#በአንተ_ነጋልኝ
የህይወቴን መስመር የምታቀና፣ የኑሮዬን አቅጣጫ የምታበጃጅ አምላኬ እና አባቴ ቅዱስ እግዚአብሔር ክበር ተመስገን። አንተ ረድተኸኝ ይኸው ምሽቴ ነጋልኝ። በክንድህ ስር ከክፉ አስጠለልከኝ፣ በመዳፍህ ላይ ተንጋልዬ ተኛው፣ የምህረት አይንህ እያየኝ ነጋልኝ፣ በግብሬ አይደለ በምህረትህ አደርኩኝ፣ በእቅዴም አይደለ በቸርነትህ ምሽቱን አለፍኩኝ ክብር ለአንተ ይሁን።
በህይወቴ ለሚሆነው ነገር ሁሉ የአንተ ፈቃድ እና መሻት ነውና በራሴ ማስተዋል ላይ ተደግፌ የአንተን ምስጋና እንዳልቀማህ በጸጋህ ደግፈኝ። ገንዘብ ቢተርፈኝ መች ሰላም ይሆነኛል? ሰውስ ቢሆነረኝ መች ማምለጫ ይሆነኛል? ክንዴ ቢፈረጥም መች ከክፉ ያደኛል? እውቀቴስ ቢሰፋ መች መሸሸጊያ ይሆነኛል?
አለኝ ከምለው ነገር ሁሉ በምትልቅ በአንተ ነው መኖሬ። የለኝም ሌላ ድጋፍ አንተ ነህ ድጋፌ። ከከበበኝ ክፉ ሁሉ የምሰወረው እቅፍ ውስጥ ስሆን ብቻ ነው። የእቅፍህ ሙቀት ሁኔተን አስረስቶ የሰላምህን ስፋስ ያነፍሳል፣ የምድሩን አስትቶ የዘላለም ሀሳብህን ያስኖራልና ክብር ይሁንልህ።
በአንተ ነጋልኝ ብዬ በራሴ እንዳልውል ደግሞ እርዳኝ። ውሎዬን፣ ቀኔን፣ እርምጃዬን፣ ሁሉ ነገሬን ለአንተ ክብር አድርጌው እንድውል በጸጋህ ደግፈኝ። መውጣቴን አቅናልኝ፣ መግባቴን አስውብልኝ፣ የእግሬን እርምጃ ወስንልኝ፣ የአንደበቴን ቀል ተቆጣጠርልኝ፣ በዋልክበት ልዋል፣ ክብር በሌለበት አይሁን ክብሬ፣ በማትገኝበት አይሁን መገኛዬ፣ ከራሴ ፈቃድ እና ሀሳብ ከልክለኝ በምክርህ እና በፈቃድህ አራምዳኝ። አሜን
✍ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
@orthodox_new_mezmur@orthodox_new_mezmur