“ እንደምናሸንልፍ አምናለሁ “ ፔፕ ጋርዲዮላ
⏩ " በርካታ ደጋፊ ያስፈልገናል "
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከነገው የክለብ ብሩጅ ወሳኝ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸው ወቅት “ በውድድሩ እንደምንቆይ አምናለሁ “ ያሉ ሲሆን ደጋፊው ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጥሪ አቅርበዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?
- “ ጨዋታውን ማሸነፍ እንፈልጋለን ማሸነፍ የማንችል ከሆነ በዚህ ውድድር መቀጠል አንችልም።
- ሁሉም የማንችስተር ሲቲ ደጋፊ በፍርሃት ውስጥ እያለፈ መሆኑን አውቃለሁ ነገርግን እንደምናደርገው አምናለሁ።
- ከምንጊዜውም በላይ በርካታ ደጋፊዎች ያስፈልጉናል ደጋፊዎች በጨዋታው የሚችሉትን ያህል ድምፃቸውን በስታዲየሙ ከፍ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።
- የክለብ ብሩጅን ድክመት አውቀዋለሁ ነገርግን ለሚዲያ ሳይሆን ለተጨዋቾቹ ነው የምናገረው።
- በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ለመሆን የተገደድነው ጥሩ ባለመጫወታችን ምክንያት ነው።
- በርካታ የክለብ ብሩጅ ጨዋታዎችን ተመልክቻለሁ ባለፉት ሀያ ጨዋታዎች አልተሸነፉም ጠንካራ የተከላካይ ክፍል አላቸው ትልቅ ጨዋታ ማድረግ አለብን።
- ኦስካር ቦብ በነገ ምሽቱ ጨዋታ ለቡድኑ ግልጋሎት ሊሰጥ ይችላል።" ሲሉ ተደምጠዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe