☕አንድ ሸክላ ሰሪ ቡና የሚያፈላበትን እቃ መስራት ቢፈልግ የሚሰራው ጀበናን ነው ።
ይሄንን ጀበና ለመስራት ያነሳሳው ቡና ለማፍላት ያለው ፍላጎቱ ነው ፤ ስለዚህ ይሄንን ጀበና የሚሰራበት ምክንያት አለው ማለት ነው ።
👉በሌላ አማርኛ ደግሞ ቡና የሚያፈላበት እቃ ባያስፈልገው ይሄንን ጀበና አይሰራውም።
⚠️ ለሰራው ጀበናም የሚሰጠው ቅርፅ ቡና ለማፍላት የሚያመቸውን ቅርፅ ነው።
እንግዲህ ይሄ ጀበና የተፈጠረበትን አላማ አሳክቷል የሚባለው "በዘመኑ ሁሉ ቡና በማፍላት የሰራውን ሰው ሲያገለግል ነው።
👉ሸክላ ሰሪ አንድ ህይወት የሌለውንና ከጭቃ የሚሰራውን ጊዜያዊ እቃ ለመስራት ምክንያትና አላማ ካስፈለገው በራሱ ምስልና እስትንፋስ ህያው አርጎ የፈጠረውን ሰው እግዚአብሄር እንዴት ያለ ምክንያት ይፈጥረዋል??
👉እንዴትስ ያለ አላማ ይፈጥረዋል??
እግዚአብሄር እኮ የአላማ አምላክ ነው። የሚያደርገውን ሁሉ የሚያደርገው ከዘላለም ሀሳቡ አንፃር ነው።
👉ጊዜ ለማባከን ወይንም ሰአት ለመግደል ብሎ ማንንም አይፈጥርም ፤ ሰማይና ምድርን እንዲሁም እስትንፋስ የሌላቸውን ግኡዝ ፍጥረታት እንኳን የፈጠራቸው ክብሩን ሊናገርባቸው ነው።
አላማ ማለት ፦እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን ከመፍጠሩ በፊት ልቡ ውስጥ የነበረ ሀሳብ ማለት ነው ።
አላማ ማለት ፦ እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን ለመፍጠር ያነሳሳው ምክንያት ማለት ነው ።
T.me/revealjesus