#MoH
የ2024 ብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡
ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም በ15 የፈተና ማዕከላት የተሰጠውን ፈተና፤ 1,811 ዕጩ ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን የአንድ ተፈታኝ ውጤት መሰረዙን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ተፈታኞች የተሰጣቸውን User ID በመጠቀም ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡
በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች፤ ሥም፣ User ID፣ ውጤት እና የፈተና ማዕከል በመግለፅ በሚኒስቴሩ ነፃ የስልክ ጥሪ ቁጥር 952 እስከ ጥር 8/2017 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል፡፡
የስፔሻሊቲ እና/ወይም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ እስከ ጥር 8/2017 ዓ.ም ማድረግ እንደሚቻልም ተገልጿል።
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (Anesthesiology CCPM and Emergency & CCM)፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ (Orthopedics) እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ (Dermatovenerology) ለዘንድሮ ERMP ስልጠና የተጨመሩ ፕሮግራሞች መሆናቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity