችሁ በመቅረታችሁ ምክንያት ትክክለኛና ለእናንተ መሆን የሚገባቸው እድሎች ያመልጧችኋል፣ ውስጣችሁ ተስፋ ይቆርጣል . . . ፡፡ ስለዚህ ስፍራችሁን ልይታችሁ ለማወቅ ማድረግ ያለባችሁን ማድረግ አለባችሁ፡፡

ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ እስክትደርሱ ድረስ አሁን ባላችሁበት የመቆየታችሁ ሁኔታ ችግር የለበትም፡፡ ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ ግን አሁን ያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ካለማቋረጥ ወደትክክለኛ ስፍራች የምትደርሱበትን እቅድ ማውጣት አለባችሁ፡፡

ያንን እቅድ ካወጣችሁ በኋላ ደግሞ ጉዞ በመጀመር ካለማቋረጥ ወደዚያ መንቀሳቀስ የግድ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ የሚያስከፍላችሁን ሁሉ መስዋእትነት ከመክፈል ወደኋላ አትበሉ፡፡

ስፍራችሁን ከለያችሁ በኋላ እዚያ መድረስ ከባድና መስዋእትነት እንደሚያስከፍላችሁ እስባችሁ ያላችሁበት ከቀራችሁ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላችኋል፡፡

አንድ ነገር አትዘንጉ፡- ወደ ትክክለኛው ስፍራችሁ ለመራመድ ከምትከፍሉት ዋጋ የበለጠ የምትከፍሉት ስፍራችሁ ባልሆነ ቦታ በመቆየት ነው፡፡ በመንቀሳቀስ የአጭር ጊዜ ዋጋ ትከፍላላችሁ፣ ያላችሁበት በመቅረት ግን የረጅም ጊዜ ዋጋ ትከፍላላችህ፡፡

ያላችሁበትን ስፍራ መርምሩ፣ ትክክለኛውን ስፍራችሁን ለዩ፣ ከዚያም በጥንቃቄ ወስኑና ካላችሁበት ወጥታችሁ ተንቀሳቀሱ!

Dr. eyob ✍️
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


ዝም ስንል ማውራት የማንችል ወይም ስለራሳችን መከራከር የማንችል ይመስላቸዋል።ዝም ስንል ፍርሃት ያለብንና ስለምንም ነገር የማንጨነቅ ይመስላቸዋል።ዝም ስንል እነሱ ብልጥ እኛ ጅላንፎ እንመስላቸዋለን።ሼም ሊያሲዙን ይሞክራሉ።ሊያሸማቅቁን ይጥራሉ።በቃ እነሱ ብቻ ንቁና በራስመተማን ያላቸው እንደሆኑ ነው የሚያስቡት....

እኔ ዝም ልል እችላላው።ትንሽ ትንሽ ነገር ላወራ እችላለው።ከተመቸኝ ደግሞ በጣም በዝምታ ውስጥ ልዋጥ እችላለው።በተለይ አንዳንድ ጊዜ በራሴ አለም ውስጥ ልጠልቅ እችላለሁ።ግን እኔ ከማስቀምጠው ገደብ ማንም ሰው ሊያልፍ አይችልም።ማንም ከፍም ዝቅም ሊያደርገኝ አይችልም።ሁላችንም የየራሳችን ገደብ አለን።

እንጫወታለን፤እንዝናናለን፤እንሳሳቃለን።ምናልባት ውስጣችን ያለውን ነገር ማወራት ካለብን እናወራለን።ነገር ግን ከዛ ውጪ ዝምትኝነትን ተገን አድርገው ክብርን መጣል ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ንግግር የለንም።የእነሱንም ህግ እናከብራለን፤የእኛንም ህግ ያከብራሉ እንጂ እኔን ብቻ አክብሩ የእናንተን ክብር እርሱት ከሚሉ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ሊኖረን አይገባም።ስለዚህ ሁላችሁም ከእንደዚህ አይነት ሰዎች የምትርቁበትን መንገድ አሁኑኑ ፈልጉ።ጊዜው በረዘመ ቁጥር በሌሎች ሰዎችም እንድትናቁ ያደርጓችኋል።

✍️ Bemni Alex
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


በልጆች ዘንድ እጅግ ተመረጫ እና ተወዳጅ የሆነውን DogMan መጽሐፍ ይዘን መተናል።

ውስጡ colorful 📚📙📘📗📕📒📔 መሆኑ ለማንበብ ይጋብዛል።

Dog Man Book series by Dav Pilkey (1-6)

The Supa Ebic Collection

1. Dog Man

2. Dog Man - unleashed

3. Dog Man - A tale of two kitties

4. Dog Man - And Cat Kid

5. Dog Man - Lord of the fleas

6. Dog Man - Brawl of the Wild

Total Price 5750 birr

ማሳሰቢያ ፦ ተነጣጥለው አይሸጡም።
✅✅✅
መጽሐፎቹን ለማዘዝ
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery


The Girl with the Dragon Tattoo Series by Stieg Larsson

1. The Girl with the Dragon Tattoo

2. The Girl Who Played with Fire

3. The Girl Who Kicked the Hornet's Nest

Total Price 1850 birr

ለየብቻ አይሸጡም።
✅✅✅
መጽሐፎቹን ለማዘዝ
📚ማዘዝ የፈለጉትን መጽሐፎች
📞ስልክ ቁጥር እና
📍አድራሻ ይላኩልን።
⛵️
Free Delivery
ለማዘዝ 👇🏾

  @Noahbook7  0939115238
 
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery



Показано 10 последних публикаций.