እንክት እንክት ዕያለ ዕምነቴ አለላው
ቅንጥስ ቅንጥስ ዕያለ ቃልሽ ሸንኮራው
መንገድ ወቶ ከዋለለ ገልሽ ሙሽራው
ይቅር ይቅር እያልኩኝ ያንቺኑን ነገር
መተው መተው ነው እንጂ ምንስ ልናገር
ፍቅርን ካሳጣሽብኝ ዋልታና ማገር
ይሆናል ብዬስ ወድጄሽ ነበር
ይዘልቃል ብዬስ አፍቅሬሽ ነበር
ባንቺ አለመፅናት አደራው ጠፋው
እስከ ማገኝሽ ቀኑ አስኪገፋው (፪)
አድቦስ መኖር ምን ነበረበት
ተማምኖስ ማደር ምን ነበረበት
መንገድ ቢረዝም መች ያረሳሳል
ሰው ለጉዳዩ የትም ይደርሳል
መንገድ ቢረዝም መች ያረሳሳል
ዕምነት በርቀት እንዴት ይረሳል
ያለፍነው መንገድ (ዐይናማዬ) የነበርንበት (ዐይናማዬ)
ፍቅርን ገላልፀን (ዐይናማዬ) ያወጋንብት (ዐይናማዬ)
መደሰቻችን (ዐይናማዬ) ደማቁ ቦታ (ዐይናማዬ)
ዙሪያው ተከቦ (ዐይናማዬ) በኛው ትዝታ (ዐይናማዬ)
ደማዬ ... የቅርብ እንደ ሩቅ ይረሳል ወይ?
ደማዬ ... ያመኑት ወዳጅ ይከዳል ወይ?
እንክት እንክት ዕያለ ዕምነቴ አለላው
ቅንጥስ ቅንጥስ ዕያለ ቃልሽ ሸንኮራው
መንገድ ወቶ ከዋለ ገልሽ ሙሽራው
ይቅር ይቅር እያልኩኝ ያንቺኑን ነገር
ፍቅርን አሳጣሽብኝ ዋልታና ማገር
ወረት ነፍሶብሽ እንደ ሽውታ
ካሳብሽ ወስዶት የኔን ትዝታ
መቻል ተስኖሽ ያደራን ዕዳ
እኔና አንቺው ቤት ፍቅር ተጎዳ
መቻል ተስኖኝ ያደራን ዕዳ
መቼም ጌጥ አይሆን ባዳ ለባዳ
አደራን አቅፈው ችለው ካልያዙት
ኪዳንን አስረው አጥረው ካልያዙት
ወረት ሲጋጋል ለመንገድ ያጫል
ዕምነት ከራቀም ፍቅርም ይቀጫል
ወረት ሲጋጋል ለመንገድ ያጫል
ቀን የበተኑት ሲመሽ ይቆጫል
ዐይኔ ቢተክዝ (ዐይናማዬ) ምንም ቢከፋው (ዐይናማዬ)
ዕችለው ነበር (ዐይናማዬ) ቀኑ እስኪገፋው (ዐይናማዬ)
ጎዳናው አርቆን (ዐይናማዬ) ባንተያይም (ዐይናማዬ)
ኪዳን እስካለን (ዐይናማዬ) አንለያይም (ዐይናማዬ)
👇👇👇
@old_musicaሼር🙏