۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡
[
ሱራ አል-ዙመር አንቀፅ 53 ]
ይሄን የቁርአን አንቀፅ እሰኪ ከፋፍለን እንመልከተው
:-👇👇1.ኛ 🌟"
ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ "🌟 አላህ እንዲህ ማለቱ:-👇👇
ምንም ያህል የወንጀል ብዛት ቢኖርብን፤ እኔ ወንጀሎቼ ብዙ ናቸው አላህ አይምረኝም ብለን ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ እንደሌለብን ያሳያል። 🍂
2.ኛ 🌟 "በእርግጥ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና" 🌟
አንድ ሰው በእውነት ከልቡ ወደ አላህ ከተመለሰ (ተውባ) ካደረገ ወንጀሉ ምንም ያህል የበዛ እና የከፋ (የገዘፈ) ቢሆንም አላህ ወንጀሎቹን ሁሉ (ትንሽም ትልቅም) ይሁን ይምርለታል። 🍂
4.ኛ 🌟 " እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና " 🌟
አላህ መሐርታው የሰፋ እና እዝነቱ ገደብ የሌለው መሆኑን ያሳያል። እናም ያንተ ወንጀል ምንም ያህል የበዛ እና የገዘፈ ቢሆንም ከአላህ ሰፊ መሓርታ እና ገደብ የለሽ እዝነት በፍፁም አይበልጥም። 🍂
📌 | የዚህ የቁርአን አንቀፅ ቱሩፋቶች | 📌
👉 ለእያንዳንዱ ወንጀለኛ ትልቅ ተስፋን ትሰጣለች:- አንድ ሰው ምንም ያህል ወንጀለኛ ቢሆን የአላህ መሐርታና እዝነት ሁሌም ክፍት እንደሆነ ታሳያለች። 🍁
👉 ወደ አላህ እንድንመለስ (ለተውባ) ታነሳሳናለች :- ሰዎች ከሰሩት ወንጀሎች ተቆጥበውና ተፀፅተው ከልባቸው ወደ ጌታቸው እንዲመለሱ ታነሳሳለች። 🍁
👉 አላህ ለባሮቹ የለውን ፍቅርና እዝነት ታሳያለች :- አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ ኃጢአተኞችን እንኳን ወደ እራሱ አስጠግቶ " ባሮቼ ሆይ!!" ብሎ ነው የጠራቸው ይህም አላህ ለባሮቹ ያለውን ወደር የለሽ ፍቅር እና እዝነት ያሳያል። የባሮቹ ሁኔታ ምንም ቢሆንም። 🍁
👉 የአላህ መሓርታ ገደብየለሽ መሆኑን ያሳያል:- አንድ ሰው ምንም ያህል ወንጀል ሰርቶ ከመሞቱ በፊት ወደ አላህ ከተመለሰ አላህ ወንጀሎቹን ሁሉ እንደሚምረው ታሳያለች። 🍁
👉 ተስፋ ከመቁረት ትጠብቃለች:- አንድ ሰው ምንም ወንጀል ሰርቶ ከወንጀሉ ብዛት ወይም ግዝፈት ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ እንደሌለበት ታስጠነቅቃለች ምክኒያቱም የአላህ እዝነት እና መሓርታ ከሱ ወንጀሎች የሰፉና የገዘፉ በመሆናቸው። 🍁
👉 ከዚህ የቁርአን አንቀፅ የምንማራቸው ነጥቦች
:-👇👇
🔺 ከአላህ እዝነት በፍፁም ተስፋ አለመቁረጥ።
🔺 በእውነት ከልባችን ወደ አላህ ስንመለስ አላህ ይምረናል።
🔺 አላህ ወደሱ ከወንጀላቸው ተፀፅተው በእውነት ከልባቸው የተመለሱትን ፀፅት ወይም ንስሓቸውን (ተውባቸውን) ይቀበላል።
🔺 ሸይጣን ወንጀል እንድንሰራ ይጎተጉተናል ከዛም ተፀፅተን ወደ አላህ እንዳንመለስ ቢፈልግም አላህ ግን ሁሌም ተስፋ ሳንቆርጥ ወደ እሱ እንድመለስ (ተውባ) እንድናደርግ ይፈልጋል።
👉 የትኛውም ወንጀል አላህ መሓርታ እና እዝነት አይበልጥም።
ባጠቃላይ ይህ አንቀፅ ቁርአን ውስጥ ካሉ መልክቶች ውስጥ ትልቅ ተስፋን የሚሰት አንቀፅ ነው። ይህ አንቀፅ በሕይወት እስካለን ድረስ ከወንጀላችን ተመልሰን የአላህን መሓርታ ማግኘት እንደምንችል ያሳያል። እናም የአላህ ባሮች ሆይ ይህን ሰፊና ወደርየለሽ የአላህ መሓርታ እና እዝነት ተረድተን ወደ አላህ መመለስ ይኖርብናል። ረመዳን ደግሞ ለዚህ በጣም ምርጥ አጋጣሚ ነው። የረመዳንን ልዩ እድል ተጠቅመን ወደ አላህ መመለስ ይኖርብናል። ረመዳን ከተገኘባቸው ምክኒያቶች ውስጥ ራሱ አንዱ ወንጀላችንን ለማስማር ነው ስለዚህ ይህን ምርጥ አጋጣሚ ተጠቅመን ወንጀላችንን ከማስማር መቦዘን የለብንም። ማስጠንቀቂያ!!🫵‼️‼️አላህ መሓሪ ነው እያልን እያወቅን ወንጀል ውስጥ በተደጋጋሚ መዘፈቅ ሌላ ከባድ ወንጀል ከመሆኑም ባለፈ አደብ ማጣትና አላህን መናቅ ነው ስለዚህ በጣም ልንጠነቀቅ ይገባል። አላህ አዛኝ እና መሓሪ እንደሆነው ሁሉ ቅጣተ ብርቱም ነው የአላህ ቅጣት ደግሞ እጅግ በጣም የከፋ ነው። ከማን ጋር እየተሳፈጥን መሆኑንም ልብ ማለት ይገባናል‼️። አላህ እንዲህ ይላል:-👇👇
۞ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው፡፡
وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الْأَلِيمُ
ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን (ንገራቸው)፡፡
[
ሱረቱል ሒጅር አንቀፅ 49 ]
እንዲህም ይላል:-👇👇
فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُعَذِّبُ عَذَابَهُ أَحَدٌ
በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም፡፡
[
ሱረቱል ፈጅር አንቀፅ 25 ]
አላህ ባነበቡት ከሚጠቀሙት ያድርገን!አሚን!!🤲
ወሰላሙ አለይኩም ወረሀመቱላሂ ወበረካቱህ 👋
@sebil_tube @sebil_tube