ብርብር ማርያምን የማያውቅ ኦርቶዶክስ የአንድ ብሔር ይመስለዋል
***
የኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ባለቤቷ ማን ነው ከተባለ በአንድ ቃል ....ኢየሱስ ከሚል ስም ላይ ይወድቃል።
ባህሪዋም ቅድስት እና ኩላዊት ሲሆን ብዛቷም አንድ ነው።
ጠላት ግን ሲከሳት የነፍጠኛ ሃይማኖት፣የገዢ መደብ ቤት ብሎ ባልዋለችበት ስሟን ይጠራሉ።
ባሻዬ ....
በእርግጠኝነት ብርብር ማርያም የሚባል ገዳምን ብታውቅ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከየትኛውም ብሔር ትከሻ ተንጠልጥላ እንዳልመጣች ትረዳለህ።
ደቡብ በሚባለው ስፍራ ህዝብ እንዲህ ሳይሰፍር ብርብር በምትባል ስፍራ ላይ ንጉስ ቆስጢንጢኖስ አርዮስን በኒቂያ ጉባኤ ይወገዝ ዘንድ ጉባኤ አበው ከዘረጋ ከ3 ዓመት በኃላ በ328 ዓ.ም
ወደእዚህች ስፍራ ታቦተ ገብርኤል እና ታቦተ ማርያምን ይዞ በመምጣት ለ1100 ዓመት በስፍራው ተሰርቶ የነበረውን መሰዋተ ኦሪት ለውጦ ወደ ህገ ወንጌል ቀይሯል።
በእዚህ ስፍራ የነበሩት ቀደምት የጋሞ ህዝቦች ከእግዚአብሔር ጋር የተዋወቁት ክርስቶስ በቤቴልሔም ከመወለዱ ከ800 ዓመታት በፊት በካህኑ ሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በኩል እንደሆነ ብነግርህስ?
አንተ ከምትከሳቸው ነገስታት የሥነ ህዝብ ስርዓት በፊት ብርብር በሚባል ማማ ላይ ከህገ ኦሪት እስከ ህገ ወንጌል ተዘርግቶ በአዲስ ኪዳን ዘመን ኦርቶዶክስ የምትባል የእምነት አስተሳሰብ የያዘች መቅደስ በእዚህ ከፍታማ ስፋራ ላይ ነበረች።
የዛሬን አያድርገው እና ይህቺ ስፍራ የእውቀት ፣የምስጋና እና የሊቃውንት መፍለቂያ እንደሆነች አባ ባሕርይ የተባሉ መኖክሴ አማናዊ ምስክር ናቸው።
የቅድስት ቤተክርስትያን የጸሎት እና የታሪክ መጽሐፍ ብርብር ከሚባል ማማ ላይ እንደሚገኝ መዝሙረ ክርስቶስን ብታገላብጥ ታውቅ ነበር።
ስለዚህ ባሻዬ.... ለኦርቶዶክስ ገዢ ፈላጭ እና ፈጣሪ አካል ስትሰጣት "ኢየሱስ" ከሚለው ስም ውጪ ዕጣ አትጣልባት።
ለኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ብሔርም ይመደብ ዘንድ ከተገባ ብሔሯ ሰማያዊት እንደሆነች ከእኛ ከልጆቿ አንደበት ሰምተህ አስተጋባ።
@ጥንታዊት ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም 2015 ዓ.ም
እግዚአብሔር ይመስገን!!!
Kune Demelash kassaye -Arba Minch
@ortodoxtewahedo