Sumeya sultan


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Цитаты


ነጻ ሃሳብ! ነጻ ግጥም!!
ሃሳብ አስተያየት በ @Sumeyaabot አድርሱኝ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


አግቡ
"ቀይ አበባ እንደምትወጂ አስቤ ነው" ብሎ 1ፍሬ ቀይ አበባ ፊቱ ሙሉ ሳቅ በሳቅ ሆኖ ሲሰጠኝ እድሜ ልኬን ነጭ አበባ እንዳልወደድኩ ሆኜ ቀይ አበባን አፈቀርኩ።
ሰርግ ሲሉኝ ሁላ "ኧረ ወደዛ ማን ከ ቬሎ ጋር ይጎትታል" የምለው እኔ "በ ቬሎ የምታምሪ ይመስለኛል" ሲለኝ የስልኬ "ጋለሪ" በ ቬሎ ዲዛይን ሞላ። የሰርጌ ቀን ቬሎሽ ሲያምር ሲለኝ ድንኳን የሚመስለውን ጎታታ ቬሎ ሳላወልቅ መቅረትን ልቤ ተመኘ። እንደዚህ ነው ከ ቃሉ ጋር ተፋቅሬ የምቀረው። "ወንድ ልጅ አግብቼ አስተምራለሁ ካለ በልጅ ነው ዲግሪ ሚያሳቅፍሽ" ያሉኝን ሰዎች እሱ ፈተና ሲኖርብኝ እሱ ልጆቼን ከስራ እየቀረ እስከ ማስተርስ እንዳስተማረኝ መንገር ያምረኛል።
"አዪ ወንድ ልጅ ባክሽ መድከም አይፈልግም ካንቺ የተሻለች የቀራች ያመጣል" ሲሉኝ በሱ እገዛ 13ጁዝ እንዳፈዝኩ አያውቁም
ብቻ ማግባት ደስ ይላል ወጣቶች አግቡ❤️
@sumeyasu
@sumeyaabot


ዝም
ሱመያ ሱልጣን
ሂጃብ ያልገራላት የ 1ልጅ እናት እና ባለትዳር አረብ ቲክቶከር አለች። ከ እናቷ ጋር አስቂኝ ቪዲዮዎች ሲለቁ ነው የማውቃቸው። ከ 2ሳምንት በፊት የሚያምር ጥቁር ረጅም ጸጉሯን "ስታይል ለመቀየር" ብላ ቨአጭሩ ስትቆረጥ በጣም ብዙ ኔጌቲቭ አስተያየቶች የ ኮመንት ቦክሱን ሞሉት። "ፋሽን ብለሽ ገና አንገትሽን ትቆርጫለሽ፣ ለምን ሙሉ አትላጪም ምናገባን..." ከቀናት በኋላ ሙሉውን ተላጭታ ኮፍያ ማድረግ ስትጀምር አሁንም እጅጉን የበዛ ሰው በስድብ አሰጣት። ዛሬ ወጥታ በ ጡት ካንሰር ምክንያት ኬሞ ላይ እንደሆነች እና በዛ ምክንያት ጸጉሯን እንዳጣች ምናምን አወራች።
ፊቱ ላይ የሳቅ ብርሃን የታየበት ሁላ ደስተኛ አይደለም። ያልወደድነውን ማውገዝ ማለትም መሳደብ አይደለም። ብዙዎቻችን በ አድካሚ የህይወት ጉዞ ፈገግ ብለን የምንራመደው ተመችቶን አይደለም ሌላው ላይ ድካም ላንጨምር ብለን እንጂ።
ዝም እንበል!
@sumeyasu
@sumeyaabot


Репост из: Ifada Community Hadra Chain
የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የYouTube ቻናል ላይ እሁድ የምናስተላልፈውን የላይቭ ስርጭት ለማስተላለፍ ቻናሉ 1k ሰብስክራይበር ያስፈልገዋል በመሆኑም እኛ ኢፋድዮች የወደድነውን ለሰዎች ማካፈል ማይሰለቸን ነንና ቻናላችን ሰብስክራይብ እንዲደረግ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ለምናቃቸው በሙሉ ሼር እናድርግ እስከ ጁምአ ማታ ዘመቻ እናድርግ።

ከላይ በተቀመጠው QR code ስካን በማድረግ ወደ ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የማህበራዊ ሚዲያ ድህረገጾችን መቀላቀል ይችላሉ ።

ይህ የyoutube ቻናላችን ሊንክ ነው ።👇👇👇

https://youtube.com/@ifadaislamicorg?si=WQ--SeP_VHVnsegm


ቂያማ እና አየር መንገድ
(ሱመያ ሱልጣን)
እንደ አየር መንገድ ትልቅ የቂያማ ማስታወሻ መኖሩን እጠራጠራለሁ። መያዝ የሚችለውን ብቻ ይዞ መሄዱ፣ ከወዳጅ ዘመድ እየተላቀሱ እና እየተቃቀፉ መለያየቱ ፣የያዝነውን በሚመለከተው አካል ማስመዘኑ፣ የ አየር መንገዱን ፕሮሰስ አልፎ እስከ ፕሌኑ መገኛ መጓዙ እና ለመዳረሻ መሮጡ ሁሉም ቂያማን የማስታወስ ሃይል አለው። ከዛ ደግሞ የናፈቁን ወዳጆቻችንን ስናገኝ ያለው ጀነትን ይመስለኛል። የሚጠብቀንን የተደበቅነውን መርዶ መስማቱ ደግሞ ጀሃነምን ያስታውሰኛል። እነዛ የናፈቅናቸውና የናፈቁንን የምናገኝበት የጌትዬን ጀናህ አላህ ይወፍቀን💚
@sumeyasu
@sumeyaabot


"ፍትህ"
(ሱመያ ሱልጣን)
ታናሽ እህት አለችኝ ስሟን በስሜ አስከትዬ እራሴን "ሱምሊና" ብዬ የምጠራባት። ሊንዬ ሲደክማት ሁላ አዝናለሁ! በጣምምምም ብዙ አመታትን "ጠበቃ" መሆን እመኝ የነበረው የመደፈር ዜናዎችን እኔም ቤት ደርሶ እስኪገድለኝ ድረስ "አዑዙ ቢላህ፣ አስተግፊሩላህ!" እያልኩ ቲቪዬን ላለማጥፋት እና ፍትህ ለማምጣት ነበር። እያንዳንዱ የመደፈር ዜናዎችን ሳይ የማለቅሰው "ሊንዬ ብትሆንስ" እያልኩ ነው። ጓደኞቼ " የሊናን ጦስ" ይላሉ። እኛ ቤት የማይደርስ ይመስል!
ሴት ሆነን ስንወለድ ጀምሮ ከሞት እኩል ተሸክመነው የምንወለደው ጉዳችን፣ ሰቀቀናችን ነው። የማዝነው እኔ እራሴን እንኳን መከላከል በማልችልበት ሁኔታ ታናሽ እህት እንዳለኝ ማሰብ ነው። ስለ 1ሄቨን አይደለም ነገሩ ስለ እያንዳንዱ ቀናችን ነው ፍትህ የምንለምነው፣ በ አባያ እና ጅልባባችንም ውስጥ ለማይቀርልን ትንኮሳ ነው፣ የመደፈራችን መልስ "ምን ለብሳ ነበር?" ስለሆነብን ነው፣ ፍትህ የምንለው እያንዳንዱ ቀናችን ላይ "ማነሽ ሰሚራ፣አታወሪም እንዴ? አንቺን እኮ ነው!" እየተባልን እየተጎተትንም ወጥተን ስለምንገባው ነው፣ በ እያንዳንዱ ቀን ሶሻል ሚዲያ ላይ ፎቶ ኖረን አልኖረን፣ ፖስት አደረግን አላደረግን በውስጥ ለሚደርሱን የጾታዊ ንግግሮች እና ዝም ስንል ለሚደርሱብን ስድቦች ነው፣ "ፍትህ" እያልን የምናለቅሰው ስለሞተችው ሄቨን ብቻ አይደለም ስለምንሞተው ብዙዙዙ ሄቨኖች ነው። እኔ "ፍትህ" ን ከመንግስትም ሆነ ከሰው ፍጥረት አልጠብቅም። ፍትህ ያለው በጌታዬ እጅ ነው "አልጀባር" በጀባርነቱ ፍትህ እንዲሰጠን ነው ዱዓዬ። ይኔ ልመና "አልሰታር" ሁሉንንንንንምምም ሴት ከ አረመኔዎች እንዲሰትረን ብቻ ነው። ፍትህ የ አላህ ነው!!!!!
ተቃጠልን
@sumeyasu
@sumeyaabot


ሰሪውን ነው ማመን
(በሱመያ ሱልጣን)
የ ልጅ እጄን በ ወፍራም መዳፉ ጥብቅ አድርጎ ይዞኝ መንገድ እየሄድን የምናውቃትን ከኔ በ 2አመት ከፍ የምትልን ልጅ ስም ጠርቼ 2ጥርስ እንዳወለቀች ነገርኩት። ወደኔ ዞር ብሎ ፈገግ ካለ በኋላ "አንቺም አሁን 6አመትሽ አይደል ልክ 7 ሲሆንሽ ታወልቂያለሽ" አለኝ። አስታውሳለሁ የጥርሶቼን ጥንካሬ ለማስረዳት የዘባረቅኩትን ብዛት። "የኔ ድርድር ያሉ የተጣበቁ ጥርሶቼ ሊወጡ?"
ደጋግሜ ስሙን እየጠራሁ" እየኝማ እየኝማ ጥርሴ እኮ አልተነቃነቀም ሁላ የኔ እኮ ጠንካራ ነው" ለፈልፋለሁ። "እሺ" ብቻ አለኝ። ከ አመት በኋላ ጥርሴ ተነቀለ። 1ብቻ አይደለም እየቆየ ብዙ ነቀልኩ። ከዛ ደግሞ ተመልሶ በቀለ።
ካደግኩም በኋላ "በጭራሽ እኔ ላይ አይሆንም" ያልኩት ሲሆን በሌላ ሲተካ አየሁና ህይወት ገባችኝ።
ዱንያ ላይ በሰሪው እንጂ በስራው መተማመን ያከስራል።
@sumeyasu
@sumeyaabot


Репост из: Fuad Muna (Fuya)
364 ሺህ ብር!

በአላህ ችሮታ የኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር አባላት ባደረጉት ልብ የሚነካ የሰደቃ ውድድር ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለእዝነት የአካል ጉዳተኛ ህፃናት እና ወላጆች መርጃ 364 ሺህ ብር በዛሬው ዕለት ስጦታ ማበርከት ችለዋል።

የኢፋዳ የሀድራ ትስስር በአላህ መንገድ ላይ ስለመተዋወስ ከሁሉም ፅንፍ የተሰባሰቡ ወጣቶች ስብስብ ነው።

ኢፋድዮቸወ አድርጋችሁታል! እንኳን ደስ አላችሁ ብያለሁ።

ሌሎችም የሀድራ ትስስሩን በመቀላቀል ስለ መልካም የምትወዳጁት ቤተሰብ ታደሉ።
.
@Fuadmu


አሹራዕ
(ሱመያ ሱልጣን)
"አለቀልን! በቃ ተያዝን" ብለው ነበር የሙሳ ህዝቦች ከፊታቸው ባህር፣ ከኋላቸው ፊርዓውን ከነ ሰራዊቱ እየደረሰባቸው መሆኑን ሲያዩ።
"በበትር ባህርን መክፈል?" የልጅ ጨዋታ እስኪመስል የማይታመን!
ሁሉን ቻይ ጌታ ግን ያንን ያስቻለው በዛሬው እለት ነበር። ጌታችንን በጾመ አካላችን እጆቻችንን ከፍ አድርገን "የማይቻል" የመሰለንን የኛን የሃጃ ባህር "በ ሰጪ እጆችህ ክፈልልን።" እንለዋለን። አላህዬ እኮ ይችላል። ወላሂ ይችላል።
@sumeyasu
@sumeyaabot


የምንፈልገውን
(ሱመያ ሱልጣን)
ህይወት ላይ ስላጋጠማት ነገር እያለቀሰች ቲክቶክ ቪዲዮ የለቀቀችውን አየሁት እና አሳዘነችኝ። የተሰጡትን አስተያየቶች ሳነብ ካሳቀኝ ውስጥ አንዱ
"በከባድ ሁኔታ ውስጥ እያለፍሽ እንደሆነ ይገባኛል። ካላስቸገርኩሽ የተቀባሽውን ሊፕስቲክ ስም ትነግሪኛለሽ?" የሚል ነው።
ያው ችግራችንን ለሚገባው ሰው ተገቢው ቦታ ላይ እንንገር ለማለት ነው😁
@sumeyasu
@sumeyaabot


ትዝብት
(ሱመያ ሱልጣን)

ቲክቶክ መንደር ገባ ብዬ አንዱን ቪድዮ ተመለከትኩ። የተለያዩ ቃሪዖችን ፎቶ እያመጣ ከ 1-10 የሚወዳቸውን መደርደር ነበር። ልጁ ያሲር አድ ዶውሰሪን 1ኛ፣ ሸይኽ ሱደይስን 10ኛ አደረጋቸው። አንዲት ሴት በኮመንት "እንዴት ያን የመሰለ የሚያምር ድምፅ ያለውን ቃሪዕ 10ኛ ትላለህ ለኔ የመጀመሪያ ምርጫ ሼይኽ ሱደይስ ነው። አስተካክለው ድምጹ እኮ በጣም ያምራል።" አለችው። ልጁ በ ሪፕላይ " ከነ ውብ ድምፁ የኔ የመጀመሪያ ምርጫ አይደለም። ይሄ የኔ ቪድዮ ነው" ብሎ መለሰ። አንዳንድ ሰው እንደዚህ ነው በነሱ ምርጫ እንድትወስን ይፈልጋል። በነሱ ልክ እንድትመዝኑ ይሻሉ። እኛም እንደ ልጁ "ከነ ውብ ምርጫችሁ ጋር ሃሳባችሁ የኛ ምርጫ አይደለም። ይህ የኛ ህይወት ነው እንላለን።"
@sumeyasu
@sumeyaabot


በሻራ
(ሱመያ ሱልጣን)
ቀለበት ያደረገውን ጣቴን እያየች "ሱም በሻራ አለን እንዴ?"
ፈገግ ብዬ "እንደዚህ እንደቀልድ?"
"የበሻራ ወጉ እንዲያ አይደል እንደ ሳራ በቆምሽበትም ሊሆን ይችላል፣ አልያም እንደ መርየም ወይም ዘከሪያ በ አምልኮትም ላይ ሆነሽ ወይም ደግሞ ነብዩላህ ኢብራሂም በ እሳት፣ እንደ ነብዩላህ ዩሱፍ በ ጉድጓድ ውስጥ ሆነሽም ይሆናል። የበሻራ ወጉ እንዲያ አይደል?" ብላኝ ፈገግ ብላ ሄደች
እውነትም ደስታ ሲመጣ ቦታ መርጦ አይደለም። ሃዘን ሲያልቅም አይደለም በቃ ከ አላህ የሆነ ደስታ ለየት የሚያደርገው ያ መሰለኝ ቦታ እና ጊዜ አለመኖሩ ። ከችግር በኋላ አለመሆኑ። ፈተና ሲያበቃ አለመሆኑ። እና በሻራ በየትኛውም ጊዜ ይመጣል። ለዛም ነው አላህ "በርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ!" የሚለውን አንቀጽ በ ሁለት ያጸናልን።
መልክተኛውስ "1ችግር ሁለት ምቾትን አያሸንፍም!" ያሉት የዚህን በሻራ ምቾትም አይደል?
ምን ልላችሁ ነው በሻራ በየትኛውም ሰዓት ስለሚመጣ ተስፋ ሳትቆርጡ ጠብቁት።
@Sumeyasu
@sumeyaabot


"እርሜን ስላወጣሁ ይወጣልኛል" ብዬ ነበር። ሃዘን ለካ አይወጣም። በቃ የወዳጅ ሞት የሆነ ውስጣችን ላይ የሚገድለው ነገር አለ። "አላህ ይርሃማት" ብዬ ባነሳሁ ቁጥር ውስጤ ላይ የሚቀሰቀስ ሃዘን አለ። በሞት የተቋጨ ወዳጅነት በምን ይድናል?
አላህ ይዘንልሽ የኔዋ! ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡት ሆነሽ እዛው ያገናኘን
ግን በምን ይድናል?
@sumeyasu
@sumeyaabot


ፍቅሬን በ አደባባይ
የልቤ ሰው ናት። ሳውቃት የኖርኩበት ሱመያነት በሷው ልብ እኔው ላይ ገነንብኝ። "እንዲህ ደስ እላለሁ እንዴ?" አልኩ። ወደደችኝ። አብሮ በተቀማመጠው ሰው ጸባይ አይደል ማንነት የሚሰራው? ገነባችኝ ። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እና ያለምንም ምላሽ ፍቅር እንዳለ እኔነት በሷ ሲወደድ መሰከርኩ። ትለያለች!! ጥፋት እና መጥፎ ጎኔን አይታለች። ሰተረችልኝ። ጥሩዬን አየችና ደግሞ አውጥታ ዘርታ የሰው መውደድ በዙሪያዬ ሲበቅል ተመለከትኩ። ዛሬ "ሱመያ" ን ስታስቡ የሚመጣላችሁ መልካም ጸባይ ሃያት በምትባል እህት ተለፍቶበታል። መልካም ያልሆነ ትዝታ ከተጫረባችሁ ሃያት ለመለወጥ እየጣረች ያለችበት ባህሪ ነው ማለት ነው። በርግጥ ዛሬ ላይ ብዙ መልካም ወዳጆች አሉኝ። ግን እርሷ በሰራችው ማንነት ነው የተወዳጀሁት እና ማንም ከቦታዋ አያንቀሳቅሳትም። በድብቅ ለሆነችልኝ መልካምነት ዛሬ በ አደባባይ ፍቅሬን እና ምስጋናዬን መግለጽ ስለፈለግኩ ነው። ይህች ልቤ አብዝታ ትወድሻለች እህቴ!
እናንተም ተመሰጋገኑ
@sumeyasu
@sumeyaabot


"በማን ሚዛን?"
እርጋታው ይመስለኛል ያሸነፈኝ። ብዙ አይናገርም ግን በሚናገርበት ሰዓት አንባቢነቱን ከቃላት አጠቃቀሙ እና ከቁጥብነቱ ይታወቅበታል። ሁሉም ነገር ላይ መመጠን እና ማመዛዘንን ያውቅበታል። ሰላምታው ላይ መጠነኛ ፈገግታ አለች። ፈገግታውን ለሚሰጠው ሰው ብቻ ፈገግ የሚል የምታስመስል ለየት ያለች እርግትትትትት የምታደርግ ፈገግታ። በየትኛውም ጉዳይ ላይ ጥያቄ ሲመጣበት ለመመለስ ከሚቸኩለው በላይ "እኔ ብዙም እውቀቱ የለኝም" የሚለውን ማስቀደም ይቀናዋል። እውነታው ግን የ እውቀት ባለቤት መሆኑ ነው። በተፈጥሮ ቀዝቃዛ የሚባል አይነት ነው። አይቸኩልም። በህይወቱ ላይ ለነገሮች የሚሰጠው ቦታ የተመጠነ ነው። "ቢመጣም ባይመጣም"አይነት። ዲኑ ላይ ያለው አቋም ይደንቀኛል። አይለፈልፍም። ቁርኣን ሲቀራ ድምፁ ያፈዛል። " ሰው በሰደቃው ነው የሚጠበቀው" ይላል ደጋግሞ
አንድ ቀን ቡና ልንጠጣ ተገናኘን። ስመጣ ብድግ ብሎ አስቀመጠኝ። ፊቱ ላይ የተለመደው እርጋታ ነው ያለው።
"ለ ትዳር እፈልግሻለሁ" አለኝ
" እኔን?" አልኩ በድንጋጤ። አንገቱን በ አዎንታ ነቀነቀው
" ካንተ ማንነት ጋር የሚሄድ ማንነት የለኝም። ባንተ አዋቂነት ስመዘን እኔ እልም ያልኩ ጃሂል ፣ ባንተ እርጋታ ስለካ እኔ እልም ያልኩ እብድ ነኝ፤ ካንተ ንጽህና አንጻር ያደፈ ልብ ያለኝ ነኝ አልሆንህም" ሳልፈልገው ቀርቼ አልነበረም። የጠራ ማንነቱ ከኔ ጋር ሲዋሃድ የሚደፈርስ መሰለኝ እና "ልቅርብህ" አልኩት።
"በማን ሚዛን ተመዝነን?" አለኝ።
"እኔ ዱዓ አድርጊያለሁ። ከጌታዬም ኸይር የሆነ ምላሽን እክጅላለሁ። ጊዜሽን ወስደሽ መልስ ትሰጪኛለሽ አለኝ።" እርጋታው መለያው አይደል። ስክንንን እንዳለ ነው የሚያወራው።
ከአመታት በኋላ ከ እናቴ ጋር ቁጭ ባልንበት እህቴን በሚያማምር ቃላት ስትመርቃት ሰማሁ። "ምናለ ለኔም ብታደርጊልኝ?" ብዬ ቀናሁ። " የተሻለውን ዱአ አድርጌልሽማ መልሴን አገኘሁ" አለች። ባሌን ነው። ያን የተረጋጋውን ሰው፣ ያ ልቡ የሰከነች ሰው አገባሁት።
"በማን ሚዛን?" የሚለው ጥያቄው እስካሁን በህይወቴ እጠቀመዋለሁ።
@sumeyasu
@sumeyaabot


ጠይቁት ብቻ( ሱመያ ሱልጣን)
ተፍሲር ላይ ነበርን። ኡስታዙ ሱረቱል ዩሱፍን እየዳሰሰልን የ ዩሱፍን "እነርሱ ከሚጠሩኝ የበለጠ እስር ቤት እኮ ለኔ የተወደደ ነው" የሚለውን አያህ እያነሳ "እርግጥ ዩሱፍን እስር ቤቱ ለትልቅ ስኬት ቢያመቻቸውም ከዚህ የምንረዳው ግን አላህ ዱዓን እና ምኞትን በየትኛውም ሰዓት ስለሚመልስ ዱዓችሁ እና ምኞታችሁ ላይ ጠንቃቃ ሁኑ!" አለን
ምን አስታውሼ መሰላችሁ? የ ፉዓድ ሙና ጽሁፍ ላይ የትኛው እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም( ስለ ገጣሚያን ያነሳው ይመስለኛል) "አምሪያ" የምትባል ገፀ ባህሪ የሆነ አይነት የጓደኛሞች ግሩፕ አላት እና በየወሩ የቁርአን ኺትማ ፕሮግራም እንዲሁም በወሩ ላይ ከነሱ እኩል ያልቀራችውን ደስ የሚል ቅጣት የሚቀጡበት ደስ የሚል ስብስብ አነበብኩ። "ምናለ እንዲህ አይነት ግሩፕ በኖረኝ" ማለቴን እርግጠኛ ነኝ። "ስጠኝ!" ብዬ ዱዓ ማድረጌን ግን እንጃ። አላህ ግን አመታትን ቆይቶ ተመሳሳዩን ነገር በኔም ህይወት ላይ ሰጠኝ እና "ካንተ ውጪ በ እውነት የሚያመልኩት አምላክ የለም! ብዬ አመሰገንኩት። እና የተመኘሁትን የሰጠ አላህ የለመንኩትን ይረሳል? በፍጹም!!!
እና ልላችሁ የፈለግኩት በዱዓችሁ ላይ በምኞታችሁ ላይ ጌታችሁን እመኑት እና ለምኑት! ምናልባት ነገ ወይም ከ አመታት በኋላ እንደኔ ትመሰክላችሁ
@sumeyasu
@sumeyaabot


ለቅሶ( በሱመያ ሱልጣን)
"የት ደረሳችሁ?" ለቅሶ ለመሄድ ተዘጋጅቼ በመጠበቅ ላይ ቀድማ ለደወለችልኝ አንዲት ጓደኛዬ
"ኬክ ልንይዝ ስላሰብን" bakery "ገብተናል። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ስለምንደርስ ታች መውረድ ትችያለሽ"
"ኬክ ለለቅሶ ቤት? ከሟች ጸብ ነበረሽ እንዴ? ልታከብሪው ነው? ትላንት የሞተ ሰው ጋር ኬክ ይዘን የምንገባው?" ብዬ እንደ ሃበሻ ተብከነከንኩላችሁ
በስልኩ ውስጥ የሳቅ ድምፅ እየተሰማኝ "" we're on the way"
እናላችሁ የ አንዲት ህንድ ወዳጄ እህት ትላንት አርፋ ዛሬ እኛ ለቅሶ ልንደርስ ከሌሎች 2ህንድ ወዳጆቼ ጋር ባይጥመኝም ኬክ ይዘን ለቅሶ ሄድን። "ቤት ተሳስተን ይሆን?" ብዬ እስክል የለቅሶ ቤት ድባብ የለውም። ለቅሶ ለሚደርሱ ሰዎች መቀመጫ የሚታይ የተደረደረ ወንበር ሳይ ነው እንዳልተሳሳትን የገባኝ።
ስንገባ የሟች እናትና እህት ብድግ ብለው፤ አባት፣ ወንድሞች እና ባል በተቀመጡበት እጃቸውን ከፍ አድርገው ሰላም ካሉን በኋላ። እዛው በሴቶቹ እቅፍ ውስጥ እንዳለን "am sorry for your loss" ብለው ሲሉ ሰምቼ እኔም አልኩ። ተቀመጥን።
ዞር ዞር ብዬ ማየት ጀመርኩ። በሁሉም ጠረጴዛ ላይ የተለያዩ ኬክ እና ጣፋጭ ከለስላሳ ጋር አሁንም አሁንም ይቀርባል። ሰውም ቶሎ "sorry for your loss" እያለ ይሰናበታል። እኛም ገብተን ከ 15ደቂቃ በኋላ ተሰናብተን ወጣን።
እስካሁን ካጋጠሙኝ culture shock ውስጥ ይሄ በደረጃ አንድነት መድቤዋለሁ። የናንተንም አጋሩኝ።
@sumeyasu
@sumeyaabot


"ተራችን እስኪደርስ" (ሱመያ ሱልጣን)
"አንዳንዶቻችን እንድናርፍ አልተፈቀደልንም መሰለኝ" አለችኝ። "ስለኔ ስንክሳራም ህይወት ማንነው ወሬ ብሎ የነገራት?" ማለት ቃጣኝ። ግን ከዛ ቀን ውጪ የምንተዋወቅም አልነበርንም።
"እስቲ ጉዱንማ በሰብር እንየው" የደከመች ነፍሴ ነች የመለሰችው።
"ይደርሰናል ግን? ከፍልስጤማዊያን ቀጥሎ?፣ ከ መካ ላይ፣ ቁድስ ላይ፣ መስጂደ ነበዊ ላይ ቆመው ከሚጠሩት ቀጥሎ?ከስንት እና ስንት አሊም ቀጥሎ? አላህ ብቻ ከሚያውቃቸው እልፍ ሳሊሆች ቀጥሎ? ከስንት እና ስንት.......ከወንጀሎቻችን ጋር ተደምሮ? ይደርሰን ይሆን?" አሳዘነችኝ። ፈራሁ!! "እንደዛ ይሆን እንዴ?" ብዬ ለራሴ ሰጋሁ። ለካ እሱ አል ራህማን ነው ።ፍርሃታችን ከምናውቀው ጭንቀታችን ነው እንጂ የመጣው ሰማይና ምድርን በ እዝነቱ ባቆመው ጀሊል ተጠራጥረን አልነበረም። እንደ ሰው ግን ፈራሁ።
በህይወት ከፍታም ዝቅታም ውስጥ ነበርኩ። የውስጥ ድካምን ትኩሳት ጀሊል ባልታሰበ ራህመቱ ሲያቀዘቅዛት መስክሪያለሁ። በ ማጣት እና ማግኘት መሃልም "ሱመያ" የምትባል ግለሰብ ቆማ አይቻለሁ። ውስጤን "ከምንም ጋር አላወዳድረውም። እንደዚህስ ታምሜም አላውቅ" ብዬ ያልኩት ህመም ቁጥሩ እልፍ መሆኑን በደንብ አውቃለሁ። ግን "ደቀቅኩ፣ አለቀልኝ" ብዬ ላቆመኝ፣ "ተጋለጥኩ" ስል በአል ሰታርነቱ ለሸፈነኝ ለነዛዛ ቁጥር አልባዎቹ ቀናት ስል ተስፋ መቁረጥን የሚባለውን ያስቀበረኝ " ይህቺንም ቀናት በሰዎች መሃከል እናዘዋውራታለን"የሚለው ቃሉ ነው። ያ ቀን ለኔ እስኪዞር ለታጋሾች ምንዳቸውን እንደሚከፍል በገባው ቃል እየተጽናናሁ።
መንገዱ ቢያደክምም ቃሉን በማያጥፈው ጌታችን ተማምነን እንታገሳለን!!!
@sumeyasu
@sumeyaabot


(በሱመያ ሱልጣን)
የተፈጥሮ ነገር ሆነ እና አርቴፊሻል የሆኑ ጌጣጌጦች ከሰውነት ቆዳዬ ጋር አይጣጣሙም። ቀበጥ ብዬ ላድርግ ያልኩ ቀን በማቆሳሰል ይኮረኩመኛል። እና ረጅም አመታትን ጆሮ ጌጥን ማድረግ ትቼ ኖሬ ከ እለታት በ አንዱ ቀን ከ እህቴ ጋር በ አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ በኩል ስናልፍ ወደ አንዱ እግረመንገዳችንን ጎራ አልን። አንድ አነስ ያለች የ ብር ጆሮ ጌጥ ደስ አለችኝ እና ገዛሁ። ለ ቀናት ተደስቼ አድርጊያት ብዙ ሳትቆይ በ አንዱ ምሽት እንዴት ብሎ እንደጠፋብኝ እንኳን ሳላውቀው አንዱ ወልቆ ጠፋ። ተናደድኩ። ደበረኝ ምናምን እና "ድሮም ስቀብጥ እንጂ ላይበረክትልኝ ነገር ማን ግዢ አለኝ?" ምናምን ብዬ ተነጫንጬ ተኛሁ። በማግስቱ አመሻሽ ላይ የሆነ እቃ ፈልጌ የእጅ ቦርሳዬን ስዘረግፍ በ ወርቅ ማስቀመጫ የሆነ ነገር "ዱብ" አለ። አየነው። ስከፍተው የሚያምር የወርቅ ጆሮ ጌጥ ነበር። ማን እንዳስቀመጠው እንኳን ያወቅኩት ቆይቼ ነው። እሱንም ያን ሰው እንዳመሰግነው እራሱ እድሉን አልሰጠኝም።
ጽሁፉ ከ ጆሮ ጌጥ የዘለለ ነው ትርጉሙ። አላህ ህይወታችሁ ላይ እናንተ" ይገባኛል!" ብላችሁ ከምታስቡት በላይ የሚገባችሁን ያውቃል። ብር ጠፋብኝ ብዬ ሳለቃቅስ በወርቅ የካሰ ጌታ እጆችን አንስተን የለመንነውን የሚረሳ ይመስላችኋል?? ሊያውም በጾመ አካላችን ተዋድቀን የለመንነውን?
በሉ በሶብር እና ሶላት እርዳታውን ሻቱ! ሃያ!
@sumeyasu
@sumeyaabot


እንግዳዬ (ሱመያ ሱልጣን)
"ቂም ይዞ ጸሎት..."የሚለውን አባባል አጣቅሳ በ ንጹህ ልብ ጾምን የመጀመርን ትሩፋት ስትተነትን በልቤ የበደሉኝን ሰዎች እያስታወስኩ " ነገ አላህ ፊት አቁሜ ካልከሰስኩ በቀር በ ይቅርታ የማድነው ቁስል የለኝም"ብዬ በማሰብ ላይ ነበርኩ።
"ምናልባት እናንተ ምን እንደበደላችኋቸው እንኳን ሳታውቁ የተቀይሙባችሁ፣ ነገ አላህ ፊት በ እልፍ በደላችሁ ሊወቅሷችሁ ያጎበጎቡትን እናንተ ዛሬ ለ አላህ ብላችሁ ይቅር ባላችሁት ምክንያት አላህ ፊት ምህረትን ሲቸራችሁስ?" ስትል ለ እልፍ ወንጀሌ ማርታ ስል "አፍወን ሊላህ!" ብዬ የበደሉኝን እና "በድለውኛል" ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ይቅር አልኩና በሬ ላይ ያለው እንግዳዬን በ ንጽሁ ልብ ልቀበለው ተሰናዳሁ።
የናንተ የ እንግዳ አቀባበል እንዴት ነው?
@sumeyasu
@sumeyaabot


ዱዓችሁ ውስጥ ይሄን አትርሱ (ሱመያ ሱልጣን)
በ ዱዓችሁ ውስጥ አል ራህማንን "አንተን ከሚያስታውሱት ጋር አወዳጀኝ!" በሉት። በ ህይወት ውስጥ ትልቁ ቅመም እሱ ነው።
ስለ ቂርዓት ጉዞዋቸው የሚያወሯችሁን እና ጀነትን በነሱ መሃል በመገኘታችሁ ለማግኘት የምትከጅሉበትን አይነት ስብስብ ውስጥ መገኘትን ደግሞ ለመታደል ተሃጁድ አብዙ።
"ዛሬ ይሄን ያህል ቅሪ!" ብሎ እያስታወሰ ካልቀራችሁ በቅጣት የሚኮረኩማችሁን ለማግኘት ደግሞ ሰደቃን አብዙ!
በወር እና በ 2ወር ውስጥ ደግሞ እጃችሁን ይዞ የሚያስኸትማችሁን ለማግኘት ደግሞ በ አዛን እና ኢቃም መሃል ባለች ሰአት ላይ ዱዓን አትዘናጉ!
ኺትማውን ደግሞ በውብ ድምፅ ምሽታችሁን የሚያሳምር አይነትን ለመታደል አላህዬን በ ትላልቅ ስሞቹ በየቂን ጥሩት! እሱ በርግጥም ሁሉን ሰሚ ነውና
ደስታችሁ በ እንባ ሊያሳጥባችሁ ከፈለጋችሁ ደግሞ ለቤተሰቦቻችሁ በጎ ዋሉ እና ዱዓ እፈሱ!!
ሁሉንም አንድ ላይ ለማግኘት ግን ይሄንን ረመዳን ጠንክራችሁ ስሩበት
በደስታ የተጻፈ!!
@sumeyasu
@sumeyaabot

Показано 20 последних публикаций.