#ፓስፖርት
በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስና ዘመናዊ ፓስፖርት ይፋ ሆነ
ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስ ፓስፖርት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት ይፋ ሆነ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትን ተግባራዊ ማድረጋችን የሀገርን ገጽታ ከመገንባት ባሻገር ለዜጎች የተሰጠውን ዋጋ ያሳያል ብለዋል፡፡
ፓስፖርቱ የግለሰቡን መረጃና የጣት ዐሻራ የያዘ የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ አለው ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረት ይህ ፓስፖርት፤ የቪዛ ገጾቹ የኢትዮጵያን መልክ የያዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።
ይህም ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር አምራች ድርጅት እጅ የነበረውን ዲዛይን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሸፈን አድርጓል ነው የተባለው፡፡
ከዚህ በፊት ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት ገቢ ወደ ማመንጨት እንደሚያሸጋግርም ተመላክቷል።
ፓስፖርቱ በቀላሉ ለአደጋ የሚጋለጥ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ የያዘ በመሆኑ የተሻለ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ መታጠፍ፣መቀደድ እንዲሁም ለከፍተኛ ሙቀት እና እርጥበት መጋለጥ እንደሌለበት ተገልጿል።
📄
@Exitnewss