ሰሌዳ | Seleda


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን ሰሌዳ ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


በቻይና ሻንጋይ ከተማ በአንድ የሮቦት አምራች ኩባንያ የምርት ማሳያ ስፍራ በስራ ላይ የነበሩ 12 ሮቦቶች በሌላ አምራች ኩባንያ ሮቦት መታገታቸው ተገለጸ‼️

ሁነቱን ተከትሎ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙሃንን አነጋግሯል።

እገታውን የፈፀመችው ኤርባይ የተሰኘችው ሮቦት በቅድሚያ ወደ 12ቱ ሮቦቶች በመጠጋት ስለ ስራ ሰዓታቸው ታነጋግራቸዋለች።

በዚህም ከተገቢው የስራ ሰዓት በላይ እየሰሩ መሆኑን በመግለፅ አብረዋት እንዲሄዱ ስታሳምናቸው እና ተከትለዋት ሲሄዱ ኦዲቲ ሴንትራል ያጋራው የቪዲዮ መረጃ ያሳያል።

በንግግራቸው ወቅት ኤርባይ፥ ትርፍ ሰዓት ትሰራላችሁ? ወደ ቤታችሁስ ሄዳችሁ ታውቃላችሁ? በማለት ስትጠይቃቸው፤ እነርሱም አርፈው እንደማያውቁ እና ቤትም እንደሌላቸው ሲመልሱላት ይሰማል።

ሲጋራ እንደ አዝናኝ ቀልድ ተቆጥሮ የነበረው ተንቀሳቃሽ ምስሉ ሮቦቶቹ በታገቱበት አምራች ድርጅቱ ካሜራ የተቀረፀ ሲሆን፤ በሻንጋይ የሚገኘው የሮቦት አምራች ድርጅት ስለ እገታው መግለጫ ከሰጠ በኋላ እውነትነቱ ተረጋግጧል።

በመጠኗ አነስ የምትለው ኤርባይ የሃንግዙ ሮቦት አምራች ድርጅት ስሪት መሆኗ ወደ ኋላ ላይ የተቋሙ ቃል አቀባይ ገልፀዋል።

ቃል አቀባዩ ኤርባይ የሌሎቹን ሮቦቶች የውስጥ አሰራር ፕሮቶኮል እንድትረዳ ለማድረግ ድርጊቱን እንደ ሙከራ መጠቀማቸውን በመግለፅ እገታው እውነት እንደነበር አስረድተዋል።

አያይዘውም፥ በንግግር ብቻ እገታው ሊፈፀም እንደማይችል በመጠቆም የሮቦቶቹን የውስጥ አሰራር እርሷ እንድትረዳው ተደርጋ መሰራቷ ዋናው ጉዳይ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በቀጣይ ግኝቶቹ ውሳኔ ማሳለፍ የሚያስችል፣ ከሌሎች ሲስተሞች ጋር በጋራ መስራት የሚችል እና ሌሎችም ከእውነታው ዓለም የተቀራረቡ ማሻሻያዎችን እያደረገ እንደሚሄድ ይጠበቃል።


ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” የተሰኘውን አዲስ ሚሳኤል በስፋት ማምረት ትቀጥላለች - ፑቲን

ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን በሚገኘው ዲኒፕሮ ከተማ በአዲሱ ሚሳኤል ጥቃት ያደረሰችው ዩክሬን የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን ተከትሎ በተወሰደ አጸፋዊ ምለሽ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ፑቲን ስለ አዲሱ “ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል ሲናገሩ “በዓለም ላይ ማንም እንደዚህ ዓይነት መሳርያ የለውም” ብለዋል። “ፈጠነም፣ ዘገየም ግን ያደጉት ሀገራት በቅርቡ ይኖራቸዋል። በመስራት ላይ እንዳሉም እናውቃለን” ሲሉ ጨምረዋል።

ስለ ሚሳኤሉ አደገኛነት ሲናገሩ በርካታ መሰል ሚሳኤሎችን በአንድ ላይ ማስወንጨፍ የኒውክሌር ጥቃት የተፈጸመ ያህል ውድመት ያደርሳል ብለዋል።

በዓለም ላይ እስካሁን ይህንን መሳሪያ በጸረ ሚሳኤል ማስቆም የሚቻልበት አቅም የለም ሲሉም ገልጸዋል። ይህንን ሚሳኤል በትክክለኛ ውጊያ ላይ በድጋሚ እንደሚሞክሩትም ተናግረዋል።

ሩሲያም እነዚህን ሚሳኤሎች በስፋት ማምረቷን እንደምትቀጥል መግለጻቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።


ባንኩ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደረግ ነው

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ለደንበኞቹ ቀደም ብሎ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም ባንኩ በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል እንዲሁም በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ላይ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡


በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መከሰቱ ተሰማ

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን አሐዱ የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡

አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡


በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የተሰጠ ውክልና የለም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ሚኒስቴሩ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና እንደሌለ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።


የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው

በዓሉ "የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ አደም ፋራህ፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዓለሙ ስሜን (ዶ/ር) ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


ህገ-ወጥ እርድ ባካሄደ ድርጅት ላይ የ15 ሺህ ብር ቅጣት እና የማሸግ እርምጃ ተወሰደ

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወሪዳ 7 ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ እንስሳት በማረድ ለህብረተሰቡ ሊያቀርብ የነበረው ድርጅትና ግለሰብ ከሌሊቱ 7:00 ሰዓት ላይ በደረሰው የህብረተሰቡ ጥቆማ ከታረደው በሬ እና ለእርድ ከተዘጋጁት በሬዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

ድርጅቱና ግለሰቦቹ የደንብ ማስከበር አባላት ከፀጥታ ጥምር ግብረ ሀይል ጋር በቦታው የተገኙ የታረደ የአንድ በሬ ስጋ ለቄራዎች ድርጅት እንዲወገድ ያስረከቡ ሲሆን በተጨማሪም ለእርድ ተዘጋጅተው የነበረ 5 በሬዎች ለቄራዎች ድርጅት በማስረከብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን አድርገዋል።

ድርጊቱ ሲፈፅም የነበረ ድርጅት እንዲታሸግ በማድረግ 15 ሺህ ብር የተቀጣ ሲሆን በቦታው የተገኙ በሬ አራጅ ግለሰቦች እያንዳንዳቸው ሦስት ሦስት መቶ ብር ተቀጥተዋል።

ባለስልጣኑ ጥቆማ ለሰጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ምስጋና እያቀረበ በሌሎች አካባቢዎችም ለህብረተሰቡ ጤንነቱን ያልተረጋገጠ ስጋ በማቅረብ የህብረተሰቡን ጤና ችግር ውስጥ የሚጥሉ ግለሰቦችን መረጃ በመስጠት ማህበራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት ማስተላለፉን የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎች ነፃ የስልክ መስመር 9995 መረጃ እንዲያቀብሉት ተቋሙ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡


ሂዝቦላህ የእስራኤል አየር ኃይል የቴክኒክ ማሰልጠኛ ጣቢያ ላይ የሮኬት ጥቃት ፈፀመ

ሂዝቦላህ በሀይፋ የሚገኘው የእስራኤል አየር ኃይል የቴክኒክ ሠራተኞች ማሰልጠኛ ጣቢያ ላይ የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ፡፡

ቡድኑ በተከታታይ በፈፀመው የሮኬት ጥቃት ከሊባኖስ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሀይፋ ከተማ የተገነባውን የእስራኤል አየር ኃይል የቴክኒክ ሠራተኞች ማሰልጠኛ ጣቢያ መምታቱን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በጎላን ተራሮች ላይ የተገነባውን የእስራኤል 210ኛ ክፍለ ጦር የቅድመ ማስጠንቀቂያ ጣቢያ በሚሳኤል መምታቱን አስታውቋል፡፡

በእስራኤል ጦር እና በሂዝቦላህ መካከል ከባድ የተባለ ውጊያ በተደረገበት በዛሬ ውሎ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ተደጋጋሚ የአየር ጥቃት መፈፀሟ መሰማቱን የዘገበው ጂኦ ፖለቲክስ ነው፡፡


በአዲስ አበባ የገበያ ማዕከል በተደረገ ፍተሻ በርካታ በኮንትሮባንድ የገቡ የሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ‼️

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ ባደረገው የክትትልና የጥናት ተግባር በርካታ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን መያዙን አስታውቋል፡፡ የፖሊስ መምሪያው የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ለማ እንደገለፁት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ/ም በክ/ከተማው ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል ውስጥ በሚገኝ የንዋየ ቅዱሳትና ሞባይል ቀፎ መሸጫ ሱቅ ላይ በተደረገ ፍተሻ በርካታ የሞባይል ቀፎዎችን ከነ ቻርጀሮቻቸው መያዙን ገልፀዋል፡፡ በፍተሻውም 301 የስማርት ስልክ ቀፎዎች፣ 61 ኖርማል በተን ሞባይል ስልክ ቀፎዎች እንዲሁም 29 የሞባይል ቻርጅሮች ይገኙበታል ብለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዘበት አንደኛው ሱቅም የንዋየ ቅዱሳት መሸጫ ቢሆንም ከውስጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የሚከማቹበት መሆኑንም ማረጋገጥ እንደተቻለ የገለፁት ኃላፊው ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ ውጪ በንዋየ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ስም የሀገርን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኃላፊው በመልዕክታቸው አስታውቀው መሰል ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር የፀጥታ አካላት የሚያከናውኑትን ሥራ ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር መልዕክት ተላልፏል፡፡


የ59 ዓመቷ ካናዳዊት በ1 ስዓት ከ1ሺህ 500 በላይ ፑሻፖች በመስራት ክብረ-ወሰን ሰበረች‼️

ይህች ሴት በአንድ ስዓት ውስጥ 1ሺህ 575 ፑሻፖች የሰራች በዓለም የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን በጊነስ ሪከርድስ ስሟን አስመዝግባለች፡፡

ዶናጄን ዊልዴ ከዚህ በፊት የነበረውን ሪከርድ በ17 ደቂቃ ቀድማ በማሻሻል የዓለም ክብረ-ወሰን የሰበረች በእድሜ ትልቋ ሴት መሆኗን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡

ዊልዴ ለጂኔስ ወርልድ በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ በስዓቱ በጣም ጠንካራና ጥሩ አቅም ስለነበረኝ በቀጣዮቹ 17 ደቂቃዎች ከዚህ የተሻለ ቁጥር ያለው ፑሻፕ እሰራለሁ ብዬ አስቤ ነበር ብላለች፡፡

ዊልዴ ከዚህ ቀደም "በአብዶሚናል ፕላንክ ፖዚሽን" ውድድር 4 ስዓት ከ30 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመቆየት ረጅሙን ስዓት በማስመዝገብ ብቸኛዋ ሴት ባለ ክብረ-ወሰን ነበረች ብሏል ዘገባው፡፡

ለዚህ ውድድር ያደረገቸው ልምምድ ለዚህኛው ሪከርድ ምክንያት እንደሆነላትም ተናግራለች፡፡


አይሲሲ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ቆረጠ

ከእስራኤል ባለስልጣናት በተጨማሪ እስራኤል ባለፈው ሃምሌ ወር በጋዛ ላይ በፈጸመችው ጥቃት እንደተገደለ የሚታመነው የሃማስ ወታደራዊ አዛዥ መሐመድ ዴይፍ በፍርድ ቤቱ የእስር ማዘዣ የተቆረጠበት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

የአይሲሲ ፍርድ ቤት ዳኞች እንዳስታወቁት፤ የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸውን ሰዎች በወንጀል ለመጠየቅ የሚያስችል መነሻ መሰረት አለ።

በእስራኤል ጋዛ ጦርነት ወቅት የጦር ወንጀል እና ሰብዓዊነት የጎደለው ድርጊት እንዲፈጸም ስለማድረጋቸው የሚያመላክቱ ማስረጃዎች እንደቀረቡ ጠቁመዋል።

እስራኤልም ሆነች ሃማስ የጦር ወንጀል በመፈጸም የቀረበውን የእስር ማዘዣም ሆነ ውንጀላ የማይቀበሉት መሆኑን በመግለጽ አጣጥለውታል።


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃት ፈጸመች

ጥቃቱ ዩክሬን በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይሁንታ በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎች በሩሲያ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ጥቃቱ የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ÷ሩሲያ በዛሬው ዕለት አዲስ የሮኬት አይነት ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏን አረጋግጠዋል፡፡

ሮኬቱም የአህጉር አቋራጭ ሚሳዔል ባህሪያት እንዳሉት ፕሬዚቱዳንቱ መናገራቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ሩሲያ ወደ ዩክሬን ያስወነጨፈችው የባላስቲክ ሚሳዔል ሳይሆን እንዳልቀረ ስማቸው ያልተጠቀሱ ምዕራባውያን ባለስልጣናት መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡


#InfinixEthiopia

ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች የሆኑትን ሆት 40 ፣ ኖት 40 ፣ ዜሮ 40 እና የኢንፊኒክስ ስማርት TVን ይግዙ ኩፖን ይወስዱ፡፡ ባሻዎት ስፍራ ፎቶ በመነሳት #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽ ታግ በመጠቀም የማህበራዊ ገጾት ላይ ያጋሩ የዛንዚባር የቢዝነስ ክላስ ደርሶ መልስ የአውሮፕላን ቲኬት እንዲሁም በርካታ የኢንፊኒክስ ምርቶችን ያሸንፉ ይሸለሙ፡፡

መመሪያ

1. የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የኢንፊኒክስ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡
3. #InfinixEthiopia የሚለውን ሃሽታግ መጠቀሞን አይርሱ፡፡

Tag ሲያደርጉ ለ Facebook @InfinixMobileEthiopia ፣ ለ Instagram @infinixethiopia ለ TikTok @Infinixet እና ለ Telegram @Infinixeth ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።




ዛሬ ጠዋት በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ መነሳቱ ተሰማ።

ተማሪዎቹ ይህንን የተቃውሞው ድምፅ ያሰሙት በህዝባችን ላይ ግድያ ይቁም በሚል ምክንያት ሲሆን ተማሪዎቹ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ነው ወደ ተቃውሞ እንደወጡ ለማወቅ የተቻለው።

ተቃውሞው እንዳይባባስ የፀጥታ ሀይሎች ጥረት አድርገዋል።










በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ስራ ተጀመረ‼️

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዛሬ በይፋ በተጀመረው ስራ፣ በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ተሃድሶ ማዕከላት ማስገባት መጀመሩን የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ተሀድሶ ማዕከላት ለመግባት በእጃቸው ያለውን ቀላል ትጥቅ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የነፍስ ወከፍ እና የቡድን ጦር መሳሪያዎች ርክክብም የአፍሪካ ህብረት፣የመንግስታቱ ድርጅትና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል።

በመቐለ፣ እዳጋ ሀሙስ እና ዓድዋ የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎች ስልጠና የሚወስዱባቸው ማዕከላት መዘጋጀታቸውን የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በትናንትናው ዕለት ማስታወቁ ይታወሳል።

የቀድሞ ተዋጊዎች በተዘጋጁ ማዕከላት ስልጠናዎችን ከወሰዱ በኋላ የመቋቋሚያ ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማህበረሰቡ በመቀላቀል መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል ተብሏል።

Показано 20 последних публикаций.