ትዝታዊ🐣


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


ስላላቹ አመሰግናለው !!
ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


💫🦋…………

ስኖር ላደርጋቸው ከምፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱን በዚህ ሳምንት ውስጥ ፈጣሪ ረድቶኝ ሆኖልኛል ………

ከአመታት በፊት**

እለቱ 21 የማርያም ቀን ነውና አያቴ ቤተክርስትያን አርፍዳ ስትመለስ ቅጠሎቹ ግቢውን አበላሹት ተብሎ በተቆረጠ ዛፍ ላይ ወጥቼ የቴዲን ዘፈን እዘፍናለው በሰዓቱ ሚሰማኝ ብዙ ሰው ባዘጋጀውት ኮንሰርት ላይ ተገኝቶ ስዘፋን እየተመለከተ ያለ ይመስለኛል ፣ ደሞ ለቴዲ አፍሮ ያለኝ ፍቅር እምም …… "የሱን ዘፈኖች እደሸመደድሻቸው የፈጣሪን ቃል ብሸመድጂ ክንፍ ይኖርሽ ነበር " ትለኛለች እየተከታተለች ጥፋቴን ማስዋብ ምትፈልክ አክስቴ ፣ እናላቹ አያቴ "ምን እየሆንሽ ነው ?" አለችኝ ከንግግሯ ውጪ ፊቷ ላይ ቁጣም ደስታም አይነበብም ነበር ………

"ኮንሰርት ነው አያቴ ኮንሰርት ፣ ከቴዲ ጋር እኮ ነኝ አስበሽዋል "

"ተይ ሆድዬ ሰው አጥብቆ የፈለገውን ነው ሚኖረው ፣ መፅሐፈ ምሳሌ ላይ ምዕራፍ 13 ላይ ደሞ እንዲህ ይላል 'አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል ፣ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል ' በአፍሽ ክፉ ምኞትን አትመኚ ፣ ሙላቱን ትኖሪዎልሽ "

"የአፌን ሙላት ?"

"አዎ የአፍሽን ሙላት "…… ወደ ፊት እራመድ ካለች በኃላ የሆነ ነገር እንደረሳ ሰው እያሰበች " ነይ በይ ምግብ እንብላ "

………

ከራሴ በጣም የምወደው ነገር ማንኛውንም የሰዎች ንግግር እንደተራ ወይም እንደቀልድ አልመለከታቸውም ፣ የደረሰኝን ቁጣም ፣ ነቀፋም ፣ ሙገሳም ወይም ምክር ወዘተዎች በትክክል ውስጤ ውስጥ አመላልሳቸዋለው ፣ ምን አልባት ለራሴ ምፈልገውን ደስታ የሰጠሁት ለዚህ ይሆናል /ለራሴ ነው ያልኩት/

ይኽን ንግግሯን ለራሴ ብዬ ብዬው እጅግ ሳምንበት " እንግድያውስ ከአፌ ፍሬ መልካምን ምበላ ከሆነ ፣ ምርጡን ነገሮች ልመኝ ……… የነፍሴ ወረቀት ላይ ፃፍኩ ከቴዲ አፍሮ ጋር ከመዝፈን በላይ እጅግ ውብ ምኞቶች ያሉሽ ሴት ነሽ ይላል ጅማሪው ፣ አንደኛ አንቺ ምንም ጥሩ ድምፅ የሌለሽ ዘፈን በደረሰበት ማደርሺ ሴትዬ ነሽ ስለዚህ ዘፋኝ አትሆኚ ፣ በዛ ላይ ቴዲ አፍሮን አገኘሽም አላገኘሽም ህይወትሽ ውስጥ ሚጨምርም ሚቀንስም ነገር የለም ፣ እና ወይዘሪት ህይወትሽ ውስጥ ሚጨምር ነገር ተመኚ ለሱም በርትተሽ ትጊ ……… ባይሳካም እንኳን ጥሩ ተመኝተሽ እሱን ለማግኘት የሄድሽበት መንገድ ደስ የሚል ደስታ ይሰጥሻል ………


……… "አያቴ ተመኘው እኮ " አልኳት ከብዙ ቀናት በኃላ

"ምን ተመኘሽ "

ብዙ ነገር እስከነማብራርያው ዘረዘርኩላት ከዛ ሁሉ ውስጥ ግን አንዱ ላይ አቁማ አጥብቃ ጠየቀችኝ " የሰው ልጆች እንደ ልጆችሽ ማሳደግ ትፈልጊያለሽ ?"

"አዎ "

" አንቺ አትወልጂም ?"

"ብዙ ወላጅ አልባ ህፃናት አሉ እኮ ፣ ወላጅ የሌለው ሞልቶ ሌላ ወላጅ ሚፈልግ ማምጣት ግፍ ነው "

" ምኞትሽን አስፊ "

"ምን አርጊው "

"አንድን ጥሩ ተግባር ለማከናወን ሌላ ጥሩ ነገርን መተው አይገባም "

"እሺ ፣ ሁኔታዎች መልስ አላቸው "
:
:
ከዓመታት በኃላ አንዲት የጡት ካንሰር ታካሚ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ታቅፋው ማያት ህፃን ነበር

"ህፃኑ አንቺን ይመስላል " ይሉኛል የስራ ባልደረቦቼ

እኔም የልጅ ነገር አይሆንልኝም ባገኘሁት ቁጥር እስመዋለው ይዛው መምጣቷ ግን ምቾት አይሰጠኝም ገና አራስነቱን ያልጨረሰ ጨቅላ እላለው በውስጤ ፣

እራሷ የሆነ ቀን

"አባቱ የሁለት ወር እርጉዝ ሆኜ ነው የሞተው፣ሁለታችንም በማደጎ ነው ያደግነው ቤተሰብ የለንም ፣ማርገዜ አደጋለው ተብዬ ነበር እራስ ወዳድነት መሆኑን ባውቅም ለባለቤቴ ቤተሰብ ልሰጠው ፈለኩ ግን አምላኬ አልፈቀደም ………"

በሌላ ቀን አቅፌ እየሳምኩት

"አንቺን ይመስላል ፣ ብሞት እናቱ ትሆኚያለሽ ?"………
*
*
*

…………እናት ሆንኩ !

@tiztawe ………/#


" የሁላችንም እቅፍ ውስጥ ' ያ ዘመን ' የምንለው  ዝምተኛ ጊዜ አለ ……! "

tizta/@tiztawe


🦋……………


ሚጨንቀኝ ትላንት ፣ ምፈራው ነገ የለኝም ………እስከነ ስህተቴ ትላንትን ወደዋለው ፣ ጥፋቴ ላይ የመቆየት ትግስት የለኝም አንድ አንዴ ጥፋት መሆኑን አውቄው ሳይሆን እንዲው ይሰለቸኝና ተወዋለው ከዛን  ካለፈ በኃላ ፈገግ እልና ለካ ስሳሳት ነበር የምልባቸው ጊዜያቶች ብዙ አሉ።

ለራሴ ስነግረው ያደኩት ነገር "ለተፈጠረ ነገር ባርያ አደለሽም " ለዚህም ምንም ነገር አይጨንቀኝም ፣ ህይወቴ ውስጥ ለሚመጡም ለሚሄዱም ነገሮች ግድ ኖሮኝ አያውቅም ፣ እስካሉ የእውነት ወዳቸዋለው  ሲሄዱ እንደነበሩኝ እንኳን ለማስታወስ ዘነጋቸዋለው …… ዝናቡ ቢያበሰብሰኝም ማንም ጥላ ይዞ እንዲመጣልኝ ጠብቄም ፈልጌም አላውቅም ።

አሁን ግን ፍርሃት ሲወረኝ ይሰማኛል ፣ መቶ እንደ ልጅ አቅፎ ውስጡ እንዲሸሽገኝ እመኛለው ……" በቃ አልሄድኩም ፣ ትቼሽ አልሄድም "  ሚለውን ቃል ናፍቃለው ………

አብረን ሆነን የምጠጣው ቡና  ሚጣፍጠኝ እኔ ጎበዝ ቡና አፊይ ስለሆንኩ እንጂ ከሱ ጋር ስለምጠጣው አይመስለኝም ነበር ፣ ቀልዶ ስስቅ ቀልድ አዋቂ ስለሆነ እንጂ እሱ ስላወራው እንደሆነ አልገባኝም ፣ሰላም ሚተነፍሰው ማንነቱን የማደንቀው ሚደነቅ ሆኖብኝ እንጂ ልቤን በተለየ እንደሚያንጫጫት አልተረዳውም

ትሁት ነፍሱ ውብ ልቡን ያዞርብኛል ብዬ ስለማላስብ ግድ የለሽንነቴን አላስተዋልኩትም ፣ ምን አልባትም ለሱ ሚሰማኝ ስሜት የፍቅር አይመስለኝም ነበር ፣ የህይወቴን ስም ባጣው ሰዓት አብሮኝ ስለነበር በየእርምጃዎቼ ስለተከተለኝ ውለታው የያዘኝ መስሎኝ  ነበር………

ግን ከዛች ጠዋት በኃላ ፈርቼ ማላውቀው ፍርሃት አለት ነፍሴን ሲርዳት ተሰማኝ ………

"ልሄድ ነው ካናዳ "

"ለስንት ጊዜ "

" አመት ወይም አመታት "

"እህ ፣ እዚህ ያለው ስራስ "

" አንቺ ስላለሽ እንጂ ፣ ቤተሰቤም ስራዬም እኮ እዛ ነው "

"ወደ ጁሩ አርሴማ ልታሰራ ስላሰብከው ጤናጣብያስ ?"

ዝም አለኝ

"እውነት ልትሄድ ነው " አልኩት ቃላቶቼን እያንቀጠቀትኩ……

" ስለምታፈቅሪው አይደል ሲመለስም የተቀበልሽው ፣ እርግጠኛ አልነበርሽ ስለሱ ስትነግሪኝ ፣ ታድያ ምን እሰራለው እዚህ ደስታሽ እሱ ከሆነ ደስታሽ ነው ደስታዬ ፣ " ምንም አልመለስኩለትም አይኖቼ በጭንቀት ካዘጋጀው ሻንጣ ላይ ተክዘዋል ………

"አፈቅርሻለው ፣ ግን ከልብሽ ጋር ታግዬ አይደለም በንፅፅር የኔ እድትሆኚ አልፈልግም ፣ ወደምትፈልጊው አቅጣጫ ብረሪልኝ "

" ባረኩት ነገር አልፀፀትም ፣ እሱን በማፍቀሬ ፣ ሲመጣም በማውራቴ ……… የትኛውም ነገር አይፀፅተኝም ፣ " አልኩት

አዎ አልፀፀትም "ባላወራው እንዴት አውቅ ነበር አንተን እንደምወድህ "ለራሴ ነው ያልኩት

"ሰላም ግባ " ቦርሳዬን ከአልጋው ላይ አንስቼ ወደመውጫው ተሳብኩ ፣

"አሚን "

እንደቆረጠ ገባኝ ………

ይሂድ ግን ተመልሶ ይመጣ ይሁን ?… ለመጀመርያ ጊዜ ፍርሃት 'ነገዬን ' ሲኮረኩመው ተሰማኝ ………

ትዝታ /@tiztawe


መሄድ ……ቻዎ መባል …መሸኘት … ደስ ይላል።… መንገድ እኮ ያምራል … መሄድ ደሞ መምጣት ከዛን መሄድ ……… ህይወት በመመላለስ ውስጥ ታምረኛለች !

ትዝታ /@tiztawe


"ንጋቴ ሲተነፍስ ይሰማኛል ፣ ያኔ ጨለማዬን አውልቄ ጠዋቴን ነፍሴ ላይ አርከፈክፋለው "

tizta/@tiztawe




💫…………

የሚስብ መልክ እማ በሀገሩ ሞልትል
ለኔ እንዳቺ ቆንጆ ማግኘት ተስኖኛል
ስፈልግ ያጣሁሽ አንቺን አይደለም ወይ
ሴቱ እማ ሞልቶቷል ምድሩ ሴት አይደል ወይ....

..  .እኔ.....

ናት አይደለች እያልኩ በፍቅር ሚዛን ቀመር
ነብስ ካወኩ ወዲህ ስጠብቅሽ ነበር

ግና

አገሩን ሳካልል ስወጣ ስወርደው
አይን አይከለከል ስት አይነቷን አየው።

ምን ያህሉን ግዜ እጠብቅሻለው
ለኔ ውብነትሽ ዛሬም ልቤ ላይ ነው
የት ትሆኚ ይሆን የቱጋ ነው ያለሽ
አንቺን እየፈለኩ ዝምብዬ ስባክን  ዝም ብለሽ ታያለሽ

ኧረ *3

እረ ተይ ጡር አለው
እዚህ ጋር ነኝ በይኝ ስከንፍ እመጣለው


ሳላገኝሽ ብሞት እኔ የለሁበት
ፀፀትሽ ከባድ ነው እንዳትሞችበት !!

/✍ግሩም ብእር.
ለ nuYeAsmck !!/


💫………………*

....ሁልጊዜ ከምተኛበት ሶፋዬ ላይ ተኝቻለሁ።ቀኑን ሁሉ...ከወዲያ ወዲህ ስኳትን ስለዋልኩ  በጣም ደክሞኛል....ከእንቅልፌ የነቃውትም ሰፈራችን ያለው የዘሀራ መስጂድ የ10:00 ሰዐት አዛን ጥሪ ስሰማ ነበር
አይገርምም....እንደ ሰው በስልኬ ማንቂያ (አለርም) ቀጥሬ አለውቅም  ሁሌም በፈለኩት ሰዐት ቀንም ሆነ ለሊት የሚያነቃኝ ይህ የመስጂዳችን አዛን ነው ።
......ዛሬም በዚህ አዛን ነቃሁ...ለምን እንደሆነ እንጃ የሆነ የመደበት ስሜት ተሰማኝና ከሶፋው የመውረድ ስሜቴ ብን ብሎ ጠፋ....ለወትሮው ከጓደኛዬ ጋር ለመገናኘት ተቃጥረናል....እንደምትጠብቀኝ ባውቅም የመሄድ ፍላጎት ከየት ይምጣ...
ይባስ ብዬ ተመቻችቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ....አይኖቼንም ቀጥታ በቤቱ ማዕዘን ላይ ወደ ተሰቀለው ስዕለ አድህኖ ተከልኳቸው.....
ክርስቶስ በቀኝ እጁ ይመስለኛል ባያረጅም ከዘራ ይዟል....ቀይና የተንዘረፈፈ ረጅም ፎጣ ለብሷል...ከስርም ከፎጣው አልፎ የወጣ ወይም በጣም የረዘመ የደመና ከለር ያለው ቀሚሱ እስከ እግሮቹ ጣቶች ደርሷል።ከቆመበት ቤት በር አፍ ላይ አንድ የውሃ መቅጃ ገንቦ ተቀምጧል...ጊቢው በለምለም ሳር የተሞላ ነው።

....በራፉ ላይከፈት የተጠረቀመ ይመስላል....ክርስቶስ ግን ያለ መታከት....በብሩህ ተስፋ ያንኳኳል
ቤቱ ውስጥ ግን ማን ይሆን ያለው??...ምን አይነትስ ፀባይ ይኖረው ይሆን??
ገዳይ ወይስ ቀማኛ፤ዘማዊ ወይስ ሀይማኖተኛ ፤ዘረኛ ወይንስ እንግዳ ተቀባይ....ምን አይነት ሰው ይሆን
ታድሎ....አልኩ ለራሴው
....መች ይሆን የኔን በር የሚያንኳኳው...መቼ ይሆን ተራ የሚደርሰኝ..."አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፤ለምኑ ታገኙማላችሁ"ያለው ክርስቶስ...የኔን ማንኳኳት ሳይጠብቅ መቾ ይሆን ደጅአፌን የሚያንኳኳው...አይኖቼ ከስዕለ አድህኖው ላይ አልተነሱም
የክርስቶስን የፊቱን ገፅ አተኩሬ ተመለከትኩት .....ለብዙ ዘመናት ሲያንኳኳ የቆየ መሰለኝ....ግን ደግሞ ከማንኳኳት ብዛት ያልሰለቸ...ምን አልባት እኮ የኔኑን በር ይሆናል የሚያንኳኳው....አልሰማሁት ይሆን????
  የልብ ምቴ ፍጥነቷ ሲጨምር ታወቀኝ...ድንገትም ከየት መጣ የሚሉት የደስታ ስሜት ወረረኝ...
ወዲያው ከሶፋው ብድግ ብዬ ወረድኩ ና ነጠላዬን ከሰነበተችበት ቁምሳጥን አውጥቼ.....ወደ ቤተ ክርስቲያን ከነፍኩ....የልቤን ደጃፍ ልከፍት....

     /ትንሳኤ ዘ ኢትኤል /  @tiztawe


ብዙ ሰዎች ስንብት አይወዱም ፣ በመሄዳቸው ውስጥ ያለው ዝምታን ይንከባከቡታል………

ትዝታ /@tiztawe #ፍትሕ ለሴት ልጆች !


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ህክምና ሚጣፍጠኝ ለዚህ ነው ፣ ተፈኩር ታረጋላቹ ……… የአምላክን ጥበብ ታስተነትናላቹ………

ኡፍፍ ❤️


🦋💚…………


"ይሆናል ……! " "አይ አይሆንም! "ይደረጋል……" "አይ አይደረግም "…………

"እያልሽ ነው እራስሽን ያሳደግሽው ፣እናም ባንቺ ደስተኛ ነኝ ፣ ኮራብሻለው "…… ይኽን ሲለኝ ሊሰናበተኝ አርባ አምስት ቀናት ይቀሩት ነበር………

"አሁን እረፍት ይሰማኛል ፣ የምትፈልጊውን ታውቂያለሽ ፣ ለመኖር ዝግጁ ነሽ ፣ ያለኔ ፣ ያለማንም ………"

ተሳስቶዋል ያለሱ ለመኖር ዝግጁ አልነበርኩም ፣ ደስታውን በማየት ውስጥ ነው እራሴ ላይ የሰራሁት ፣ ያበበውን መሰራት አይቶ እየተደሰተ ማይኖርልኝ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ምኖረው ?……ምክንያቴ እሱ ነው ……እንደማስበው ፣ እንደሚያስበው ጠንካራ አደለውም …… ላሳካ ስላሰብኩት ነገር ነግሬው ፣ ትችያለሽ በርቺ ብሎ ሳይመልስልኝ በምን ተስፋ እሮጣለው ?…… አዎ ያለማንም መኖር እችላለው ፣ ያለሱ ግን እንዴት ኖራለው ?

እያወራልኝ ማስበው ይኼን ነበር

" ምኞቴ አንቺ ለኔ እንደ ሺ እድቶኚ ሳይሆን ፣ አንቺ ለራስሽ ሺ እንድትሆኚ ነበር…… ከህይወት ምትፈልጊውን እንድታውቂ ፣ እንደ ልጅነትትሽ ጨለማን ብትፈሪም ከጨለማው ለመውጣት ግን እያለቀሽ ሰው ምትጠሪ ሳይሆን እራስሽ ለጨለማው መውጫ መፍትሔ እንድታበጂ ነበር ፍላጎቴ ፣ ያን አይቻለው ……በቃ !"


……ከጨለማው መውጣት ምፈልገው እኮ አንተ ስላለክ ነው ፣ አንተን ለማየት ፣ ስታረጅ ፣ ከልጅ ልጆችህ ጋር ስትጫወት " ኦ ሚገርም አያት እኮ ነው ያለን " ሲሉ ለመስማት ፣ እናታቹ እኮ እያልክ ልጅነቴን ስታወራላቸው ፊትክ ላይ ያለውን ደስታ ለማየት ነው ከድቅድቁ ሚያስመልጡኝን ብዙ ብልሃቶችን የገነባሁት ፣ እንዳልወድቅ  አቋቋሜን ያሳመርኩት ከኔ ቀጥሎ ስላለው ስምክ ስላለኝ ክብር ነው ……… ትላለች ነፍሴ ለራሷ ………ግን ንግግሩን በመልሷ አታቋርጠውም ፤ ያለሱ ጠንካራ መሆኔ ደስታ ከሰጠው ለምን ያን ደስታ ነጥቀዋለው ?
:
:
. ኖሮ ነው ያኖረኝ ፣ እጆቹ እየኮተኮቱኝ ሲሻክሩ ፣ "ለኔ ነው" ይለኛል ላንቺ ነው ብሎ ውለታ እደሆነ ነግሮኝ አያውቅም. .ለሚፈቀር ነፍስ የሚሰራ ሁሉ ለራስ እደሆነ እያስተማረኝ ነበር  . . ታላቅ ዓለም ነው !!

. . .ቃላቶቹ  ከአንደበቱ ሲወጡ የነፍሴ አክናፋት ዙሪያዩን ያቅፉታል ፣ ቃሉ የተስፋ ዜማ ታዜማለች ፣ በአዲስ ብርታት ኃይልም ትሞላለች ። ሁሉን መሆን ይችላል፣ ሁሉንም ማስሆን ይችላል. .

ከቅርፊቴ በብልሃት ተፈልፍዬ ጫጩነቴን በማስተዋል እዳልፍ መንገድም ሂወትም ሆኖኛል ………

ነፍሴ አደገኛ ተናዳፊ እባብ ከማይደርስባት የመንፈስ ከፍታ ላይ እድትሆን ጥበባዊ ስሪቱ አለበት………

ይኽ ሰው ነው ህይወቴ ላይ የጎደለው ……… ይኽን  አባት ነው  ነፍሴ ያጣቹ ………ይኽን መጠርያ  ነው ሞት የነጠቀባት ………
:
:
እንዳልኩት አበቃልኝ ብዬ ነበር ፣ ግን እሱ እንዳለው ቆምኩ ፣ ሰሪ ከስሪቱ በላይ አዋቂ ነውና ……"ትቆምያለሽ !" አለኝ ቆምኩ

አንዳንዴ ባይኖሩም ፣ ለመኖር ግን አዲስ ሃይል የሚሆኗቹ ታላቅ ነፍሶች አሉ ……… አባቴ !

/ትዝታ / @tiztawe

#ፍትሕ ለሴት ልጆች


"የእኔንትክክለኛ የፍቅር ታሪኬን የኖርኩበት የተሳስተህ ሰው ነህ ፣ እና በስህተት ወደ ህይወትህ የገባሁት ትክክለኛ ሰው ነኝ!"

/የአረብ - ቅኔ ……/@tizatawe/




ትንሽ ነፍስ ፣ ቆንጆ ልብ በነበረኝ ጊዜ ያኔ ትንጥ ሆኜ

"ምን መሆን ትፈልጊያለሽ ስታድጊ " ሲሉኝ

"እንደ አያቴ ፣ እንደ እናቴ ፣ እንደ አባቴ ……… ማደግ ፣ ትልቅ መሆን " እላቸው ነበር

ሳድግ የማደግ ክፍት ውብ ትንሽየዋን ልቤ እንደሚያሰፋብኝ አውቄ ኖሮ ቢሆን

"ማደግ አልፈልግም እዚሁ እንዲው ሆኜ ልቅር" እላቸው  ነበር……


ትዝታ /@tiztawe #ፍትሕ ለሴት ልጆች !


ሲዘንብ  ሁሌም የሚሰማኝ አንድ ድምፅ አለ ፣  ደርቆ እየረጠበ ያለ ያላስገባሁት  ልብስ  ለቅሶ
:
:ያኔ ነው መልፈስፈሴም ፣ መጠንከሬም እኩል ሚሰማኝ …………


ምን አልባት ከፀሃይ በፊት ያለው የዝናብ ውድቀት ይጣፍጠኝ ይሆናል ……

ትዝታ /@tiztawe




*ስምንቱ በአባታቸዉ የተደፈሩ (ከ9 እስከ 16 እድሜ ዉስጥእያሉ) አንድዋ ወልዳለች
*ስድስቱ አብረዋቸዉ በሚኖሩ ቤተዘመድ የተደፈሩ( ከ 10 እስከ 14 እድሜ ውስጥ እያሉ)
*ዘጠኙ በአጎትና በቅርብ የአክስት ልጅ የተደፈሩ ( ከ 8 አመት እስከ 16 አመት ድረስ አንዳንዶቹ ለአመታት ነዉ የተደፈሩት) አንድዋ ወልዳለች።
*አምስቱ በጎረቤት ሰዉ (ከ 7 አመት እስከ 13 አመት ድረስ)
*ዘጠኙ  በእንጀራ አባት (ከ 8 እስከ 15 አመት ድረስ ) ሶስቱ ከእንጀራ አባታቸዉ ወልደዋል ።
*ሰባቱ በወንድማቸዉ (ከ 10 አመት እስከ 14 አመት ድረስ)
ሁለቱ ወልደዋል ከወንድማቸዉ ።
*ሶስቱ በወንድም ጎደኛ (ከ 12 አመት እስከ 14 አመት ድረስ )
*አንድዋ በሰፈርዋ ሌጅ (በ13 አመትዋ)

ከሀምሳዎቹ ስምንቱ ልጅ ወልደዋል ። ዲቃላ አመጣሽብን ተብለዉ ተሰድበዋል ፣ተሸማቀዋል አንዳንዶቹ ቤተሰብ አታሰድቢ ተብለዉ ወደ ገጠር ዘመዶቻቸው ጋር ተልከዋል ። ዲቃላ የተባለዉ ልጅ አንዳንዱ አባቱም አያቱም ነዉ፣ አንዳንዱ አባቱም አጎቱም ነዉ ።

ለመሆኑ ማኅበረሰባችን ችግሩን ተረድቶታል ወይ? የስፋቱን ያክልስ ይታወቃል ወይ? እነዚህ ሃምሳዎቹ ሴቶች ከአዲስ አበባ ነዉ የመጡት አንድዋ በቀር! አስቡት የችግሩ ግንዛቤ ዝቅተኛ በሆነባቸው በየመለስተኛ ከተሞች እና በየገጠሩ ያሉት እህቶቻችን እንዴት እየተጋፈጡት ይሆን? እንደምታውስ የት ድረስ ሊሄድ እንሚችል ማን ያወቀዋል? የአንድ ስሜቱን መግዛት ያቀተው እና አውሬነት የተጠናወተው የአምስት ደቂቃ እኩይ እርካታ በአንዲት ሴት ህይወት ላይ ትቶት የሚያልፈው የህይወት ጠባሳ ምን ያክል የከፋ ሊሆን ይችላል? አስቡት፤ የስነልቦና ምሁራን ችግሩ በሴቷ ህይወት ውስጥ ዘላቂ የሆነ የስብዕና ስብራት እንደሚፈጥር ደጋግመው ያስቀምጡት ጉዳይ ነው፤

ከተገዶ መደፈር የተረፈች ሴትስ ምን አይነት ህይወት ይተርፍላታል? ይህንን የህይወት ጠባሳ ይዛ ስትኖር ማህበራዊ ህይወቷ ምን ይሆን? ለቤተሰቦቿ፣ ለቤተዘመዶቿ፣ ለልጆቿ እና ለባሏ ምን ያክል ስሜታዊ አብሮነት (emotionally available) ኖሯት ሙሉ ፍቅር ልስተሰጣቸው ትችላለች? ምን ያክል ለልጆቿ በየዕድገት ደረጃቸው ተፈላጊዋን እናት ሆና ልትገኝላቸው ትችላለች? ምን ያክልስ ስሜታቸውን ተረድታ በፍቅር እና በእንክብካቤ ልታሳድጋቸው ትችላለች? እንደ ቁጣ፣ ቂመኛነት፣ ህቡዕ እና የማትገልጸው ትካዜ፣ አይነት አሉታዊ ስሜቶች ጥንውትስ ምን ያክል ህይወቷን ይመርዘው ይሆን? ለባሏስ ምን አይነት ሚስት ልትሆን ትችላለች? ንጹህ ፍቅር መስጠት ትችል ይሆን? ቤታቸው የቀዝቃዛ ፍቅር እና የፍቺ ቀኑን የሚጠብቅ የጸብ እና የጭቅጭቅ ጎጆ ይሆን ይሆን? ባልስ ችግሯን ሊረዳላት እንዴት ይችላል? የልጆቿን ስብዕናስ እንዴት በፍቅር ልታንጽ እና ልትገነባ ትችላለች?

በየቤቱ እንዲህ አይነት ሴት ተቀምጣስ ምን አይነት ማኅበረሰብ ነው መፍጠር የሚቻለው? ይህ ችግር ማኅበረሰባዊ እና ሃገራዊ እንደምታውስ ምን ሊሆን ይችላል?

ጉዳዩን አንስተን ብንወያይበትስ ምን አይነት የተዘጋ ቤት ነው ከፍተን የምንገባው? ስንት ጉድ ልናገኝ እንችላለን? ከየትስ ነው የምንጀምረው? ወገን ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው እኮ! ተረድተነው ይሆን? እናውቀው ይሆን?

ወደ እራሴ ስመለስ እንዴት እድለኛ ነኝ እንደዚህ አይነት ፃታዊ ትንኮሳም ሆነ ሌላ ያልተገባ ነገር ስላልደረሰብኝ 🙏
ለአባቴ ፣ወንድሜ፣አጎቶቼን ማለት የምፈልገዉ እግዚአብሄር  ያክብራችሁ የቤተሰብ ፍቅርና እኔን protect ስላደረጋችሁ 🙏ነፍሴን አድናችሁልኛል ።

ተገዶ መደፈር፣ እንግልት፣ እርግዝና ፣ ለብቻዋ ልጅ ማሳደግ ፣ ተስፋ የሚስቆርጡ ቃላት ፣ የማዋረድ ተግባር ፣መታለል 😕
ነገር ግን ይህን ሁሉ ተቋማተቋቁመው ቆመዋል 💙
Women Are The Strongest Creatures Alive 💜
ፍትህ የት ይሆን ያለዉ?

"መልካም መሥራትን ተማሩ፥ ፍርድን ፈልጉ፥ የተገፋውን አድኑ፥ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ"
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 17


ሩት ሰለሞን


#ተደፍረሽ ታውቅያለሽ ወይ?



ማኅበረሰባዊ ሱሳይድ

እንደ እናት፣እንደሴት ፣ እንደ እህት ያለፉት ሳምንታት ለእኔ ቀላል አልነበሩም። የሴት ልጅ እና የህፃናት ህይወት በኢትዮጵያ ዉስጥ የሲኦል ያህል መራራ ነዉ ። ለዛዉም በሚወዱት፣ በሚያምኑት ፣ በሚያከብሩት የቅርብ ሰዉ ፣የቤተሰብ አባል ነዉ መደፈር የሚደርስባቸዉ ። በአባት፣ በወንድም፣በአጎት፣ በእንጀራ አባት፣ በቤተሰብ ጎደኛ እና በቅርብ ዘመድ! ከዛም ተርፎ ለማን ይነግሩታል  የባህል ተፅእኖዉ ፣ ፍራቻዉ፣ ዛቻዉ እና የሚሰጠዉ ስም ሌላ ጠባሳ ነዉ የሚተወዉ ።

የሰው ልጅ ጭካኔ በአንዲት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የ7 ዓመት ብላቴና ሄቨን ላይ መፈጸሙን ከሰማሁ በኋላ እረፍት አጣሁ፤ በሰላም ልተኛ አልቻልኩም፤ ያላዋረሁት ሰው የለም፤ ተደጋገመ በዛ፤ ያስጨንቀኝ ጀመር፤ ነፍሴ እረፍት አጣች፤ ከማገኘው ወገኔ ጋር ሁሉ ከዚህ ሌላ ርዕስ ማውራት አቃተኝ፤ ዕንባዎቼ ያለምንም ስሜታዊ መነካት በድንገት ይፈሳሉ፤ ራሷን መከላከል እና መጠበቅ የማትችል፣ ክፉና ደጉን የማታውቅ፣ የምታገኘው ሁሉ ትልቅ ሰው ደግ እና አባት የሚመስላት፤ ያችን ቀን የተደገሰላት ክፋት እንደነበረ አላወቀችም፤ ልጅ አደለች፤ አሳዛኙ እና ሃገራዊ ውርደትን ያከናነበው ድርጊት ተፈጸመባት፡፡

ማህበራዊ ሚዲያው ተቀባበለው፤ በከፈትኩና ባየሁ ቁጥር በተለያዩ ፎቶዎቿ ታሪኳ የሚነገርላት ብላቴና አንጀቴን አላወሰችው፤ ቀኗ እየቆየ ሲሄድ እንኳን ነፍሴ ከተያዘችባቸው ጥያቄዎች ልታርፍ አልቻለችም፤ የብዙ ኢትዮጵያውያን ህፃናትና እህቶቼ ሰቆቃ እንደሆነ የታወቀ ነው፤ በተለይ ደግሞ በጦርነት ድባብ ስር ሆነው ቀናቸውን ለሚገፉ እህቶቻችን አሰብኩ፤ አገራችንን በጭካኔ ዳመና ስር ያለች የእህቶቻችን የሰቆቃ ምድር ሆና ታየችኝ፤ የተለያዩ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፤ እንዴት ይህን ማኅበራዊ ጋኔል ማስቆም ይቻላል? እንዴት በደለኞቹን መቅጣት ይቻላል? እንዴትስ ተበዳዮቹን መካስ እና ወደ ሙሉ ሰውነት መመለስ ይቻላል? ብዙ ብዙ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሳሉ፤ የችግሩን ጥልቀት እና ስፋት ማጥናት ፈለኩኝ፤ ነፍሴ በሄቨንና በሄቨኖች ጩኸት ተይዛለች፤ ጆሮዎቼ የነገ እና የከነገ ወዲያ ሰለባዎችን ጩኸት እና ቃተቶ እየሰማች አስቸገረችኝ፤

ያኔ ነው ችግሩን በቀላል መንገድ መዳሰስ እና መረዳት፣ ቆይቼ ደግሞ ጊዜና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ጥሩ ጥናት ማካሄድ የሚመኘው የልቤ መሻት ፈነዳ እና ቅድሚያ ሰጥቼው መጠናት አለበት ብዬ ወሰንኩ፤ ብዙ የጥናት ልምድ የለኝም፤ ነገር ግን ጥናት ማለት ጥያቄ ማንሳት እና መልስ መፈለግ እንደሆነ ይገባኛል፤ የተወሳሰበ ሳይንስ ሊሆን ቢችልም ቀለል ባለ መልኩ ልሰራው እንደምችል አሰብኩ፤ ብዙ ጥያቄዎች አወጣሁ አወረድኩ፤ በመጨረሻ ግን አንዲት ቀላል ጥያቄ መረጥኩ፤ “እህቴ ሆይ ተደፍረሽ ታውቂያለሽ ወይ?” የምትል ባለ አምስት ቃላት ጥያቄ ነች፤ ፍጹም ወዳልገመትኩት እና ወዳላሰብኩት የጨለማ ዋሻ እና ብዙዎች በዝምታ ወደሚጮሁበት ጽልመት ያመራችኝ ጥያቄ፤

አትጠይቁ እየተባልን ባደግንበት ማኅበረሰብ ውስጥ እንዲህ አይነቱን ከትላንት እና መራራ ትዝታ ጋር የሚያላጋ ጥያቄ ማንሳት ከባድ ነው፤ ደግሞስ ማን ነች የህይወቷን ገመና እና የተቀቀበረ ቁስል ከፍታ ማውራት የምትፈልገው? ማንስ ነች ይህን ጥያቄ እንደ “ቁርስ ትበያለሽ” አይነት ጥያቄ በቀላሉ እና ወደ አእምሮዋ ጓዳ ዘው ብላ ከዘመናት በፊት ወይም በቅርብ የተዘጋን በር ከፍታ የምታሳየኝ? ፈራሁ፤ ድፍረት ይሆንብኝ ይሆን? ግን ደግሞ ነውርን ፈርቼ የሃገሬን ሴቶች መከራና እና ቁስል እንዴት እያየሁ ዝም እላለሁ፤ ከብላቴናዋ ሄቨን የበለጠ ምን ሊደርስብኝ ይችላል?  ኃላፊነት የለብንም ወይ?

ለማንኛውም ያለ የሌለ ድፍረቴን አሰባስቤ በቅርበት የማውቃቸውን አምስት ሴቶች መረጥኩና ስማቸውን ጻፍኩኝ፤ ስልካቸውን አወጣሁ፤ ማስታወሻ ደብተርም ያዝኩ፤ ስፈራ ስቸር ሰ….. ጋር ደወልኩ፤ የሄቨን ጉዳይ ሰሞኑን ያወራነው ወቅታዊ እና አስደንጋጭ ክስተት ስለነበረ ከሁለታችንም ህሊና ያልጠፋ እና በየዕለቱ ከሚለቀቁት ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች እያነሳን ማውራት ቀጠልን፤ ሁለታችንም እየተነፋረቅን ነበር፤ እንደምንም ወደ መረጋጋት ስንመለስ ስፈራ ስቸር ያቺን ባለ አንድ አረፍተነገር ጥያቄ በትህትና እና በጥንቃቄ አነሳሁላት፤

“አንቺ ግን እንደው አገራችን ስትኖሪ ሳትፈልጊና ሳታስቢው እንዲህ አይነት ክስተት ያጋጠማት ጓደኛ ታውቂያለሽ?” አልኩ ቢቸግረኝ አቅጣጫዬን ወደ ሌላ ሰው ቀይሬ፤ ስልኩ ጸጥ አለ፤ የተቋረጠም መሰለኝ፤ “ወይኔ ጉዴ” አልኩኝ በልቤ፤ የሳግ ድምጽ ሰማሁ፤ ከሃገር ከወጣች ብዙ ዓመት አስቆጥራለች፤

“ሁሉም ጓደኞቼ ተደፍረዋል፤ እኔም አላመለጥኩም፤ ምን አይነት ማኅበረሰብ ውስጥ እንደኖርን፤” አለችና ለቅሶዋን ቀጠለችው፤ ደነገጥኩኝ፤ አንዳንዶቹን ጓደኞቿን አውቃቸዋለሁና እነሱን መገመት አቃተኝ፤ ግን ጓደኛዬ እዛ ላይ አላቆመችም፤ እሷም ራሷ የደረሰባትን ነገረችኝ፤ ለዛውም በቅርብ ቤተሰብ ዘመድ፤ ዝርዝሩን ለመጻፍ አቅምም ፈቃደኛነቱም የለኝም፤

ቆየሁና ሌላዋ ጋር ደወልኩ፤ ከዛም ሌላዋ ጋር ከዛም ሌላዋ ጋር፤ አምስቱም ጓደኞቼ ለማንም ነግረውት የማያውቁትን የህይወታቸውን ጥቁር ጠባሳ ከፍተው ቁስላቸውን አሳዩኝ፤ በጣም ደነገጥኩ፤ ሌሎች አምስት ጓደኞቼን ስም ጻፍኩ፤ ቁጣዬ እየጨመረ ሄደ፤ ሃዘኔም፤ ቁጣዬና ሃዘኔ እየተደበላለቁ ሃሳቤን መሰብሰብ አቃተኝ፤ ስልኩን አቁሜ ትንሽ መረጋጋት እና ማሰብ ፈለኩኝ፤

-----ከዕረፍት መልስ------ 

ከረጅም ዕረፍት በኋላ ስልኩን እና ማስታወሻ ደብተሬን አነሳሁ፤ ደወልኩ፣ ትንሽ አወራን፤ እራሷ ስለሰሞኑ አጀንዳ አነሳች፤ ጊዜ ሳትሰጠኝ የሷንም ሳግ ሰማሁት፤ ተያይዘን አነባን፤ ወደ ልባችን ስንመለስ ጥያቄውን አነሳሁላት፤ “እህቴ ሆይ አንቺስ ተደፍረሽ ታውቂያለሽ ወይ?” እሷም ጸጥ ብላ ቆየች፤ ሳጓን ሰበሰበችና “አዎ” አለችኝ፤ ዝርዝሩ ለህትመት የሚመች አይደለምና ልተወው፤ ግን ሌላ አስለቃሽ ታሪክ ነው፤ በጣም ልብ የሚሰብር ።

እንደቀላል የጀመርኩት ባለ አንድ ጥያቄ ጥናት ?ሳምንቱን ተቆጣጥሮኝ የሰነበተው ሃምሳ የሃገሬ ሴቶች ጋር አስደወለኝ፤ እያንዳንዱ ስልክ ቀላል ሂደት አልነበረም፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ከሃምሳዎቹ ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማት ያመለጠችው አንዲት ሴት ብቻ ነች፤ አዎ አንዲት ሴት ብቻ፤ ሳምንቴን ከባድና የስቃይ አደረገው፤ ከዚህ በኋላ ሌሎች ሴቶችን መጠየቅ ፈራሁ ፣ ከእያንዳንድዋ ሴት በስተጀርባ ያልተነገረ ፣ያልታከመ፣በየጊዜዉ የሚያመረቅዝ ህመም አለ።

አብዛኞቹ ማለት ይቻላል በለቅሶ እና ሳግ የታጀቡ ናቸው፤ እኛ በተለያየ ጊዜ ምናልባትም ደህና ይባሉ በነበሩት ዘመናት ከሃገር ወጥተን እዚህ ውጭ አገር ያለነው ኢትዮጵያውያን ሴቶች ይሄን ያክል የምናወራው ነገር ካለን፣ አገራችን ላይ በዚህ በከፋ ጊዜ ያሉት እህቶች ምን ያክል እየተሰቃዩ ይሆን? 

የሀምሳዎቹ ሴቶች ታሪክ
*ሁለቱ በማያዉቁት ሰዉ የተደፈሩ (አንደኛዋ በ 12 አመትዋ አንደኛዋ በ15 አመትዋ ) አንድዋ ወልዳለች


🦋……………

ዝምታውና ግድየለሽነቱ ነገሩን ምን ያኽል እንደተለማመድነው ያሳየናል………

ኢትዮጵያ ሴት ልጆች ከሚደፈሩባት የዓለም ሃገራት ማሃል አስር ውስጥ አለችበት ……… ስሰማ አልገረመኝም ቅዱስ ሃገር ትባላለች እንጂ እንዳልሆነች ቀድሜ ካወኩ ቆይቻለው ………

የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ስለህጉ መሻሻል ተሰብስበን እያወራን አንዷ ልጅ ህንድ ውስጥ በ 24 ሰዓት ውስጥ ከሰባ በላይ ሴቶች እንደሚደፈሩ እያወራችልን በመሃል ግቢ ውስጥ "ኦ ሃይማኖተኛ እኮ ነው" ሚባለው ልጅ ጣልቃ ይገባና

"ካላቸው የህዝብ ብዛት አንፃር ትንሽ ነው እንደውም " ብሎ ሲናገር ሌሎቹ ሲያማትቡና ሲደናገጡ አይቼ ነበር ፣ እኔ ግን አልገረመኝም

ሲጀምር እዝች ሃገር ላይ ያሉ የእምነት ተቋማት ስለእርስታቸውና ስለወንበራቸው ሲቆሙ በዘመኔ አይቻለው ነገር ግን እንደተቋም የአንዲት ሴት በደል ስለወለደው እንባ ትንፍሽ ሲሉ አልተመለከትኩም ……

' የሃይማኖት ሃገር ናት' ከምትባል ሃገር ውስጥ ብዙ ደፋሪዎችን ከልላና ተንከባክባ አወድሳ እንደምትኖር መስማት ባያስገርምም መታለል ግን ያማል !

ነፍሴን እርር ያረጋት ደሞ የህፃን ሔቨንን በአሰቃቂ ሁኔታ መደፈርና መገደል በአንድ በኩል ለፖለቲካዊ አጀንዳ መጠቀምያ አርገው የሁለት ጎራ የብሔር ፍጅት መፍጠሩን ሳይ፣ በሌላ በኩል ደሞ "አንዲት ዶሮ እንቁላል መውለዷን" እንኳን ሳይቀር ትልቅ ሽፋን የሚሰጡ ሆድ አደር ሚዲያዎች ሳይቀሩ ቀባ ቀባ አርገው ማለፋቸው ስመለከት ፣ በዚህ በኩል ደሞ አንድ አንዱ ለዮቱዮብ መሸቀያ በሌላው ስቃይ ሲቀልድ ሳይ ከአንዲት ሴት ህይወትና ክብር በላይ አንድ የበሰበሰ የሃጥያት ወንበር ዋጋ አለው የሚል መልዕክት አይቻለው ፣ ሃገሪቷ ምትመራው ፣ ስትመራ የነበረው ፣ በቀጣይም ምትመራው በእንደዚህ የወደቀ አስተሳሰብና ቁሽሽና በተሞሉ አመራራሮች ስለሆነ አስር ውስጥ መግባታችን አይግረማቹ !



እኔ ግን አሁንም ለታናናሾቼም ሆነ ፣ለታላላቆቼ ሴቶች ለራሴም ጭምር ይኼን እላለው ፣……………:
:

"የበቃሽና ጠንካራ ሴት ሁኚ በዙርያሽ ያሉትንም ሴቶች ጠብቂ ፣ ሃገር ምትቃናው ባንቺ ነው ፣ የራስሽ ፍርድና አቋም ይኑርሽ ፣ ሃጥያት እራስን መሆን ሳይሆን እራስሽን እንዳትሆኚ የሚጨቁኑ እጆች ላይ ነው ያለውና ያን እጅ ሰብረሽ ቁሚ !……… ምታፈቅሪውን፣ ምታገቢውን ምትመርጪበት ፣ ወንድ ልጅሽን ሴት ልጅሽን ምታሳድጊበት መንገደሽ የበሰለ ይሁን:( ስለደበደበሽ ፣ ስለሰደበሽ ፣ ስለቀና እያፈቀርሽ ሳይሆን መጥፍያ መንገድሽን እየቆፈረልሽ ነው እና ምርጫሽ ጤነኛና ሰላማዊ የፍቅር ምርጫ ይሁን : ስላፈቀርሽው ብቻ አታግቢው የሰውነት ስብዕናው ያልተጓደለና ለሰውነት ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን አረጋግጪ ፣) ጤነኛ ልጆች በመረጥሽው ጤነኛ ትዳር ላይ ይመሰረታል !  ጤነኛ ቤተሰብ ደሞ ጤነኛ ሃገር ይሰራል !
………… ምን ልልሽ ነው ቁልፉ በእጃችን ነው !


ምን አልባት ያን ፍትሕ አንድ ቀን ታመጪው ይሆናል በራስሽ ታላቅነት ውስጥ ፣ አሁንም ቢሆንም ግን በብዙ ጠላቶች ተከበሽ ቢሆንም ስለራስሽ መጮኽ እዳታቆሚ !! "



ፍትሕ !!!

ፍትሕ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍረው ህይወታቸውን ላጡ ሴቶች ፣ ህፃናት !

ፍትህ ተራቸውን ለሚጠብቁ በፍርሃት ለተደበቁ ሴቶች ፣ ህፃናት !

ፍትሕ ጓዳው የደበቃቸው እንባቸው ደም ሆኖ የስቃይ ድምፅ ለሚያሰሙ ሴቶች !

ፍትሕ !!


……………/

ካንተ ለመራቅ እጅግ ብዙ ቀናት ከራሴ ጋር ቃልኪዳን ገብቻለሁ ....አይገርምህም ወዳንተ አጥብቄ እቀርብ  የነበረው በነዛ በማልኩባቸው ቀናቶች ነበር
      በመርሳት ውስጥ አጥብቆ ማስታወስ እንደነበር አልገባኝም ነበር
   በመተው ውስጥ የተሸሸገ መፈለግ እንዳለም አልተገለጠልኝም
     ከልቤ ላስወጣህ ላርቅህ ልተውህ በማልኩ እለት ነው ለካ ጠቅልለህ ልቤ ውስጥ ግዛት የመሰረትከው
  አንዳን ሰዎች በረሳናቸው መጠን አብረውን አሉ
በተውናቸው ልክ አጥብቀው ይይዙናል

      /ትንሳኤ ዘ ኢትኤል/



:
:
:#……… ደፍሪን የሚፈለፍል ፣ ህግ ይውደም
………… ጠንካራና ማስተማርያ ቅጣት እንሻለን!!!

ፍትሕ !!

1k 0 10 1 16
Показано 20 последних публикаций.