ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Транспорт


╔════◈◉◈════╗
                     أهل السنة والجماعة
            ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⚪️አህለሱና ወልጀመዓህ ስንል የሰለፎችንና የኸለፎችን የግንዛቤ ዘይቤ የሚከተሉ ማለት ነው።
🔴ይህ መንገድ ሌሎች የኢስላም አስተሳሰብ ተከታዮችን አያከፍርም
🔎አመላካች የሰሪን ምንዳ ያገኛልና ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩልን
╚════◈◉◈════╝

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Транспорт
Статистика
Фильтр публикаций


የእንጀራ የመጨረሻ ክፍቱ ለእንጀራ ብለህ ሞራል እምነት አኽልቅ እንድትሸጥ ማድረጉ ነው።

አይ እንጀራ


Репост из: ABRET PRO
የማንቂያ ጥሪ! [አብሬት]

በአብሬት ሸይኾች የቆመውንና እስካሁን አብርቶ ያለውን ታላቁ የአብሬት ሀድራ ተርቲቦችን ለማፍረስ ፥ በሀሪማው የነበረውን የተሰውፍ መስመር ፥ ዒባዳና የትምህርት አሰጣጥን በልማት ስም ወይም የሂፍዝ መሀከል በማቋቋም ስም አስታኮ መስመር በሳቱ አካሄዶች ለመቀየር ታቅዷል::

የመሻኢኾቻችንን አቂዳ ሙሉ በሙሉ በሚቃረኑ በእነ አዩብ ደርባቸው ፥ ኑረዲን ደሊል ፥ ሙኣዝ አሊ እና ባቂል በደዊ የሚመራ ስብስብ ወደ አብሬት ሐሪማ በልማት ስም ለመግባት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ነው:: ጉዳዩን በደምብ ያልተገነዘቡ አንዳንድ ሙሪዶችን እና አንዳንድ የሸኾችን ቤተሰብ አካታው ይዘው በግልፅ እንቅስቃሴ ጀምረዋል::

አብሬት ማንነታችን ፣ ህልውናችን ነው! ለሀገራችን እስልምና ታላቅ መሰረትም ነው:: ከመሻኢኾቻችን መንገድ ባፈነገጡ ስብስቦች የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲለወጥ ልንፈቅድ አይገባም! ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን ሊያውቅ አውቆም ከዚህ ሴራ ሐሪማውን ሊታደግ ይገባል::

መልእክቱን copy & post ወይም share በማድረግ ተደራሽ እንድታደርጉልን እንጠይቃለን 🙏🏻


አሻዒራዎች እነማን ናቸው ??

አንዳንድ ወገኖች አሻዒራዎች የሆነ ጭራቅ አድርገው ለመሳል የሚሄዱበት ርቀትና ድካም ያዝናናኛል

ተራው ህዝብ የማያውቃቸውን ትተን አብዛኛው ህዝብ በተለይ ወደ መስጂድ ቀረብ ያለ ሱፊይ ይሁን ሰለፊይን ነኝ ባይ ፣ ኢኽዋኒም ይሁን ኡኽዋቲይ የሚያውቃቸውን ልጥቀስ

1/ ኢማም አንነወዊይ
    ዒልም ቀማምሻለሁ የሚል የትኛውም ሙስሊም አርበዑን አንነወዊያህ እና ሪያድ አስሷሊሂን ሳይቀራ ያለፈ የለም

2/ ኢማም ኢብኑ ሀጀር አል ዐስቀላኒ

ትላልቅ ሸርሆቻቸውንና የሀዲስ ጥናት መስክ ኪታቦቻቸውን ትተን “ ቡሉግ አል መራም “ የተሰኘችዋን የአሀዲሰል አህካም ኪታብ መውሰድ በቂ ነው

❇️ ከላይ የጠቀስናቸው ኪታቦች ሁሉም ወገን የሚቀራቸው ኪታቦች ናቸው ፣ እንደውም አብዛኞቹ ሰለፊይ ነን የሚሉ ወገኖች ዘንድ የዒልም ጣሪያዎቻቸው ናቸው ፣ ስለዚህ አሽዐሪያ ሲባል አትንደንበር ይሀው በየቤትህ አሉልህ ፣ አሽዐሪያን ማጥፋት ከፈለግክ እነዚህን መፅሀፍት ከቤትህ በማውጣት ጀምር


ለመሻይኾቻችን ያለን ፍቅርና ክብር እንደተጠበቀ ሆኖ አጉል ኢጎ ውስጥ መግባት ግን አስፈላጊ አይደለም


እርሱ : የአለም ኡለሞች ለእስልምና ያልከፈሉትን መስዋእትነት የሀበሻ ዑለሞች ከፍለዋል

እኔ : የስንት አገር ዑለሞችን መስዋእትነት አንብበህ ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የደረስከው ?

እርሱ : የየትኛውንም ሀገር

እረ ሀበሾች ተው ረጋ በሉ 😁😁😁 የአለም አህለሱና ለእስልምና ተመሳሳይ መስዋእትነት ነው የከፈለው


የሶሪያ ጦር ውስጥ ሰላት መስገድ በህግ የተከለከለ ተግባር ነበር

የበሻር ስርአት ወታደር መድቦ ሴቶችን ሂጃብ ያስወልቅ ነበር

ሶሪያዊው ዐሊም ዶ/ር አብዱልቃዲር ሁሰይን

❇️ ስልጣኑን ሲረከብ ቁርአን ይዞ ቃለ መሀላ የፈፀመ ፣ ሙስሊም ነኝ ብሎ የሚሟገት መሪ እንዲህ ሲያደርግ የፖለቲካ ክፋት ምን ያክል እንደሆነ ያሳያል


የጁሙዐ ሰጋጆች

በሳምንት ጁሙዐ ብቻ መስጂድ የሚመጡ ወንድምና እህቶችን ብዙ ሰዎች የጁሙዐ ሙስሊሞች ወዘተ እያሉ ሲያጭረፈርፏቸው እንሰማለን

መሆን ያለበት ይህችን በሳምንት ጁሙዐ መምጣታቸውን አበረታትተን ሌሎቹንም ቀኖች እንዲመጡ ማነሳሳት ነው ፣ ብልጥ የያዘውን ይዞ ነው የሚያለቅሰው ሲባል አልሰማችሁም ??

ለማንኛውም ጁሙዐ ብቻ የሚመጡ ወንድምና እህቶች እናመሰግናቸዋለን ፣ እነርሱ ባይመጡ ጁሙዐችን የጁሙዐ ድባብ አይኖረውም ነበር



1k 0 2 10 13



خطابا شرعيا (صح)
والاستنباطِ(صح)

العبد الفقير يناقش بعض الآراء في بحثه

هذه تحفة بمناسبة انتهاء الفصل 😊😊😊


🌹✨ሀዘል ሀቢብ✨🌹

✍ለትልቁ ሠውም ሆነ ለሶሐቦችም ከባድ በነበረው ዘመቻ ላይ ዘይነልዉጁድን ﷺ ለመከላከል ከጎናቸው ጦርነትን መካፈልን የተጠማው ጦልሓ ኡሁድ ላይ ጀግንነቱን አሳየ!

ዘይነልዉጁድ ﷺ በተጣሩ ቁጥር ቶሎ የሚመልሰውና ካጠገባቸው ስለማይጠፋው ጦልሓ አንዲህ አሉ፡

«♦️لقد رأيتُني يومَ أُحُدٍ ، و ما في الأرضِ قُرْبِي مخلوقٌ ، غيرُ جبريلَ عن يميني ، وطلحةَ عن يَسَاري♦️»

✨♦️የኡሁድ ወቅት እራሴን ተመለከትኩት ማንም ለኔ ቅርብ አልነበረም። በቀኜ ሰይዲና ጂብሪልና በግራዬ  ጠልሓቱ ውጪ...🥹

ወደ ዘይነልዉጁድ ﷺ የሚወረወሩትን እያንዳንዱን ቀስቶች በአንድ እጁ እየተከላከለ በሌላኛው እጁ ደግሞ በሰይፍ ይዋጋ ነበር..መገን እሱን😍

... ቁስል ቁስል ላይ ቢደራረበበትም እስከሚችለው አቅም ለዘይነልዉጁድﷺ ተከላከለ። ሠይደልዉጁድንﷺ በቆሰለው ጀርባው ላይ ተሸክሞ ተጓዘ! እሳቸውን ማትረፍ ላይ ቁዋው መጣለት።

ጌታው ሸይኽ ሚስባህ ዳና ከነቢ ዘይኔ ድርሳናቸው፡

        ለዕነቱላህ አለይ ኢብነ ቀመዐት፣
        በሰይፍ መታና አቆሰለዎት፣
        ትካሻዎን ገፍቶ ጉርቢያ ዶለዎት፣
        በፊተዎ ደሙን አፈታበዎት፣
       ልበዎ ፈሰሰ መቼም ሰው ነዎት፣
       በወገቡ አድርጎ ጦልሀቱ አወጣዎት ፣
       የዚያንለታ ታየ የጦልሀቱ ኦኔ፡፡
♦️✨♦️✨♦️✨💚✨♦️✨♦️✨♦️
        ያንን ሁላ ቁስል ምንም አላጀበዉ፣
        የነቢ ደም መፍሰስ ነው ያንገበገበዉ፣
        እንኳን እሱን እኔን ልቤን አዋከበዉ፣
        አይኔን አስለቅሶ ዛቴን አራገበው፣
        ዋ ከቶ ዋ ከቶ ዋልኝ ዋልኝ ለኔ
🥹በማለት ቃኙ።

ሙሉ ሰውነቱ ቁስል ብቻ የሆነው ጠልሓ ሠይዲን ﷺ በነበሩበት ሁናቴ ዳግም ሩህ ዘራበት፤ እግሮቹ ተንቀሳቀሱለት። ተሸክሟቸውም ወደ ተራራው ወጣ! ይህንን ክስተት ከሩቅ የተመለከቱት ሲዲቂዩ እና አቡ ኡበይዳ ኢብኑል ጀራህ ሲመጡ ሠይዲምﷺ በደከመው አንደበት ወደ ጠልሓ እየጠቆሙ «እኔን ትታቹ ጓድ'ኣቹ ጋር ሂዱ!»አሏቸው።
ሲዲቂዩ አህዋሉን ሲናገገሩ : «ጠልሓን ስናየው ሙሉ ሰውነቱ ቁስል በቁስል ነበር..ከእያንዳንዱ ሰውነቱ ደም ይፈስ ነበር! ከቀስት፣ ከድንጋይ፣ ከጦር፣ ከጎራዴ ብዙ ቁስሎች አርፈውበት ነበር። እራሱንም ስቶ ከአፉም ደም እየተፋ ነበር»አሉ።
«ጀነት ጦልሓቱ ላይ ዛሬ ወጅቦበታል!»አሉ ዘይነልዉጁድ😭... አወይ መሐባ.. የማያደርገው የለምስ!

https://t.me/sufiyahlesuna


ታላቋ እንስት
= = = - - - -

በዛች ደሳሳ ክፍል ውስጥ ምን አይባልም ።! ድካም የሚያስረሱ ጫውታውች የሚያስነቡ በደሎችየማይጠገቡ ትውስታውች የማይፈቱ ችግሮች ብቻ የያዘችው ጉዳይ ከክፍሏ ሰፍት በላይ ነው። እንደተለመደው በስራ የደከመውን ጉናቸውን ለማሳራፍ የፀሀይን መጨፍገገ ተመልክተው ብቸኛ በጉጉት ወደ ምትጠብቃቸው ክፍል አመሩ ።እነዚህ አጋዥ እረዳት የሌላቸው ችግራቸውን እራስ በራስ ወይም ለክፍላቸው ከመንገረ ውጪ ሌላ ሰሚ የሌላቸው በሰው ምስል ያሉ የሰው እቃዎች ብቻኛ የማውራት መብት የሚሰጣቸው ቦታ ሲደርሱ ድካማቸው ይጠፍል ጊዜው ለሊት ቢሆንም ለነሱ ግን ቀን ነው ክፍሉ እራሱ የዛሬ ዕርዕስ ምንድ ነው ብለው የሚጠብቅ ይመስላል ።

ፀጥታ ሰፍኖል ሁሉም በአይነ ህሊናው እርቆ የተጓዘ ይመስላል  ድንገት ከመሀል አንድ ደንገ ጡር ለምን  ሱመያ የበፊት ታሪዃን  አታወጋንም ስትል ከህልማቸው አባነንቻቸው ።

ሱመያም በሚያሳዝን ድምፅ አካባቢያችን ላይ ወረራ ከመፈፀሙ በፊት ከአባት ከእናቴ ጋር የተደላቀቀ ኑሮ የምኖር አባት በጉሳው ዘንድ የተከበረ የሚባል ሰው ነበር  አልች ምን ያርጋል በሚል ስሜት እየተቆጨች።

አሁን ያለችበት የሚያውቁ ጓደኞቿ ምን አክል እንደተጎዳች ገባቸው ከዛ ከትንደላቀቀ ሂወት ወደ ባርነት ምን አክል አስቸጋሪ እንደሆን  ለማንም ግልፅ የሆነ ጉዳይ ነው።

ታዲያ ቤተሰቦችሽ አሉ ከመሀል አንዷ ጠየቀች?
ቤተሰቦቼማ አለች ሱመያ እንባ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ የቤተሰብ ናፍቆት እሳቱ ከስር እየለበለባት ከፊሉ ተገደለ እኛም ወደ ባሪያ መሸጫ ተነዳን እኔና እናቴ ነበርን ነገር ግን እናቴ ለሌላ ሰው ተሸጠች እኔም ለሌላ ግለሰብ ተሸጥኩኝ ከእናቴ ጋር ላለመለያየት  የሚረዳኝ ካለ ብይ ጩኩኝ አልሄድም ብይ ተንከባለልኩኝ በዙሪያ የሚያዝን ካለ ብይ ደም እንባ አለቀስኩኝ ምን ያደርጋል አላች እልህ እየተናነቃት ከአለንጋ ውጪ የተረፈኝ ነገር የለም የተገረፍኩት ግርፍት አሁን ደርስ ይታወሰኛል አለች የጨካንችው ጥግ አሁን የምትገረፍ አክል እያንዘፈዘፋት።

ጊዜ በጊዜ ተተካ የነ ሱመያን ግፍ የሚበቀል ካሉበትን
የባርነት ቀንበር ነፃ የሚያወጣ አልተገኝም እና ላታ ኡዛ የደካሞች ሳይሁኑ የጠንካራውች ጌቶቾ ናቸው ይላሉ ግፈ  ሲያንገሸገሻቸው እነ ሱመያ

ዛሬ እነ ሱመያ ጋር አንድ እንግዳ ብቅ ብሎል ሱመያ ለእንግዳው የሚበላ ነገር እንድታቀርብ ታዛለች።

ነገሩ እንዲህ  ነው ከየመን አከባቢ የጠፍ ወንድማቸውን ፈላገ ወደ መካ ከተማ የተወሰኑ ወንድሞች ይከትማሉ።የፍለጋቸው ውጤት አመርቂ እንዳልሆነ የተረዱት ወንድማማቾቹ ወደ ሀገረ የመን ለመመለስ ይወስናሉ ከመሀከል ግን በመካ የተሳብ ወደ ሀገሩ ከመሄድ ይልቅ መካ ላይ መስፈርን የመረጠ ነበር ወንድሞቹን ተስናብቷ እሱ እዛ ለምኖር መካ ላይ ተቀመጠ

ይቀጥላል

✍ዘ.ሐ


✍የፍቅር ሐይል ግን ዐጂይብ ነው.. ሩሀችንንና ጀሰዳችንን የሚያጣምር አንዳች ውበት... ናፍቆቱ የማያልቅ፤ ውዴታው የማይሰለች፤ ትውስታው የሚነዝር አንዳች ነገር!

🌹ያ..የዘይነልዉጁድﷺ ፍቅር...ዱንያ ላይ በሚኖረን ቆይታ ህይወታችንን ሙሉ እሳቸውን አለመናፈቅ አይቻለንም። የናፍቆታችንን ሮሮ ለማስታገስ...አሏህ ይወፍቀንና ጀነት ላይ እስክናገኛቸው በትንሹም የሚያረግብልን ደግሞ ሰለዋት ነው!

« أَوْلَى النَّاسِ بِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَكْثَرُهُمْ عَلَىَّ صَلاَةً »

«የዉመል ቂያማ ላይ ለኔ ቅርቡ ሰው ማለት እኔ ላይ ሰለዋትን የሚያበዛው ነው»አሉ ዘይነልዉጁድﷺ♥️

✍🌹اللهم صلّ وسلم وبارك على سيدنا محمد النبى الأمي الزكي البهي الصفي النجي الوفي وأمطر علينا سحائب لطفك الخفي وحبك الجلي وعلى آله وصحبه وسلم🌹

https://t.me/sufiyahlesuna


ኢብኑ ሙነወር
~ ~ = ~ ~

ጅላልጅል መድኸሊ ነው መጅሊስ በአቂዳ ማቋቋም የሚፈልግ ቂላቂል ወሀብያ መጅሊስ በአቂዳ ማቋቋም ከፈለክ እራስህን ችለህ መድኸሊ መጅሊስ ማቋቋም ትችላለህ ደግሞ በጣም የሚገርመኝ ሱፊያ ያከፍራል ብሎ አፋን ሞልቶ ሲያወራ እንደው ተክፊር ጀማአ ፣ደኢሽ የመሳሰሉ በአለም ላይ ሰቅጣጭ የሙስሊም የኢስላም ጠላት ምንጭ የወሀብያ አቂዳ አደል
ከእኔ በፊት ላኢላኢለላህ የተረዳ አነበረም ያስተማሩኝ ኡለማውች እንኮን የላኢላሀ ኢለላህ ትርጉም አይገባቸውም ነበር ሲል ከሱ በፊት ያሉት ሁሉ ያከፈረው ሸህ ሙሀመድ ኢብኑ አብድል ወሀብ አደለም በቲኒሽ በትልቁ የኩፍር እሮኬት ምታስወነጭፉት ወሀብዩች አይደሉም ከማንም ጋር የማያስግዱ ፍርቃን የሚል ጀማአ የወሀብያ ጀማአ አደለም? በአንዋር መስጂድ ኢማም አንሰግድም በማለት ለብቻቸው የሚሰግዱ የወሀብያ ጭፍራ አደሉ ?ትላልቅ አሊሞችን ቄስ እያሉ የሚሳደቡ እነዚህ የወሀብያ እንጭጮች አደሉ?እነ ያሲን ኑሩ እነ አቡ በክር አህመድ በአጠቃላይ ኢኽዋን ካፊር ነው የሚለው እራሱ የመድኸሊ ቡድን አደለ ?ታላቁ አሊም የምትለው ፈውዛን አደል ኢርሻድ በሚለው ኪታቡ ላይ ከአይሁድ ከክርስቲያን በፊት አጠገብ ያሉ ሱፊያውችን ግደሉ እያለ የሚያዘው ?እረስቼው አንተው እራስህ ይህን ሱፊያ ቋንጃውን በለው እያልክ ስታነሳሳ የነበረው ።ታዲያ ሙፍቲ ላይ የምለጠፍው የውሸት ክስ ደደብ ተከታዩችህን ለማስደሰት ካልሆነ አሏህ ዘንድ በወሬ የሚታለፍ ነገር የለም ጅልም ቢሆን አንድ ቀን ይገበዋል።

✍ዘ.ሐ


መራራ እወነታውች

ወሀብያ ከአይሁድ ጋር አንድ ቀን ጦርነት ከፍቶ አያቅም ።
ታላቁ ሙጃሂድ ሰላሁዲን አል አዩቢ ሙሀመዱል ፍቲህ ኡመር ሙኽታር የቱኒሱ ሰኑሲ ጀማአ የሱዳኑ ደርቡሽ የሀበሻውቹ ኡለማውች ከአፄውች ጋር የተዋደቁት ሁሉም ሱፊ ናቸው እስኪ አንድ ከአይሁድ ጋር የተፍለማቹበትን አምጡ? የወሀብያ ገድል የተዘገበበት ኡንዋኑል መጀድ ፊ ታሪኺ ነጅድ የሚለው መፅሀፍ ያነበበ ወሀብዩች ዘመናቸውን የጨረሱት ሙስሊም እየጨፈጨፉ መሆኑን ትገነዘባለህ ።

✍ዘ.ሐ


አል ቃኢዳ፣ አልሸባብና ዳኢሽ ከወሀብያ አቂዳ የተቀዱ መርዛማ አስተሳሰቦች መሆናቸውን ሳዉቅ ፤ " እኛም ብሎ ሰለፊ , አሜሪካንና እንግሊዝ የመሰረተቱን እምነት የሰለፊ እምነት ብለው ይሸውዱኝ ወይኔ


በምክንያትና ውጤት ላይ የአሽዐሪዮች ዐቂዳ
———-

ከአሏህ ውጪ ያልለ ሁሉ ከአሏህ ከጃይ ( ፈላጊ ) ነው ፣ ይህም ከአሏህ ውጪ የሆነ ነገር አንዳችንም ነገር ማስገኘትና ማጥፋት እንደማይችል ያስይዘናል ፣ የትንኝ ክንፍን ማንቀሳቀስም ሆነ ማርጋትም ቢሆን እንኳ ያለ አሏህ ፍቃድ ማንም ሊፈፅመው አይችልም ።

ኡሙል በራሂን ከአንዋር አል በሂያህ ሸርህ ጋር


ፎቅ ገንብተዋል ያልከው : በቅድሚያ ይህን ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሄዱት ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ከሚወክሉት የቀድሞው የዑለሞች መንገድ ጋር በሀሳብ የማይስማሙ አካላት ናቸው ፤ የስም ማጥፋቱ መነሻ የፊቅህና የዐቂዳ አስተሳሰብ ልዩነት መሆኑን በደንብ አስምርበት ፤ በአሁኖቹና በዱሮዎቹ ዑለሞች መካከል ያለውን ልዩነት አንተም በተወሰነ መልኩ አይተሀዋል ።

እነዚህ አካላት የሙፍቲን ስም ሲያጠፋ መነሻቸው ይህ ልዩነት እንጂ የምር ሙፍቲ ስልጣን ወዳድ ወይም ሌባ ስለሆኑ አይደለም ይህን ደግሞ ከርሳቸው ጋር በሀሳብ የሚለያዩት እነ አቡበከር አህመድ እንኳ መጀመሪያ አካባቢ የመሰከሩት ጉዳይ ነው።

አንድን ወገን በሀሳብ ስለተለያዩት ብቻ የውሸት ፍረጃዎችን መደርደር ከሙስሊም የማይጠበቅ ጉዳይ ነው ፣ ስለ ሀብታቸው ያነሳሀው ነጥብ የምር ይገርማል ፣ ዐሊም ደሀ ይሁን ፣ ሀብት አያፍራ ብሎ የወሰነው ማነው ? ሙፍቲ ነጋዴ እንደነበሩና የሀብታም ልጅ እንደነበሩ ደጋግመው ተናግረዋል ፣ ሰርተው ማግኘታቸው ምን ያስገርማል ?

የተወሰኑ ኢኽዋኖችን ጠቀስኩለትና እገሌ እገሌ በጣም የለጠጡ ባለሀብቶች ናቸዉ ነገር ግን እኔ በሀሳብ ስለምቃረናቸው ብቻ ይህን ሀብት ሰርቀው ፣ ህዝብ አጭበርብረው ነው ያገኙት ማለት አልችልም ።

በመጨረሻ የምመክርህ አንተ እንዲህ አይነት ነገር ውስጥ አትግባ ፣ ስራህን ስራ ፣ ሰላትህን ስገድ ፣ ከሀራም ተከልከል ፣ የቻልከውን ያክል ሱና ዒባዳ አብዛ ።

ፅሁፋ ረዘመ አይደል ? አፍወን ሰሞኑን ፈተና ላይ ስለሆንኩ እዚያ ላይ ለምዶብኝ ነው 😁


ዒድ አል አድሀ አካባቢ ከሁለት ወንድሞች ጋር ተቀማምጠን በምን አጋጣሚ እንደሆነ ትዝ ባይለኝም አንደኛው ስለ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ማወራት ጀመረ ። ሁለት ወንድሞች አንደኛው ወሀቢያ ኡስጣዝ ሲሆን ወሬውን የጀመረው ደግሞ ወሀቢያ ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖር ኖርማል ሰው ነው ።

እርሱ : ሀጅ ጠሀ ለ40 አመታት የመጅሊስን ወንበር ላይ ቆይተዋል ፣ ከዚህ ስልጣን ባገኙት ገንዘብ ፎቅ ሁላ ሰርተዋል አለ

እኔ: ካደግንበት የጭምትነትና ፍርሀትን በጥሩ በአኽላቅ የመጥራት እሳቤ እንደምንም ታግዬ ወጣሁና ፣ ማውራት የፈለግከው ስለ ሀጅ ጠሀ ሳይሆን ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ነው አይደል ? አልኩት

እርሱም : አዎ ተደባልቆብኝ ነው ፣ ስለ ሙፍቲ ነው ፣ በዚህ መሀል ወሀቢው ኡስታዝ ጥልቅ አለና : እረ እሱንማ( ሙፍቲ ሀጅ ዑመርን ) ጭራሽ እስከ ማምለክ ደርሰዋልኮ ፣ ውዱእ ያደረገበትን ውሀ ሁሉ ይጠጣሉ አለ

እኔ : ውዱእ ያደረጉበትን ውሀ መጠጣት እንዴት ሆኖ አምልኮ ሊሆን ይችላል ወዘተ ወደ ሚለው መግባት አልፈለግኩም ፣ ኡስጣዝየውን “ ይህ ሲደረግ አይተሀልን “ ? ወይም ሌላ ተጨባጭ ማስረጃ አለህን ??

ኡስጣዝየው : ሲባል ሰምቼ ነው

እኔ : ማስረጃ በሌለህ ነገር ላይ እንዴት እርግጠኛ ሆነህ ታወራለህ ?

ወሀቢው ኡስጣዝ : ዝምምምም

እኔ : ገለልተኛ ወደሆነውና ነገሩን ወደጀመረው ወንድም ዞሬ : ሙፍቲ ሀጅ ዑመር አንተ ያልከውን ያክል እድሜ ወንበር ላይ አልቆዩም ፣ ድሮም በግድ ነበር ስልጣን የተሰጣቸው አሁንም ዶ/ ር አብይ በግድ ነው ከቤታው አውጥቶ ለሹመት ያበቃቸው ።

ስልጣን ፈለጉ ብንል እንኳን ስልጣን መፈለግ አሁን ላይ በስልጣን ላሉት አካላት ሀላል ሆኖ የኛ ሸይኾች ላይ ሀራም የሚሆንበት ምክንያት የለም ፤ በዚህ ሰአት ወሀቢው ኡስጣዝ ሹልክ ብሎ ወጣ ።
👇👇👇👇👇👇👇👇 ቀጣዩ ከታች አለ


🌹✨ሰዎች ሲያስታዉሷችሁ ለመታወስ የምትመቹ ሁኑ፣ በህሊናቸው ውስጥ ቢያንስ የማይረሳ አንድ ትከሻቸውን መታ መታ ያደረጋችሁበት ደግ ስራ አይጥፋችሁ፣ ሁሉም ከጭንቀት የተፃፈለትን ተሸክሟል፣ አሏህ በቸራችሁ በዱዓ ፣ በይቅርታ ወይም በስጦታ አውርዱለት ፣ቀለል በሉ አትክበዱ♦️

አሏህ አሳማሪዎችን ይወዳል...🌹

Показано 20 последних публикаций.