💫………………*
....ሁልጊዜ ከምተኛበት ሶፋዬ ላይ ተኝቻለሁ።ቀኑን ሁሉ...ከወዲያ ወዲህ ስኳትን ስለዋልኩ በጣም ደክሞኛል....ከእንቅልፌ የነቃውትም ሰፈራችን ያለው የዘሀራ መስጂድ የ10:00 ሰዐት አዛን ጥሪ ስሰማ ነበር
አይገርምም....እንደ ሰው በስልኬ ማንቂያ (አለርም) ቀጥሬ አለውቅም ሁሌም በፈለኩት ሰዐት ቀንም ሆነ ለሊት የሚያነቃኝ ይህ የመስጂዳችን አዛን ነው ።
......ዛሬም በዚህ አዛን ነቃሁ...ለምን እንደሆነ እንጃ የሆነ የመደበት ስሜት ተሰማኝና ከሶፋው የመውረድ ስሜቴ ብን ብሎ ጠፋ....ለወትሮው ከጓደኛዬ ጋር ለመገናኘት ተቃጥረናል....እንደምትጠብቀኝ ባውቅም የመሄድ ፍላጎት ከየት ይምጣ...
ይባስ ብዬ ተመቻችቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ....አይኖቼንም ቀጥታ በቤቱ ማዕዘን ላይ ወደ ተሰቀለው ስዕለ አድህኖ ተከልኳቸው.....
ክርስቶስ በቀኝ እጁ ይመስለኛል ባያረጅም ከዘራ ይዟል....ቀይና የተንዘረፈፈ ረጅም ፎጣ ለብሷል...ከስርም ከፎጣው አልፎ የወጣ ወይም በጣም የረዘመ የደመና ከለር ያለው ቀሚሱ እስከ እግሮቹ ጣቶች ደርሷል።ከቆመበት ቤት በር አፍ ላይ አንድ የውሃ መቅጃ ገንቦ ተቀምጧል...ጊቢው በለምለም ሳር የተሞላ ነው።
....በራፉ ላይከፈት የተጠረቀመ ይመስላል....ክርስቶስ ግን ያለ መታከት....በብሩህ ተስፋ ያንኳኳል
ቤቱ ውስጥ ግን ማን ይሆን ያለው??...ምን አይነትስ ፀባይ ይኖረው ይሆን??
ገዳይ ወይስ ቀማኛ፤ዘማዊ ወይስ ሀይማኖተኛ ፤ዘረኛ ወይንስ እንግዳ ተቀባይ....ምን አይነት ሰው ይሆን
ታድሎ....አልኩ ለራሴው
....መች ይሆን የኔን በር የሚያንኳኳው...መቼ ይሆን ተራ የሚደርሰኝ..."አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፤ለምኑ ታገኙማላችሁ"ያለው ክርስቶስ...የኔን ማንኳኳት ሳይጠብቅ መቾ ይሆን ደጅአፌን የሚያንኳኳው...አይኖቼ ከስዕለ አድህኖው ላይ አልተነሱም
የክርስቶስን የፊቱን ገፅ አተኩሬ ተመለከትኩት .....ለብዙ ዘመናት ሲያንኳኳ የቆየ መሰለኝ....ግን ደግሞ ከማንኳኳት ብዛት ያልሰለቸ...ምን አልባት እኮ የኔኑን በር ይሆናል የሚያንኳኳው....አልሰማሁት ይሆን????
የልብ ምቴ ፍጥነቷ ሲጨምር ታወቀኝ...ድንገትም ከየት መጣ የሚሉት የደስታ ስሜት ወረረኝ...
ወዲያው ከሶፋው ብድግ ብዬ ወረድኩ ና ነጠላዬን ከሰነበተችበት ቁምሳጥን አውጥቼ.....ወደ ቤተ ክርስቲያን ከነፍኩ....የልቤን ደጃፍ ልከፍት....
/ትንሳኤ ዘ ኢትኤል / @tiztawe