🫴ትንሽ ደቂቃ ስጠኝ ....🙏 ከዛ በኋላ ሞግተኝ ..
በአንድ ወቅት (2006/7 ) ሰር አሌክስ የተከላካይ መስመሩን መሳሳት ተመልክተው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ተከላካዮች አመጡ ( ቪዲችና ኤቨራ ) ሁለቱም በ January ዝውውር የመጡነበሩና ሞከሯቸው አልሆነም ሊጉእንደ አለትነበር የከበዳቸው መሮጥ እስኪቸግራቸው ተልፈሰፈሱ ... ሜዳውስጥ እስከ ማስመለስ ደርሰውም አይተናል .... ግንኮ ፖቴንሽያል ነበራቸው ወደ ዩናይትድ የመጡትም ፖቴንሽያል ስለነበራቸው ነው
ፈርጌ ምን አደረጉ መሰለህ ሁለቱንም ለስድስት ወራት ከሜዳ አርቀው ሊጉን እያስተማሩ በአካል ብቃት አዳበሯቸው በሚገርም ለውጥ ወደ አዲሱ ሲዝን ሲመጡ ቦታቸውን አስከብረው የሚደርስባቸው ጠፋ በአእምሮ በአካል የዳበሩት ሁለቱም ያማረ ቆይታን በዩናይትድ አደረጉ ...
ተመልከት በባርሴሎና ያየነውን አስቀያሚ ተጨዋች ፊሊክ የቀየረበትን ሁኔታ ስመለከት እደነቃለሁ የከሰረውን ራፊንሃ አሁን የቡድኑ ወሳኝ ተጨዋች አድርጎታል ሚናው ተቀይሯል የአጨዋወት ሀሳቡ ግልፅ ሁኖለታል የተፈላጊነት ስሜት ስለተሰማው በራስ መተማመኑ አድጓል ... አሁን ራፊንሃን ሊነካው አይችልም ...
ሰወች አሁንም አንቶኒ አይችልም ይሉኛል እኔደሞ በዩናይትድ ስኬታማ አልሆነም እንጂ በቅርቡ ካየናቸው ወጣት ብራዚላዊያን ምርጥ ታለንቶች አንዱነው እላለሁ
ለዚህ ደሞ ምክንያቶች አሉኝ ሂዱና በአያክስ የነበረውን እንቅስቃሴ ተመልከቱ በብሄራዊ ቡድኑ እንኳን በተደጋጋሚ እየተመረጠ ቆይቷል .... ይህ ያለምክንያት አልሆነም ዩናይትድም ቢሆን 100ሚዮ ( የተጋነነ ) ቢሆንም የከፈለበት ምንም ፖቴንሽያል ሳይኖረው አደለም ትልቁ ችግር ግምገማ አለመስራታቸውነው ለሊጉ ይመጥናል ይቋቋመዋል በቡድኑስ ምንያህል ተፅዕኖ ይኖረዋል እያንዳንዱን ነገር መገምገም ነበረባቸው ... በወቅቱ የነበረው የዩናይትድ አስተዳደር ደሞ እግርኳሱን በሚያውቁት ሰወች የሚመራ አልነበረምና ብዙ ስህተቶች ሰርተዋል አሞሪም ነገሮችን ካልቀየረም የዛኛው አስተዳደር ትልቅ ስህተት አንቶኒ ይሆናል
በዩናይትድ ያስቸገረው ብዙነገርአለ ዋናው ግልፅ የጭዋታ ፕላን ያለው ቡድን አለመሆኑነው እንኳን ለተጨዋቾች ለተመልካች የቴንሀጉ ዩናይትድ አይገባም ነበር ... ተጨዋቾች ሀሳቡን መረዳት ካልቻሉ አንድም በአሰልጣኙ ሌላምደሞ በተጨዋቹ ነገሮችን የመረዳት ድክመት ይመጣል
በአያክስ በቴንሀግስር እንደዛ ከደመቀና በዩናይትድ ከተቸገረ
ልጁ ስላልቻለ ብቻ አደለም እራሱ አሰልጣኙም ግልፅ ፕላን አልኖረውም እራሱ አሰልጣኙም በሆላንድ የሰራውን በእንግሊዝ ሊደግመው አልቻለም አሰልጣኙ በዚህልክ ከተቸገረ የተቸዋቹ መቸገር አያስገርምም ....
የተጋጣሚውን የመከላከል አደረጃጀት ለማፈራረስ ዩናይትድ ብዙ ፓተርኖች የሌሉት በመሆኑ እንደ አንቶኒ አይነት ተጨዋቾች ግራ ተጋብተዋል አንቶኒ ብቻኮ አደለም ጀደን ሳንቾ ሚምፍስ ዲፓይ አንሄል ዲማሪያ ሲቸገሩ አይተናል ...
ይሄው በብዙ ተስፋ የጠበቅነው ራሽፎርድምኮ እየከሸፈነው
ልጁ የተጫወተበት ሊግ ብዙ ስፔስ ሚገኝበት በነፃነት መቦረቅ ሚቻልበት በዚህ ላይ አያክስ ተሰርቶ ያለቀና እንዴት እንደሚጫወቱ ግልፅ ሀሳብ የነበረው ቡድንነው የእንግሊዝ ሊግ ስፔሶች አይተውልህም በብዙ ተጨዋቾች መከበብ መጋጨት በፍጥነት ማሰብ ካልቻልክ ነገሮች አስቸጋሪ ይሆናሉ ይህን ለልጁ ማስጠናት የሚችል አሰልጣኝ አልነበረም ... የዩናይትድ ስህተት ገና ታለንቱ ጨርሶ ያልወጣን የመስመር ተጨዋች ቡድኑ ተሰርቶ ሳያልቅ ማምጣት ለኔ ስህተትነው ... ምክንያቱም ገና ተማሪነበር ...
ታድያ በአሞሪም ቡድንስ ልጁ ምንአይነት ሚና ሊሰጠው ይችላል የሚለውን መመልከት ተገቢ ይመስለኛል በእርግጥ አንዳንድ መረጃዎች ስመለከት አሰልጣኙ ልጁን አይፈልገውም ይላሉ የመወጣት እድሉ ሰፊነው ነገርግን አሞሪም በ Back 3 የመጫወት በመሆኑ 3-5-2 3-4-3
3-3_1-3 አይነት ፎርሜሽን ሲጠቀም ሁልጊዜም ሁለት wingbacks ይጠቀማል በዚህ ምክንያት ኦፌንሲቨ ማይንድ ያላቸውን ነገርግን ለመከላከል ማይሰንፉ ተጨዋቾችን ይመርጣል ይህልጅደሞ በአንድ ወቅት v Liverpool ለሀያ ደቂቃዎች LB ሁኖ ሲጫወት ያየነው ከመሆኑ ጋር rwf ላይ እየተጫወተም ወደኋላ ተመልሶ በመከላከል ምንም ድክመት ስንፍና የለውም እናም አሞሪም
ከሁለቱ ተመላላሾች አንደኛው ቢያደርግና ቢሞክረው አልገረምም ....ሌላው በሚወደው RWF እንዲጎለብት መርዳት ሊሆን ይችላል .... አሞሪም ከሶስቱ የመጨረሻ ተጨዋቾች ሁለቱን ወደ ሀፍስፔሱ አጥበው እንዲጫወቱ በማድረግ ኮሪደሩን ለዊንግባኮች መተው የሚፈልግ በመሆኑ
በዚህም ሲስተም ከሶስቱ አንዱ ሊያደርገው ይችላል ....
እራሱ አሞሪምምኮ ትልቅ አሰልጣኝ መሆኑን ማሳየት ከሚችልባቸው ነገሮች አንዱ እንደዚህ አይነት ተጨዋቾችን አጎልብቶ ማሳየት ሲችልነው .....
ዋናው ነገር መጫወቻ ቦታ መስጠት ብቻአደለም ሚጫወትበትን ሀሳብ በግልፅ ማስረዳትና ምርጡን ብቃቱን አውጥቶ እንዲጠቀም መርዳትም እንጂ ፊሊክ በራፊንሃለይ ያመጣውን ለውጥ አሞሪም በአንቶኒ ለመድገም ከሰራበት ሊቀይረው ሚችልበት ብዙ ምክንያት አለ ዋናው ደሞ ተጨዋቹ ያለው ጥሩ ሰራተኝነትነው ... ብዙ ፕረስ ማድረግ ለሚፈልጉ አሰልጣኞች የሚመች ታታሪነት ያለው ልጅነው
አሁንም ብዙዎች በተቃራኒው ትሟገቱኛላችሁ እኔግን ፖቴንሽያል ያላቸውን ተጨዋቾች አጠቃቀም ላወቀበት አሰልጣኝ ማይቀየር ተጨዋች የለም ጋርናቾ ያለበትቦታለይ ብሩኖና አማድ ያሉበት ላይም ሊሞክረው ይችላል ።
#Manchesterunited
https://vm.tiktok.com/ZMhp6kMbM/