አዶናይ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


በዚህ ቻናል በኩል የታረደውን የእግዚአብሔር በግ እያከበርን ፣ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በውስጥ ሰውነታችንን በሀይል እንበረታለን።
መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር ነው 🥰
@AdonaiComments_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


አሳ ነባሪውና እኛ 🥰

ከላይ በምስሉ ላይ ስለምትመለከቱት ሰማያዊ አሳ ነባሪ ስለሚባለው አሳ ዝርያ ሳነብ ያገኘሁትን ላካፍላቹ...የአሳ ነባሪው ቁመት ቢያንስ 30 ሜትር ይደርሳል በአጠቃላይ ክብደቱ 180,000 ኪሎ ግራም ይሆናል ልቡ ብቻ ደግሞ ከ590 ኪሎ ግራም በላይ ይመዝናል (የአንድ ትንሽ መኪና መጠን ያክላል ማለት ነው) አስገራሚው ነገር ደግሞ የአንዳንድ ሰማያዊ አሳ ነባሪ ዝርያ የደም ማስተላለፊያ ትቦዎች ስፋት ትልቅ ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ጎረምሳ የሆነ ሰው ያስዋኛሉ 😊 ግን የሚያሳዝነው ነገር ይሄ ግዙፍና አስፈሪ አሳ ነባሪ ከውሀ ውጪ መኖር አለመቻሉ ነው 😢 ግዙፍ ነው ግን ውሀ ውስጥ ብቻ ፣ አስፈሪ ነው ግን ውሀ ውስጥ ብቻ ... ይሄን የሚያክል ፍጥረት ለትንሽ ደቂቃ ከውሀ ውስጥ ቢወጣ ይሞታል🤦 ልክ እንዲሁ እኛም ትልቅ ነን ግን በክርስቶስ ውስጥ፣ ለጭለማው መንግሥት አስፈሪዎች ነን ግን በክርስቶስ ውስጥ ፣ ከአሸናፊዎች ሁሉ እንበልጣለን ግን ሁሉም የሚሆነው በክርስቶስ ውስጥ ስንሆን ብቻ ነው።

ሀያላን የእናንተ ገዢነትና ጥንካሬ የቱ ጋር እንደሚሰራ ለዩና እወቁ።

@thedayofPentecost
@thedayofPentecost

755 0 20 3 60

አንዴ ልይህ

የአባቴ ልጆች ከኢየሱስ ጋር የሆነ የደማስቆ ህይወት አልናፈቃቹም😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

839 0 16 6 37

ፊልሞችን አትመልከቱ

ከዚህ መልዕክት በኃላ ብዙ ሰዎች ቻናሌን ጥለው ሊወጡ ይችላሉ ነገር ግን እየመረራቹም ቢሆን እውነቱን ብነግራቹ ይሻላል፤ አዎ ከእናንተ ማንነት ጋር የማይሄዱ ፊልሞችን አትመልከቱ በተለይ ደግሞ ተከታታይ ፊልሞች እያሳደዳቹ የምታዩ ልጆች በጊዜ ይህን ልማዳቹን አቁም፤ ፊልሞች በባህሪያቸው ልባቹ ላይ የሚቀሩ መልዕክችን ከማስተላለፋቸው በተጨማሪ ለእናንተ በጊዜው Normal የሚመስሉ ነገር ግን ቀስ በቀስ ህይወታቹን አደጋ ውስጥ መክተት የሚችሉ ትዕይንቶች አይምሯቹ ውስጥ ያስቀምጣሉ... በተለይ ደግሞ Sexual እና Demonic የሆኑ ምስሎችን በልባቹ ውስጥ በማስቀረት ህሊናቹን ያረክሱታል፤ ውሏቹ ፣ ለሊቶቻቹን even አካሄዳቹንና ንግግራቹን ሳይቀር ይቆጣጠሩታል፤ አሁን ላይ ደግሞ የሚታዩት አብዛኛዎቹ ፊልሞች Almost ከ 90% በላይ የሚሆኑት እናንተ ለመንፈሳዊ አለም ያላቹን ንቃት እንዲያጠፋ ታስበው የሚሰሩ ናቸው ስለዚህ በጌታ ፍቅር መንፈሳዊነታቹን የምትፈልጉት ከሆነ ከእንደነዚህ አይነቶቹ ገዳዮቻቹ ጋር ከልክ በላይ ባትወዳጁ መልካም ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

2.4k 0 31 11 132

ካለህበት ቦታ ተነስ 😁

የአባቴ ልጆች እኔ ወንድማቹ ሰሞኑን ቤተ ክርስቲያን የገጠመኝን ላወራቹማ ስሙኝ... 🥰 ሰዓቱ የእግዚአብሔር ቃል የምንሰማበት ሰዓት ነበር እና አንድ የእግዚአብሔር ሰው መድረኩን ይዞ የጌታ ቃል በሚገርም መልኩ መስበክ ጀመረ እኔና አንድ ወንድሜ ደግሞ ከበስተዋላ ጥግ ላይ ተቀምጠን ስብከቱን እየሰማን ነው ከጎኔ ደግሞ አንድ ልቤ ያረፈባቸው ቢበዛ የ ስድስት አመት ልጅና አባት ተቀምጠዋል፤ ሰባኪው በሰዓቱ እንደማንኛው ኢትዮጵያዊ ሰባኪ ከጎናቹ ያለው ሰው ያዙ እና እንዲህ በሉት ማለት ያበዛል😀( ይቺም ደግሞ ቃል ሆና እንዳሰነጥቋት Just የተለመደ ስለሆነ ነው) እና ከጎኔ ያለውን ወንድሜን እንዲ እንዲያ ስለው ቆየውና ፤ ከስድስት አመት ልጇቸው ጋር ተቀምጠው የነበሩትን አባት አየት ሳደርጋቸው ከጎናቹ ሰባኪው በሉ የሚሉትን ሰው አጥተው ያንኑ ከጎናቸው ያለውን ልጃቸውን እጁን ይዘው ሰባኪው በሉ ያለው ቃል በሙሉ ሲነግሩት አስተዋልኩ በመሀል ላይ ግን ሰባኪው ከጎንህ ያለውን ሰው ካለህበት ቦታ ተነስ በልና ንገረው ብሎ ሲያውጅ እኚህ አባትም እንደለመዱት ልጃቸውን ይዘው በሉ የተባሉትን ቃል ቢሉት ልጃቸው ግን ከወንበሩ ተነስቶ አባ ልወጣ ፈቀድክልኝ ብሏቸው አረፈው😁 አባት ልጃቸውን ምን ማለት እንደፈለጉ ሊያስረዱት ቢሞክሩም ልጃቸው ግን ልቡ ውጪ ውጪውን ያይ ስለነበር ሊሰማቸው አልፈለገም ኃላ ላይ ግን አባት ሳይፈልጉ ልጃቸውን ቆጣ ብለው ወንበሩ ላይ አስቀመጡት... ምን ልላቹ መሰላቹ 🥰 አንዳንዴ እግዚአብሔር አንዳንድ ነገሮች የማይነግረን እኛ ለራሳችን በሚመቸን መልኩ ተርጉመን እንዳንረዳውና እንዳንጠፋበት ስለሚፈልግ ነው፤ እኚህ አባት ልጃቸውን በቅጡ እንዲህ በል ለማለት በአይምሮ ሳያሳድጉት ስለነገሩት ልጃቸው ማጥፋቱን ሳያውቀው ጥፍተኛ ሆኖ ተገኘባቸው፤ እግዚአብሔር ግን ይህ ህይወት በእኛ እንዲፈጠር አይፈልግም ለዚህም ነው ከእርሱ ለምንሰማቸው ነገሮች መጀመሪያ ሳያሳድገን ምንም ነገር የማያደርግልን፤ የተወደዳቹ ምንም ያህል ልጆች ብትሆኑም የታሰበላቹ ሁሉ ግን ይነገራቿል ማለት አይደለምአንዳንድ የእግዚአብሔር ዝምታዎች የእናንተን ማደግ ነው የሚጠብቁት።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


Profile challenge 🥰

ለእኔ ባይነገረኝም 😇 የኢየሱስን መምጣት የናፈቁ ልጆች ግን ይሄን መልዕክት ትልቅ ቻሌንጅ አድርገውታል 🥰 እና እናንተ ምን ትጠብቃላቹ...

ሁላቹም በዚህ ሳምንት ቴሌግራማቹን በዚህ ድንቅ መልዕክት አጨናንቁት፤ የእናንተን Profile የሚመለከት ሰው ሁሉ የምጠብቁት አንድ ትልቅ ተስፋ እንዳላቹ ማወቅ አለበት።

ኢየሱስ በቅርቡ ሊወስደን ይመጣል💯

@thedayofpentecost

2.7k 0 35 13 64

ከዚች ትርጉም ከሌላት እና ራሷን ካዋረደች አለምና ስርዓት ለዘላለም ለቀን የምንሄድበት ጊዜው በጣም የቀረበ ይመስለኛል ምናልባት ሰሞኑን ሊሆን ይችላል 🤗 ብቻ ጌታ በቅርቡ ይመጣል፤ ዘወትር ልባቹ ለዚህ ፅኑ ተስፋ ንቁ ይሁን።

ኢየሱስ ይመጣል

@thedayofpentecost


በመንፈሳዊ ህይወታቹ እንድጠነክሩ ስለሚረዷቹ እነኚን ሁለት ቻናሎች ሁላቹም እንድትቀላቀሏቸው ጋብዛቿለሁ 🥰

@Teme_Cloud

@PRAYANYTIME


ጥያቄ ?

ከቅርብ ጊዜያት በኃላ በፀሎት ሰዓት ላይ የባዶነት ስሜት እየተሰማኝ ነው ፣ እንደ ቀድሞ መጽሐፍ ቅዱሴን ባነብም ነገር ግን ይሄ ስሜት አልጠፋም ?

መልስ

ይህ የወንድሜ ጥያቄ የእናንተም ጥያቄ ሊሆን ስለሚችል በሚገባቹ መልኩ ለማስረዳት ሞክራለው እናንተ ብቻ ማንበቡ ላይ በርቱልኝ 🥰 አብዛኞቻቹ በፁሎት ሰዓት ወይም ከፀሎት በኃላ ውስጣቹ የባዶነት ስማት የሚሰማቹ ሰዎች ከነኚ ሁለት አይነት አማኞች መካከል ልትሆኑ ትችላላችሁ...

የመጀመሪያዎቹ... በመንፈሳዊ ህይወታቸው ገና ያላደጉ፣ በግላቸውም ብዙም የመፀለይ ልምድ የሌላቸው ሰዎች ሲሆኑ እነኚ ሰዎች ለብቻቸው መፀለይ ሲጀምሩ መጀመሪያ አካባቢ ላይ በፀሎት ሰዓታቸው ላይ ምንም አይነት የተለየ መነቃቃት ላይሰማቸው ይችላል ይህ የሚሆነ በደንብ የውስጥ ሰውነታቸው መጠንከር ስላልጀመረ ነው በተጨማሪም ደግሞ የምታሰላስሉት የእግዚአብሔር ቃል እውቀት በውስጣቹ ከሌለ የፀሎት ጊዜያቹ ድካም የበዛበት ብሎም እንቅልፍ እና ድብርት የተጫጫነው ሊሆን ይችላል... በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳላቹ የሚሰማቹ ልጆች ካላቹ በሚቀጥለው ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት በቀላሉ መውጣት እንደምትችሉ እነግራቿለው🥰

ወደ ሁለተኛዎች ስመጣ... በፀሎት ውስጥ ወይም ከፀሎት በኋላ የባዶነት አይነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ከመጀመሪያዎቹ በተቃራኒ በመንፈስ አለም የጠየከሩ፣ ውስጣቸውም በመንፈስ ርሃብ የሚቃጠልባቸው ልጆች ሊሆኑ ይችላል እኔም ብዙ ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ አልፌ ስለማውቅ ሁኔታ ይገባኛል፤ እንደ ጤና ባለሞያ ነገርዬው በምልክት ባስቀምጠው በቀላሉ ትረዱኛላቹ ☺️...ለምሳሌ የ 15 ቀን ፆም ፀሎት ይዛቹ በደንብ እየፀለያቹ እያለ የሆነ ሰዓት ላይ ውስጣቹ ባዶ ይሆናል ተነስታቹ መጽሐፍ ቅዱሳቹ ታነባላቹ አሁንም ግን ከዚያ ሁኔታ ውስጥ መውጣት ይከብዳቿል ፤ በቀን 2 እና 3 ሰዓታት ከጌታ ጋር ጊዜ አሳልፋቹ ስትወጡ እንዳሰባቹ የመንፈስ እርካታ ላይሰማቹ ይችላል... ይህ የሚሆነው አንደኛ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሌለበትን የሆነ Mistake በህይወታቹ ከሰራቹ እግዚአብሔር በዚህ አይነት መልኩ ወደ ፍቃዱ እንድትመለሱ ሊያደርጋቹ ይችላል ሁለተኛው እና አብዛኛው ጊዜ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ የምትገቡበት ምክንያት ከልክ ያለፈ መንፈሳዊ ርሃብ ውስጥ በምቶኑበት ጊዜ ነው አለ አይደል በቃ እስከ ጥግ ድረስ ውስጣቹ የእግዚአብሔር ክብር ሲፈልግ የሚሰማቹ መንፈሳዊ ርሃብ አይነት ልክ ያዕቆብ አለቅህም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ትግልን እንደገጠመው ማለት ነው 🔥እናንተም የምትፈልጉት እስካላገኛቹ ድረስ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ መርካት አትፈልጉም በዚህም ምክንያት ከፀሎት በኋላ እንኳን ምንም እንዳልተቀበላቹ ሊሰማቹ ይችላል ነገር ግን ይህ ትግል የሆነ ከፍታ ላይ ሲያደርሳቹ ትናንት ያልረካቹበት ፀሎት ቀስ በቀስ የእናንተ መዋያ ይሆናል ።

እወዳቿለሁ 🥰

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


የሚጮህ ደም 🗣️

የሰው ደም በባህሪው ለእግዚአብሔር የሚሰማው ድምፅ አለው ብዬ አምናለሁ ትዝ ካላቹ ቃየል አቤልን ከገደለው በኋላ የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር እንደጮኽ መጽሐፍ በግልፅ ይነግረናል ልክ እንደ አቤልም እስከ ዛሬ ድረስ የሰዎች ደም ለፍርድ ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ ለምን አትፈርድም ፣ አታይም ወይ የሚሉ የደም ጩኽቶች በእግዚአብሔር ዘንድ እስከ አሁን ድረስ ይሰማሉ፤ ከዛሬ ሁለት ሺ አመታት በፊት መስቀል ላይ የታረደው የእግዚአብሔር በግ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ የሌሎች ሰዎች ደም ለፍርድ ሲጮኽ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብቻ ግን ለህዝቦች ምህረት ወደ እግዚአብሔር ይጮሃል፤ አሁን አብ የሚሰማው መስቀል ላይ የታረደውን የገዛ ልጁን ደም ነው ይሄ ክቡር ደም ደግሞ ይቅርታ እና ምህረት እንጂ ፍርድን ወደኛ ለማምጣት አይጮህም ለዛም ነው መጽሐፍ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ፣ እንዲሁም ከአቤል ደም የተሻለ ቃል ወደሚናገረው ወደ ተረጨው ደም ደርሳችኋልብሎ ያለን ፤ እኛም በዚህ ምክንያት ነው በሙሉ ልብ ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ ያለ ጠበቃችን ነው ለማለት ድፍረትን ያገኘነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


እነኚ የመዝሙር ስንኖች አንብቧቸው

ባየው ባየው አይለወጥም ፍቅሩ ፣
ባየው ባየው አልቀዘቀዘም መውደዱ ፤
ባየው ባየው አይቀየርም እንክብካቤው
እንደ ትናንቱ እንደ ልጅነቴ ሲወደኝ ያው ነው


ስንደክም አቅም ሳጣ ፣ እጆቼ እጆቹን መያዝ ሲከብዳቸው የእርሱ ፍቅር ግን ያው ነው በኛ ድካም የማይቀዘቅዝ ፍቅር በኛ ጥፋት የማይለወጥ ርህራሄ እያሳየ የሚያኖር ድንቅ አባት፤

ጌታ ሆይ በኛ ላይ ስላልተቀየረው ፍቅርህ እናመሰግንሃለን 🥰


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በጣም ድንቅ መልዕክት 💪

ከወንድማቹ ኤርሚያስ 🥰


@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


ድሉን ከማ ጋር ?

በመንፈስ አለም በጌታ ፍቃዱ የዘገየ ሰው ብቻውን ሮጦ ካሸነፈው ሰው በላይ ፈጣን ነው፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ድል ሁል ጊዜም የሚገኘው ከሰዎች ጋር በመሮጥ ሳይሆን እርሱን በመጠበቅ ውስጥ ነው። የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ለማሸነፍ ማርፈድ ካለባቹ አመታቶችንም ቢሆን እንኳን አርፍዱ ፤ የምታውቋቸው ሰዎች ከእናንተ ርቀው ቢሄዱም እናንተ ግን ከእርሱ ጋር ሆናቹ መቆምን ምረጡ፤ እርሱ ሳይኖርበት ብዙ ጦሮችን ከምታሸንፉ ይልቅ ጌታ ኖሮላቹ ደጋግማቹ ብትሸነፉ ይሻላቿል፤ ደግሞሞ ለኛ ድል ትክክለኛ ትርጉም የሚኖረው እግዚአብሔር ከፊት ሆኖ የሚመራው ከሆነ ብቻ ነው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አባ እወድሃለሁ 😭

በቅርቡ በ TikTok በኩል በእንደነዚህ አይነት ጥልቅ መልዕክቾች እመጣለሁ 🥰


ከመነካት የመነጨ የፍቅር ቋንቋ 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


በሰማሁት ቁጥር የምነካበት ድንቅ መዝሙር

መዝሙሩ ከወጣ ከ 8 አመት በላይ ቢሆነውም ዛሬም ድረስ ግን ነፍስን የሚነካ ሀይል አለበት🔥

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


በየቀኑ እኔን ከጌታ ለመለየት የምትሰሩ መናፍስቶች ግን ምን ነክቷቹ ነው ቆይ ለምን ተስፍ አትቆርጡም ደግሞ አይደክማቹም እንዴ 😁 እኔን ለመጣል ምን ያልፈነቀላቹት ድንጋይ አለ እኔ እንደው አሁንም በጌታዬ እቅፍ ውስጥ ነኝ 😇.. እንደኔ በግ መሆን እና እንደናንተ ተኩላነት ቢሆን ኖሮ ገና ዱሮ ነበር የሚያልቅልኝ ነገር ግን በእኔ እና በእናንተ መካከል አንድ እኔን የሚጠብቅ መልካም እረኛ አለ💪 እና ብዙ አትድከሙ ኢየሱስ የሚባል ጀግና እረኛ አለኝ 🥰

3.1k 0 11 5 109

ኑሮ ያልከውን መኖር 😭

ሰሞኑን የዘማሪ ሐዋሪያው ዮሃንስን አንድ መዝሙር እየሰማሁ ከእኔ አልፎ ለናንተም የማካፍለውን ትልቅ መልዕክት በውስጡ አገኘው... መልዕክቱ ከመናገሬ በፊት ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹ አሁን ላይ መኖራቹ ትርጉም ያለው ይመስላቿል ? ትርጉምስ አለው ካላቹን ህይወታቹ ትርጉም የኖረው ለእናንተ ነው ወይስ ለእግዚአብሔር ? ? ገና ሳትፈጠሩ በማህፀንም ሳይሰራቹ እግዚአብሔር እንድትኖሩለት ያሰበውን ያንን መኖር እየኖራቹ ከሆነ አዎ መኖራቹ በርግጥ አሁን ላይ ትርጉም አለው፤ ያሰበላቹን ሳይሆን ያሰባቹትን ፣ ፍቃዱን ሳይሆን ፍቃዳቹን ከኖራቹ ደግሞ ምንም ያህል እናንተ እየኖራቹ እንደሆነ ብታስቡም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ገና መኖር አልጀመራቹም፤ ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ የምናገኛቸው ስኬቶችና ድሎች ትክክለኛ ትርጉም የሚኖራቸው ከእግዚአብሔር እንፃር ልክ ከሆኑ ብቻ ነው ካለዚያ ግን ድል ላይ ብዙ ድሎች ቢከመሩም እንኳን ሁል ጊዜ ተሸናፊዎች ነን።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


እንደ ምክር ያህል 😇

መቼም ቢሆን በህይወታቹ ውስጥ ዙሪያቹ ያሉትን ሰዎች ላለማስቀየም ብላቹ የእግዚአብሔር ሃሳብ የሌለበትን ውሳኔ በራሳቹ ላይ አትወስኑ ... አሁን ላይ ከጌታ ቤት ስትርቁ፣ ፀሎት ስታቆሙ እና በህይወታቹ ውስጥ የተሳሳተ ውሳኔ ስትወስኑ ልክ ናቹ ብለው ያጀቧቹ ሰዎች ነገ ላይ ስትጎዱ እና ስትደክሙ እናንተን ለማገዝ ማናቸውም አብረዋቹ አይቆሙም...church ስትሄዱ የሚደብራቸው ሰዎች ካሉ እነርሱ ለማስደሰት ብላቹ Church ከምትቀሩ ለዘላለም እነርሱ እየደበራቹ ቢቀጥሉ ይሻላቸዋል፣ በመንፈሳዊ ህይወታቹም ስትበረቱና ፀሎት ስታበዙ ሙድ ለመያዝ የሚሞክሩ ጓደኞችም ካሏቹ እነርሱን ለመምሰል ብዙ አትጣጣሩ ተዋቸው ... አንድ ወርቅ የያዘ ሰው ከዘጠና ዘጠኝ ድንጋይ ከያዙ ሰዎች ጋር አብሮ ብሆንና ድንጋይ የያዙት ሰዎች ሙድ ቢይዙበት ይህ ሰው የግድ እነርሱን ለማስደሰት ብሎ የያዘውን ወርቅ መጣል ሳይሆን ያለበት እነርሱን ትቶ ወርቅ ከያዙ ሰዎች ጋር ነው መቀጠል ያለበት ካልሆነ ግን እነኚ ሰዎች በጊዜ ሂደት እነርሱ የያዙት ወርቅ እርሱ የያዘው ደግሞ ድንጋይ እንደሆነ አሳምነውት ትክክለኛ ወርቅ ያስጥሉታል፤ Be Wise 😇 አሁን ያላቹበት ህይወት በጣም ውድ ነው፤ ሰዎች በዚህ ህይወት ላይሀሳብ እንዲሰጡበት አትፍቀዱላቸው።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


አሁን ይሄን ጽሑፍ በምታነቡበት በዚህ ሰዓት ብዙ ሰዎች በራቸውን ዘግተው የእግዚአብሔር ፊት እየፈለጉ እንደሆኑ ስንቶቻቿ አስተውላቿል... በዚህ ሰዓት ተንበርክከው አባ ክብርህ አሳየኝ ፣ ለራስ አድርገህ ለየኝ እያሉ አባታቸው እግር ስር እያለቀሱ ያሉ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ እናንተ ከነኚ ዘወትር የእግዚአብሔርን ፊት ከሚፈልጉ ሀያላን መካከል ትሁኑ ፣ አትሁኑ አላውቅም ነገር ግን በዚህ ሰዓት ከነኚ ሰዎች በላይ የት መዋል እንዳለባቸው በትክክል ያወቁ ሰዎች አይገኙም... ብዙዎች በየ መጠጥ ቤቱና በየእርኩሰት ስፍራ ላይ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት በጌታ እግሮች ስር ተንበርክኮ እንደመገኘት ያለ ትልቅ እድል የለም😭 የተወደዳቹ ጌታ በየቀኑ ኑሩበት ብሎ በእድሜያቹ ላይ ቀኖች ከተጨመረላቹ ላይቀር እነኛ ቀኖች እግሮቹ ስር ተንበርክካቹ የምታሳልፏቸው ቀኖቹ ይሁኑላቹ🔥

3.6k 0 16 10 117

🎙️ አንተን ፍለጋ

ፍለጋ...ፍለጋ...ፍለጋ
ቀኞቼ ይለቁ አንተኑ ፍለጋ 😭

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost


አንተስ ምን ትላለህ ?

ብቻዋን ያመነዘረች ይመስል እሷን ብቻ ይዘው ባንዴ ፀጥ የሚያደርጋትን ድንጋይ እየመረጡ በየአደባባዩ ትወገ ትወገ ብለው ሞቷን ደገሱላት...... ኢየሱስም አይቶ የድርሻውን ድንጋይ እንዲጥል ፈልገው ወደ እርሱ አመጧትና አንተስ ምን ትላለህ ? ብለው ጠየቁት፤ እርሱም ድንጋይ መወርወር ሲገባው ጥቂት ቃላት ወደ ከሳሾቿ ወርውሮ በድብቅ የሰሩትን ኃጢአት በግልፅ ገለጠባቸው ከዛም ድንጋይ ተሸክመው የመጡትን ሰዎች የሰሩትን ኃጢአት አሸክሟቸው ሸኛቸው ኃጢአቷን ይዛ የመጣችውን ሴት ግን የእርሱን ፅድቅ አካፍሏት በሰላም ሂጂ አላት.... የተወደዳቹ ሰዎች ስለናንተ ህይወት እድሉ ቢያገኙ ብዙ የሚያወሩት ይኖራቸዋል... ትወገር ፣ ትሙትትጥፍ ፣ አይለፍላት ፣ አይሳካላት ፣ ብቻ ብዙ ነገር ይላሉ ነገር ግን በእናንተ ህይወት ማንም ምንም ቢናገር መፍረድ እስካልቻለ ድረስ ምንም ማድረግ አይችልም፤ ለዚህ ነው ምን ይላሉ ሳይሆን ምን ይላል ብለን መጠበቅ የሚኖርብን።

@thedayofpentecost
@thedayofpentecost

Показано 20 последних публикаций.