የካቲት_26
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም
የካቲት ሀያ ስድስት በዚህች እለት ነቢይ_ሆሴዕ አረፈ፣ ለቅዱሳን_ሳዶቅና ከእርሱ ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉ ሁለት_ሺህ_ስምንት ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
#ቅዱስ_ሆሴዕ_ነቢይ
የካቲት ሀያ ስድስት በዚህች እለት ዖዝያ ይባል የነበረ እውነተኛ ነቢይ ሆሴእ አረፈ። ዳግመኛም ይህ ነቢይ በአራቱ የይሁዳ ነገስታት ዘመን ትንቢት ተናገረ። እሊህመ ዖዝያን ኢዮአታም አካዝ ህዝቅያስ ናቸው። በትንቢቱም ድንቆች ስራዎችን ተናገረ የእስራኤልንም ልጆች ብሎም ጠራቸው እግዚአብሔርም ቁጣውን ከእርሳቸው እንደማይመልስ አስረዳቸው።
እንዲህም አለ የእስራኤል ልጆች ቁጥራቸው እንደማይሰፈርና እንደማይቁጠር የባህር አሸዋ ቢሆን ከጥቂት በቀር አይተርፍም አለ። ስለ አህዛብም በ እግዚአብሔር ማመን ተናገረ እንዲህም አለ እኔ ወገኖቼ ያልሆኑትን እጠራቸዋለሁ እነርሱም ይሰሙኞል።
ዳገመኛም ስለ መድኃኒታችን መከራ መቀበልና በከበረ ደሙ ስለ መዳናችን ስለ ትንሳኤውም እንዲህ ብሎ ተናገረ። እሱ በመከራ ገርፎ ያድነናል እርሱም በመከራ አቁስሎ ይቅር ይለናል ሲያድነንም በሁለተኛው ቀን ነው ።
በሶስትኛውም ቀን ድነን በሱ ፊት እንነሳለን እግዚአብሔርንም አውቀን እንከተለው ዘንድ ስለ ሞት ስልጣን መሻር ስለ መቃብርም መሸነፍ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ሞት ይዘህ ማስቀረትህ መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት ነው ትንቢትን እየተናገረ ሰባ ዓመት ያህል ኑሮ በበጎ ሽምግልና አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በነብዩ ቅዱስ ሆሴዕ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
#ቅዱስ_ሳዶቅ
በዚህችም እለት የከበሩ ሳዶቅና ከእርሱ ጋር የሆኑ ሁለት ሺህ ስምንት ሰዎች በሰማእትነት አረፉ። ይህንንም የከበረ ሳዶቅን ለፀሀይ ይሰግድ ዘንድ የፋርስ ንጉስ ብርህም ፈለገው ቅዱሱም ለፈጣሪዋ እንጂ ለዚች ለምትታይ ፀሀይ ልሰግድ ከእናቴ ማህፀን አልወጣሁም ብሎ መለሰለት።
ብርህም ንጉስም መልሶ ለዚች ፀሀይ አምላክ አላትን አለው ቅዱስ ሳዶቅም አለሙን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ አምላክ ነው አለው ። ንጉሱም የቅዱስ ሳዶቅን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የከበረ ሳዶቅም ቁሞ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከዚህም በኃላ ራሱን ዘንበል አድርጎ ቆረጡት።
ያን ጊዜ ከሰማይ ብርሀን በላዩ ወረደ ከዚያ ያሉትም ሁሉ አይተው እኛ ሁላችንም በቅዱስ ሳዶቅ አምላክ የምናምን ክርስቲያን ነን ብለው ጮኹ ንጉሱም ሁሉንም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማእትነት አክሊልንም በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ ቊጥራቸውም ሁለት ሺህ ስምንት ነፍስ ናቸው።
††† "ኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንመለስ:: እርሱ ሰብሮናልና: እርሱም ይፈውሰናል:: እርሱ መትቶናል: እርሱም ይጠግነናል:: ከሁለት ቀን በሁዋላ ያድነናል:: በሦስተኛውም ቀን ያስነሳናል:: በፊቱም በሕይወት እንኖራለን:: እንወቅ:: እናውቀውም ዘንድ እንከተል . . . " ††† (ሆሴዕ 6:1-3)
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን አሜን፡፡
@sebhwo_leamlakne ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞