Yezeginet Kibir


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Искусство



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Искусство
Статистика
Фильтр публикаций


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
" ለኔው እንጂ ለሌላ አይደል እንዲህ ነኝ የምለው
በእኔነት ውስጥ ራሴን ችዬ ራሴን አውቄአለሁ
በማያውቀው ባልዋለበት ራሱን ያገኘ
ቀድሞ አልፃፈም እንዲነበብ እሱን ያሰኘ
እኔ እንዲህ ነኝ ማለት ለኔ ሊያኮራኝ እንጂ
ልሸማቀቅ ላፍር አልያም ልደት እንጂ"

ስለዚህ....
#pridemonth2022 #ዜጋ #ክብር #ፍቅር #የራስፍቅር #ኢትዮጵያዊዜጋ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ቤተሰብ የደም ትስስር ብቻ አይደለም :: በህይወታችን ዉስጥ ያሉ በህይወታቸው ውስጥ እንድንኖር የሚፈልጉ ሰዎች ሰብሰብ ነዉ፤ በማንነታችን እንዳለን የሚቀበሉን ፣ ደስታችንን ለማየት ምንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይሉ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚወዱን ናቸው::

Family isn't always blood. It's the people in your life who wants you in theirs; the ones who accept you for who you are; the ones who would do anything to see you smile and who love you no matter what.

#pridemonth2021 🌈
#chosenfamily #familybychoice #family #queerfamily #ethiopianqueer #zega #zegafamily #EthiopianLGBTIQ
#love


#3 ፍቅር/Love
ፍቅር ባለበት ህይወት አለ!
Where there is love, there is Life!

~Ghandi / ጋንዲ

#love #reasontobeproud #pridemonth2021 #pride #lgbtiq #lgbt #queer #EthiopianQueer #EthiopianLGBTIQ #Life #QueerHabesha


#2
ዕድለኝነት ይሰማኛል - የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሬ (ዜጋ) በመሆኔ፡፡

በዕድገቴ… “ልዩ” ጾታዊ ተማርኮዬን በአካባቢዬ ከማየው እና ከተማርሁት ማንነት ጋር ለማስማማት እና ለማስታረቅ ያደረግሁት የራስ ፍለጋ ዘመቻ ከተማርኮዬ እና ከአስቸጋሪ እድገት በዘለለ ራሴን እንደ ሰው እንድመዝን እና እንድመረምር ስላገዘኝ፤

ይህ አስቸጋሪ የራስ ሽኩቻ ጊዜ የተሻለ በነፃነት የማሰብ ዕድልን የሰጠኝ ሲሆን ስለህይወት ያለኝን ጠቅላላ አስተያየትም ለበጎ ቀይሮልኛል ብዬ አምናለሁ፡፡

Growing up to now, my self-discovery journey to reconcile my sexuality with what I saw and learned in my environment helped me evaluate and examine myself as a person beyond my sexuality.

I believe that these difficult times of conflict and self-discovery have given me a better chance to think freely and be open minded about life in general.

I am proud i get to learn new opportunities in life disguised as problems.

#pridemonth #pridemonth2021 #proudqueer #Zega #Ethiopian #Ethiopianqueer


ዜግነቴ ኩራቴ #1
ፅናት

ብዙ ጊዜ ስለመጣንበት መንገድ ፣ ስላሳለፍነው ህይወት እንዲሁም በዑደታችን ስላጋጠሙን መሠናክሎች መለስ ብለን ስናስታውስ ቀድሞ ትውስታችንን የሚሞላው ምን ያህል ከባድ እና አስቸጋሪ እንደነበረ ነው፡፡ ነገር ግን ያንን ሁሉ አልፈነው እዚህ የደረስንበትን ጥንካሬአችንን እና ፅናታችንንም አብረን ማስታወስ አለብን፡፡

ከየአቅጣጫው ከህይወት የሚወረወርብንን ጦር በሙሉ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ፣ በብርታትም ውስጥ ይሁን በስንፍና ፣ በራሳችንም ይሁን በሌሎች ርዳታ መክተንም ይሁን አምልጠን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡

አያኮራም?

የነገውንም መሰናክላችንን እናልፍ ዘንድ የእስከዛሬውን ፅናታችንን መለስ ብለን እያየን ለነገ እንበርታ!

ዜግነቴ ኩራቴ!
የዜግነት ክብር




እናንተዬ …. ኧረ እንዴት ከረማችሁ?
በኹሉ ነገር መሐል እንኳን የደህንነት ምኞት እንካችሁ!!!

መፅሔታችን 2ኛ ዕትም ደረሰች እኮ!

በመጀመሪያ ዕትማችን በሰጣችሁኝ ገንቢ እና አበረታች እንዲሁም ገሳጭ አስተያየቶች እንዴት እንደኮራሁ እና እንደተደሰትኩ ብታውቁ! …. ደስስስ ነው ያስባላችሁኝ፡፡ ይኸው ሁለተኛዋንም ለናንተ ለማድረስ ተፍ ተፍ እያልኩ ነው፡፡

የተለያዩ ጉዳዮችን ትዳስሳለች! ለዜጋው ይጠቅማል ፣ ያዝናናል ፣ ያስተምራል ፣ አዲስ ነገር ያስጨብጣል ፣ ያስተዋውቃል ፣ ይሞግታል ፣ ያስቃል ፣ ያስለቅሳል ……. ያልነውን ሁ….ሉ በሚመጥነን መልኩ በዓይነት በዓይነቱ እያሰነዳዳን ነውና …. እናንተም ይኼ ይጨመር ፣ ይኼ ሀሳብ ይነሳ … የምትሉትን በፌስቡክም ሆነ በቴሌግራም ወይም በኢሜይል ላኩልኝ!

ታሪካችንን እንከትብ ፣ ለቀጣይ ትውልድ መሠረት እናስቀምጥ ፣ በዕውቀት የዜግነታችንን ክብር እንጎናፀፋለን!!!

#የዜግነትክብር #መፅሔት #ሁለተኛእትም




የዜግነት ክብር ፡ የፊልም ምሽት (የመጀመሪያው ምሽት!!!)

በመጀመሪያም ምሽቱ እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 “In a Heartbeat” የሚል አጭር ተንቀሳቃሽ ምስል (አኒሜሽን) ፊልም ይዞላችሁ ቀርቧል፡፡

በ Esteban Bravo and Beth David አዘጋጅነት እና ደራሲነት እ.ኤ.አ በ2017 ለተመልካች የቀረበ ሲሆን በአንድ ሼርዊን በሚባል አይናፋር የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ ከጾታዊ ተማርኮው ጋር በሚያደርገው ግብግብ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ልቡ የከጀለውን ልጅ ጆናታንን አይቶ ልቡ ስትመታ ፣ ከዛም እሱን ተከትላ ስትሄድ ፣ ሼርዊንም በተማሪዎች ፊት ምስጢሩ እንዳይታወቅበት ሲጣጣር … ሰዎች ሲጠቋቁመበት ሲያይ ፣ ልቡ ስትሰበር…. የሚያሳይ ልብን ሞቅ የሚያደርግ ደስ የሚል ታሪክ ነው፡፡

ፊልሙ በወጣበት ዓመት በ8 የሽልማት መድረኮች ታጭቶ በ7ቱ ያሸነፈ ሲሆን ፣ በምርጥ አጭር አኒሜሽን ዘርፍም ለኦስካር እጩነት ለማለፍ ከተመረጡ 10 ፊልሞች ውስጥም መግባት ችሎ ነበር፡፡

እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 … ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በዜግነት ክብር ፌስቡክ ገፅ ላይ በቀጥታ ይጠብቁን፡፡

ከያለንበት - አንድ ላይ ሆነን ፈንዲሻችንን ይዘን እንኮምኩም!

የፊልሙ ርዝመት፡ 4 ደቂቃ
ዓይነት ፡ ተንቀሳቃሽ ምስል (አኒሜሽን)

#የዜግነትክብር #ዜጋፊልም #ፊልምምሽት


ሃይ ሃይ ቤተሰብ
እንዴት ናችሁ?

ስሙኝማ…. ሰሞኑን ብዙ ሰዎች ዜጋ ነክ ይዘት ያላቸውን ፊልሞች እንድንጋብዛቸው የሚጠይቁ ፖስቶችን ሲለጥፉ … የምናውቃቸውንም ኮመንት እያደረግንላቸው ነበር፡፡ እኔም እንደ ፊልም አፍቃሪነቴ ከዱሮ ጀምሮ ብዙ የዜጋ ፊልሞችን ያየሁ ሲሆን … በርከት ያሉም እጄ ላይ ይገኛሉ፡፡

ታዲያ እየተቀባበልን ማየታችን እንዳለ ሆኖ … የምወዳቸው ፣ የተዝናናሁባቸው ፣ የሳቅሁባቸው ፣ ያለቀስኩባቸው …. ከተወሰኑ ደቂቃዎች የማይበልጡ ምርጥ ምርጥ አጫጭር ፊልሞች ስላሉኝ …. ለምን በሳምንት የሆነ ቀን ላይ … በተስማማንበት ሰዓት በፌስቡክ ቀጥታ እያጫወትኩ ከእናንተ ከቤተሰቦቼ ጋር በያለንበት ሆነን አብረን አንኮመኩምም ብዬ አሰብኩ…. ጎበዝ አይደለሁ?

እና መቼ እናድርገው?
እስቲ ከእነዚህ ቀናት ውስጥ መረጥ መረጥ አድርጉልኝ ….

https://poll.app.do/movie-night-3087159


“አድራጊ” ሲባል “ወንዳወንድ” ፣ ተደራጊ ሲባል ደግሞ “ሴታሴት” ናቸው ብለን የምንፈርጃቸው ሰዎች ወይም ማንነቶች ቶሎ ወደ ጭንቅላታችን የሚመጡ ብዙዎች ነን፡፡ ነገር ግን ይህን ስል ውስጣዊ ስሜታችን የሚነግረንን ነገርን በመዘንጋት አይደለም፡፡ በፍላጎታችን ወይም መርጠን እነዚህን ነገሮች እንድንባል ወይም በዛ መንገድ እንድንታይ የምንፈልግን ሰዎችም መርሳት የለብንም፡፡ ይህም ስሜት ፣ ፈቃድ ፣ ፍላጎት ወይም ምርጫ ወደምንለው ነገር ያመጣናል፡፡

ወሲባዊ ሚና የፍላጎት ጉዳይ ነው፡፡ ፍቅርም ሆነ ጊዜያዊ የወሲብ ስሜት የሚኖረን አንድን ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ ባየንበት አፍታ ወይም ደግሞ በደንብ ስንላመድ እንደመሆኑ ፣ እነዚህ ስሜቶች በዛ ሰው ወሲባዊ ሚና ላይ የተመረኮዙ አይሆኑም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በማንነቱ ተስበናልና፡፡ ከዛ ዘለል ሲል ነው ሚናችንን የምንተዋወቀው፡፡

ከምንም በፊት ሰዎች ነን ፣ ከዛም በማህበረሰባችን የተገፋን ሰዎች ፣ ከዛ ባለፈ አንድ ዓይነት ፆታዊ ተስህቦ ኖሮን ፣ አንድ ዓይነት ኑሮ እየኖርን ፣ በአንድ ስም እየተጠራን ሌሎች ተጨማሪ የሚከፋፍሉ ወይም ደግሞ ከፍ እና ዝቅ አድርገው የሚያስተያዩንን ክፍፍሎች መፍጠር የለብንም፡፡

ይሁን፡ ስያሜዎቻችን ይኑሩ፡ ነገር ግን ከጀርባቸው ያለውን ትርጓሜ ማስተካከል ያሻል፡፡
በዚህ ግለሰባዊ ነፃነት በሚሰበክበት ዘመን ፣ ዓለም ወሲባዊም ሆነ ሌላ ፍላጎቶቹን በፈለገው መንገድ ፣ እሱን በሚያስደስተው ሁናቴ መግለፅን ባህሉ እያደረገ በመጣበት ዘመን ኋላ ቀሩን እና አንዱን የበላይ አንዱን የበታች አድርጎ የሚያስብ ትውልድ ሊኖረን አይገባም፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በጣም ብዙ ልንኮራበት እና ልንታይበት እንዲሁም ልናከብረው የሚገባቸው ባህሎች እና ትውፊቶች ቢኖሯትም ልንቃወመው እና በተቻለን ሁሉ ለሚቀጥለው ትውልድ እንዳይተላለፉ የምንታገልላቸው መጥፎ እና የአንድን ሰው ሰብዓዊ መብት የሚገፍፉ ስርዓቶች እና ህግጋቶች አሏት፡፡

በእኛ (በዜጎች) ላይ የሚሰነዘረውን ጥላቻ ፣ ስድብ እና ማንቋሸሽ በብቃት ልንቋቋም እና ልንታገል የምንችለው እርስ በእርሳችን በእኩልነት ስንተያይ እና ስንከባበር ብቻ ነው፡፡

ሁሉም እንደየስሜቱ ይተግብር ፣ ሁሉም እንደ ፍላጎቱ ይከበር።

ቸር ያውለን
ቤን ዶሚነስ
©የዜግነት ክብር


ከታ/ቦተም vs ከላ/ቶፕ
ወሲባዊ ሚናዎች ፍላጎት ወይስ ማህበረሰባዊ ዕርከኖች?
(ዶሚነሷ)

ይኼ ወንድን የበላይ ፣ ሴትን ደግሞ የበታች አድርጎ የሳለልን ያደግንበት አባታዊ ስርዓት (Patriarchy) ምንም ያህል እንኳን ነፃ እና ዘመናዊ አስተሳሰብ ቢኖረንም በዚህ በእኛ ከባህላዊው እና የተለመደው የፍቅር ግንኙነት ለየት ባለ መልኩ በእኛው በዜጋው ማህበረሰብ ውስጥም ሰርጎ በመግባት አንዳንድ አላስፈላጊ ልዩነቶችን እየፈጠረ እንደሆነ የምንክደው ሃቅ አይደለም፡፡

በተለይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ሚናችን ላይ በጉልህ ይንፀባረቃል፡፡ ከስም አጠራራችን ጀምሮ “ከላ/ቶፕ” ወይም “ከታ/ቦተም” የሚሉት አመዳደቦቻችን የግንኙነት ሚናችንን ከመግለፅ ባለፈ በህይወታችን ውስጥ የበላይነት እና የበታችነት ስሜትን የፈጠረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ከዛም ባለፈ ከላይ የጠቀስኩትን የአባታዊ ስርዓት መዋቅር እዚህም በማውረድ የ ወንድነት ሚዛን መለኪያ እየሆነ ነው፡፡

እርግጥ ነው ሰዎች በባህሪያችን እና በቋንቋዎቻችን ፣ የዕለት ተዕለት ክዋኔዎቻችንን ለመለየት እንዲያስችለን ነገሮችን የምንለይበት ፣ የምንግባባበት መጠሪያ ፣ መለያ ስያሜ መስጠት ልምዳችን አድርገነዋል፡፡ ነገር ግን የምንሰጣቸው ወይም የምናወጣቸው መጠሪያዎች በተወሰነ መልኩ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩብንም እሙን ነው፡፡

ለምሳሌ “አድራጊ” እና “ተደራጊ” በሚል በእኛው በዜጋው ማህበረሰብ ውስጥ የከፋፈልነው ሚና ፣ ፍትወታዊ ፍላጎቶቻችንን እንድንተዋወቅ እና መግባባትን እንድንፈጥር በሚያስችሉት መጠን ፣ በዛው ልክ በሰፊው ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን እና የተለመደውን የበላይነት እና የበታችነት ስሜት እንደሚፈጥር ግን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
(ይቀጥላል…)


shorturl.at/mqvFI

ሰላም ሰላም ዜጎች!
እንዴት ናችሁ!? እንዴት ሰነበታችሁ!? ሰሞኑን አንባቢ ሆናችሁ እደከረማችሁ አንዲት ወፍ ነገረችኝ፡፡
የዜግነት ክብር መፅሔትን እንዴት አገኛችሁት?
ዕውነት ለመናገር ጠብቄው ከነበረው በላይ ብዙ ሰው ዘንድ ደርሶ በማየቴ ምን ያህል እጅግ ደስ እንዳለኝ … እንዴትስ በዜጋው ማህበረሰብ እንደኮራሁ … እንዴትስ ለሚቀጥለው ዕትም በፍጥነት ወደስራ እንዳስገባችሁኝ …. ደስ ሲል!
ስለ መፅሔቱ ብዙ አስተያየቶችን ተቀብያለሁ ፣ ብዙ ፖስቶችንም አንብቤአለሁ፡፡ መጀመሪያ ላይ ለዚህ ስራ ስነሳም ዓላማዬ የነበረው በመፅሔቱ ይዘት ላይ የሚነሱ ውይይቶችን ፣ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ልምድ ልውውጦችን በመፍጠር አንዳችን ከአንዳችን የምንማማርበትን መድረክ መፍጠር ነበርና … ከሞላ ጎደል በመሳካቱም ደስተኛ ነኝ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡
ነገር ግን አስተያየቶቻችሁ የበለጠ አስራቡኝ፡፡ ተጨማሪ ፈለግኩ
ከዚህ በጣም የተሻለ ፣ የተለያዩ ያልተዳሰሱ ጉዳዮችን ፣ መልስ የሚሹ ጥያቄዎችን ፣ አከራካሪ ሀሳቦችን ፣ የተዘነጉ ጉዳዮችን … ሌላም ሌላም ያካተተ ሁለተኛ ዕትም ይዤ እንድመጣ …. 5 ጥያቄዎችን ብቻ አዘጋጅቻለሁ::

ሊንኩን ይጫኑና መጠይቁን በመሙላት ያሻሽሏት!

shorturl.at/mqvFI
#የዜግነትክብርመፅሔት #ዜጋ


እዚህ ያውርዱ
https://t.me/yezeginetkibir/6


የዜግነት_ክብር_መፅሔት__ቅፅ_ 1_HD.pdf
2.0Мб
የዜግነት ክብር መፅሔት ፡ 1ኛ ዕትም


እልልልል….

እንግዲህ እንትፍ እንትፍ እያላችሁ … ያሳድግልህ በሉኝ! ስትጠብቋት እንደነበር አውቃለሁ …. እኔም ስጠብቃት ነበርና፡፡

ይኸው ጊዜዋ ደርሶ ከች ብላለች፡፡ ብዙ ከባድ አይደለችም … ያን ያህል ፍራንክም አትፈጅም ፡ የሴንዶች ዳውንሎድ ብቻ፡፡

ሼር ማድረግም እንዳትረሱ ደግሞ!

በፌስቡክ | ኢንስታግራም | ትዊተር እና ቴሌግራም ላይ /YezeginetKibir ብለው ያገኙናል!

ክብር ለሁሉም!



Показано 18 последних публикаций.

232

подписчиков
Статистика канала