ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


ይህ ቻናል ዓላማው የሰው ልጆችን በተለይም የኢት.ኦ.ተዋህዶ እምነት ተከታዮችን የኢትዮጵያ ትንሳኤ እጅግ ቅርብ መሆኑን ለማሳውቅ፤ ዝግጅት እንዲያደርጉ እና ተደብቆ የቆየውን ''ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክታትን'' ለሰው ልጆች ማዳረስ ነው። መልእክቱን አዳምጡ።ለአዳም ዘር ሁሉ እንዲዳርስ የበኩሎዎን ይወጡ!!
ግሩፑ @yealemberhan

ለጥያቄ @etberhan

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እግዚአብሔር በዚ ዘመን ፈቃዱን የገለጸበት መልእክትና ከዘመኑም ጥፋት በሥጋም በነፍስም መትረፍያ ቃልኪዳን እንጂ ሃይማኖት አይደለም። ይሄ ለሚያምን ሰው የእግዚአብሔርን ቸርነት ማድነቂያ እንጂ መሰናከያ መሆን አልነበረበትም። እውነቱን በምን ልወቅ፣ በጥርጥርም ያለ በምን ልጽና ለሚል ሰው-
፩. በእምነት እግዚአብሔርን በመጠየቅ- ይሄ እግዚአብሔርን አባቱ ላደረገ፣ በንስሐ፣ በአቅሙ እንደፈቃዱ እየኖረ ላለ ሰው እርሱን መጠየቅ ድፍረትና ግብዝነት ሳይሆን የልጅነት ሥልጣኑ ነው። መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የቅርብ አምላክ እንጂ የሩቅ ስላልሆነ በንስሐ፣ በጾም፣ በጸሎትና በዕንባ ለሚጠይቀው በሕልምም በራእይም በሕይወትም በሰውም ልቡናንም በመምራትና በማብራት እንዲሁም እንደየጸጋው ለጠየቀው ሰው እርሱ ባወቀ በተለያየ መንገድ መልስን ሊሰጥ የታመነ አምላክ ነው።
፪. መልእክቱን ከቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አንፃር በመመርመር- ሁሉንም መልእክቶች ሆነ አባቶች ያስተላለፉትን ትምህርቶች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዶግማና ቀኖና መነጽርነት ብንመረምረው ከአዕማደ ምሥጢር፣ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ከነገረ ማርያም፣ ከነገረ ቅዱሳን፣ ከአበው ትውፊትና ወግ ያፈነገጠው የቱ ላይ ነው? ስለቃልኪዳኑ ሰንደቅ ዓላማና የተከበሩ ቃላት ብናነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የነ ሊቀ ነቢያት ሙሴና እስራኤላውያን፣ ከቅዱሳን ታሪክ ደግሞ የነ ቅዱስ አንባ አብራም ግብጻዊ ምሥክር አለን። ስለውግዘትም ብናነሳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የነ ነቢዩ ኤልያስ ከቅዱሳንም የነ ቅዱስ በጸሎተ ሚካኤል ምሥክር አለን። ስለጽዋም ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከታሪክ፣ ከአበው ትውፊት ብዙ ምሥክር አለን። በእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ መሪነት ብንመረምረው ስለእውነተኝነቱ እንጂ የምንነቅፍበትን ነገር አናገኝም።
፫. የሕሊናና የዘመኑ ምሥክርነት- ራሱን ለማያታልልና እምነት ላለው ሰው በሐገራችንም ሆነ በዓለም እየሆነ ያለው በእግዚአብሔር ቁጣ እንደሆነ ይረዳል። መልእክታቱም ገና ከዓመታት በፊት ስለመጻኢ ሁኔታ በርግጥ መናገራቸው ከእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ስለመሆናቸው ማስረጃ ነው። “ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤”— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥20-21 እንደሚል መጽሐፍ ማነው ተናጋሪው በሚል የተላለፈውን መልእክት ሐሳብ ችላ ማለትና መናቅ ከጥፋት ይጥላል። ድምጹን ብቻ የሰሙት እነ አብርሃም እነ ኖኅ አንተ ማነህ ብለው እግዚአብሔር በክፉ ቢመራመሩት ዛሬ የእምነት አባቶቻችን አይሆኑም ነበር። የነነዌ ሰዎችም ከዛ በፊት ስለማያውቁት ስለነቢዩ ዮናስ ማንነት ቢመራመሩና ቢንቁ ንስሐም ባይገቡ በተቀጡ ነበር። ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ በፊት አይቶት ስለማያውቀው ስለቅዱስ ፊልጶስ ማንነት ቢመራመርና ቢንቅ ባልተጠመቀ ለኢትዮጵያም ምክንያት ባልሆነ ነበር። አሁንም እነማን ናቸው ሳይሆን መልእክቱ ምን ይላል ብለን በቅንነት እውነትን በመፈለግና በእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ መሪነት እንፈትሸው። እኛም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነታችን፣ በተስፋችነ በቃልኪዳናችን እንጽና። ጌታችን እንዳለው “ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው።” — ሉቃስ 9፥62 
ወደ ኋላ እንዳንመለከት ዕንቁአችን እንዳንጥል እንጽና እንበርታ !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር!

19/05/2017 ዓ.ም


መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው ወገኖቼ!!
-----/////////-------/////////--
በሩጫ የሚሮጥ ሰው ውድድር ውስጥ የገባ ሰው፡፡42 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውስጥ ገብቶ ከሆነ ያን ለመጨረሽ ብዙ ይሮጣል ብዙ  ይደክማል ፡፡ብዙዎች አስር ሺሆች ሆነው ሲሮጡ አይታችኀችኀል፡፡
ወደ መጨረሻ የሚመጡት  መቶ ሰው ሁለት መቶ ሰው   ምናምን ነው ወደ መጨረሻ የሚመጣው፡፡
መጨረስ በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ወገኖቼ !!
በማረግ በአንደኝነት በሁለተኝነት በሥስተኝነት በዓራተኝነት በአምስተኝነት በአስረኝነት እያለ መውጣቱን ተውት፡፡መጨረስ በራሱ በጎዳናው ላይ በሩጫው ላይ ተገኝቶ እፍጻሜው ድረስ መሄድ   ትልቅ ነገር ነው ወገኖቼ !!
📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት  ፤ ተስፋ ፤ ፍቅር ትምህርት  ክፍል -3ቀ ላይ የተወሰደ፡፡


ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም።
===================
ለነቢዩ ኢሳይያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ኤርምያስ የተገለጸለት
ለነቢዩ ሕዝቅኤል የተገለጸለት
እንዲሁም ለሁሉም ነቢያቶች የተገለጸላቸው ይለያያል።
ነገር ግን አንዱ ነቢይ ሁሉንም እኔ ብቻ ነው የማውቅ ብሎ ሌላውን ነቢይ ሲነቅፍ ሲተች አልታየም።
ለምሳሌ ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ስሙንም አማኑኤል እንደምትለው ለነቢዩ ኢሳይያስ ተገልጾለት።ተናገረ።
ለነቢዩ ኤርምያስ ደግሞ በሠላሳ ብር እንደሚሸጥና ክርስቶስ እንሚባልም ተገልጾለት ተናገረ።
ነቢዩ ሚክያስም ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደሚወለድ ተገልጾለት ተናገረ።
ሁሉም እግዚአብሔር የገለጸላቸውን ተናገሩ።
እግዚአብሔር እኮ ሁሉንም ለነቢዩ ኢሳይያስ  ገልጾለት ሁሉንም መናገር ይችል ነበር የሁሉም ክብር ይገለጽ ዘንድ እንጂ።
እናም ነቢዩ ኢሳይያስ  ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ ነቢዩ ሚክያስ የተናገረውን ውሸት ነው ክርስቶስ በቤተልሔም አይወለድም አላለም።
ስለዚህ ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና
ሁሉን አውቃለሁ ብሎ ምሥጢሩን ሁሉ ሳይመረምር ዝም ብሎ ከሚናገር ሰው በዚህ ዘመን መራቅ ብልህነት ነው።

ማቴዎስ 11፥6 ላይ እንደተጻፈው።ጌታ
ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

ሲል ተናገረ።እውነት በዚህ ዘመን በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት የማይሰናከል ምንኛ ብጹዕ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይና ምድርን አሳልፎ ለፍርድ የሚመጣው እኮ ቀድሞ መጥቶ ተወልዶ ተጠምቆ ተርቦ ተጠምቶ ንስሓ ግቡ ብሎ የታመሙትን ፈውሶ ለምጻሞችን አንጽቶ ወንጌልን አስተምሮ ተሰቅሎ ሙቶ ተነስቶ አርጎ ይህንን ሁሉ አድርጎ ቃሉን በናቁት እና ባቃለሉት ላይ ነው የሚፈርደው።ይህንን ሁሉ ባያደርግ ኑሮ ለፍርድ ባልመጣም ነበር።
ታድያ ዛሬስ በዚህ አመጸኛ ትውልድ ላይ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን የተሠጠው ንጉስ ቴዎድሮስስ ቀድሞ ሳያስተምር የሚገሰጸውን ሳይገስጽ ሳያስጠነቅቅ እንዴት ይመጣል?
የሚፈርደው እኮ በዚህ መልእክቴ እንዲህ አላልኩህም ነበር?ለምን ቃሉን ሰምተህ ንስሓ አልገባህም ብሎ እኮ ነው?

እናም ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን መልእክትን  አጣጥሎ ልክ አዲስ እምነት እንደሆነ አድርጎ ህዝቡን ማሰናከል እጅግ ከባድ ፍርድ ውስጥ መግባት ነውና።
ሁሉም ሰው ሁሉን እንደማያውቅ ተረድተን መልእክቱ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን አምነን እስከ መጨረሻው ድረስ መጽናት ከመታደልም በላይ መታደል ነው።
የእግዚአብሔር እውነት ሁሌም አያዳላም።
ዲያቆን ቄስ ጳጳስ መነኩሴ መምህር ብሎ አያዳላም ካጠፋ አጠፋ ነው ንስሓ እንዲገባ ይገስጻል።ያማ ካልሆነ ምኑን እውነት ሆነ ታድያ?
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅምና በማንኛውም ሰው መሰናከል ከእውነት ፈቀቅ ማለት እውነትን አለማወቅ ነውና እስከ ሞት ድረስ የታመንን እንሁን
እውነት አርነት ያወጣናል እና።
ሁሉም ሰው ሁሉንም አያውቅም። አራት ነጥብ።
17/5/2017




👆በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንዴትሰነበታችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴትሰነበታችሁ በየአላችሁበት የእግዚአብሔር ሠላም ከእናንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁንልና ሰሞኑንን አንድ የዩቲዩብ ቻናል ላይ የተለቀቀ የሚዘዋወር ቪዲዮ አለ ስለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ተናገሩ ከበረሃ አባቶች የሚል ነገር እየተዘዋወረ ነው ግን ይኼን መልዕክት በደንብ ከሰማችሁት መልካም የሚመስል ነገር ግን በማር የተለወሰ መርዝ ስለሆነ ባታጋሩ መልካም ነው።እስኪ አንዳንድ ነገሮችን እናንሳ የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘት ውግዘቱ የተካሄደው በአባ ጳውሎስና በሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው መካከል ብቻ እንደሆነ ይናገሩ ።ግን ውግዘቱ እንደዚያ ነው የሚለው? አይደለም በተዋረድ ከሲኖዶስ ጀምሮ እስከ ምዕመን የሚመጣ ነው እናንተም እንደምታውቁት በድምጽ አለ ተመልሳችሁ ስሙት ለማስታወስ ያክል በራሳችሁ በሊቀ ሊቃውንት አያሌው አንደበት ።
ሁለተኛ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ገና አልተቀባም አሉ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ከተቀባ ሌሎች በንጉሥ ማዕረግ ያሉ ሁሉ አብረው ያሉ እንደተሾሙ ነው እኛ ከእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ባሮች በራሳቸው አንደበት የተነገረን ወደዱም ጠሉም ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ከተቀቡ ቆዩ ጊዜያትም አልፈዋል። እነዚህ ሰዎች አሁን ካለው ከአጥፊው ከቤተክህነት መዋቅር ያልተላቀቁ ናቸው ብዙ ነገር ስለአለው ጥንቃቄ ብናደርግና አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ የተናገረ ሁሉ እውነተኛ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ።በአደባባይ ይውጡ እንወቃቸው ይላሉ እንነጋገር ይላሉ እኛ በአባቶች በኩል የተነገረን የክርክር ጊዜ እንዳበቃ ነው። ስለዚህ እባካችሁ ሁሌም አንድ ሰው እየመጣ ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ እየመጡ በተናገሩ ቁጥር የነሱን ንግግር የምናስተጋ አንሁን።ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ እነ መምህር ዶ/ር ዘበነ ፣እነ መምህር መስፍን፣ይኼ ዘመድኩን  የሚባል የኢትዮጵያ ትንሳኤ በ2015 ዓ.ም ይሆናል ንጉሡ በ2015 ይመጣል እያለ ብዙውን ሰው ጊዜ እየገደበ ሲያሰናክል የቆየ ፣ይቺ ስንዱ የምትባል ሳይቀር የዛር መንፈስ የሚጫወትባት ጭምር ፣ባህታዊ ነኝ የሚሉ መምህር ገብረ መስቀል የሚባሉት ፣ ሌሎችም ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ይናገራሉ ዳር ዳር ይዞራሉ ግን እውነተኛ አይደሉም በጎን የእግዚአብሔርን እውነት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክትን የሚነቅፉ የሚተቹ በተቃራኒ የቆሙ ናቸው።ስለዚህ እነዚህ ትምህርት ሊሆኑን ይገባል አብዛኛዎቹ የራሳቸውን ፈቃድ እንጅ  የእግዚአብሔርን ፈቃድ አይደለም የሚናገሩት። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ከእናንተ የበለጠ እግዚአብሔር ስለሚያደርገው ነገር በአባቶች በባሮቹ በኩል ምስጢር የገለጸለት እንዲያውቅም ያደረገው የለም።
ትናንት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባል የለም የጅል ስብስብ ነው እያሉ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሲሉ የነበሩ እኛ ቸሩ መድኃኔዓለም  ክብር ይግባናው የዓለም ብርሃን አይደለም ያልን ይመስል ለምን እንዲህ እንደተባለ ሳይረዱ በራሳቸው በሥጋ ስሜት እየተነዱ የፈለጋቸውን እየተናገሩ ሲያስቱ ቆዩ ዛሬ ያኔ የተናገሩትን እያስተጋቡ እንደ አዲስ ያሉ አሉ።አንዳንዶች ደግሞ ዛሬ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ልክ ነው እያሉ መጠዋል ግን ደግሞ እኛን የሚተች ነገር  በአባቶቻችንን  እውነተኛዎቹ የዚህ መልዕክት አስተላላፊ አይደሉም የማለት ያክል የሚመስል ንግግር እየተናገሩ ነው።ልብ በሉ በፊት መልእክቱን አዲስ ሃይማኖት :አሁን ደግሞ  መልዕክት እንደሆነ እና ትክክል እንደሆነ ግን አስተላላፊዎች ትክክለኛ እንዳልሆኑ የሚመስል እየተናገሩ ነው ።አንዱ አልሳካ ሲል ሌላ ሊበሏት ያሰቧትን ምን እንደሚባለው...
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት አባቶቻችን ማስተላለፍ የጀመሩት በ1998 ዓ.ም ነው  የተላለፈውም ለአዳም ዘር በሙሉ ነው ዛሬ አዲስ የመጣ ይመስል ሥራቻችን አጓተቱ ይላሉ።እኛ ዛሬ ሰምተን እንዲህ የገረመን ቀዳይ የሥላሴ ባሮች ምን ይሰማቸው ይሆን እጅግ የሚገርም እኮ ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር የምንሮጥ አንሁን።ይሄን የምለው በየማህበራዊ ሚዲያው ስታጋሩ ስታሸራሽሩ ስለምናይ ነው።
ልታውቁት የሚገባ ነገር እዚህ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ገጽ ላይ ተሰግስገው ተደብቀው የሚሰሙና እዚህ እየወሰዱ የሚመቻቸውን ብቻ እየወሰዱ የሚናገሩ አሉ ።እኛ የምንጠቀምባቸው ምስሎች ሁሉ እየወሰዱ የሚጠቀሙ አሉ። ወደ ፊት የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክትን በገሃድ እየተናገሩ የሚመጡ ይኖራሉ ጥንቃቄ አድርጉ። አንዳንዶች ደግሞ ተሰንገው ተገደው የሚናገሩ ይመጣሉ አምነውበት አይደለም ተገደው በየሚያዲያ ጣቢያው ሁሉ ይለፈልፋሉ ያን ካላደረጉ እረፍት እንቅልፍ ስለማያገኙ ይኼ ደግሞ በመልዕክታቱ ተነግሯል ይሄን ከወዲሁ ተረዱ።የሚገርመው ደግሞ የእግዚአብሔር ፍርድ ሲጀምር ሁሉ በየአፉ ብለን ነበር ተናገረን ነበር ማለት ጀምሯል መናፍቃን እንኳ ሳይቀር ተናግረን ነበር እያሉ ማለት ጀምረዋል እነሱን ብሎ ትንቢት ተናጋሪ።
ስለዚህ ወገኖቼ ጊዜ ካላችሁ የማንም ነገር እያያችሁ ጊዜ ከምታጠፉ የእግዚአብሔርን እውነት ተመልሳችሁ ስሙ እራሳችሁን ለእግዚአብሔር አገልግሎት አዘጋጁ ለዚያ የሚገባ ሰው እንድትሆኑ እግዚአብሔርን ጠይቁ እንጠይቅ እንለምን።ወርቅ እጃችን ላይ እያለ ሌላ ፍለጋ አንሂድ የእግዚአብሔር እውነት አንድ የቤተ-ክህነት ሰው ነኝ ባይ ስለተናገረ ስለአልተናገረ አይደለም እውነትነቱ የሚጸናው የእግዚአብሔር እውነት እውነት ነው ማንም ሊቀይረው አይችልምና ነው።
ቀዳማዊ የእግዚአብሔር ባሮችና እኛም የመንፈስ ልጆቻቸው ቤተሰቦቼ የሚሉን በስሜታዊነት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በገሃድ እንድንገለጥና ለማወቅ የሚደረግ ጥረት ይመስላልና ጥንቃቄ አድርጉ በገሃድ ራሳችሁን ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አታጋልጡ ።
"ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋል ይጋርድሃል ይላል የእግዚአብሔር ቃል " ይሄን ደግሞ አስተምረውናል የእግዚአብሔር ባሮች።
ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው የነገሩንን መታዘዝና ወደ ተግባር መለወጥ ነው።
ሌላው ከላይ በፎቶ የተጠቀሱትን የእግዚአብሔር ቃሎች እዩአቸው።
ከእኛ የሚለዩም ካሉ አትገረሙ የተጠራው ሁሉ የተመረጠ አይደለምና።ስለዚህ "ከእኛ ዘንድ ወጡ  ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢኾኑ አለ አያችሁ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነግር ግን አለ ተመልከቱ ኹሉ ከእኛ ወገን እንዳልኾነ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።ይላል የእግዚአብሔር ቃል በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት ምዕ 2:19 ላይ ስለዚህ አብረውን የነበሩ የሚመስሉ ግን ያልነበሩ ሲወጡ ይሄን የእግዚአብሔር ቃል ማሰብ ነው።እንደ አንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ እግዚአብሔር ሁሉን ይችላልና በጸሎት ማሰብ ነው።ከዚህ ውጪ ምን ማድረግ ይቻላል እንደ ፈቃድህ ይሁን ብቻ ነው።
ይቺን ለማስተላለፍ ነው ስለዚህ ዝምብላችሁ የአገኛችሁት ሁሉ ከማጋራትና ከመስማት ይልቅ የያዛችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙ ተረዱት ገና አልተረዳነውም።ቀዳማዊ የሥላሴ ባሪያ አባታችን ገብረ መድህንም እንዲገባችሁ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት እየጠየቅን እንድናነበው እንድንሰማው መክረውናል።
ሠላም እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር።
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን።
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ።
አሜን!
15/05/2017












ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20
15/04/2017 ዓ.ም




ኅዳር 26

#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጎንደር የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ።

የተፀነሱት ነሐሴ 26፣ የተወለዱት ግንቦት 26 በ1196 ዓ.ም ነው። አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው)።

ጻድቁ የመነኮሱት በቅዱስ ገብርኤል ምሪት በደብረ ዳሞ በአባ ዮሐኒ እጅ ነው። ኋላም ወደ ደብረ ሐይቅ (ሐይቅ እስጢፋኖስ) መጥተዋል።

አርድእትን በቅድስናና በትምህርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው።

ከእነዚህ መካከልም፦ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን፣ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን፣ አቡነ ሕዝቅያስን፣ አቡነ ገብረ እንድርያስን፣ አቡነ አሮንን እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን።

በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ።

ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በሰንበተ ክርስቲያን በ1286 ዓ.ም. ኅዳር 26 ቀን ዐርፈዋል። ጌታችንም ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ 7 ትውልድ የሚያስምር ቃልኪዳን፣ እንዲሁም 'የኢየሱስ ሞዐ አምላክ ሆይ፣ ከረሀብና ከችግር አድነኝ፣ ምግቤንና ልብሴን ስጠኝ ብሎ የሚለምነኝንም ልመናውን እሰማለታለሁ፣ ሲሳዩንና ምግቡን እሰጠዋለሁ' የሚል ሌሎችንም ቃልኪዳኖች ሰጥቷቸዋል።

#አቡነ_ሃብተ_ማርያም
ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ፣ ምጽዋትን ወዳጅ፣ ቡርክት ሴት ነበረች።

ልትመንን ከቤቷ ብትወጣም በባሕታዊ ትእዛዝ ተመልሳ ጻድቁን ወልዳ አሳድጋ እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች።

ጻድቁም እለአድባር በምትባል ገዳም በአባ መልከጼዴቅ እጅ መንኩሰዋል።

አባታችን በባሕር መካከል በመቆም ሙሉውን የዳዊት መዝሙርን በመድገም ግምባራቸው አሸዋ እስኪነካው 500 ጊዜ ይሰግዱ ነበር። አራቱ ወንጌላትንም በቀን በቀን ያደርሱ ነበር።

ከብዙ ተጋድሎ በኋላ በዚች ቀን ሰባት አክሊላትን፣ ደግሞም መታሰቢያውን ለሚያደርጉ፣ ስሙን ለሚጠሩ፣ መጽሐፈ ገድሉን ለሚያነቡና በማየ ጸሎቱ ለሚረጩ ከመጥምቁ ዮሐንስ ሐገር ተጠጋግታ ወዳለች ርስታቸው ከርሳቸው ጋር ሊያገባላቸው እንዲሁም ሌሎችንም ቃልኪዳናትን ከጌታችን ተቀብለው ዐርፈዋል።

#ሰማዕታተ ናግራን
በዚችም ዕለት የሐገረ ናግራን ሰማዕታት የአባታቸውም የቅዱስ ኂሩት መታሰቢያቸው ነው።

ፊንሐስ የተባለ አይሁዳዊ ይህቺን የክርስቲያኖችን ከተማ በመሸንገል ገብቶ ስለክርስትና እምነታቸው ቅድሚያ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን፣ መነኮሳትን በእሳት ውስጥ ጨመራቸው።

እኚህንም ቅዱስ አባት፣ ሚስታቸውንና ልጆቻቸውን በሰይፍ አንገታቸውን ቆርጧቸዋል። እኚህም አባት ራሳቸውን በሚቆረጡበት ጊዜ የሮምንና የኢትዮጵያን መንግሥት ያጸና ዘንድ የተረገመ የአይሁዳዊውን መንግሥት ያጠፋ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለይው ነበር።

ኋላም የክርስቲያን ወገኖች የአይሁድ ጉባኤ ዕጹብ ዕጹብ ብለው እስኪያደንቁ ድረስ እኩሌቶቹ ወደ እሳት እኩሌቶቹ ወደ ሰይፍ ተቀዳደሙ። እሳቱም እስከ አርባ ቀንና ሌሊት ታየ።

ኋላም የኢትዮጵያ ንጉሥ ካሌብም መልእክት በደረሰው ጊዜ በዋሻ ከሚኖር ከአባ ጰንጠሌዎን በረከትን ተቀብሎ የፊንሐስን ከተማ አጥፍቶ የናግራንን ከተማ አድሶ፣ የሰማዕታትን መታሰቢያ አቁሞ በድል ወደሐገሩ ተመልሷል።

#ዳግመኛም በዚች ዕለት ከሐገረ ሮም የሆኑ ቅዱስ ቢላርያኖስ፣ ሚስቱ ኪልቅያና እኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት ዐረፉ።




🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🟢.ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ።

🟢.ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

🟡.ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

🔴.ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
     
➻ሠላም እንዴትሰነበታችሁ እኛ ደና ነንን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ አባት ገድላቸው ላይ የተገለጸውን እስኪ አንብበነው እንማርበት ከበረከታቸውም እናገኝ ዘንድ እንማጸናቸው።

➻እንደ ነብዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማህፀን የተመረጡ ናቸው ብሉይንና ሀዲስ ኪዳንን ያጠናቀቁት በ12 ዓመታቸው ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብችኝ ብለው ጠይቀዋል ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደ ሚገኘው ደብረ ፀራቢ ወደ ሚባል ገዳም ገቡ።

➻ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስ የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ የከበደ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢነግሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነግረዋቸው ከብዙ ፈተና በኋላ ጽናታቸውን አይተው አመንኩሰዋቸዋል።

 ➻በገዳሙ እንጨት እየለቀሙ ውኃ እየቀዱ የክርስቶስን ሕመሙንና ሞቱን እያሰቡ በፀሎት ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ከነገራቸው በኋላ በሽሬ አዲ አቦ በተባለ ስፍራ ሂደው ብዙ አስደናቂ ታምራትን ካደረጉ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡት 16 መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ።

    ➻ጻዲቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባህር በታምራታቸው ያቃጠሉ አባት ናቸው።
በንጉሡ በአፄ ዳዊት ዘመን ሰንበት አንዲት ናት እያሉ በሰንበት ስራ እንደሚሰሩ ሰምተው ሰንበት አንዲት ናት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው ከግብፅ የመጡት ጳጳሳትም ቀደም ብለው ከአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ አሁን ደግሞ ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ አፄ ዳዊት አከራከሯቸው ጳጳሱም ተረቱ ።

➻ክፉዎችም በአቡነ ፊልጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው በአቁማዳ ጠቅልለው ሀይቅ ውስጥ ጣሏቸው።በዚህ ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባህር በእሳት ተቃጥሎ እንዲታይ አደረጉ።በጽኑ ሥልጣን ህዝቡንም መንግሥቱንም ረገሟቸው።

🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

➻ይህ ውግዘት ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ለአሁኗ ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) ልጆች የተላለፈ እርግማን ነው።

 ➻ በዚህ ጊዜ ንጉሡም ህዝቡም ሁሉም ተረበሸ።
እንደ ምጽአት ቀን ያስፈራ ነበር። እርግማናቸው ከመባርቅት ጎልቶ በሚያስፈራ ነጎድጎድ ይሰማ ነበር።

 ➻.ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባህር ዳርቻ ላይ የተቃጠሉ ድንጋዮች ይገኛሉ።

➻.በወቅቱም የንጉሡ ሚስት በዋናተኞች አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አሰወጥታቸው እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው።ወዲያውም ከማህፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ይወጣል ብለው ትንቢት ተናግረዋል።በትንቢቱም መሰረት ንጉሡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ተወለደ።

➻.በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባትና ክፉዎችም በባህር ውስጥ ስለጣሏቸው እርግማንን በህዝቡ ላይ አምጥተዋል።
ንጉሡ አፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያውም ታርቀዋል።
በዘመናቸውም ርሃብ ስለነበረ ፃዲቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለው አማክረዋቸዋል።
ጻዲቁም የጌታችንን መስቀል ያስመጡ ብለው መከሯቸው ንጉሥ አፄ ዳዊትም በአቡነ ፊልጶስ ምክር መሠረት ከእየሩሳሌም መስከረም 10 ቀን አስመጥተውታል።

➻.አቡነ ፊልጶስ በደብረ ቢዘን ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኑረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለዋል።
ላንተ የተሰጠህ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠውም
➻.ክብርህ ገናና ነው።

➻.በቃል ኪዳንህ ለተማፀነ የማልፈጽምለት የለም።
➻.ገዳምህን ዘወትር በበረከት ደመና ከብቤ አኖረዋለው ።

➻.ምሕረትን ፈልጎ ደጅህን ለረገጠ አንተን ባከበርኩበት ልክ አከብረዋለሁ።
➻.አስተዋይ ልቦናን እሰጠዋለው።

➻.የኢትዮጵያን ምስጢር እገልጥለታለው ብሎ ጌታ ቃል ገብቶላቸዋል ።

➻.ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር አርፈዋል !!!
           
➻.እንግዲህ ዛሬም እየሆነ ያለውን ማየት ነው እየተፈጸመ ነው እንሰደዳለን :ሀገር እንጠላለን ከውስጥ ይልቅ ውጭነት ይማርከናል ።

➻.እንደ ሀገር እንደ ህዝብ ታመናል ብሎ የሚመረምር ትውልድ እንኳ ጠፍቷል።

 ➻. የእውነተኛ አባቶቻችን ውግዘት ምን ያህል ከባድና ለቅጣት እንደሚዳርግ ከዚህ መረዳት ይቻላል።ዛሬም በዚህ ዘመን የተላለፈውን የአባታችን ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘትን የማናከብር ከሆነ ከዚህ የከፋ መከራ ውስጥ እንገባለን ማለት ነው።ያው እንደምናየው ህዝቡም እያከበረው አይደለም ያው የሚሆነውን ማየት ነው እንግዲህ።
➻. እግዚአብሔር ይመስገንና እኛ ግን እውነትን ሰምተናል በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እውነት እስከመጨረሻው ያጽናን!
➻.የጻዲቁ አቡነ ፊልጶስ በረከታቸው ይደርብን።

➻.በአንድ ወንድም ምክንያት ገድላቸውን ሠማሁና ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው ያጋራሁአችሁ


.ሠላመ እግዚአብሔር ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት ከሆነ ኢትዮጵያን ከልቡ ከሚወዳት ጋር ይሁን።
13/03/2017 ዓ.ም




📌ማስታወሻ
➖ ➖ ➖
ክፉ ትውልድ እንዲህ ይላል እስከ ዛሬ ለ18 ዓመት ለፍልፋችኋል የምትመኩበት አምላክ እስከ ዛሬ መቸ መጣ :ምንስ አደረገን:እናንተ ትጮሃላችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ ፍርድ ትላላችሁ ጆሮአችን እስከሚታክተው ሰማናችሁ ምንም የሚመጣ የለም።እኛም ለሥልጣኔአችንም ስለሥልጣኔአችንም ጉልበታችንም ሀብታችንም በዓለም የዘረጋነው ሥርዓታችንም ሁሉ አንዳች የሚነካው የለም።የእናንተን ሥላሴ: የእናንተን መድኃኔዓለም: የእናንተን ማርያም:የእናንተን መልአክ:የእናንተን ቅዱሳን ታሪክም ገድልም ሁሉንም አናውቃቸውም ።ግብረሰዶምነት መብታችን ነው ዓለምንም ሁሉ ከድኗል የምንሻውን ከመፈጸም የሚያግደን የለም።ዘወር በሉ አናውቃችሁም ብላችሁ ቁማችኋል ዲያብሎስን ታምናችኋል አምላካችሁ አድርጋችሁታል ፤በአዘዛችሁም ቁማችኋል ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋል።ልብ በሉ ምስክሩ እኛም ነንን ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ :ምስክሩ እራሳችሁም ናችሁ እንግዲህ እውነቱ ይለያል።እኛ የሥላሴ ባሮች: የድንግልም ልጆች:የሊቀ መላእክቱም ወዳጆች የቅዱሳንም ፍሬዎች የታመንበት አምላክ የአብርሃሙ ሥላሴ በእኛ አንደበት እንደተናገረው እንደ መልዕክቱ አገላለጽ :እንደ ደብዳቤዎቹ አገላለጽ:እንደ መግለጫዎቹ እንደ ትምህርቶቹ እውነትነት:የእኛም ታማኝ አገልጋይነት ይታወቅና እና ይገለጽ ዘንድ እግዚአብሔር በታላቅ የበቀልና የፍርድ ሂደት በታላቅ ቁጣ ትቢያ ሊያደርጋችሁ ደርሷል በደጃችሁም ነው።
ከዲያብሎስ የታጠቃችሁትን ትዕቢታችሁ ክህደታችሁ ንቀታችሁ እኒህ ሁሉ በምድር እንደጸኑ ያኖሯችኋል እንደሆነ እነሆ ልናይ ነው።የእኛ አምላክ ስለባሮቹ ስለቃሉ ስለትዕዛዙ ስለሥርዓቱ ሲል በቅናት እና በቁጣ ካልተነሳ እርምጃውንም በማትገምቱት በማታስቡት መልኩ ይዞት ካልመጣ በእርግጥ እንዳላችሁት እኛ አምላክ የለንም ውሸታም ነንን ማለት ነው።
ስለዚህ የእናንተ አምላክ ከእግዚአብሔር ታግሎ ከአሸነፈ እኛም ተሸንፈናል ማለት ነው።እንግዲህ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ ተዘርግቷል ሁሉንም እናየዋለን።ሲድራቅ: ሚሳቅ :አቢዲናጎምን ከእሳት ያወጣው አምላካችን: በእርግጥ ለአምላክነቱ: ለስሙ: ለክብሩ: ለፈቃዱ ቀናይነቱን ለልጆቹ ፈራጅነቱም በግልጽና በማትክዱበት መልኩ ሲውጣችሁ ተረት ብላችሁ የናቃችሁት ቃሉ ሲተገበርባችሁ አይ ተሳስተናል ማሩን እ ከልሉን አስጥሉን ማለት የለም።የለም የለም።መዳንም የለም።ከእነ ክህደትህ ከእነ ትዕቢትህ ሰዶሞን የበላው እሳት በሺ እጥፍ ተባዝቶ ይበላሃል።ፌዝህ ንቀትህ ያድንህ በቃ እሱኑ ተማመን ።ያ የተማመንህበት ዲያብሎስ እሱ ያድንህ በቃ።
ያሳደድኸን የገደልኸን የአሰርኸን እኛ የልዑልም የድንግልም ታማኝ ባሮች ብትጮህ ብታቅራራ ሺ ጊዜ ብትኳትን ከእንግዲህ አታገኜንም ለአንዴም ለመጨረሻም ተሰነባብተንሃል።
➖ ➖ ➖
📌የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በእምነታችሁ ጽናት በምክር መስማታችሁ ምክንያት አሸናፊ ሁናችኋል።ዓለምን አሸንፋችኋል። ኮንናችሁታል ታገሱ በጾም በጸሎት ትጉ።ለእኛም ደካማ አገልጋዮቻችሁ ጌታ ምሕረቱን :ቸርነቱን :ፀጋውን አብዝቶልን በትህትና እንድናገለግላችሁ ፀልዩልን።

📌ክርስቲያን መሠል አስመሳዮች ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን የምታመልኩ ወዮላችሁ! የሚገርም ክርስቲያን ተብየ ምዕመን ፡በተለይ ሴቶች አንድ ሊቅ ነኝ ሊቃውንት ነኝ የሚሉ እግር ስር ወድቃ አባቴ በእርስዎ እግር ሥር በመባረኬ እጅግ ተደስቻለሁ ብላ እንደ ምሳሌ በማሕበራዊ ሚዲያ ስታስተጋባ ሰማናት።እሺ አምላክስ መቼ ነው እግሩ ስር ወድቀሽ የሚባርክሽ እ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰው የሰጠሽ አባት ተብዮች ያጠፉሽ ከንቱ ትባያለሽ።እንደ እሷ መሰል የሆናችሁ ሁሉ ከንቱ ተብላችሁ ፍርዳችሁን ታገኛላችሁ።
በቀን 21/02/2017 ዓ.ም ከወጣው ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ ከ46 እስከ 51 ደቂቃ ላይ የተወሰደ።
22/02/2017 ዓ.ም


እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ። ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፤ ከፊቴ ጣላቸው፤ ይውጡ።
እነርሱም። ወዴት እንውጣ ቢሉህ፥ አንተ። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥
ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥
ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥
ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ ትላቸዋለህ።
ሰይፍን ለመግደል ውሾችንም ለመጐተት የሰማያትንም ወፎች የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ በምድር መንግሥታት ሁሉ መካከል ለመከራ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው?

ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 15:1-5


ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ፍርድ አዘል መግለጫ
21/02/2017 ዓ.ም



Показано 20 последних публикаций.