ትምህርት በቤቴ®


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Образование


A channel created for sharing
🔺study tips,
🔺short notes,
🔺tutorials,
🔺educational news,
🔺life tips and some motivational quotes ...

Buy ads: https://telega.io/c/temhert_bebete
📩 For comment- @Tmhert_bebete_info_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций




Репост из: In Africa Together
🚀 መልካም ዜና ከ ኢንአፋሪካ ቱጌዘር🚀

✅ በ🇺🇸 አሜሪካን ሚቺጋን እና 🇪🇹 አዲስ አበባ እውቅና ያለው

✨ ለሀይስኩል ተማሪዎች 10% ቅናሽ ✨
🎉 ወደውጭ ሀገር ሄዳችሁ መማር የምትፈልጉ በሙሉ የዚህ እድል ተሳታፊ መሆን ትችላላችሁ

📅 ቀን: እሁድ፣ ፌብሩወሪ 9 (የካቲት 2)
📍 ቦታ: ካሌብ ሆቴል (ሐርሞኒ ሆቴል ጎን)
⏰ ሰዓት: 2:00 – 8:00

🎓 ያለምንም ቀድመ ክፋያ
📜ያለ ምንም እንግሊዝኛ ብቃት ፈተና
✅ 100% የተረጋገጠ ቅበላ

🇺🇸 አሜሪካ – 66% ስኮላር ሺፕ + 34% በተማሪ ብድር
🇨🇳 ቻይና – ሙሉ ስኮላር ሺፕ + ከኪስ ገንዘብ ጋር


- በመጀመሪያ ዲግሪ
- በማስተርስ
- ፒኤችዲ ፕሮግራም

📦 ቪዛ የማግኘት እድሎን ይጨምሩ📢

🔗 ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇🏾
https://
forms.gle/aWzxNFkQJS8ozaLU7


#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

[ዘገባው የአሃዱ ሬድዮ ጣቢያ ነው]

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


የሐኪሞች የስራ አጥነት ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ በተጨማሪ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ነዉ ተባለ፡፡

በህክምና የተመረቁ ስራ አጥ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሐኪሞች ተገቢውን ሕክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የሕይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ማህበሩ ሀኪሞች ብዙ ጫናዎችን ተቋቁመው ስራ እየሰሩ ቢሆንም የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይከፈላቸዉ የሚቆዩባቸዉ ክልሎች መኖራቸዉን አንስቷል፡፡

ክፍያ የሚጠይቁ ሐኪሞችም ለእስር የሚዳረጉበት ሁኔታዎች የታዩበት ዓመት ነበር ሲል ማህበሩ ገልጿል፡፡

እንደሕክምና ማህበር ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ለማድረግ ቢሞከርም፤ አሁንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ለብዙዎች ችግር ምላሽ መስጠት አልተቻለም ነዉ ያለዉ፡፡

ከዚህ ቀደም ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተግባር ይግዛዉ ፤ በአገራችን ያሉ የሀኪሞች ቁጥር ወደ 17ሺህ ነዉ ያሉን ሲሆን፤ ከዚህ መሃል ወደ 40 በመቶ የሚሆነዉ ወይም 1ሶስተኛዉ ብቻ የማህበሩ አባል መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሙያ ማህበር መቅጠር አይችልም ፤ማድረግ የሚችለዉ ጉዳዩን ማሳወቅ ነዉ ያሉት ዶ/ር ተግባር፤ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸዉን በወቅቱ አንስተዉ ነበር፡፡

ዘንድሮ 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 – 15/2017ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱንም ማህበሩ አስታዉቋል፡፡
በጉባዔዉ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱም ለማወቅ ችለናል፡፡

ማህበሩ ከተመሰረተበት 1940 ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣  ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

#EthioFM

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ጥንቃቄ #CBE

አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ‼️

ከጫናችሁ ያለፈቃድ ገንዘብ ይቆረጥባችኃል!

ደንበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል። ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


በአዲስ የመመዘኛ መስፈርት ዳግም ምዝገባ ካደረጉ 273 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አንድም ተቋም መስፈርቱን እንዳላሟላ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ገለፀ፡፡

ባለሥልጣኑ አዲስ ባወጣው መመዘኛ 273 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን፤ 84 ተቋማት ባለመቅርባቸው መሰረዛቸው ይታወሳል፡፡

ተቋማቱ መስፈርቱን እንዲያሟሉ ተጨማሪ 45 ቀናት የጊዜ ገደብ መቀመጡን በባለሥልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።

በተጨማሪ የጊዜ ገደብ ተማሪዎች መመዘኛውን አሟልተው ወደሚገኙ ተቋማት ተዛውረው እንዲማሩ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን ባለሥልጣኑ እንደሚጠቀም አመልክተዋል። #FMC
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#Exit_Exam

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር በድጋሜ አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


Репост из: Daily inspiration™
Fullstop is not an end;

Because we can write a new sentence after it.

Same is the case with life -

as failure is not the real end,

it can be a real beginning of success!

More ⬇️
🍁 @daily_inspiree 🍁


" ያለ አሜሪካ ፍቃድ/ይሁንታ ቲክቶክ የለም " - ትራምፕ

👉 " 50% የቲክቶክን ድርሻ አሜሪካ መያዝ አለባት ! "

ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል ሊያደርጉ ነው።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገጻቸው ላይ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ፤ ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራቱን እንዲቀጥል እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

ለዚህም በስልጣን ዘመናቸው የመጀመሪያ ቀን (ነገ ማለት ነው) ቲክቶክ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል የሚያስችል እርምጃ ይወስዳሉ / ልዩ የሆነ ትዕዛዝ ይሰጣሉ።

ትራምፕ በዚሁ ፅሁፋቸው አሜሪካ የማህበራዊ ድረ-ገፁን ግማሽ (50%) በባለቤትነት መያዝ እንዳለበት ጠቁመዋል።

ነገ ወደ ቢሮ ገብቼ ስራ ከጀምርኩ በኃላ " ቲክቶክ እንዲጨልም አልፈልግም " ሲሉ ገልጸዋል።

ትራምፕ እንደ ጋራ ሽርክና አሜሪካ በቲክቶክ ውስጥ የ50% የባለቤትነት ድርሻ እንድትወስድ ሀሳብ አቅርበዋል።

ይህ ማለት ከወላጅ ኩባንያው ባይትዳንስ ወይም ከአዳዲስ ባለቤቶች ጋር " በአሜሪካ እና በመረጠችው ግዢ መካከል ትብብር ሊፈጥር ይችላል።

ትራምፕ " ይህንን በማድረግ ቲክቶክን እንታደገዋለን ፣ በጥሩ እጆች ውስጥ እናቆየዋለን " ብለዋል።

" ያለ አሜሪካ ፍቃድ ቲክቶክ የለም " ያሉት ትራምፕ " ከኛ ይሁንታ ጋር በመቶ ቢሊዮን ዶላር ምናልባትም ትሪሊዮን የሚቆጠር ዋጋ አለው " ሲሉ ጽፈዋል።

@temhert_bebete


በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በታህሳስ 30 /2017ዓ.ም በቁጥር 11/77/1201/17 ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባወጣው ማስታወቂያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኞቻቸውን መረጃ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ማስገባታችሁ ይታወቃል:: ነገር ግን በተሰጠው ጊዜ ቀን ገደብ ያላስገባቹ ተቋማት እና ማስተካከያ እንድታደረጉ እድል የተሰጣቹ ተቋማት በድጋሜ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ከ09/05/2017 ዓ.ም እስከ 14/05/2017 ዓ.ም ድረስ እንድታስገቡ እያልን ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


#Update

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ከጥር 8-14/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et

ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራችሁ ጥያቄ ዘውትር በሥራ ሰዓት በተከታዮቹ አማራጮች ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡

Email: ngat@ethernet.edu.et
☎️ 0911824528 / 0913678404 / 0913949676 / 0910076453 / 0923106826 / 0913866717 / 0911335683

Note:
➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና መሠጠት ጀምራል።


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ለሚወስዱት የከተማና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በቂ ዝግጅት ለማድረግ እገዛ የሚያደርግ ሞዴል ፈተና በ11 ድም ክፍለ ከተማዎች በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መሠጠት ጀምራል።


የሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።
ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Via_Atc


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና መስጫ መርሀ ግብር


የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የ6፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና የሚሰጠው ከጥር 06-08/2017ዓ.ም ነው፡፡ በመሆኑም ፈተናው በተመሳሳይ በሁሉም ት/ቤቶች በተዘጋጀው የፈተና መስጫ የጊዜ ሰሌዳ በየትምህርት አይነቱ እንዲሰጥ ክትትል እንዲደረግ እና ከፈተና በኋላ የፈተናው ውጤት በሶስቱም ክፍል ደረጃዎች ከ20% ለተማሪዎቹ እንዲያዝ እንዲሁም የመጀመሪያ ሴሚሰተር ውጤት ትንተናው ቀደም ሲል በተላከው ቅጽ መሰረት ተተንትኖ እስከ የካቲት 03/2017ዓ.ም ድረስ ገቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

[የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ]

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete


ዛሬ ይጠናቀቃል!

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና #በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ ዛሬ ታህሳስ 30/2017 ዓ.ም ይጠናቀቃል!

በመደበኛ መርሐግብር ከዚህ ቀደም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ #ያላለፋችሁና በድጋሜ ፈተናውን መውሰድ የምትፈልጉ አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም የሚሞሉ ቅጾችን በመሙላት፣ አስፈላጊ ሰነዶችን በመጫን እና የምዝገባ ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን በቀሩት ሰዓታት ያከናውኑ፡፡

ኦንላይን ለመመዝገብ 👇
https://register.eaes.et/Online

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!

https://t.me/temhert_bebete
https://t.me/temhert_bebete

Показано 15 последних публикаций.