Aman እባላለሁ በ Civil Service ዩኒቨርስቲ 4ኛ አመት የManagment ተማሪ ነኝ ፍቅረኛ ነበረችኝ በጣም አብዝቼ የምወዳት ከማንም እና ከምንም በላይ የማፈቅራት ለሷ የነበረኝ ስሜት አብረውኝ ከነበሩት የድሮ ፍቅረኞቼ ጋር ቢደመር ሁላ ከሁሉም ይበልጣል ብዙ ፍቅረኞች ነበሩኝ ነገር ግን እንደዚህ አይነት ፍቅር ይዞኝ አያቅም ሁላ ለሷ ያለኝ ስሜት በጣም ይለያል
ግን አሁን ብንለያይም በየቀኑ አስባታለሁ ያሳለፈችውን Life ስለማቅ በጣም ታሳዝነኛለች እሷን ሳስባት ይጨንቀኛል አዝናለሁ ሁለታችንም እየተፋቀርን እየተዋደድን መለያየታችን ማመን ያቅተኛል።
የተለያየንበት ምክንያት የወንድ ጓደኛዋን ለምን አወራሃው እና የሴት ጓደኛዬን ለምን አወራሃት በሚል ነበር ፀብ የተነሳው ማታውኑ ካልተለያየን አለቺኝ በግዜው ትንሽ የከበደኝ ነገር ቢሆንም አሁን ላይ ግን ትንሽ እየተረጋጋሁ ነው ከተለያየን አንድ ወር አድርገናል።
እና ምን መሰላችሁ ቤተሰቦቼ አሁን ላይ 2 ሴቶች የፍቅር ስሜት ለኔ ቢኖራቸውም እኔ ግን እሷ ላይ Cheat ያደረኩባት መስሎ ይሰማኛል አንድ ቀን የምትመለስ መስሎ ይሰማኛል ከነሱ ጋር እየተዝናናሁ እያለ ሳስባት ታዝንብኝ ትሆን እያልኩ አስባለሁ ምን ላድርግ በጣም ጨነቀኝ ሃሳባችሁን አጋሩኝ 🙏🙏🙏🙏
የሚቀርብ ታሪክ ካላችሁ በ @MKFREZO መላክ ትችላላችሁ