TIKVAH-ETHIOPIA


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


የመውጫ ፈተና ከጥር 26 እስከ ጥር 30 ይሰጣል።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

Via @tikvahuniversity


#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት (4:38 ላይ) ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 36 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል ገልጿል።

መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 መመዝገቡን አሳውቋል።

በርካታ ሰዎች የዛሬው ከወትሮው የተለየ ነበር ብለዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የነበረበት አካባቢ ያሉ ወገኖች " አስፈሪ " ሲሉ ገልጸዋል።

ንዝረቱ የተሰማባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከወትሮው የተለየ እንደነበር ታውቋል።

ለአብነት አዲስ አበባ ብዙ ሰዎች ህንጻ ላይ የነበሩ ተሰምቷቸው መደናገጣቸውን ገልጸውልናል። ለተወሰኑ ሰከንዶች የቆየ ቢሆንም የህንጻ ንቅናቄ ስሜት ፣ የመንስታወት መርገፍገፍ እንደተመለከቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል " 4ኛ ፎቅ ላይ በተቀመጥኩበት መስታወቱ ፣ የቤት እቃዎች ሲነቃነቁ፣ እኔም በተቀመጥኩበት በወትሮ በተለየ ንዝረት ሲሰማኝ ነበር " ብሏል።

ሌላ 12ኛ ፎቅ ላይ የነበረ የቤተሰባችን አባል " ያስፈራ ነበር " ሲል ክስተቱን አስረድቷል።

ከዚህ ባለፈ ንዝረቱ ከተሰባቸው ቦታዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ አካባቢ ሲሆን የወረዳ አስተዳደር ህንፃ ላይ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች በድንጋጤ ከህንጻው መውረዳቸውን ከሰራተኞቹ ለመረዳት ተችሏል።

Photo Credit - Omer Al Faruq

@tikvahethiopa


🚨#Alert

ከደቂቃዎች በፊት ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ አካባቢ ተከስቷል።

ንዝሩት በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች ተሰምቷል።

ቃላቸውን የላኩልን የቤተሰባች አባላት " ዛሬ በጣም የሚያስፈራ ነበር። ሰሞኑን ድግግሞሹ ቀንሶ ነበር። ዛሬ በድንገት በሚያስፈራ ሁኔታ ነው የተሰማን " ብለዋል።

@tikvahethiopia


በአዲስ አበባ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ለሞት የሚዳርጉ 5 መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

➡ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር ከፍተኛ የሞት አደጋ የሚያስከትሉ 5 መንገዶች ተለይተዋል።

➡ ከፍተኛ የሞት አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የተለዩት ፦
° መገናኛ፣
° ኃይሌ ጋርመንት፣
° ቦሌ ሚካኤል፣
° ጦር ኃይሎች
° ቻይና ካምፕ መንገዶች ናቸው። በአማካይ በዓመት ከ6 እስከ 13 ዜጎች በእነዚህ መንገዶች በሚደርሱ የተሽከርካሪ አደጋቸው ሕይወታቸውን ያጣሉ።

➡ ከመንገዶቹ አንዳንዶቹ የእግረኛ መተላለፊያ የላቸውም ፤ አሽከርካሪዎች ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከፍጥነት ወሰን በላይ እያሽከረክሩ አደጋ ያደርሳሉ።

➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር በሚደርሰው የትራፊክ አደጋ፣ በአብዛኛው ሕይወታቸውን የሚያጡት ወንዶች ናቸው። መገናኛ አካባቢ አደጋ ከደረሰባቸው 13 ሰዎች አብዛኞቹ ወንዶች መሞተዋል።

➡ አደጋ የሚደርሰው ከቀኑ 6፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን በተለይም ሰንበት ወይም የዕረፍት ቀናት ከመንገድ መጨናነቅ ነፃ ስለሚሆኑ፣ ተከትሎ በፍጥነት ማሽከርከር ምክንያት የሞት ምጣኔው ከፍተኛ ነው።

➡ አደጋዎች የሚያሳዩት ተቆጣጣሪ ተቋማትም ሆኑ አደጋ አድራሾችና ተጎጂዎች የሚያደርጉት ጥንቃቄ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው።

➡ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ናቸው። ከሌሎች የተሽከርካሪ ዓይነቶች አብላጫውን አደጋ የሚያደርሱትም እነሱ ናቸው።

➡ በዓለም የጤና ድርጅት የትራፊክ አደጋ ሥጋት መንስዔዎች ተብለው የተለዩት በፍጥነት ማሽከርከር፣ ጠጥቶ ማሽከረከር፣ የደኅንነት ቀበቶ አለመጠቀምና የራስ ቅል መሸፈኛ አለመጠቀም ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።

➡ 43 በመቶ የሚሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረክራሉ። በዚህ ምክንያት ችግሩ ትኩረት ያሻዋል።

➡ በየዓመቱ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በትራፊክ አደጋ ይሞታሉ። የጥናቶች የትኩረት አቅጣጫ የፍጥነት መገደቢያ መጠቀምና ሥር ነቀል የማኅበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያስገልጋል።   

(የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት መረጃ)

#ሪፖርተርጋዜጣ

@tikvahethiopia


በፓኪስታን ሀገር " እስልምና ላይ ተሳልቀዋል " በሚል የተከሰሱ 4 ሰዎች የሞት ፍርድ ተላለፈባቸው።

4ቱ ሰዎች " ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ የእስልምናን ዕምነት እሴቶችን ጎድተዋል " በሚል ነው የሞት ፍርድ የተላለፈባቸው።

ተከሳሾቹ " የእስልምና እምነትን የሚያንቋሽሹ ይዘቶችን በማህበራዊ የትስስር ገጾች አሰራጭተዋል " በሚል ክስ ተመስርቶባቸው ክርክሩ ሲካሄድ ቆይቷል።

ከሰሞኑ በራዋልፒንዲ ከተማ በተካሄደ ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል በሚል 4ቱም ተከሳሾች የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ተብሏል።

ግለሰቦቹ የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እሴቶችን፣ ቅዱስ ቁርዓንን፣ እምነትን እና ሌሎች ተያያዥ እሴቶችን አንቋሸዋል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ላይ ከሞት ፍርድ በተጨማሪ 16 ሺህ 500 ዶላር እንዲከፍሉ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል።

የተከሳሾቹ ጠበቃ ፤ በደንበኞቹ ላይ የተላለፈው ፍርድ ተመጣጣኝ አይደለም በመቃወም ፤ የተላለፈውን ፍርድ ለማስቀየር ይግባኝ ለማለት በዝግጅት ላይ እንደሆነም አሳውቋል።

መረጃው የአል አይን ኒውስ / አል አረቢያ ነው።

@tikvahethiopia


#Tigray

ዛሬ በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች በኩል የፓሊስ ትእዛዝ የጣሱ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት የጠራቸው ሰልፈኞች ፥ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  ጥር 14/2017 ዓ.ም የወጣውን የውሳኔ ሃሳብ የሚደግፉና እና ሌሎች መፈክሮች አስተጋብተዋል።

በራሳቸው ተነሳሽነት ሰልፍ መውጣታቸው የሚናገሩት በብዛት ወጣቶች ያካተቱ ሰልፈኞች ደግሞ " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚነት (null and void እንዲሆን) እንዳይኖረው ፤ ጦርነት የሚፀየፉና ጅምር ሰላም እና ለውጡ እንዲቀጥል የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

በሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላዊ ዞኖች መቐለ ከተማ በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት ብቻ የጠራቸው ሰልፎች ሲካሄዱ ፤ በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች በደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ ጊዜ የተጠሩ ሰልፎች ተከናውነዋል።

በውቅሮ ከተማ የፀጥታ አካላት በራስ ተነሳሽነት ለመውጣት በሞከሩት ላይ ለመበተን የሞከሩ ሲሆን ፤ በዓዲግራት የነበሩት የለውጥ ደጋፊዎች ላይ ግን ለመበተን የተደረገ ሙከራ እንደሌለ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዘግቧል።

ትናንት ጥር 17/2017 ዓ.ም  በደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል  የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ጦርነት የሚያወግዝ ሰላምና ለውጥ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ የተካሄደ ሲሆን ዛሬ እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት የጠራው ሰልፍ በዞኑ አልተካሄደም።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራ ህወሓት በጠራው ሰልፍ የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የትግራይ ሰራዊት ውሳኔ ይተግበር !!
- የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ይስተካከል !!
- የፕሪቶሪያ ውል ይተግበር !!
- የትግራይ ሉአላዊ ግዛት ይከበር !!
- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ !!
- የህወሓት ህጋዊነት በአስቸኳይ ይመለስ !!
- የውጭ ጣልቃ ገብነት አንቀበልም !!
- ሰራዊታችን ለማፍረስ እየተደረገ ያለው ሴራ አንቀበልም !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት መተግበር ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ዋስትና ነው !!

በራስ ተነሳሽነት ወጣቶች በብዛት በተሳተፉባቸው ሰልፎች የተደመጡ መፈክሮች ምን ይመስላሉ ?

- የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም !!
- የትግራይ የፀጥታ ሃይሎች የህዝብ አገልጋዮች እንጂ የአንድ ቡድን ከለላ አይደሉም ! 
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
- የሚቆም ትግል እና ለውጥ የለም !!
- ወጣቶች ለልማት እንጂ ለጦርነት አንሰልፍም!!
- የተረጋጋ መንግስት ለመትከል የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው !!
-ጊዚያዊ አስተዳደሩ ወደ መደበኛ መንግስት የሚያሸጋግረን በቸኛ ህጋዊ ተቋም ነው !!
- የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲፀና እንፈልጋለን !!

... ሲሉ ተደምጠዋል።

በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ፤ ዛሬ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረገበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው ያለ ሲሆን ጊዚያዊ አስተዳደሩ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በኩል ጥር 17/2017 ዓ.ም  ባወጣው መግለጫ ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተጠራ እና የተፈቀደ ሰልፍ የለም ብሎ ነበር።

የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት በመቸገሩ ምክንያተት ቀን እንዲቀየርለት ሲጠይቅ : የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ  ትእዛዝ ተላልፈው ስበብሰባ እና ሰላማዊ ሰልፍ በሚያካሂዱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ማስጠንቀቁ መዘገባችን ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እስከ አሁን ባለው መረጃ በድጋፍ እና በተቃውሞ በኩል የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ሰላማዊ የነበሩ ሲሆን ከክልሉ ፓሊስ እንዲሁም የሰላም እና  የፀጥታ ቢሮ የሚሰጥ መረጃ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

@tikvahethiopia


ከፍርድ ውጭ ግድያ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ !

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሩብ ዓመት ሪፖርት በኢትዮጵያ በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካባቢዎች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በተመለከተ።

@tikvahethiopia


#MPESASafaricom

እኛ ለወዳጅ ለመላክ እንዘጋጅ እንጂ ብሩን ፈጥኖ በማድረስ M-PESA አለልን ፤ ከM-PESA ወደ M-PESA ገንዘብ ስንልክ ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ በነፃ እንስተናገዳለን!

#FurtherAheadTogether


' ልጄን ትተህ እኔን ብላኝ ! '

🙏" ከእግዚአብሔር በታች እኔና ልጄን የታደገችን ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ናት " - መምህርት ደንበሌ አስራት

➡️" እናትና ልጅን ለማዳን ከ10 ደቂቃ በላይ ከጅቡ ጋር ታግለናል" - ወ/ሮ መቅደስ ተካ


ከሰሞኑ መምህርት ደንበሌ አስራት የተባሉ እናት በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ 'ጃሎ ናራሞ ' ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ የ12 ዓመት ልጃቸዉን ሊበላ ከያዘ ጅብ ጋር በመታገል ልጇን ማዳኗን ሲዘገብ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ወደ መምህርት ደንበሌ አስራት የእጅ ስልክ በመደወል ስለጉዳዩ ጠይቋቸዋል።

መምህርት ደንበሌ ስለ ጉዳዩ ሲያስረዱ" ጥር 11/2017 ዓ/ም ረፋድ 3 ሠዓት አከባቢ ዉሃ ለመቅዳት ከልጄ ጋር ሽላንሻ ወደተባለው ምንጭ በወረድንበት አጋጣሚ ነበር አፉ በደም የተለወሰ አንድ ጅብ ወደ እኛ በመምጣት በእኔና በጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ መሃል የነበረዉን የ12 ዓመት ሕፃን እግር ነክሶ በመያዝ ወደ ጫካ ዉስጥ መጎተት ሲጀምር ዐይኔ እያዬ ልጄን አይበላብኝም በማለት ቀኝ እጄን የጅቡ አፍ ዉስጥ በመክተት 'ኤ ሲቴ' ኤ ሲቴ'በሀዲየኛ (ልጄን ትተህ እኔን ብላኝ) እያልኩ መጮህ ጀመርኩ " ብለዋል።

" ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ተካ በጄርካንና በመዘፍዘፊያ ጅቡን እየመቱ መጯጯህ ቀጠልን ፤ በመሃል ትግልና ጩኸታችን ስለበዛ ጅቡ እኔንም ልጄንም ትቶ ወደ ወ/ሮ መቅደስ ሲዞር አፉ ደም በደም ሆኖ ነበር " ሲሉ አስረድተዋል።

መምህርት ደንበሌ አስራት " እየጮህን ስንታገል የሰሙ ሰዎች ደርሰዉ ጅቡን በመግደላቸዉ እኛ ወደ ሆስፒታል ተወሰድን " ብለዋል።

" ከፈጣሪ በታች እኔንና ልጄን የታደገችን ጎረቤቴ ወ/ሮ መቅደስ ናቸዉ " የሚሉት መምህርት ደንበሌ አስራት ለተደረገላቸው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል።

ወ/ሮ መቅደስ ተካ በበኩላቸው " ልጅና እናቱን ከጅቡ አፍ ለማስጣል ከ10 ደቂቃ በላይ ታግለናል " ያሉ ሲሆን " የናቲቱ ወ/ሮ ደንበሌ ለልጇ መስዋዕት ለመሆን መዘጋጀት እኔም እናት ነኝና ሆዴን አባብቶ ጅቡን በጋራ ታግለን የከፋ አደጋ እንዳይደርስ አድርገናል" ብለዋል።

ከዚህ ቀደም አንዲት እናት ተመሳሳይ አደጋ በራሳቸዉ ላይ መድረሱን የሚያስታውሱት ሁለቱ እናቶች ከአደጋዉ ባሻገር በሀዲያ ዞን ዋና ከተማ ሆሳዕና ዉስጥ ሆነን " ከጅቦች ጋር ታግለን የምንጠቀመዉ የዉሃ ችግር እልባት ሊሰጠዉ ይገባል " ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia

291k 1 395 7.1k

#Update

🚨 " ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የተፈቀደ የተጠራ ሰልፍ የለም " - የትግራይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

🔵 " እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም መቐለ ጨምሮ በመላው ትግራይ የሚካሄደው ሰልፍ መግባባት የተደረሰበት እና የተሟላ ጥበቃ የሚደረገበት ነው " - በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት

🔴 " ህወሓት ለእሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በቂ ጥበቃ ለመስጠት ስለምንቸገር ቀን እንዲቀይር እናስታውቃለን " - የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን


እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም ጥር 14/2017 ዓ.ም " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚደግፍ እና የሚቃወም ሰልፍ መጠራቱን ተከትሎ ፓሊስ ሰልፉን መሸፈን የሚችል የሰው ሃይል ስለሚያንሰው እንዲቀየር ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ ጥር 17/2017 ዓ.ም ፓሊስ የሰጠው የሰልፍ ክልከላ ማሳሰብያ በመጣስ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተለያዩ ከተሞች " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂደዋል።

እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች ነን " በሚል የተሰጠው ውሳኔ የሚደግፍ ሰላማዊ ስልፍ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ ፓሊስ " በቂ ጥበቃ ስለሌለኝ ሰላማዊ ስልፍ የሚካሄድበት ቀን እንዲቀየር " ቢያሳስብም በሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ሰልፉ የተሟላ የፀጥታ ጥበቃ ያለውና ተፈፃሚ የሚሆን ሲል የፅሁፍ መግለጫ ሰጥቷል።

" እሁድ ጥር 18/2017 ዓ.ም መንግስት በመቐለ የጠራው ሰብሰባም ይሁን ሰልፍ የለም " ያለው የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ፤ " ሰልፍ ይካሄዳል " በማለት ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የሚያደናግሩት አካላት እና ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia

Показано 10 последних публикаций.