✞ ጋሜል - የመዝሙር ግጥሞች ✞


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✟ የኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ የምስጋና ቤት ✟
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
ለማስታወቂያ ሥራ➝ @Naolviva
💿 የተዋሕዶ የመዝሙር ግጥሞች 💿
   ✍ / ትምህርቶችን ለማግኘት ✍
👇👇👇
https://t.me/maedot_ze_orthodox

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

"ከሁሉ አስቀድመን በአካል ልዩ በክብር አንድ የሆነውን ሦስትነቱን እንሰብካለን
እነሱም አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ናቸው።"

     ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ...

✞ መቅድመ ኲሉ ✞

መቅድመ ኲሉ ንሰብክ ሥላሴ ዕሩየ
ወንዌጥን ሎቱ አኮቴተ ዕሩየ
የዝማሬ አልፋ የአገልግሎት መቅድም
ሥላሴን ማወደስ ብለን አንድም ሦስትም
   
መሠረተ ሃይማኖት እርሱም በኩረ  አእማድ
ምስጢረ ሥላሴን ማጉላት በአበው ልማድ
ተምረናልና በየ መጻሕፍቱ
ወጠነ ስብሐተ በስመ ሠለሥቱ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በስም በአካል በግብር በከዊን ሦስት ብለን
ወእንዘ ሠለሥቱ አሐዱ ነው አሚን
አይደርስበት ጠቢብ የተመራመረም
ብሎ ያደንቃል እንጂ ትትነከር ትትረመም
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ንግበር ሰብአ ብለው በአርአያ በአምሳል
መልክአ ሥላሴ በማኅጸን ሲሳል
የሰው ልጆች ሆነን የተፈጠርን ሁሉ
ንበል ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ይደሉ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አድባራቱ መምሬ ድንኳን ሆኖ መቅደስ
አብርሃም ካህኑ እንዳገኘ ሞገስ
አሐዱ አብ ሲባል ተገለጥ ሥላሴ
በረከትህን ላክ በጊዜ ቅዳሴ

በገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም
መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

በዓለ ግዝረት

         ከርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም በህሊና ያሰበውን፤ ድኅረ ዓለም በነቢያት ያናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነ፣ ሥጋ ለበሰ፤ ሕግ ጠባያዊን ሕግ መጽሐፋዊን እየፈጸመ በጥቂቱ አደገ። ሕግ ጠባያዊ፤ አበ፣ እመ ማለት፣ ለዘመድ መታዘዝ፣ በየጥቂቱ ማደግ ነው። "ወልህቀ በበኅቅ እንዘይትኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይእቲ እሙ"እንዲል።

ሕግ መጽሐፋዊ በስምንት ቀን ቤተ ግዝረት በአርባ ቀን ዕጉለ ርግብ ዘውገ ማዕነቅ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት የመሳሰሉት ናቸው፤ በማለት የመጻሕፍተ ሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት በሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መግቢያ ላይ ያመሰጥራሉ፣ ያስተምራሉ።

ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፶፱ ላይ ዘግቦልን እንደምናገኘው፤ በዘመነ ብሉይ ወንድ ልጅ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ሲገረዝ ስም ይወጣለት ነበር።በመሆኑም ግዝረት የሥጋ ሸለፈት መቆረጥን ያመለክታል።

የግዝረት ሥርዓት ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው የቃል ኪዳኑ ምልክት ነው። ዘፍ፲፯ ፥ ፯-፲፬

በሙሴ የመሪነት ዘመንም ለእስራኤል ህዝብ ምልክትና መለያ ነበር።
ዘፀ ፲፪፥፵፫

ፈሪሳውያን ግን ከአብርሃም የመጣ መሆኑን ሳይረዱ በሙሴ እንደተሰጠ ሕጋዊና ሕዝባዊ ምልክት አድርገው ያምኑ ነበር።የሐዋ፲፭፥፲-፭

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን፤ መጀመሪያ ራሱ የሰጠው ለአብርሃም እንደነበርና መንፈሳዊ ምልክትም እንደሆነ አስረድቷቸው ነበር።ዮሐ ፯፥፳፪

የሚከተሉት ሦስት ነጥቦች የግዝረት ዋና ዋና ዓላማዎች ናቸው።

፩. እግዚአብሔር የተገረዘውን ሰው ለራሱ መርጧልና አምላኩ ነው። ዘፍ ፲፯፥፰

፪.የተገረዙት የእግዚአብሔር ህዝቦች ናቸውና ክፋትንም ከህይወታቸው ማስወገድ አለባቸው። ዘጸ፲፥፲፮

፫. እግዚአብሔር በእምነት ስለተቀበላቸው የጽድቃቸው መሠረት ነው። ሮሜ፬፥፲፩

ሆኖም በሐዲስ ኪዳን ሥርዓት ሣይሆን፤ የሚያድነው የእግዚአብሔር ህግ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ ያብራራል።
ሮሜ፪፥፳፭

ዋናው ነገር የሥጋ ሸለፈት መገረዝ ሳይሆን የልብ መለወጥና በእግዚአብሔር ማመን ሕጉንም መፈጸም ነው፣ ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ምዕመናኑን በመንፈስ የተገረዙ መሆናቸውንም ጨምሮ አብራርቷል።ፊሊጵ ፫፥፴

በተለይም ህዝብና አህዛብ ማለትም ትንቢት የተነገረላቸው፣ ተስፋ የተነገራቸው እስራኤላውያን እና ከአህዛብ ወገን የመጡት ሁለቱም የክርስትና አማኞች በግዝረት ምክንያት ያስነሱትን አለመግባባት አስመልክቶ በጻፈው መልእክቱ በሐዲስ ኪዳን ዘመን ጥምቀት በግዝረት ፋንታ መተካቱን ያስረዳል።ቆላ፪፥፲፩

ግዝረትም አሁን አይጠቅምም ይለናል። ገላ ፭፥፮

ወደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግዝረት ስንመለስ ደግሞ፤ በመግቢያው እንደተገለጸው ኦሪትና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣሁም እንዳለ፤ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና እርሱ ራሱ ሥርዓቱን ለመፈጸም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በስምንተኛው ቀን እናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ወስዳው ሊገረዝ በታሰበ ጊዜ በፍጡራን እጅ አልተገረዘም።

ምላጩ በገራዡ እጅ እንዳለ ውኃ ሆኖ ተገኝቷል (መጽሐፈ ስንክሳር ጥር ስድስት)።ይህም በመለኮታዊ ኃይሉ ነው። እርሱም በግብር መንፈስ ቅዱስ ተገርዞ ተገኝቷል።ይህንንም ያደረገው ሰውን ንቆ ስርዓቱንም ጠልቶ ሳይሆን ደመ መለኮቱ ያለ ዕለተ ዓርብ የማይፈስ ስለሆነ እርሱ ባወቀ ይህን አደረገ ስሙንም አስቀድሞ በመልአኩ እንደተነገረ ኢየሱስ አሉት። ሉቃ፪ ፥፳፩

በዚህም ምክንያት ቅድስት ቤተክርስቲያናችንም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የግዝረት በዓል በየዓመቱ ጥር 6 ቀን ታከብራለች (መጽሐፈ ስንክሳር ጥር ስድስት)።

ስታከብርም በግዝረቱ እለት የተፈጸሙትን ተአምራት በማስተማርና በማሳወቅ ነው።

ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ምስጋና  ይሁን!

አሜን ! 🙏


የአሜሪካ ማዕከል - በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ - ማኅበረ ቅዱሳን

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ✞

ገብረ መንፈስ ቅዱስ አባቴ
ግባልኝ ይባረክ ቤቴ
[፪]
የበረከት ምንጭ ሆነሃል
በቃል ኪዳን ታምነናል [፪]



ንጹሕ ባህታዊ እውነተኛ አገልጋይ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆነ ለኛ ሲሳይ
ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለህ የለመንክ
በዝቋላ ባሕር መቶ ዓመት ጸለይክ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የእምነት ወታደር የጸሎት ወዳጅ
የአቅሌስያ ጸጋ የስምዖን ልጅ
ዝናህ እጅግ ሰፍቶ ተሰማ በዓለም
ጻድቅ ሐዋርያ የፍቅር የሰላም

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ጸበልህን ጠጣው ከደጅህ ደርሼ
ከሕመሜ ዳንኩኝ በእምነትህ ታብሼ
አንበሳና ነበር የሚታዘዙልህ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ልዩ ነው ተጋድሎህ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ግብፅም ትናገረው ታላቋ በእንሳ
የወንጌል መምህር የተዋሕዶ አንበሳ
ምስራች ነጋሪ የጽድቅ ባለሙያ
በረከትህ በዝቷል በኢትዮጵያ

                መዝሙር|
    ዘማሪ| ዲያቆን እንዳለ ደረጀ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ሰላም ለከ ✞

ሰላም ለከ ጸሐፌ ራብዓይ ወንጌል /፪/
ወልደ ነጎድጓድ ዮሐንስ ድንግል /፪/


መልአክ ቅዱስ ዮሐንስ መልአክ
ለወንጌል የታጨህ በክርስቶስ በአምላክ
ነጻሬ ምስጢር የመላእክቱ አርክ /፪/
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ኮከብ ወልደ ዘብዴዎስ ኮከብ
ደምቀህ ምታበራ ያጌጥክ በጥበብ
ኀበ እግዚአብሔር የምታደርስ መርከብ
ወደ እግዚአብሔር የምታደርስ መርከብ
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፍቁር ፍቁረ እግዚእ ፍቁር
አበ ልሳናት ወንጌላዊ ክቡር
አርከ መለኮት ደም ግባትትህ ሥሙር /፪/
     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፀሐይ አቡቀለምሲስ ፀሐይ
ዓይነ ልቡናህ የደረሰ ሰማይ
ምድራዊ መልአክ ቃልህ ጥዑም ሰናይ /፪/

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ አባ ሊባኖስ ✞

በሰማይ መላእክት ስምህ የተጠራ
አባ ሊባኖስ ክብርህ[፪] እንደ ፀሐይ በራ


ከጫጉላው ይልቅ በልጦብህ የጌታ ፍቅር
በእውነት ወጣህ ልትሆን ታማኝ ምስክር
ሦስት ጊዜ መላኩ ጠራ የአንተን ስም
ትጉ ነህ በፀሎት ከቶ የማደክም
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ለዘለዓለም ይወሳ ስምህ በኢትዮጵያ
ቅድስት አገር ነች ምትሆን ለአንተ መጥሪያ
ከግብፅ ወደ አክሱም መራኸ ቅዱስ መላእክ
በብርሀን መስቀል ሕዝቦቿን እንድትባርክ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ብርሀን ሆንክለት ለአመጣ ሞገስ ክብሯ
ድውያን ዳኑ በገድልህ ስምህ ሲጠራ
ሁሌ በትውልድ እንደ አዲስ ክብርህ ይወሳል
ያከበረህን እግዚአብሔር እጅግ ያከብራል
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
መንነህ ወጣህ ልትፈፅም ትልቅ ተጋድሎ
የክርስቶስ ፍቅር በልጦብህ ደምቆ ተስሎ
ዘመርን እኛ ለክብርህ ብለን ሊባኖስ
በዝቶ አይተናል በአንተ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ

                መዝሙር|
    ዘማሪት| ሲስተር ሕይወት ተፈሪ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ተመስገን ✞

ተመስገን [፫] ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን (፪)


ሁሉን ስሰጠን ያለ ዋጋ ነው
ግን ምንዘምረው ተደርጎልን
ነው
በነፃ አይደለም የምናዜምልህ
ተቀብለን ነው ወስደን ነው ከእጅህ
ተመስገን ነው - - የአንተ እጅ ሲሰጥ
ተመስገን ነው - - ሰቶ እንዳልነበር ነው
ተመስገን ነው - - የዃላን አይሰፍርም
ተመስገን ነው - - ወስዶ ነበር አይልም
    አዝማች
ለሁሉም ፀሐይ ቀን የምታወጣ
ድሃን አትንቅም ገንዘብ ስላጣ
ባይኖረው እንኳን በአንተ ይኖራል
ቆርሰህ ስሰጠው ተመስገን ይላል
ተመስገን ነው - - ክብርህ አይጓደል
ተመስገን ነው - - በሰማይ በምድር
ተመስገን ነው - - የድሃ አደጉ አባት
ተመስገን ነው - - ደጉ እግዚአብሔር
    አዝማች
ውጊያን ለራስህ ለእኛ ድል ሰተህ
ከክብር ሰገነት ታኖረናለህ
ጠላት እያየ ዘይት የምትቀባ
ፅኑ ግንብ ነህ መጠጊያ አንባ
ተመስገን ነው - - በመልካምነትህ
ተመስገን ነው - - ያላሰብከው ማነው
ተመስገን ነው - - ከአንተ ያገኘነውን
ተመስገን ነው - - ቆጥረን አንጨርሰው
    አዝማች
በስደት ሀገር ወተን እርቀን
አንተን ለመማር ሰበሰብከን
የእኛ የምንለው ባይኖረን እኛ
አንተ አለኸን ብርቱ መፅናኛ
ተመስገን ነው - - በማለዳ አውጥተህ
ተመስገን ነው - - ሰርክ የምትመልስ
ተመስገን ነው - - መልካም እረኛነህ
ተመስገን ነው - - ኢየሱስ ክርስቶስ
    አዝማች
በጌታ ድጋፍ የቆመ ሰው
ምድር ገፍትራ ጠልፋ አትጥለው
የሺውን ታሪክ በቀን ይሰራል
ሁሉን በሚችል ሁሉን ይችላል
ተመስገን ነው - - ሌላ ምን ይባላል
ተመስገን ነው - - ለአንተ ምን ይሰጣል
ተመስገን ነው - - ሁሉን አሳለፍከው
ተመስገን ነው - - አዲስ አደረከው

ዘማሪ| ዲያቆን አቤል መክብብ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ኦ እስጢፋኖስ ✞

ኦ እስጢፋኖስ ሰማዕት(፪)
አክሊልን አገኘ ከጌታ በእውነት


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የወንጌልን ትምህርት - - ቀዳሚ ሰማዕት
ስለመገብካቸው  - - ቀዳሚ ሰማዕት
አይሁዶች ወገሩህ ጨክኖ ልባቸው
በድንጋይ ሲወግሩት - - ቀዳሚ ሰማዕት
በጣም ተጨነቀ - - ቀዳሚ ሰማዕት
ለሚወግሩት ሰዎች ይቅርታን ጠየቀ(፪)

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የወንጌል በር ከፋች - - ቀዳሚ ሰማዕት
የተባልከው ቅዱስ - - ቀዳሚ ሰማዕት
ተመሰከረልህ በእውነተኛው ንጉሥ
ሥራህ ያስደንቃል - - ቀዳሚ ሰማዕት
እጅግ ድንቅ ሥራ - - ቀዳሚ ሰማዕት
በአንተ ተበተነ የወንጌል አዝመራ(፪)

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የዲቁናን ሥራ - - ቀዳሚ ሰማዕት
በክብር የፈፀምክ  - -  ቀዳሚ ሰማዕት
የሥላሴን ዙፋን ተከፍቶ ያየህ
የድንጋይ እሩምታ - - ቀዳሚ ሰማዕት
ያላዘናጋህ   - - ቀዳሚ ሰማዕት
ቀዳሚ ሰማዕት እስጢፋኖስ ነህ(፪)

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዙፋኑ ተከፍቶ ቀዳሚ ሰማዕት
ቀና ብሎ አየ - - ቀዳሚ ሰማዕት
ነፍሴን ተቀበል በማለት ጸለየ
ጌታን ተቀበለው - - ቀዳሚ ሰማዕት
ቃሉንም ሰማለት - - ቀዳሚ ሰማዕት
ሰማያዊ አክሊል ወደሱ ላከለት(፪)

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ተወለደ ጌታ ✞

ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ /፪/


አንዲት ብላቴና የአስራ አምስት ዓመት ልጅ
ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ
በህቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ
ዓለምን የሚያድን የሰዎች አለኝታ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት
ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት
እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ
አየነው አምላክን እንደሰው ተወልዶ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደችው ጌጠ የሔዋን አለኝታ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም
በምድር ተፈልጎ እንዳንቺ አልተገኘም
በሀሳብ በግብር ንፁህ ስለሆነች
የአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፍጹም ድንግልና ክብር የተመላች
እንደምን አምላክን በማህፀን ያዘች
ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ
ወለደቸው ድንግል የሔዋን አለኝታ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ አንቺ አንቺ ቤተልሔም ✞

አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
በአንቺ ተወለደ የዓለም መድኃኒት (፪)


ለአዳም ክብር ሲሻ       ቤተልሔም
ለሁሉም ሰላም            ቤተልሔም
ጌታ ተወለደ                ቤተልሔም
ከድንግል ማርያም       ቤተልሔም
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እጅ መንሻ አቀረቡ      ቤተልሔም
የምስራቅ ነገሥታት      ቤተልሔም
በከብቶቹ በረት          ቤተልሔም
ተኝቶ ላገኙት             ቤተልሔም
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እስራኤል ሕዝቤን           ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው              ቤተልሔም
ከአንቺ ይወጣል ብሎ      ቤተልሔም  
እንደ ነገራቸው                ቤተልሔም
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቅዱሳን መላእክት            ቤተልሔም
ያሸበሸቡልሽ                   ቤተልሔም
ስብሐት ለእግዚአብሔር    ቤተልሔም
ብለው ዘመሩልሽ            ቤተልሔም
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አንቺ ቤተልሔም         ቤተልሔም
እንዴት ታድለሻል         ቤተልሔም
እዮር እና ራማ            ቤተልሔም
ኤረርን መስለሻል       ቤተልሔም
     

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ የዋሻ አንበሳ ✞

የዋሻ አንበሳ ነው የፀሎት ሰው
የተክልዬ ስም ላወድሰው
ክብር ፀሎቱ ነፍሴን ስጋዬ እንዲቀድሰው(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በእጆቹ ይዞ ወንጌል መስቀል
ወጣ ከቤቱ ሊያገለግል
አዳኝ ነበረ ዝነኛ አዳኝ 
በጥዑም ስብከት ልብን ከመስቀል የሚያገናኝ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ያፅምህ ሰባሪ ያስተምረናል
ዘምሩ ብሎ ይቀሰቅሳል
ካስማ ሰክተህ በግርግዳ ላይ ወዝህ ፈሰሰ
ፀሎት ልመናህ ሰማይ ደረሰ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ያንጎደጉዳል መብረቅ ስብከቱ
ተሰባበሩ ጣዖታቱ   
ህልቁ መሣፍንት ከፊቱ ወደቁ 
የተክልዬ አምላክ ታላቅ መሆኑን እያደነቁ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በቅዱስ ማርቆስ ሰብከቱን ሰጠ
የአባ ሰላማ ፋናውን ይዘህ
የኢትዮጵያ ሐዋርያ ነህ 
ችግር ቢመጣ ይጠብቀናል ምልጃ ፀሎትህ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ምግባረ ተክለአብ ✞

በቃልኪዳኑ አምኖ ለሠጠሽ ፈጣሪ
በምግባረ ሠናይ ነፍሴ ተጣጣሪ (፪)

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምግባረ ተክለአብ ብእሲ ሞገስ [፪]
ይነገር ይሰማ እስካጥናፍ ድረስ
የሚሆንነው እና የሕሙማን ፈውስ [፪]

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ጋሻና ጦር ይዞ ለማደን አራዊት
የሰውን ልጅን ሊያድን ሥላሴ መረጡት [፪]
አጋዕዝተ ዓለም ጸጋን የሚሰጡ
ተክለሃይማኖት ብለው ስሙንም ለወጡ [፪]

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በኪነተ እግሩ ኢትዮጵያን ቀድሶ
ወጣ ደብረ አስቦ ብፍጥነት ገስግሶ [፪]
እግሩ እንኳን ቢቆረጥ በመቆም ብዛት
ለሰባት ዓመታትን ጸና በጸሎት [፪]

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ሃሌ ሃሌሉያ ✞

ሃሌ ሃሌ ሉያ (፪)
በሰማይ በምድር ምሕረት ሆኗልና
ሃሌ ሃሌሉያ አሜን ሃሌሉያ


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
መላአክት ዘመሩ አመሰገኑት
እየተደነቁ በአምላክ ቸርነት [፪]
ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት አሉ
እረኞችም አብረው እርሱን አከበሩ [፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዓለምን ለመፍጠር ከተጠበበት
ይበልጣል ከሁሉም እኛን ያዳነበት[፪]
ከዳግማዊት ሔዋን ከእመቤታችን
በረቂቅ ጥበቡ ተወልዶ አዳነን [፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሁላችሁም ሂዱ ከቤተልሔም
ታገኙታላችሁ በከብቶች ግርግም[፪]
ኢየሱስ ክርስቶስ ወኃቤ ሰላም
ሞታችንን ወስዶ ሕይወቱን ሰጠን [፪]

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ታትመሻል ✞

ታትመሻል በሰው ልቦና
የደካሞች ምርኩዝ ነሽና
ላመስግንሽ በአዲስ ዝማሬ
እመቤቴ ገና ነው ፍቅሬ [፪]


            አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የተፅናናንብሽ የድሆች ማረፊያ
ነፋስ ውቅያኖሱን ወጀቡን መቅዘፊያ
ወርሰናል ስምሽን ከወርቁ መዝገብ ላይ
ወለድሽልን ድንግል የሕይወትን ፀሐይ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን [፪]


            አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቀስተ ደመናዬ ሁነሽ ምልክቴ
አለሁ እስከዛሬ በአንቺው በእመቤቴ
ልጅሽን አምኜ ምን ይጎድልብኛል
ያስጨነቀኝ ሁሉ ይታዘዝልኛል
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን [፪]


            አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተከቧል ተራራው በብሩህ ደመና
የአብ ልጅ ክርስቶስ በአንቺ ወርዷልና
ይባቤ ምስጋና አፋችን ይመላ
መቅደስ አላየሁም ድንግል ከአንቺ ሌላ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን [፪]


            አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የከሳሼን ጉልበት ጽናቱን ሰብረሻል
የአዳም ልጅ ከሲኦል ከሞት ወጥቶብሻል
ጣፈጣት ለነፍሴ የማህጸንሽ ፍሬ
ስጠራሽ እኖራለሁ በያሬድ ዝማሬ
ጽዮን ብለናል ነሽ መማፀኛችን
ሞትን አናይም ካለሽ እናታችን [፪]


   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ወደ አንቺ የመጣው ✞

ወደ አንቺ የመጣው በብሩህ ደመና
ከሦስቱ አካል አንዱ ክርስቶስ ነውና
የጠፋ በግ አዳም ታደሰ በጌታ
በአንቺ ተፈጸመ የሰው ልጆች ደስታ(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በደይን የተጣለች ሔዋን ተደሰተች
የደስታ መፍለቂያ አንቺን ስላገኘች
የበረከት ፍሬ ከአንቺ ተገኘልን
የወይን ቦታ ነሽ ድንግል እናታችን

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ወልድም ባሕርይሽን ባሕርይ አድርጎት
ለፍጥረታት ጌታ መዓዛሽ ተስማምቶት
ከአንቺ ይወለድ ዘንድ ፍጹም ሊላላክሽ
በጥቂት አደገ ተልኮና ታዞሽ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከድንግልና ጋር አንድ የኾነ ሐሊብ
በሩካቤ ሳይሆን በብሥራት እንደ ንብ
ከሆድ መጥበብ ጋር የመለኮት ስፋት
አንቺ ኾነሽ ሳለ ታናሿ ሙሽሪት

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በፍጡር ሕሊና የማይመረመር
ዕጹብ ነው ድንቅ ነው የመፅነሷ ነገር
እሳተ ነበልባል በሆድሽ ውስጥ ሲያድር
ነደ ነበልባሉ አልፈጀሽም ነበር

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ስምህ በሁሉ ተመሰገነ ✞

ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
አንተን ማወደስ ያስደስተናል
ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አምላክ ተመስገን በሰማያት
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ ዕጣ
[፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በምግብ እጦት ብንሰቃይም
ማኅሌትህን አናቋርጥም
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም
እንዘምራለን ለአምላካችን ስም
[፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣም
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም
ቸርነትህን እንጠብቃለን
ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሄዳለን
ቸርነትህን እንጠብቃለን
ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ማርያም ብዬ ✞

ማርያም ብዬ እዘምራለው
እንደ አባቶቼ እጠራታለው
በያሬድ ዜማ በአዲሱ ቅኔ
ልዘምርላት በዕድሜ ዘመኔ (፪)



ማርያም ብዬ በእሳት መታጠቂያ ታጥቋል ባለቅኔ
ማርያም ብዬ መንፈስ ይማርካል ማኅሌተ ገንቦ
ማርያም ብዬ በወርቁ ፅናላይ አርጓል ፀሎቴ
ማርያም ብዬ ባአማኑኤል እናት በአንቺው በእመቤቴ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ በክብር ደመና ተሞልቷል መቅደሱ
ማርያም ብዬ ድንግል የአንቺ ምልጃ ስቦናል ወደሱ
ማርያም ብዬ ሆነሽ ተገኝተሻል ሁለተኛ ሰማይ
ማርያም ብዬ ጌታ ከአንቺ ወቷል የጽድቃችን ፀሐይ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ አልጠግብም ስጠራሽ ማር ነሽ ለከንፈሬ
ማርያም ብዬ ሳሊለነ እያልኩሽ አለው እስከዛሬ
ማርያም ብዬ ፀጋሽ ቤቴን ሞልቶ ተትረፈረፈልኝ
ማርያም ብዬ ሐዘን እና ለቅሶ ከኋላ ቀረልኝ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ የባለጋራዬ ምሽጉ ፈረሰ
ማርያም ብዬ በመስቀል ስር ክብሬ እንባዬ ታበሰ
ማርያም ብዬ አልፈራም ከንግዲ አለችኝ መከታ
ማርያም ብዬ ቁስሌን የምትፈውስ እስሬን የምትፈታ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ማርያም ተዐቢ ✞

ማርያም ተዐቢ እምኲሉ ፍጥረት [፪]
ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

መላእክት በሰማይ ፊቱ የሚቆሙት
ክንፋቸውን ለብሰው የሚሸፈኑት
ባይችሉ ነው የአምላክን ፊት ማየት
ማርያም ግን ችላዋለች በእውነት

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ልብሱ እሳት የኾነ ቀሚሱ እሳት
አጅግ የከበረ ኃያል መለኮት
ተዘረጋ ሰባቱ መጋረጃ
በሆድሽ ውስጥ የሰላም መታወጃ

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ሙሴ በተራራ ጫማውን አውልቆ
ለመቆም ተስኖት ነበረ ተደንቆ
ዕፀ ጳጦስ አንቺ ነሽ በሐዲስ ኪዳን
የታቀፍሽው አሳተ መለኮትን

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ሙሴ እግዚአብሔርን ስላነጋገረ
ሕዝቡ ፊቱን ሊያየው እጅግ ተቸገረ
ድንግል አንቺ ታቀፍሽ ይህን መለኮት
እንዴት ልቻል ብሩህ ፊትሽን ለማየት

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ማርያም ተዐቢ እምኲሉ ፍጥረት [፪]
ኢያውዐያ አሳተ መለኮት [፪]

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ​​የብርሀን ደጅ ናት ✞

የብርሀን ደጅ ናት ድንግል እናታችን
ከሰማይ እያበራች ደስ አለው ልባችን
ፍቅርሽን ሰላምሽን ድኅነት ይኹነን ኦኦ
ፍጥረት /በሙሉ/[፪] ፊትሽ ይወድቃሉ
ፀጋሽ ይድረሰን[፪] ይሰጠን እያሉ


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የእኔ ልብ ምን ጽድቅ አለው አንቺ ለማስተናገድ
የኃጢአት ጎተራ ነው የተሞላው በስስት
ኧረ እንዴት[፪] ድንግል ትኑርበት ኦኦ
አትጸየፍም የእኔ ልብ ታሰናዳዋለች
ስለኃጥአቴ የእኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት
ሕሊናቸው ይመለስ እንጸልይ ለዚህ ጥፋት
አምላክን ይዛ ነው ድንግል የምትመጣው ኦኦ
እሷን ስንመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ቂርቆስ ለወዳጁ ✞

ለወዳጁ ቂርቆስ ለወዳጁ
ያነሳዋል ላደገ ከደጁ
በብርቱ ሰልፍ ለእኔ ሆኖ ብርቱ
ሰው አርጎኛል በምልጃው ሰማዕቱ(፪)


እንደ ቤተልሔም ቤቱ ነው ልደቴ
ማረፊያዬም እርሱ ናዝሬት ሰገነቴ
አንዳች ያልነበራት ቤቴ ተጎብኝታ
አወጀች ለክብሩ የድሉን እልልታ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ግሩም ቃልኪዳኑ በውስጤ እየሰራ
ሜዳ ያረግ ነበር ግዙፉን መከራ
አበባ ነው ስሙ ዕፍራን የተባለ
ስንቱን አልፎ አየው ቂርቆስ ቂርቆስ ያለ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በወዳጅ ንክሻ ሲዛነፍ ሰላሜ
ገድሉን እየሰማሁ ቀለለ ሸክሜ
በናቀኝ ዓለም ፊት  አርጎኝ ባለዋጋ
ጨለማውን ይኸው ሰማዕቱ አነጋ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከማውጀው ቃላት ንግግር በላይ ነው
በመውጣት መውረዴ ቂርቆስ ያደረገው
ዛሬን ለመዋጀት መሠረት ሆነና
መጽሐፈ ዜናውን ቃኘው እንደገና
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ውለታውን ሳስብ እንባ ካይኔ ይፈሳል
ስለ እርሱም ስከትብ ብዕሬ ኅይል ያጣል
ከመቅደሱ ጽድቅን ታጥቄ በረከት
አጉራሼ ሰማዕቱ ይታያል በኔ ፊት
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


            መዝሙር|
  ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ ✞

ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
እመቤቴ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
ደካማ ነኝ እኔ ምግባር ይጎድለኛል [፪]

ወደ ተራራማው ይሁዳ ከተማ
ፈጥነሽ ስትመጪ ድምፅሽ የተሰማ
የኤልሳቤጥ ዘመድ የዘካርያስ
ድምፅሽን አሰሚኝ በአንቺ ልቀደስ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በማኀፀንሽ ይዘሽ የሰማይ እንግዳ
አንዴት ትመጫለሽ ከታናሽዋ ጓደ
አንዴት ልቀበልሽ እምላኬን ይዘሽ
መንፈስ ቤቴን ሞላው ሲሰማ ድምፅሽ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በሥጋዊ ሳይሆን በመንፈስ ዓይኖቼ
ለማየት እሻለሁ ከልቤ ጓጉቼ
ሥራዬ የከፋ መሆኑን አውቃለሁ
ድምፅሽን ለመስማት አጅግ እፈራለሁ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አንቺ ቡርክት ነሽ ቡሩክ የአንቺ ፍሬ
ላመንሽዋ ብፅዕት ትዘምር ከንፈሬ
ፅንሰን ደስ አሰኘ የድምፅሽ ሰላምታ
ለዚህ ታላቅ ነገር ይገባል እልልታ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በሁሉ የሞላው ዙፋኑ ቢያደርግሽ
የመላእክት መዝሙር ተሰማ ከሆድሽ
ሁለተኛ ሰማይ ድንግል ማርያም
በአንቺ ድንቅ አድርጓል መድኃኔዓለም

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

Показано 20 последних публикаций.