🙏ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬ🙏


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Эзотерика


ገና እንዘምራለን እንደ መላእክቱ
ብርሃንን ለብሰን ገና እንዘምራለን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርሰቲያን አሰተምሮ ና ሰርአት የጠበቁ
✥👉መንፈሳዊ ትምህርቶች
✥👉መንፈሳዊ መዝሙሮች
✥👉መንፈሳዊ ንግሰ እናሳዉቃለን
✥👉መንፈሳዊ ምክር ነክ ፁሁፍ
✥👉መንፈሳዊ ታሪኮች
📢ለማስታወቂ ሥራ @Mane_tekel

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Эзотерика
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
🗓ድጓ ከምን ያድናል❓🧠
አንድ መናፍቅ  ታላቁን የድጓውን መምህር የናቀ መስሎት "የኔታ ድጓ ከምን ያድናል "ሲል ጠየቃቸው እሳቸውም ቀበል አድርገው "እንዲህ ከማለት ያድናል" አሉት ይባላል።
↗️#ድምፀ_ተዋህዶ ↗️


✞ በዋጋ ገዝተኸኛልና ✞


በዋጋ ገዝተኸኛልና
ስለኔ ደም ከፍለሃልና
ልሳኔ ያውጃል ክብርህን
አረሳም ጌታ ውለታህን


ሕይወት ሰላሜን ትቼ
የማይታይ አይቼ
ላንተ ብሰጥ ጀርባዬን
ልተዋወቅ ጠላቴን

የጠበቀኝ ውጊያ ነው
የተረፈኝ ፀፀት ነው
የሻረልኝ ቁስለቴን
ተሰቅሇህ ነው አባቴ

አዝ...
እጓዛለሁ በምናብ
ወደሰላሜ ወደብ
እጄን በአፌ እጭናለሁ
ዛሬም እፁብ እላለሁ

ለክብርህ መሠለፌ
በለመለሙ ማረፌ
ዋጋ ከፍለህ ነው ጌታ
ያኖርከኝ በፀጥታ

አዝ...
ከውሃና ከመንፈስ
ተወልጄ ከመቅደስ
ልጅህ ሆንኩኝ ዳግመኛ
የመስቀልህ ሙርከኛ

ባንተ ሰለመዳኔ
ምስክርህ ነኝ እኔ
ላይታጠፍ ምላሴ
እቀናሇሁ በነፍሴ


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex)መፈጸም ምን ችግር አለው❓
      
          (ክፍል ሁለት)


🔸የተከበርክ ወንድማችን ፍቅራችሁን በመሳሳም ልትገልጹ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን #መሳሳምእሳትላይጋዝእንደማርከፍከፍ ነውና “ እውነት ይሄ መሳሳም ፍቅራችሁን ብቻ ገልጻችሁበት ታቆማላችሁ?” የሚለው ይታሰብበት፡፡ ዕለቱኑ ወደ sex ባያመራም መሳሳምን ከለመዳችሁ በኋላ ደግሞ ሰው ለውጥን ይፈልጋልና " የተሻለ የፍቅር መግለጫ" በማለት ወደሩካቤ ( sex ) ታመራላችሁ፡፡ መሳሳምን መቋቋም አቅቷችሁ እንደፈጸማችሁት ሁሉ sexንም የማትፈጽሙበት ምንም ዋስትና የላችሁም፡፡

🔸መዘንጋት የሌለብህ ግን የፍቅር መግለጫም ይሁን የአክብሮት መግለጫ #ሰላምታችንክብርያለው እንዲሆን #ቅዱስጳውሎስ በመልእክቱ ይመክረናል:- “ ክብር ባላት ሰላምታ እርስ በርሳችሁ ሰላም ተባባሉ፡፡” 2ኛ ቆሮ 13 ፤ 12፡፡ መሳሳም ዓለም ነገሩን አስረስቶ እጅግ ወደሚያስጠላ ፣ #ክብርምወደጎደለውድርጊት ያመራልና ይህ ይታሰብበት፡፡

🔸ለፍቅረኛ ፍቅርን ወይም ስሜትን ለመግለጽ ያለው
#የተሻለአማራጭስ መሳሳም ወይም መተሻሸት ነው እንዴ? ፍቅረኛህን ስታገኛት #ሥጦታ ይዘህላት መሄድ ፣ ሁሌም #እንደምትወዳት መንገር ፣ በጨነቃት ወይም ባዘነች ግዜ #ከአጠገቧመሆን… እና የመሳሰሉት የፍቅር መግለጫዎች አሉ፡፡

#ታድያ በሰላም አገር ይሄን ሁሉ ፈተና በፈቃዳችሁ ከምትስቡ መሳሳሙ ቢቀርባችሁ አይሻልም! ደግሞስ የምትተማመኑ ከሆነ መሳሳሙ የት ይሄድባችኋል!

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ከትዳር በፊት “ሩካቤ መፈፀም በቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ እንዴት ይታያል?” የሚለውን እንመልከት፡፡ ለድንግልናችን ክብር የማንሰጠውና ድንግልናችንንም የማንጠብቅበት አንደኛው ምክንያት
#የድንግልናንጥቅምበአግባቡአለመረዳት ነውና የድንግልናን የነፍስና የሥጋ ጠቀሜታዎቹን በአጭሩ እንመልከታቸው፡፡

🔸ከእግዚአብሔር ዘንድ #የድንግላችንንዋጋ እናገኛለን፡፡

🔸በአግባብ
ለመኖር - በድንግልና መኖር ሕግና ሥርዓት እየፈፀሙ በአግባቡ ለመኖር ይጠቅማል፤ ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ሕጋዊሰው ሆኖ  መኖርን ያለማምዳል፤

🔸ሳይባክኑ መኖር - በድንግልና የሚኖር ሰው አይባክንም፡፡ ወዲህና ወዲያ አይልም፤ ወንዱ የሴት ገላ ፍለጋ ጊዜውን አያባክንም፡፡ ሴቷም ያማረ ቁመና ያለው ወንድ ፍለጋ ጊዜዋን አታባክንም፡፡
#ሁሉምበጊዜው እንደሚሆን አምነው መደረግ ያለበትን በትክክለኛው ጊዜ እየሰሩ ይኖራሉ እንጂ፡፡

🔸ድንግልናን መጠበቅ #በሃይማኖትያጸናል -  ድንግልናን ለመጠበቅ የቆረጠ ሰው #ሃይማኖቱንበመጠበቅና #ለፈጣሪውባለውፍቅር ፀንቶ ይኖራል፡፡ ድንግልናን  መጠበቅ በራሱ ፅናትንና ትዕግስትን ይጠይቃል፡፡

🔸ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ታማኝነትንያረጋግጣል - ምክንያቱም ድንግልና በሥርዓት ጠብቀን እንድንይዘው #በአደራእንደተሰጠንየከበረንብረት ነው፡፤ ባለአደራው ፈጣሪያችን በሚያስፈልግ ግዜና ሰዓት ለትዳር አጋራችን እንድንሰጠው ይጠበቅብናል፡፡

🔸ድንግልናን መጠበቅ #መጠንቀቅ ነው - በድንግልና የኖረ ከበሽታ ፣ ካልተፈለገ እርግዝና፣ ከፀፀት እና በአጠቃላይ ለወደፊት መንፈሳዊ ሆነ ስጋዊ ችግር ከሚፈጥሩ የኑሮ ጠንቆች ይጠበቃል፡፡

🔸ባል የሚስቱን ማኅተመ ድንግልና ሲያገኝ ደስ ይለዋል፤ ሚስትም ባሏ እሷ የመጀመርያው እንደሆነች ስታውቅ ትደሰታለች፡፡
-  ድንግልናን ካጠፉ በኋላ የሚደረግ ጋብቻ አግብቶ የፈታ ሰው እንደሚፈፅመው እንደ ሁለተኛ ጋብቻ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም የተጋቡ ሰዎች ብቻ ሊፈፅሙት የሚገባውን ሩካቤ-ሥጋ ከጋብቻ በፊት ፈፅሞ በመገኘቱ ነው፡፡

🔸ድንግልናን ጠብቆ መኖር #ጋብቻሳይዘገይ በጊዜው እንዲፈፀም ይገፋፋል፡፡
-  ማንኛውም ጤናማ ሰው የተቃራኒ ፆታ አቻውን የመሻት ዝንባሌ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ዝንባሌውን እና ድንግልናውን ጠብቆ መኖር የሚታረቅለት ሲያገባ ነው፡፡ እናም ድንግልናውን ጠብቆ እስከጋብቻ ለመቆየት ዓላማ ያለው ሰው በውስጡ ያለውን የፍትወት ግፊት ለማብረድ ሲል ሊያገባ ይችላል፡፡ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ሩካቤ የጋብቻን ቀነ ቀጠሮ እንዲራዘም ከማድረጉም በላይ ለመለያየትም በር ከፋች ነው፡፡

       •••
#ይቀጥላል •••

        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆


#ሥርዓተቤተክርስቲያን!!!

#ጥያቄ፡- በቤተ-ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለጋብቻ የሚፈቀደው አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ነው፡፡ እና አንድ ልጅና አንዲት ልጅ ከልብ ተዋድደው ሊጋቡ ነው፡፡ ከመዋደዳቸው የተነሳ ሳይተያዩ ካደሩ ምግብ አይቀምሱም፡፡ ሥራ መሥራት አይችሉም፡፡ ብቻ ስሜት የሚባለው ነገር በጣም ገኖባቸዋል፡፡ በቤተ-ክርስቲያችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል? ነው ወይስ የራሱ እስከሆነች የራሷ እስከሆነ ድረስ ምንም ቢያደርጉ ኃጢአት አይሆንም? ከትዳር በፊት #መሣሣም ( የከንፈር ወዳጅ / kiss ) ወይም ሌሎች የስሜት መግለጫዎችን መፈፀም ይቻላል? ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚዋደዱ ከትዳር በፊት #ሩካቤ ( #sex ) መፈፀምስ ምን ችግር አለው?

#መልስ፡- ውድ ጠያቂያችን ከሁሉም አስቀድመን የድንግልናን እና የጋብቻን ትርጉም መረዳት ያስፈልገናል፡፡ ድንግልና የሚለው ቃል ተደንገለ፣ ተጠበቀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጠበቅ ማለት ነው፡፡ ሰው ድንግል ሲባል ወንድ የማታውቅ (sex ፈጽማ የማታውቅ) ልጃገረድ ወይም ሴት የማያውቅ (sex ፈጽሞ የማያውቅ ) ወንድ ማለት ነው፡፡ ሰው ከሩካቤ ሥጋ ( sex ) የሚጠበቀው እስከጋብቻው ወይም እስከሕይወቱ ፍፃሜ ነው፡፡ እግዚአብሔር ጋብቻ ክቡር መሆኑን ያስተማረን ድንግልናን ሰጥቶን ነው፡፡ ስለዚህ #ድንግልና ማለት እስከጋብቻ ድረስ በጥንቃቄ የሚያዝ #የክብርዕቃ  ፤ #በዕለተጋብቻ ለትዳር አጋራችን የምናበረክተው #ውድሥጦታ ማለት ነው፡፡

በመሰረቱ #የሩካቤስሜት ተፈጥሮአዊ በመሆኑ አብዛኛው ሰው በዚህ ስሜት ይፈተናል፣ ለምን ይህ ስሜት ተሰማህ ተብሎም አይወቀስም፤ ነገር ግን የሩካቤ አፈፃፀም #በሥርዓት እንዲሆን #ክርስትናችን ያስገድደናል፡፡ ይህም ማለት እስከጋብቻ ድረስ በድንግልና ቆይተው ከዚያ ከጋብቻ በኋላ ሩካቤ እንዲፈጽሙ ነው፡፡ በዚህ ግዜ  ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል ይፈጸማል፡፡ “ #ጋብቻክቡር ነው ፤ #መኝታውምንጹህ ነው፡፡” ዕብ 13፣4፡፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ጋብቻን የሰራበት አንዱ ምክንያት የሩካቤ ስሜት ስላለ እና ይህም ይፈፀምበት ዘንድ ነው፡፡
✝️✝️✝️

✅ከጋብቻ
በፊት የሚደረግ #መሳሳም እና #መተሻሸት ወይም ሌላ የስሜት መግለጫ

🔸ከጋብቻ በፊት የሚፈፀም መሳሳምና መተሻሸት ለግብረ ሥጋ ግንኙነት መንገድ ይከፍታል፡፡ ውድ ጠያቂያችን:- #እጅግርቦህ እያለ #እጅግየጣፈጠ ምግብ ከፊት ለፊትህ ቢቀመጥ ከዚያ #የምግቡመዓዛ መጥቶ አፍንጫህን ጎብኘት ቢያደርገው ሆድህ እየጮኸ ዝም ትላለህ? መሳሳምም እንዲሁ ነው፡፡ ውስጥህ #የወጣትነትስሜት እየታገለህ ፣ ከፊት ለፊት ደግሞ #የፍቅረኛህመዓዛ እያወደህ ፣ #ከንፈርህንከከንፈሯ አጋጥመህ ከዚያ ምን የሚቀጥል ይመስልሃል? “ ለዛሬ ይበቃናል:: ” ትላላችሁ? “ ከጋብቻ በፊት sex አንፈጽምም አይደል!? መሳሳምና መተሻሸት ብቻ፡፡” ትላላችሁ? በፍጹም፡፡ ወደመሳሳምና ወደመተሻሸት ያደረሳችሁ የወጣትነት ስሜት ወደሩካቤ ይመራችኋል ፤ ምክንያቱም ያንን ጣፋጭ ምግብ አስብና ምራቅህን ላለመዋጥ ሞክር፡፡

       ••• #ይቀጥላል •••

        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆


✞ ቤተክርስቲያንን ✞

ቤተክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ 
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
አዝ

ሁሉንም በሁሉ በሚሞላው ጌታ 
ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ 
በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ 
ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ/2/
አዝ

ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ
ወጥመድ ቢዘረጋ በጉዞአችን ሁሉ
እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን 
አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን/2/
አዝ

በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት 
ስለ ስሙ መኖር ለስሙ መሞት 
ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት 
ይህ ነው ክርስትና ይኼ ነው ሕይወት/2/
አዝ

ከትውልድ ለትውልድ የምናስረክበው
ለልጅ ልጅ አውርሰን ደስ የምንሰኘው 
አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት 
ሃይማኖታችን ነው የእኛ ርስት ጉልት/2/

ዘማሪት  ፋሲካ መኮነን
💚@zmaredawt_zeortodocs💚
💛@zmaredawt_zeortodocs💛
❤️@zmaredawt_zeortodocs❤️


✞ ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር ✞

ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር
የአበው ቅዱሳን ምድር
ህዝቦች ሆነው ሰላምን
ኑሪልን ለዘላለም x2

አዝ

ከመጀመሪያው አብሳርሽ
ከጃንደረባው ባኮስ
በኋላም እውነትን ካስፋፋው
እስከ ሰላማ ድረስ
ወንጌልን ሰምተሽ ኢትዮጵያ
በተሰአቱ ቅዱሳን
ዛሬም ጠብቀሽ ይዘሻል
የነገው ትውልድን እንዲድን

ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖቴ x2


አዝ

ብዙአላውያን ነገስታት
ሊያጠፉሽ ታትረው ቢነሱ
ሰይፍና ጎመድ ቢመዙ
ቅዱስ ስፍራሽን ሊያረክሱ
የሚጠብቅሽ አይተኛም
የምታመልኪው እግዚአብሔር
ዘላለም ላንቺ  ብሩህ ነው
አይሰራም ያህዛብ ምክር

ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖቴ x2


አዝ

ባጥንትሽ ብዕር አቅልመሽ
በደምሽ ቀለም ያስተማርሽ
ፊደልን ቀርፀሽ ያቆየሽ
የእውቀት ገበታን አንቺ ነሽ
ዘመንን ሰርተሽ ለትውልድ
ወንጌል የሰበክሽ በፍቅር
ተዋህዶ ነሽ ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያም ሀገረ እግዚአብሔር

ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖት x2


አዝ

በተዘረጉት እጆችሽ
እግዚኦ ባልሽው ተማጽኖ
ምህረት ሆኗል ለህዝብሽ
አምላክ ቀርቦሻል ባድኖ
ለሊት እና ቀን በምልጃ
ሰርክ እና ነገን በጸሎት
እየማለደሽ ዘወትር
ለህዝብሽ ሆኗል አብረሆት

ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሀይማኖት x2


አዝ

ወርቅ ላበደረ ጠጠር
ነገሩን አበው እንዲሉ
ጠላት በማይተብሽ መጣ
ስለሚሰበቅ መስቀሉ
እውነትን እንገልጣለን
ስላንቺ ክብር ላልሳማ
እየነደድሽ እንዳበራሽ
እየቀለጥሽ እንደሻማ

ሰማያዊት ናት እርስቴ
ተዋህዶ ናት ሃይማኖት x2


https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


✞ ሶበ ተዘከርነሀ ለጽዮን ✞

ሶበ ተዘከርነሀ ለጽዮን [፪]
ውስተ አፍላገ ባቢሎን እየ
ነበርነ ወበ ከይነ እንዚራቲነ
ሰቀልነ ውስተ ኩይሀቲያ [፪]

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን [፪]
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠናል አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ [፪]

ጽኑ መከራ ተቀበልን ተጨንቅን በፈተና
የደውይ ሞት በላያችን እንደ ዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘመሩለት ለአምላካችን ቢያድናቸው ከመከራ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግሥቱ መርጧታልና ማደርያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤቴ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

    
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለ ፍርሀት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረን የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግሥቱ መርጧታልና ማደርያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤቴ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

    
ስጋችንን ይገል ዘንድ የሞት ጥላ ቢያጠላ
እናልፋለን ሁሉን ባ'ንቺ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን እንድናለን ከድዌአችን
ለስጋና ለነፍሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን

እግዚአብሔር ጽዮንን....
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን.....


https://t.me/zmaredawt_zeortodocs
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::

     (መልክዐ ገብርኤል)

"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †

       (ዳን. ፱፥፳)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ የሆነብንን አስብ

#ድምፀ_ተዋህዶ


ይኸው ተወለደ


ይኸው ተወለደ የዓለም መድኀኒት /3/
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኀኒት /3/
አዝ
ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ /3/
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ /3/
አዝ==========

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ /3/
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ /3/
አዝ==========

ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው /3/
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው /3/
አዝ
ምዕመናን እንሂድ ከልደቱ ቤት /3/
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት /3/
አዝ==========

በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ /3/
ብሥራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ /3/

https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


ቸርነትህ ብዙ


ቸርነትህ ብዙ ምሕረትህ ብዙ
በጉዟችን እርዳን ጠባብ ነው መንገዱ
ድንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለእኛ
ድንቅ ነዉ ለእኛ አንተ ነህ መልካም እረኛ

አስራኤል ወደቀ እስራኤል ተነሳ (2x)
መንገዱ አልቀናውም አምላኩን ቢረሳ (2x)
የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔርን ይዞ (2x)
ምን እንዳተረፈ አውቆታል በጉዞ (2x)
አዝ==========

መንገዱ አይታክትም ጎዳናዉ የቀና (2x)
እግዚአብሔር በፊትም ከኋላሞ አለና (2x)
እርሱ በሌለበት ቢመችም መንገዱ (2x)
አቅጣጫው ወደ ሞት አይቀርም መውሰዱ (2x)
አዝ==========

በመንገዱ ዝለን ወድቀን መች ቀርተናል (2x)
የያዕቆብ አምላክ ደግፎ አንስቶናል (2x)
እግዚአብሔር ሲጠራን በቀደመው መንገድ (2x)
ጉዞአችን ወዴት ነው በሞት ለመወሰድ (2x)
አዝ==========

አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልባችን ሳለው (2x)
እስከሞት በመስቀል የወደደን ማነው (2x)
በበረሃዉ ጽናት ሲጸናብን ርሀቡ (2x)
በረከት ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ (2x)

https://t.me/zmaredawt_zeortodocs




Репост из: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
የቀድሞው ዘማሪ ሐዋዝ ተገኝ ወደ ቀደመው የአባቱ ቤት ወደሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ተመልሷል
***

በተ*ዶሶ እንቅስቃሴ ላይ የነበረው የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘማሪ የነበረው ሐዋዝ ተገኝ

ቀድሞ ያገለግልባት ወደነበረችው ቅድስት እና ንጽሕት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ መቅደስ በንሰኃ ጥምቀት ተመልሷል።

እግዚአብሔር ይመስገን !!!

#ድምፀ_ተዋህዶ


ነገ ኅዳር 16 ኪዳነ ቃሏ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ናት እንኳን አደረሳችሁ።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትጠብቀን።🙏
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
@zmaredawt_zeortodocs
✨✨✨✨✨✨✨✨✨


MUUDAMEERA MIKAA'EEL

Muudameera Mikaa'eli
Kan nuun loluu kufeera saaxnaa'eeli (2)
Kan nu gargaaru muudameera Mikaa'eli(2)

Karaa keenyaa isat geggeessaa
Harkaa diinatti yoom nuun nu dhiisa
Mikaa'el jechuun isa waammanna
Araarsummaasaas nut nii amanna


Maqaan Waaqayyoo kan irra jiru
Yeroo rakkinaa kan nama furuu
Kabajni isaa akka aduu ifaa
Fayyina fidee garkeenya dhufaa

Fuuldura bala'aam inni dhaabbateera
Abaarsi darbee Eebba ta’eera
Saba Waaqayyoof inni ni dhaabbataa
Qulqulluu Mikaa'el hangafa Ergamoota


Daandii jireenyaa nutti agarsiisa
Galaanaa du’aa hiree nu ceesisaa
Mootummaa Waaqayyoof inni nu qopheessa
Mikaa'el jechuun ni waamna maqaasaa

Sher tasisaa


✞ቅድስት ሐና✞

መርአተ ኢያቄም ፀጋዊተ ህይወት
ቅድስት ሐና  ብርሃን ለፍጥረት
አዝ
ሐና ኅሪት ወለተ ብሩካን
የወለደች ለኛ ቅድስት ቅዱሳን
አሰራሯ ያማረ የምስክር ድንኳን/2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ሐና ቡርክት ወለተ ቡሩካን
ለፍጥረት ያስገኘች የሚያበራ ተስፋን
በሐዘን ለነበርን ማይቋረጥ ደስታን /2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ሐና  ቅድስት ንግስተ ሃይማኖት
ተስፋ የወለደች በስለት በጸሎት
ለደከመው ዓለም በመድኃኒት እጦት /2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/
አዝ==========
ብፅዕተ ብፁዓን እናታችን ሀና
እመ ማርያም ይድረስሽ ምስጋና
አወድስሻለሁ በፍጹም ትህትና/2/
ተፈፀመ ሐና በወለትኪ
ተስፋ ቅዱሳን አበውኪ /2/

ዘማሪ ዲ/ን ማኑሄ ዳዊት


✞ከሊባኖስ✞

ሐና እና ኢያቄም ወለዱ ሰማይ
አዲሷም ሰማይ አስገኘች ፀሐይ
ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
#ከሊባኖስ ድንግል ነይ ወደኛ(፪)

ተጨነቀ አዳም በመከራ
በእርግማን ቀን ለቅሶ እየዘራ
በልጅሽ ሞት ዓለም ተቀደሰ
የፍጥረቱ ዕንባ በመስቀል ታበሰ(፪)
አዝ= = = = =
የሕያዋን እናታቸው ሆነሽ
ለቀደመች ሔዋን ጠበቃ ሆንሽ
ደስተኛዋ ደስ ይበልሽ ማርያም
ከአንቺ ወጣ የዓለሙ ሰላም(፪)
አዝ = = = ==
ጽኑ ገመድ በአንቺ ተቆረጠ
የፍዳ ዓመት ይኸው ተለወጠ
በሐና ልጅ በኢያቄም ፍሬ

በወለዱሽ በሐና በኢያቄደስታ ሆነ ቅኔ እና ዝማሬ(፪)
አዝ= = = = =
ተማጽነናል ድንግል ማርያም
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ልጆችሽን ጠብቂን ከጥፋት
ከአዳኝ ወጥመድ ከክፉ ጠላት
ኢትዮጵያን ጠብቂያት ከጥፋት


ዘማሪ ዲያቆን አቤል


✞ የጽዮን ደጆች ✞

የጽዮን ደጆች ቅኔ ተሞሉ
ለድንግል ክብር እልል እያሉ
አንደነጭ እንቁ የሚያበራ
አልፈናል ስሟን ስንጠራ/2/

ሀይልን ለሚያደደርገው ለተወዳጅ ስምሽ
የዜማ እቃችንን አነሳን ልጆችሽ
መሀተበ ቡራኬሽ በልባችን አለ
አፋችን ማሪያም ሲል ጭንቃችን ቀለለ
           
         አዝ=====

የምስጋና ጥበብ የቅኔ ሀብት ጸጋ
ከደጃፍሽ መጥተን ገዛን ያለዋጋ
ጥልቁን ለቀነዋል በትከሻሽ ሆነን
ጽዮንን በእልልታ በዜማ ሸፍነን
          
        አዝ=====

ጠቢባን ምክራቸው ታየ ተሰውሮ
ሚስጢር ተገለጠ በህጻናት አእምሮ
ቤተልሔም ሰማች የብስራቱን ዜማ
ፍቅር ተለቀመ ከእግዚአብሔር ከተማ
            
         አዝ=====

ከአሸናፊው ልጅሽ ከክርስቶስ ጋራ
አንደዘበት ወጣን የሞትን ተራራ
ፍሬሽን ቀመሰነው ልቦናችን ረጋ
ሰላም ነው ከእንግዲህ አንኖረም ስንሰጋ

https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


ወደ ቀድሞ ነገር

ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ
የአምላክን እናት እናወድስ
ከፍቅሯ ርቃችሁ የምትኖሩ /2/
ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ /2/

ቃል ተጽፎባታል የመዳኛ ፊደል ጥበብየሚሞላ ጨለማን የሚሰቅል
ለቃል ስጋ መሆን ምክንያት ስለሆነች
ቀርባችሁ ተማሩ ማርያም ፊደል ነች


አዲሱ ቃልኪዳን ከላይ የተጻፈው
በገሊላ ናዝሬት ገብርኤል ያበሰረው
በማርያም እቅፍ ላይ ታገኙታላቹ
የሚስጢር መዝገቡን አንብቡ ገልጣቹ

ያዘለችው ወንጌል ቃሉ ያፈውሳል
አምኖ ላነበበው ነፍስ ያለመልማል
በጀርባዋ ያለው እግዚአብሔር ነውና
አቅርቡ ለማርያም ውዳሴ ምስጋና


ቡዙዎች ተማሩ ስሟን እየጠሩ
በአባታቸው መንግስት እንደ ጸሀይ በሩ
ክብረ ልዕልናዋን ገብርኤል ነግሮናል
ካወደሷት ጋራ ለክብሯ ቆመናል

9.8k 0 104 1 84

🌹 “ማርያም ማርያም“ 🌹

ማርያም ማርያም ልበል
እረፍቴ ሆይ በስምሽ ልጠለል
የቃል እናት ያድናል ቃልሽ
ታምር ይሰራል ስምሽ


አዝ==========

ማር ልበል በምድር ያም ልበል በሰማይ
የማይጠግቡት መና የማይጨርሱት ሲሳይ
መንፈስ ቅዱስ ቃኝቶ ሰርቶ በሚስጥሩ
አፌ ላይ ጣፈጠኝ ስምሽ አጠራሩ (2)

አዝ==========

መዳኒት ታቅፈሽ የአለሙን ጌታ
ከቤተልሄም ደጅ እስከ ጎለጎታ
የዓለሙን ህምም የዓለሙን በሽታ
ታክሚው ነበረ ድንግል በዝምታ (2)

አዝ==========

በምን እንመስልሽ የለሽም ምሳሌ
አንጠግብም ብንጠራሽ ብንዘምርልሽ ሁሌ
ምስክር አያሻም ያንቺ ልእልና
የአለሙን ንጉሥ ወልደሺዋልና (2)

አዝ==========

የወርቅ ማእጠንት እሳት የታቀፍሽ
የአዲስ ኪዳን ኪሩብ ማርያም አንቺ ነሽ
የአርያም እጣን ነሽ መአዛሽ ያማረ
ዘላለም አይወድቅም አንቺን ያከበረ (2)

🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺🕊🌺
https://t.me/zmaredawt_zeortodocs


✞ ዮም ፍስሐ ኮነ ✞

ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን - - - ፍስሐ ኮነ
ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ
ልትሆኚው እናቱ - - - ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ

አዝ = = = =

የሔዋን ተስፋዋ - - - ፍስሐ ኮነ
የአዳም ዘር ህይወት - - - ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ
ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ
የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ

አዝ = = = =

በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ
የአለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ

@zmaredawt_zeortodocs
@zmaredawt_zeortodocs
@zmaredawt_zeortodocs

Показано 20 последних публикаций.