🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Эзотерика


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች
ለማስታወቂያ ሥራ👉 @mane_tekel21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Эзотерика
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ሰበር ዜና
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው
የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታግዷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።

                ሚያዚያ ፲፭ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                     አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ

          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                      ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
በከመ ተብህለ" ሰናይ አርዝ ይፈሪ ሰናየ ፍሬ" ናሁሰ ፈረየት ጉባኤነ ሰናየ ፍሬ!
"መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራል" እንደተባለው  መልካሟ ግቢ ጉባኤያችንም መልካምን ፍሬ ማፍራቷን ቀጥላለች!
ጥዑም ዜማ: መዝገበ ርህራሄ
በዘማሪት ነፃነት ሲሳይ ፡የአንጋፋው ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ግብርና ግቢ ጉባኤ አገልጋይ                                                                                                                                          
እሁድ ሚያዚያ 19 በ"ጊዜ" ሚዲያ ይለቀቃል።
ሁላችንም እናበረታታት🙏


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !

ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።

በብፁዕነታቸው  የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።

በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

©የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ
#ድምፀ_ተዋህዶ


ብፁዕ ኾይ፦
እመቤታችን 'እንደ ቃልህ ይሁንልኝ' ያለችው ቃሏ የእርስዎም ቤዛ ነው።

"ከእናንተ መኖር ይልቅ የክርስቶስ ትንሣኤ ብዙ ማስረጃ አለው"
ክርስቶስ አልተነሣም ላሉ ሰዎች አንድ ሊቅ የተናገረው ቃል ነው።
የእመቤታችን ቤዛነትም እንዲሁ ነው። ከአቡኑ ማብራሪያና ዕውቀት ይልቅ  ብዙ ማስረጃ አለው።ሌላውን ብዙ ጥቅስ ትተን
"ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ፤
እንደቃልህ ይሁንልኝ" ያለችው ቃል ብቻ በቂያችን ነው። የመጣው ለዐለም ኹሉ ቢኾንም የተወለደው ከእርሷ ነውና። 'ይሁንልኝ' ያለችው መልሷ የእርስዎም የእኛም ቤዛ ነው። ህየንተ (ምትክ) ማለት ነው።
ደግሞስ የድንግል ማርያም ቤዛነት ምኑ ይገርማል?
"ይኽ መስቀል ቤዛችን ነው" እያለ ቅዱስ ያሬድ ለመስቀሉ ዘምሮ የለምን?
"መስቀልከ ዕፀ ተነብዮ መስቀልከ ለሰይጣን ሞዖ ዝንቱ መስቀል ቤዛነ።"
አኹን ቅዱስ ያሬድ ዕንጨቱን ቤዛ በማለት አምላክ አደረገ ብለን እናርመው?በፍጹም!
እንኳን እሱ፥ እኛ ስለ እመቤታችንም ኾነ ስለመስቀሉ ይኽን ስንል የፈጣሪን ቤዛነት ከፍጡራን ለይተን ዐውዱን ጠብቀን ነው።

ተሳስቻለሁ ይቅርታ ማለት ጴጥሮሳዊነት ነውና ቃልዎን እንደሚያርሙ ተስፋ አደርጋለኹ።

ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ብፁዕ አባታችን። ድንግል ማርያም ቤዛዊት አትባልም ብለው ድምዳሜ ሰጥተው ሲያስተምሩ ሰማሁ። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይባልም ብለን ከምንደመድም እንዲህ ብንል አይሻልምን?

🥀እናታችን ድንግል ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም እንላታለን። ክርስቶስን ቤዛችን ስንለው በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ስላዳነን ነው። ድንግል ማርያምን ቤዛዊት ስንላት ግን ቤዛኩሉ ክርስቶስን ስለወለደችልን ነው። ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን አድኗልና ነው። ምክንያተ ድኂን ስለሆነች ነው። ልጇ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ ብሎ እንዳስተማረን እሱን ብርሃን እርሷን ደግሞ የብርሃን እናት እንላታለን። ልጇ አምላክ ስለሆነ እርሷ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ትባላለች። አምላክን የወለደች የአምላክ እናት ማለት ነው። ቤዛዊት ናት ስንል በጸጋ እንደሆነ ልብ እናድርግ። ምናልባት በባሕርይው ቤዛ ሆኖ ያዳነን ክርስቶስ ብቻ ነው ለማለት ፈልገው ከሆነ መልካም ነው።

🥀ንስጥሮስን ክርስቶስ ላይ ያለው የምንታዌ (Dualism) እይታ ድንግል ማርያምን ወላዲተ ሰብእ ከማለት አደረሰው። ድንግል ማርያም የወለደችው ሰው የሆነ አምላክን አምላክ የሆነ ሰውን ነው እንጂ ዕሩቅ ብእሲ (ሰው ብቻን) አልወለደችም። ነገረ ክርስቶስን ከድንግል ማርያም በበለጠ የሚያውቀው ፍጡር የለም ። እርሷ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር ተንከራታለች። በመስቀልም ጊዜ ከጽንዐ ፍቅሯ የተነሳ ከመስቀሉ ሥር አልቅሳለች። ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናመሰግናታለን፣ እንሰግድላታለን። ነገር ግን ለእርሷ የምናቀርበው ስግደት እና ምስጋና የአክብሮት ስግደትና ምስጋና ነው እንጂ እንደ አምላክ የአምልኮ ስግደት አይደለም።  

🥀ድንግል ማርያም ዓለም ጣዖትን በማምለክ ጨለማ ውስጥ ሳለ ብርሃንን የወለደችልን እናታችን ናት። ድንግል ማርያም ዓለም ለሰይጣን በመገዛት ባርነት ውስጥ ሳለ በመስቀል ተሰቅሎ የእኛን ሞት ሞቶ ነጻነት የሚያጎናጽፍ ጌታን ወለደችልን። ዓለም ተርቦ ነበር። እሷ ግን የሕይወት እንጀራን ወለደችልን። ድንግል ማርያም የትሕትና እናት ናት። ምሥጢራዊም ናት።ማርያም ግን ይህንን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው ነበር ተብሏል። እውነትን ይዛ ሳለ በሐሰተኞች ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሆነች።

የቤዛነትን ትርጉም ንገረን ላላችሁኝ እነሆ

ቤዛነት ምንድን ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች በሰው ልጆች ምትክ ያደረገው ሥራ ቤዛነት ይባላል። ቤዛ በአገባቡ "ስለ" ነው። ምሥጢሩ ምትክነትን፣ መቤዠትን ይገልጻል። ቤዛ "ቤዘወ-አዳነ" ከሚለው ግሥ ሲወጣ መድኃኒት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። በሁለቱም ለክርስቶስ ቢነገር ያስኬዳል። መድኃኒታችንም ነውና። ቤዛ-ስለ በሚለው አገባብ ከተተረጎመ ስለእኛ በመስቀል ተሰቅሎ ማዳኑን ይነግረናል። ክርስቶስ ያደረገው ሥራ ሁሉ ስለእኛ ነው። በትርጓሜ በሐተታ በእንቲኣነ (ስለእኛ) እየተባለ የሚገለጸው እንደ ኃጥኣን ስቶ፣ እንደ ሰማዕታት ዕሴትን ሽቶ ያደረገው አለመሆኑን ለመግለጽ ነው።

ይህ ክርስቶስ ያደረገው የቤዛነት ሥራ የባሕርይ ሥራ ነው። ቅዱሳን ደግሞ አምላካቸው ክርስቶስን መስለው ስለሌላው ሰው ብለው የሚቀበሉት መከራ ቤዛነት ነው። ግን የጸጋ ቤዛነት ነው። "ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" የሚለው ቃል ሰዎችም በአቅማቸው አንዱ ለአንዱ ቤዛ መሆን እንዲችሉ የተነገረም ጭምር ነው። ግእዙ "አልቦ ዘየዐቢ ወይኄይስ እምዝ ፍቅር ከመ ብእሲ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ" ይለዋል (ዮሐ.15፥13)። ቅዱሳን ክርስቶስን አብነት አድርገው ስለሌሎች ሰዎች ሲጸልዩ፣ ሲጾሙ፣ ሲሞቱ አይተናል። ጌታም የእነርሱን ፍቅር አይቶ ኃጥኣንን ሲምር በብዛት ተጽፏል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐዲስ ኪዳን ላይ ስንገባ በሰፊው እንመለከተዋለን።

©በትረ ማርያም አበባው

#ድምፀ_ተዋህዶ


☞ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
☜ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን!
☞ አሰሮ ለሰይጣን!
☜ አግዐዞ ለአዳም!
☞ ሰላም!
☜ እምይእዜሰ!
☞ ኮነ!
☜ ፍስሐ ወሰላም!

[ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣  በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ፣ ሰይጣንን አሠረው፣ አዳምን ነጻ አወጣው ፣ ሰላም፣ ከዛሬ ጀምሮ ፣ ይሁን ፣ ሰላም]

እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል


✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ

ትንሣኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ /2/

      
የትንሣኤው በኩር የሰው ልጆች ሕይወት
ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት
በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው
አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሲኦል መውጊያዋ ፍላጻው ተነስቷል
የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል
የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን
ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነፍሳቱን

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


አዝ__

ማርያም መግደላዊት የጠራሽ በስምሽ
በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ
መላእክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል
የነገራችሁን እዩት ተፈፅሟል

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__

የሞት ኃይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ
በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አለኝታ
እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው
በትንሣኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


አዝ__

ለትንሣኤው ልጆች ለምናምን ለእኛ
ብርሃንን ላክልን ላይጨልም ዳግመኛ
እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ
ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ

በትንሣኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን ዓመታት መቁጠር ጀመርን/2/


                   ዘማሪ
       በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


✞ እሰይ እሰይ የምሥራች ✞

እሰይ እሰይ የምሥራች ደስ ይበለን
ሞትን አሸንፎ ተነሳልን
በሞቱ የእኛን ሞት አጠፋልን

ሲኦል ባዶ ሆነ ዘንዶው ድል ተመታ
ሞትን በሞት ሽሮ የትንሳኤው ጌታ
እንባችን ታበሰ አገኘን ነጻነት
ከሲኦል እስራት ወጣን ከባርነት
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
ቁልፎቿ ሲወድቁ የሲኦል መዝጊያዋ
ከዙፋኑ ሲወርድ ዲያቢሎስ ጌታዋ
አርነት ስንወጣ በጌታ ትንሳኤ
በእልልታ ደመቀ የሰማይ ጉባኤ
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
የሞታችን መውጊያ ተሰበረ ቀስቱ
ጥልም በመስቀሉ ፈረሰ በሞቱ
የትንሳኤው ብርሃን ወጣ በላያችን
አምላክ መድኃኔዓለም ሲነሳ ጌታችን
አዝ••••••••••••••••••••••••••••••••
እንደ ህልም  አለፈ የኲነኔው ዘመን
ዲያብሎስን አስሮ አሳየን ብርሃን
ሞትና መከራ ከእኛ ተወግዷል
መቅበዝበዙ ቀርቶ ክብርን አግኝተናል

             መዝሙር
       ዘማሪ ፍቃዱ አማረ

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የማርያም ለቅሶ

ልጄ ወዳጄ ሆይ ለእኔ ወዮታ አለብኝ ... በጦር ሲወጉህና ሲገድሉህ ዓይኖቼ ከምያዩ ይልቅ ልጄ ወዳጄ ሆይ ነፍሴን ከስጋዬ ትለያት ዘንድ እማልድሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ በራስህ የተቀዳጀኸው የእሾህ አክሊል ምነው እኔ በተቀዳጀሁትና የመከራህ ተሳታፊ በሆንኩ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተን በእሱ ላይ በሰቀሉበት መስቀልህ በሰላም እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አይሁድ መራቃቸውን በተፉበት ብርሃንንም በተሞላ ፊትህ እሰናበትሃለሁ: ንጉስ ሆይ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እርቃኑን ለቆመው አካልህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ እጣ በተጣጣሉበት ክብር ልብስህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።
ልጄ ወዳጄ ሆይ አክሊለ ሶክክን ለተቀዳጀ እራስህ ሰላም እያልኩና እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ምንጭ ግብረ ሕማማት

#ድምፀ_ተዋህዶ
#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ




✞ ንሴብሆ ✞

ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 
       አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
       አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
       አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️

✨✨✨✨✨✨✨
✝️#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ✝️
✨✨✨✨✨✨✨

      👍    🔄      🙅‍♂️         ✍️  
      ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ   ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


ስርዓተ ስግደት ዘ፫ቱ ሰዓት

ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ
አርዐተ መስቀሉ ፆረ
አርዐተ መስቀሉ ፆረ
ይስቀልዎ ሖረ።
ዬ ዬ ዬ
ከመ ኪያነ ይቤዘ
እግዝኦ ኮነ ገብረ
እግዙኦ ኮነ ገብረ።

ነው፦

✥ "ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም ፡፡"

✥ "አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡"

✥ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

✥ " ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ፤ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኰቴት ፡፡"

❖ " ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡

❖ "ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖"ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለስልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

"ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለሕማሙ  ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም"፡፡

❖ "ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም፡፡ "

❖ "ለከ ይደሉ ኃይል፣ ወለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኰቴት ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም"

እምድህረ ንባብ ይበል ዲያቆን
ግፍኦሙ እግዙኦ ለእለ ይገፍኡኒ 
ጽብኦሙ እግዙኦ ለእለ ይጸብኡኒ።
ግፍኦሙ እግዙኦ ለእለ ይገፍኡኒ

በዜማ


ይ.ዲ ምስባክ፦ መዝ ፳፩፥፲፮
ዐገቱኒ ከለባተ ብዘኃን 
ወአኅዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን።
ዐገቱኒ ከለባተ ብዘኃን

በዜማ


እምድህረ ማቴዎስ ወንጌል
ጊዛ ሠለስቱ ሰዓት ኣኃዜዎ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቀልዎ።

እምድህረ ማርቆስ ወንጌል
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ቀሰፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቀልዎ።

እምድህረ ሉቃስ ወንጌል
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሃቦሙ ለኢየሱሃ ይስቀሉ።

እምድህረ ዮሐንስ ወንጌል
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ አውደ ምኩናን።

ካህኑ ‹ጸልዩ በእንተ ጽንዓ ዛቲ . . .› ብሎ በሚያነብ ጊዜ በየምዕራፉ "እግዚኦ ተሳሃለነ" ወይም "አቤቱ ይቅር በለን" እየተባለ ይሰገዳል፡፡

   "ክርስቶስ አምላክነ፤ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲአነ በሕማማቲሁ ቤዝወነ፤  ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ፤ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በዕበየ ሣህሉ" (በዐርብ) ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ይባላል፡፡

ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን፤

#አብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ ኪርያላይሶን

#ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን ፤ኪርያላይሶን ፤

#ታዖስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ማስያስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ኢየሱስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ክርስቶስ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#አማኑኤል ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን፤

#ትስቡጣ ናይን፣ ኪርያላይሶን፤
ኪርያላይሶን፤ኪርያላይሶን

ከዚህ በኋላ አርባ አንድ ጊዜ  ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  ኪርያላይሶን  እየተባለ ይሰገዳል፡፡

ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ...

መልክዓ ሕማማት ዘሰለስቱ ሰዓት ይደርስና ሲያልቅ፡-

✥ ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ (እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግእዝትነ ወመድኃኒትነ (እመቤታችንና መድኃኒታችን ለሆነች ለአምላክ እናት ለማርያም ምስጋና ይገባል)፡፡

✥ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወፀወንነ(ኃይላችን መጠጊያችን ለሆነ ድኅነት ለተገኘበት ለክርስቶስ ምስጋና ይገባል)፤፤ ጸሎተ ሃይማኖትን ሐመ  እስከ ሚለው ድረስ መድገም ነው፡፡

#ኦርቶዶክሳዊ_ዝማሬ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
በሰሞነ ሕማማት የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር በግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ቅዱር ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታውድሮስ ዳግማዊ በተገኙበት ተከብሯል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የጸሎተ ሐሙስ ሕጽበተ እግር ሥነ ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መሪነት ሲፈጸም በምስል

ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ተዋሕዶ ሚዲያ ማከል የተወሰደ

#ድምፀ_ተዋህዶ

Показано 14 последних публикаций.