🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
ҒϴᏞᏞϴᏔ ϴΝ ҒᎪᏟᎬᏴϴϴᏦ = https://www.facebook.com/fikrenbegtm
ᶠᵒʳ ᵃⁿʸ ᵖʳᵒᵐᵒᵗⁱᵒⁿ
= +251931374891
= t.me/Abate_Hiwote

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


⚽️⚽️ ለቤቲንግ ተጫዋቾች በሙሉ  መልካም የሆነ ዜና አለኝ
📭እነሆ እሰከ ዛሬ ድረስ ቤቲንግ ስትጫየ
ወቱ እናም ብዙ ጊዜ ብራችሁን የገፈገፋችሁ ሰዎች በሙሉ ከእዚህ ቡሀላ ሁል ጊዜ fixed ticket የሚሳካበት ቻናል ውስጥ ገብታችሁ ከፍተኛ ብር💶💵💸 አሸናፊ ሁኑኑ።።።።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???


🆕 🆕 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

➕➡️ የ ቻናል ማስታወቂያ
➕➡️
የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
➕➡️
የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
➕➡️
የ ድርጅት ማስታወቂያ
➕➡️
የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
➕➡️
ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች

💻 እንዲሁም የተለያዩ የ Business 🆕🆕 ስራወችን ከእኛ ጋ መስራት ለምትፈልጉ በራችን ክፍት ነው ። 🔸

🔺 ምርትና አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለብዙሀኑ ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ።

ከ እኛ ጋ በመስራትዎ ይደሰታሉ። ❤️

አሁኑኑ ያናግሩን 👇⬇️⬇️⬇️

❓ •    @Abate_Hiwote
.   +251931374891
.   +251912453800


የክረምት ጭቃ


ዝናቡ ዘነበ መሬት በሰበሰ ፣
ብርዱም እያየለ እሸት አሰጠበሰ ፣
የተጣለውንም Rain ኮት አስነሳ ፣
በትሸርት ሃጁን ጃኬት አስለበሰ ፣
ነገርግን ኣንዳንድ ሚያሳልፍ አለ ከዚህም የባሰ ፣

ዝናብ ማይበግረው ቢዘንብበትም ዶፍ ፣
ብርዱ የሚሞቀው እሳት ሚመስለው ጎርፍ ፣
የክረምቱ ጭቃ የሚመስለው ምንጣፍ ፣
አለ የሚዋኝም ፍቅር በሚሉት ወልፍ ፣

ለኣፍቃሪ ሰዎች ሁሌም ክርምት ነው ፣
ብርድ ብርድ ይለዋል ተፈቃሪን ሲያጣው ፣
ጃኬቱን ቢደርብ እሳቱን ቢሞቀው ፣
ከአካሉ አልፎ ለልቡ አይደርሰው ፣
ሻዩንም ቢጠጣ ቡናውን ቢደግመው ፣
ከአካሉ አልፎ ልቡን አያሞቀው ፣
ሁሌም ይበርደዋል በፎንቃ ያለ ሰው ፣

ባካችሁ ተረዱ የተፈቀራቹ ፣
በብርድ አይገረፍ ሰው ያሳዝናቹ ፣
በክረምቱ ጭቃ እያስዘፈቃቹ ፣
ብቻውን እንዲስቅ ስንቱን ጋበዛቹ ፣
ስንቱንስ ጤነኛ እብድ አስመሰላቹ ፣
ክርምቱን በጋ ነው ማለት ጀምረዋል ኣሁን ኣንዳንዶቹ ፣

እያለ ያወራል የክረምቱ ጭቃ ፣
ልቡ ነጉዶበት  ተይዞ በፎንቃ ፣
ያንን ነጩን ወተት ያለውን በእቃ ፣
ጥቁር ነው እያለ በአራት ነጥብ ደምድሟል በቃ ፣


         ግጥም


Semer muhidin
/Almeshan

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

4k 0 24 1 23

━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ከፈገግታ ጀርባ


ልሳቅ እንዳመሌ ሁሌም ልፍለቀለቅ
የፊቱም የኋላ ጥርሴ ወቶ እስክያልቅ
የውስጤን ልብ ምት በጥርሴ ልደብቅ
ችግሬን ጉዳቴን ማንም ሰው እንዳያቅ
ይህም ያልፋል በሚል ተስፋየን ልሰንቅ
😅😅😅😅😅😅😅😅😅😅
ማን ቀርቦ ጎበኘው የልቤን ትርታ
ደህና መሠልኩንጂ በፊቴ ፈገግታ
የሳቀ ሰው ሁሉ ከተሰማው ደሰታ
አልቃሽ አይገኝም ሳቅን ትቶ ላፍታ
💔💔💔💔💔💔💔💔💔
ሁሌም የምስቀው ጠፍቶኝ አይደል እንባ
ጤፍም ከፍሬው ይልቅ ብዙኣለው ገለባ
በሰላም ያለእንከን ወጥቼም ብገባ
ደም ነው የማለቅሰው ከፈገግታ ጀርባ
ደም ነው የማለቅሰው ከፈገግታ ጀርባ
👀👀👀💔💔💔💔💔👀👀👀


ግጥም  Śemeř muhidin/Ãlmeshan


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

8.5k 0 111 1 88

━━━━━━━✦✦━━━━━━━

የናፍቆት መዶሻ ®

ባካል ተራርቀን የናፈቅሽኝ ለታ
ልቤ ይሰቃያል ያጣና እርጋታ
ሆዴም የሚራበው አይደለም ገበታ
ናፍቆቱ ነው እንጂ ልቤ ኣንቺን አጥታ
ቀልቤ ትረካለች ኣንቺን በማየቷ
ውሃ እንኳ ባትጠጣ ይጠፋል ጥማቷ
ልቤ ያጣጥማል በቀንም በማታ
በክፉም በደጉም ሄዶ በትውስታ
አብረን እየኖርን ያለፍነው ትዝታ
እማ የኔ አለም የልቤ መንገሻ
የሂይወቴ ማማር መነሻም መድረሻ
ሌላሰው አይደለም ኡሚ ኣንቺ ነሻ
የእንጀራ ነገር ማራራቁን ሲሻ
እኔን ካንቺ ኣርቆ አርጎኝ ሆደ ባሻ
ይቀጠቅጠኛል የናፍቆት መዶሻ

Semer  አል ጋዚ ...

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

11k 0 141 3 77

እንኳን ለጌታችን
ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ
የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !


ልካም በዓል 🙏

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ውበት ቃል ቢኖረው አውቃለው ልክሽ ነው
ማስተዋል ስም ኖሮት ቢጠራም ባንቺው ነው
ቁመትም ቢለካ ውበትስ ቢመዘን
እንድ አንቺ ጋር ሚደርስ አላቅም በዘመን
ታሪክ ያወራሉ ታሪክ ይነገራል
በጨርቅም ሸራ ላይ ስዕልስ ይቀራል
ስዕልስ ይቀራል በጨርቆች ሸራ ላይ
እንዴት አመለኩሽ ከአምላኬ በላይ
ድርሳን ተፃፈለሽ ያለምንም ገድል
ሴት አምላክ የሆንሽው በልባችን በኩል

ጠዋት 3ሰዓት ላይ ጥለሺኝ ስትሄጂ
ከግቢ ስትወጪ
ምትሸጪኝ መሰለኝ በ30 ዲናር ዳግም ማትመጪ
ትዝ ይልሻል ውዴ ያኔ ተቀምጠን
ምን አንዳልኩሽ ያኔ
ትናቴም ይፈርሳል, ዛሬዬም ይወድቃል
ነገ ያልኩት ሁሉ ብቻውን ይቀራል
ትናፍቂኛለሽ ብዬ ነግሬሽ ነበር ያኔ ስትለይኝ
ክብደቱን ሳላውቀው ነበር  ያልኩሽ ያኔ አሁን ይቅር በይኝ
ትናፍቂኛለሽ ከአምላኬ በላይ ከደመኛዬ እኩል
7 ቀን ሆኖሻል ለአምስት ስድስት ተኩል

ትናፍቂኛለሽ ከ የአቆብም በላይ
እንደው ባገኘሁኝ 14አመት ሆኜልሽ አገልጋይ
ልክ እንደ አብርሃም በ መቶ አመቴ ካንቺ በወለድኩኝ
ልክ እንደ ሮሚዬ አይንሽን አያየው ኑሬዬን በሞትኩኝ
ልክ እንደበዛብ ቅኔው በጠፋብኝ አንቺን ስመለከት
አምላኬን ካልከፋው ቆሜ ልያዝልሽ ቅኔና ማህሌት

ደግሞ እኮ ችግሩ ጎበዝ ገጣሚነሽ
ምለው ነገር ሁሉ አይደለም ሚከብድሽ
በምን ልሸንግልሽ
ፍቅር እንዲይዝሽ ድክመትሽ ምድነው
ልባም ሴት መማረክ ለካ እንዲ ከባድነው
እውነት ግን ከባድ ነው
በእውቀት ማህደር የሰማይ ጥግ ነሽ
በምድር ደረጃ ደግሞ ልባም ሴት ትሁት ነሽ
ቆንጆ ነሽ
ጠይም ነሽ
ቀጭን ነሽ
ጎበዝ ነሽ
ትሁት ነሽ
ይሄን ሁሉ መሆን ባንድ ገላ ባንድ ሰውነት
እረ እንዴት ተቻለሽ

አው ናፍቀሺኛል
አልናፍቅም ያልኩት ቃሌም ተቀይራል
ተብታባ ብሆንም ከምር ናፍቀሺኛል
ኮልታፋ ብሆንም ቃላት የሚጨንቀኝ
ዛሬ ግን ተናገርኩ ናፈቅሺኝ መሰለኝ
ብሶብኝ መሰለኝ።
አዎ ናፍቀሺኛል

ናፍቆትሽ ይሆን እንዲ የከበደኝ
ቁንጅናሽ መሰለኝ ግርጌሽ ያስቀመጠኝ
ሰው ነሽ እንዳልል የሚገርም ቁንጅናሽ
መላእክት እንዳልል አጥፍተሽ አልተጣልሽ
እምላክስ ቸር ሆኖ እንቺን የመረጠሽ
መደነቅ ጀመረ የሱ ፍጥረት ሆነሽ
ደንግል ሆይ ስሚኝ ነብሴን ተማለጂያት
አንዴ ብቻ ሳይሆን
እድሜ ዘመኔን እሳን ብቻ ልያት

አሜን😊!!!

https://t.me/zzzzaa123
@mikimekonen9

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

13.4k 0 111 10 96

☀️☀️ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኛ ምን አይነት ስጦታ ልስጥ ብለው አይጨነቁ !

የ ስዕል ( Art ) ስራወችን በስጦታ መስጠት ለምትፈልጉ ከታላቅ  ቅናሽ ጋር አሁኑኑ ይዘዙን ።
ጥራት ያላቸውን ስራወች ሰርተን በፍጠነት እናስረክባለን ።
መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ቅናሽ አድርገናል ።

order ለማረግ 👇👇👇

☎️ 
+251912453800
☎️ 
+251931374891
     ይደውሉ 👆👆👆

በቴሌግራም
@Abate_Hiwote ላይ ያናግሩን።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

ብታውቂ ነይ ከእኔ...
ባታውቂ ነይ ወደ እኔ
...
             (ርዕሱ ነው)


ከውቢት ከተማ አንዲት ሴት ነበረች፣
ሁሉ የሚመኛት በግብር ያማረች፤
                    አንዲት ሴት ነበረች።

ከሴቶቹ መሃል ትመስላለች ንግሥት፣
ብቻዋን ስትገኝ ታስንቃለች እንስት።

ውዴ! ከእግዜሬ በታች የዓሳ ሕይወት ያለው፣
በሠማዩ ሥሪት፣ በምድር በሰፋው በሚታየው ማይ ነው።
ታድያ የእኔ ልብ ያለው አንቺ ጋር ነውና፣
ወይ ነይልኝ ወይ ና በይኝ እወድሻለሁና።

አውቃለሁ! ዓይን ዓይንሽ እያየሁ ፍቅሬን አልገለጥኩም፣
አውቃለሁ! እሞትልሻለሁ ብዬ አልተናገርኩም፣
ታውቂያለሽ? ኃይል ማጣቴና እንደሆንኩኝ ድኩም?

አላምንህም ብለሽ ብትዞሪ ዓለም፣
እመኚኝ! ከአፍቃሪሽ በላይ ላ'ንቺ 'ሚሆን የለም።
ብታውቂ ነይ ከእኔ ጋር ድመቂ፣
ባታውቂም ነይ ወደ'ኔ ከጎኔ አትራቂ።
ላገኝሽ እተጋለሁ...፣
ደግሞ እንዳትርቂኝ እሰጋለሁ።

አሰብኩትና ለአንቺ መንበርከኬን ... ፈራሁት አምላኬን
አትታዘበኝ ጌታዬ ... አንተም ታ'ቃለህ ከፍቅር ለፍቅር መላኬን።
በእርግጥ አንተ ለእኔ ምላሽ አለህ፣
አንተ ራሱ አፍቃሪ አይደለህ?

አስታውሽ? ሳጥናኤል በምኞት መውደቁ፣
ከንቱነት ለእሱ ማሳበቁ፣
    እናማ...
የእኔም ምኞት አውጥቶ ቢጥለኝ፣
የአንቺ እሺታ እንጅ ሌላ መጽናኛ የለኝ።
ግዴለም ሐሳብሽ ሐሳቤ ይሁን፣
ልዕልት ላግባና እኔም ንጉሥ ልሁን።
አትፍሪኝ፣ ቅረቢኝ...
ዓይንሽን ግለጭ፣ አንብቢኝ።
የፍቅረኛሞች ሰፈር ውሰጂኝ፣ አድርሺኝ፤
ጠይቂኝ ልቤን ልስጥሽ ከዚያም አድሺኝ።

ይኸውልሽ ሃ!   የእኔ ስኬት...
አንቺን ማኖር ነው ወሰን በሌለው ልኬት!
           ●| HT |●

✍ መንገደኛው (
@MekuriyaM )
            The traveler


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​▓▓▓▓▓▓▓ ግጥM  ▓▓▓▓▓▓▓



Block......un block
   

ቀን አትናፍቀኝም
ጭራሽ ትዝ አትለኝ

ስምህም ሲጠራ ድንቄም አልደነግጥ
ፎቶህንም ሳየዉ ልቤ አትልም ድልቅ።

ድንገት ትዝ ካልከኝ
ራሴን 'ረግማለሁ
ምን አጃጅሎኝ ነዉ ብዬ እገረማለሁ።

ያንተ ስም ሲጠራ
ብዙ መሠል ስሞች ይመጣል ከኔ ጋር
ሌላም አስባለሁ ከትዝታ ጋራ

የአፍቃሪዬን ብዛት..............

በቃ ረስቻለሁ ብዬ ስደሳሰት
                      Block🤜

ልክ ሲመሻሽ ደርሶ
ስምህ ይጨንቀኛል
ሳቅህ ይሰማኛል

እንደ ቀኑ አይደለ ፎቶህ ግርማ አለዉ
መፀፀት አይደለ ልቤ አምጪዉ ነዉ ሚለዉ

ምን አተሽ ነዉ ከሱ
እድል ነበር እሱ

እያለኝ እንደቀልድ
ቀን ያመንኩት ልቤ ካንተ ጋራ ሲነጉድ
እንዲሁ አነጋለሁ
ስላንተ አነባለሁ።


ከዛ..............
un block ሳደርግህ ራሴን አገኛለሁ።

ድሮስ ከጨለማ ምን ነበር ጉዳዬ
አንተ መቼም አታዉቅ ሆነ እድል ፈንታዬ

አንተና ጨለማዉ ግብራችሁ አንድ ነዉ
ብቸኝነት ፍርሀት መልሳችሁ ዝም ነዉ።

ደሞ ዛሬም ነጋ.................


ተፃፈ በትዝታ ወልዴ✍


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ ፍቅሬን በግጥM


➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢


የኔና ያንቺ ህይወት
━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት...
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት....

እውነት እውነት ስልሽ...
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።

                        ✍️-ዳዊት(የለትዬ ልጅ)
                            

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

15.5k 0 213 30 130

       ━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━

አልናፍቅሽም ወይ

እርግጥ ብትለያኝ ባትሆኚ ከአጠገቤ
ትናንት ብንለያይ ሳትወጪ ከሃሳቤ
ቻው ያልኩሽ እኮ እማ ባፌ ብቻ እኮ ነው
ተለያይተን እንኳን ትናፍቂኛለሽ ምጠራው አንቺን ነው
በሰአት ቅፅበታት በእያንዳንዱ ቦታ
አብረን በሄድንበት የሸኘውሽ ለታ
በተዋወቅንበት ባቀፍሺኝ ያ ሰአት
ባገኘውሽ ጊዜ በሳምሺኝ ቅፅበታት
ልረሳቸው አልቻልኩም እነዛን ደቂቃት
ብቻ ትናንት ተነፋፍቀን አሁን አንቺን ማጣት

አብረን ባንሆን እንካን እኔ ናፍቀሺኛል
የማይደክመው እግሬ ሰፈርሽ ያትታል
አይኔ አማትሮ ደጅ ደጁን ያያል
ሴት ባየው ቁጥር እሳናት እያለ ልቤ ይደነግጣል
እኛ ብንለያይ ፍቅሬ ግን ገርሽቷል
ሰው እንደሞተበት አካሉን አንዳጣ ሃዘኔ በርትቷል
አካላችን ቢለያይ አጃችን ቢላቀቅ
አንቺን እያሰብኩ በፍቅር ስማቅቅ
እና ምን ዋጋ አለው በአካል ተለያይቶ
አንቺን ብቻ እያልኩ በልብ ተቆራኝቶ

አፌ ለካ ዋሽቷል ተያኝ ያልኩሽ ለታ
አሁን እየጠራሽ ጠዋት እና ማታ
ልቤ ግን ልክ ነው ድሮም ያፈቅርሻል
አሁን ተለያይተን እንታረቅ ይላል
ሂይወት ላትገፋ ጭራሽ ላትፋቀቅ
አንቺንስ በድዬ ነፍስ ስጋዬ ላይፀድቅ
እባክሽ ታረቂኝ እኔ ናፍቀሺኛል
ነፍስ ስጋዬ ሁሉ ስምሽን ይጠራል
ልቤ እንኳን ተጣላኝ ስጋዬም በድናል
እሳን ታረቅልን አምጣልን ብለዋል

     እናልሽ የኔ ውድ

እኔ አንቺን በማጣት ስጋዬ ከነፍሴ
ልቤ እረፍት አታ ዝም ብዬ ማልቀሴ
ቁመናሽ ከፊቴ የሳቅሽ ፈገግታ
ደግሞ ስትቆጪ ግልምጫሽ ለአፍታ

      እናልሽ እናቴ 

ይሄን ሁሉ መርሳት እንዳልሆነ ማሰብ
እንዴትስ ይረሳል በአስባቡ ሰበብ
በአልናፍቅሽ ነው ወይ ፀጥታሽ በርትቶ
ትውስታሽን ልከሽ ትዝታሽ አጥቅቶ
እኔው ቁስለኛ ሆኜ ተማራኪ
ሆነሽ ባለድሏ ብስራትን ሰባኪ
በመሃል ምጎዳው ምቆስለው እኔው ነኝ
አንገቴን ደፍቼ እንባዬን አንብቼ አፌ በለጎምታ ይልሻል ታረቂኝ

https://t.me/zzzzaa123
@mikimekonen9


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

18.6k 0 139 3 114

━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━

#ታውቂያለሽ?

ፎቶሽ ላይ ጠረንሽን መፈለጌ
የእኔን ስም ከግርጌው ማድረጌ
.   .   . አታውቂም!

እኔ ውድቅ ሆኜ የአንቺን ክብር አግዝፌ
ስወድሽ ከልቤ እንዳይደለ ከአፌ
.   .   . አታውቂም!

ገብቶሻል?
እንደ ከሰልኩ እንደ ከሳኹ
በአዝማድ እንደተረሳኹ
.   .   . አልገባሽም!

ቢሆንም
እኔ እያለኹ መቼም አትወድቂም
ደግሞ'ኮ ይሄንንም አታውቂም
እንዲህም ስልሽ እንኳ በደስታ አትስቂም
.   .   . አታውቂም!

ደግሞ
ሳኮርፍሽ ወዲያው ስትናፍቂኝ
አፍቅሪኝና በናፍቆትሽ ይባስ አጨናንቂኝ
“አፈቅርሃለኹ!” በዪኝና ከልቤ አስታርቂኝ!

✍Meku_Mura ●HT●


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


Репост из: Dubai furniture ethiopia ዱባይ ፈርኒቸ ኢትዩጵያ🇪🇹
🎁🔔የገና በአልን በማስመልከት አዳዲስ እቃዎችን በማስገባት  የ30% ቅናሽ ማድረጋችንን ስንገልፅ በታቅ በደስታ ነው::

በውብ እና ቅንጡ በሆኑ እቃዎቻች ቤትዎና ቢሮዎን ያስጊጡ 🎁

📍ቁ.1 መስቀል ፍላወር ኤያና ሆቴል ህንጻ 1ኛ ፎቅ
📍ቁ.2 ሳሊተምህረት ት/ራት አጠገብ ጋብሬላ ህንጻ
📍ቁ.3 ቦሌ አትላስ ማዶሆቴል ጀርባ

📱 +251984272727
📱 +251969333333
📱 +251993858585

🏖 በሁሉም ሶሻል ሚዲያችን ይከተሉን🆓

📱  🤡OIN
📱  🤡OIN
📱  🤡OIN
📱  🤡OIN

#dubaifurniture #expertadvise #designtips #modernfurniture #timelessdesign #luxuryliving #homeinspiration #functionaldesign
#interiordecor #officefurniture #commercialinteriors #furnituregoals


ጣዕሙን የሚያውቀው
(ሳሙኤል አለሙ)

እንደ ሌላው
እንደ ሌላው፤
ሰርክ...
ጉንጭሽ ጋ አይደረስም
ረ------ጅም ነው ኬላው።

እያዩት...
ያስውላል።
ዕሮብ ለት
እያዩት...
ያፆማል።
አርብ ዕለት

እንደ እኛው
እንደ እኛው፤
አንቺ...
ከቶ አልተፈጠርሽም
በቀን ስድስተኛው።

ለምን...?
አይባልም።
አይጠየቅም።
እንዴት...?
አትለውም።
አትከራከርም።

ከአፈሩም ፣ ከውኃውም
ከእስትንፋሱም ፣ ሌላም
አለው... ሌላም...ሌላም
ሌላም አለው ያከለበት፤
ወተቱን እንዳ---
ፈሰሰ---
---በት
ጉንጭሽን የሳመው።
ጣዕሙን የሚያቀው።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

@getem


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


🚨📱 የሚሸጡ የፌስቡክ ግሩፖች 🚨

🎯 900,000  Members 👍
🎯 158,000  Members 👍
🎯  88,000   Members 👍

INBOX ME ✉️ @AbenaG
CALL ME   ☎️ +251923715770


༻༺༺  ግ  ጥ  ም   ༻༻༻




  ♥️♡+:。.。 ልውደድሽ ደግሜ  。.。:+♡♥️


ያኔ ትዝ ይልሻል በልጅነት እድሜ
እወድድሽ ነበረ እኔም በአቅሜ
በትንሿ ልቤ ማንነትሽ ሰርፆ
ብዙ አንገላቶኛል ፍቅር ተፀንሶ
መውደዴን ሳታቂ ችላ ብትይኝም
ያንቺ ችላ ማለት ፍቅሬን አልቀነሰም

       ወድዬ....................

ያለ አንቺ ፍቃድ    ልቤ ፍቅርን ቢሻ
ላንቺ ያለኝ መውደድ የለው መጨረሻ 
እያለ ነበረ ሲያፈቅርሽ የኖረው
የጊዜው እርዝማኔ ፍቅሬን ቢያስታግሰው
ያ ሁሉ አመታት ግን አልቻለም ሊሽረው

ውድዬ.................

በአፍቃሪው ልቤ ፀባይሽ ተዘርቶ
መፍትሄ አልባው ፍቅርሽ ዳግም አገርሽቶ
መድሀኒት የሌለው ሆነሻል ህመሜ
እባክሽ ፍቀጅልኝ ልውደድሽ ደግሜ

       ውድዬ..............ላንቺው ነው


    Bekalu MESERET
         

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 🙏

Join us 👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

Показано 18 последних публикаций.