መሪጌታ አምደብርሃን የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል 🌿🌿🌿


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Видео и фильмы


☑ ከጥንት አባቶቻች በተቸረን ሰሎሞናዊ ጥበብ ተፈጥሮ ያበቃላቸው የእፅዋት መድሀኒቶችን በመጠቀም ክፉ ዓይነ ጥላ ፣ በቤተሰብ ወይም በዘር የሚተላለፉ መናፍስት መፍትሔዎቻቸው ይተነተናሉ።
☑ አድራሻ ቁጥር 1 ምዕራብ ጎጃም ቡሬ ቁጥር 2 አ/አ እንዲሁም በተለያዩ የክልል ከተሞች እንልካለን
📞#0918834904
📞#0915310455
መልዕክት ካለዎት @merigetaamedeberhan

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Видео и фильмы
Статистика
Фильтр публикаций


የእግዚአብሔር ምሕረት እና ቸርነት ከእናንተ ጋር ይሁን ።
            💚 ዝግባ 💚
ዝግባ እጅግ በጣም ውድ እና ብርቅየ ከሚባሉ እጽዋቶች አንዱ ሲሆን ቅጠሉ ቅርፊቱ ሥሩ እናም ሙጫው የየራሳቸው የሆነ ጥቅም ያለው መልካም  ዕጽ ነው።

ዛሬ ስለ ዝግባ ሙጫ እናውራ! ሙጫ ማለት  የአንድ ዛፍ ግንድ ቅርንጫፍ ሲቆረጥ ፣ሲሰነጠቅ ፣በስለት ነገር ሲወጋ፣ ከውስጥ የሚወጣ ዕዥ ወይንም ፈሳሽ ተሰብስቦ ሲደርቅ በምስሉ እንደምታዩት ሁኖ ሲገኝ ሙጫ ይባላል።

የዝግባ ሙጫ ጥቅም፦
🌿ለራእይ
🌿ለመፍትሔ-ሥራይ
🌿ለህዝብ ፍቅር
🌿ለስኳር በሽታ ተጨምሮ ይገባል!
🌿ለጠላት መፍዝዝ...እና የመሳሰሉት መፍትሔ ይሰጣል።

1ኛ, ለራእይ!
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ጸሎት በእንተ ራእይ ወምክስተ ምስጢር

ኦ መድሙጦስሙት አርእየኒ ግብረ ጸላእትየ ወግብረ ፈተውትየ
ኦ ሙርድያል ክስት ልየ ህቡዓተ ምስጢራተ ሰማይ ወምድር
ኦ አአትማይያል አርእየኒ ምስጢረ አዝማድየ ወአብያጽየ
ኦ አፍድክያል ክስት ልየ ስውራተ ወህቡዓተ ዘተኃለዩ እምላዕለ ነብስየ ወስጋየ
ኦ ሰምራካኤል አርእየኒ ሀብታተ ዕዮብ ወጥበበ ሰለሞን በዝንቱ ቃልከ አውሎግሶን
ኦ መቅጀሐቡር  ክስት ልየ በኅልም ወበገሀድ ዘተገብረ በላዕሌየ
ድማክል
ድማክል
ድማክል
ህልድጣኤል
ህልድጣኤል
ህልድጣኤል
ዝምራኤል
ዝምራኤል
ዝምራኤል
ድልካም
ድልካም
ድልካም
ኦ አጥዮንዮስ ክስት ምስጢራተ ዓለም በዛቲ ዕጽ ተመሲለከ ለለዕለቱ ወለለሰዓቱ በእንቲአየ እኩይ ነገር ዘይሔሊ ወዘይገብር አርእየኒ ወአስምዓኒ በእዝነ ልቡናየ ለገብርከ (ስም)

ገቢሩ፦የዝግባ ሙጫለ ፯ ቀን ማታ ማታ በመኝታ ሰዓት ታጥኖ  በንጽሕና መተኛት።
ቀድሞ የተደረገውን ለወደፊት የሚደረገውን በህልም ይታያል።
በተለይ መድኃኒት፣ ውለሽ ፣የሴት ዛር፣ሥራይ..በሰው ዘንድ ተደርጎብናል ብላቹ የምታስቡ በሙሉ በራእይ ሁሉም ነገር ይታያችኃል።
ይህ ጥበብ በምትሰሩበት ሰዓት ተራክቦ(ወሲብ) አይቻልም።

2ኛ,ለመፍትሔ ሥራይ
የዝግባ ሙጫ፤ ሥር ፤ቅጠል፤
የእንቧጮ ሥር፤ ቅጠል ፤ተቀጽላ
የሎሚ ሥር፤ ቅጠል፤ ተቀጽላ
የሴት ዕሬት ሥር ፤ግንድ
ከከርቤ ዕጣን ጋር ለሳምንት ያክል መታጠን ማንኛውም ሥራይ ውለሽ ዓይነጥላ ይለቃል።

3ኛ, ለህዝብ ፍቅር

የዝግባ ሙጫ
ቅብዓ ሜሮን
የ ጥርኝ  ሽቶ
ከቀዘው(አሞጭ) ሥር ጋር ለውሰው ለሳምንት ያክል በስሱ ሴት ልጅ ትኳል ወንድ ልጅ ግንባሩ በትእምርተ መስቀል ይቀባ።

4ኛ, ለስኳር በሽታ

የዝግባ ሙጫ ፤ቅጠል ቀንበጥ
የቁልቋል ቀንበጥ
የዶግ(ዕጸ ራምኖን) ቀንበጥ
የዕንጭብር ሥር
ከርቤ ዕጣን
የወርቅ በሜዳ ሥር በአንድ ላይ አልሞ ደቁሶ በጣዝማ ማር አዋህዶ በግማሽ የሾርባ ማንኪያ ከምግብ በኃላ ለ 21 ቀን መብላት ነው።
ፍቱን ነው። በተለይ ለኢንሱሊን መርፌ የማይወጉ ለውጡ ውጤታማ ነው።

5ኛ, ለጠላት ለሌባ መፍዝዝ

የዝግባ ሙጫ
የአበዘንጣ(የአሽኮኮ ጎመን ሥር
የዋርካ ተቀጽላ
የጠምበለል ተቀጽላ በአሽኮኮ ሓሞት አንግሰህ ከትበህ ያዝ ጠላትህ ደፍሮ አይናገርህም ሌባም ኪስህ ውስጥ አይገባም።

እነዚህ ጥበቦች ተፈትነው ተግባር ላይ የዋሉ ናቸው ማየትም ማመን ነውና !
ሞክረው ውጤቱን ይንገሩን።

መሪ አምደ ብርሃን !!!
ለበለጠ መረጃ 0918834904 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።
✅ቴሌግራም መልክት የምቀበልበት
@merigetaamedeberhan




ሌላው በልብሶቻችን ወዝ የሚመተተው መተት የሰውነታችንን ጠረን በከፋ ሁኔታ ያበላሻል፡፡ የመተት ጠባዩ አንዱ የሰውነትን ጠረን በማሽተት ከሰው እንዳንቀላቀል፣በክፉ ሽታ እንድንሰቃይ ማድረግ ነው፡፡ መተት ያለብን ሰዎች አፋችን፣ብብታችን የውስጥ ገላችን፣አንቀጸ ሥጋችን፣ማኅፀናች ጥሩ ባልሆነ ጠረን ይሸታል፡፡ በወዛችን መተት ተመተተ ማለት የሰውነታችን መዓዛ ይጠፋል፡፡ በዚህም ሰውነታችን በአስደንጋጭ ሁኔታ ይሸታል፡፡

ወዳጆቼ በአጠቃላይ በልብሳችን፣በቁሳችን ወዝ መተት ተመተተብን ማለት ብዙ እድላችንን እና ጤናችንን እናጣለን፡፡ እንዲሁም የሰውነታችን ጠረን እየሸተተ እንሰቃያለን፡፡ አጠቃላይ መፍትሔዎችን መጨረሻ ላይ ብመጣበትም በወዛችን አስመትተው እድላችንን ቀምተው የቁም እስረኛ እንዳያደርጉን ልብሶቻችን፣ቁሳቁሶቻችንን ለሰው ባናውስ እና በውጭ ባናሰጣ እመክራለሁ፡፡ እኛ ሰዎች በተንኮል ከአጋንንት እኩል እየሆንን ስለሆነ እየተጠነቀቁ በጸሎት መበርታቱ መልካም ነው፡፡

የአንድን ሰው ተሰጥኦ በምቀኞች በመተት አጋንንት ወደራሳቸው ማድረግ ልክ በእኛ ያለን የስልክ ካርድን ለሌላ ሰው ትራንፈስ እንደማድርግ የቀለለበት እኛም የቀለልንበት ዘመን ነው፡፡


〰   በወዝ የሚተት መተት

ብዙዎች ልብሳቸውን፣ጫማቸውን፣ደብተራቸውን፣ብዕራቸውን ወዘተ ጓደኛ ለተባሉ ጉደኛ በማዋስ እድላቸውን በመተት በመቀልበስባዶ አድርገዋቸዋል፡፡ በወዛችን መተት የሚመተተው እና እድላችን የሚወሰደው በሁለት መልኩ ነው፡፡ አንደኛው የራሳችን እና የቅርባችን ለምንላቸው ሰዎች ልብሳችንን፣የምንጠቀምበትን ቁስ በማዋስ ነው፡፡ ከእኛ የተዋሱትን ነገር አጋንንት ጎታች እና መተት መታች ጋር ይዘው በመሄድ በወዛችን ያስደግማሉ፡፡ ከዛማ የእኛ የሆነው ሁሉ በተዘዋዋሪ ሳይሆን በቀጥታ የእነሱ ይሆናል፡፡

ሁለተኛው የእኛ የምንላቸው እኛ በምቀኝነት እና በቅናት የሚያዩን፣በመልካም ነገሮቻችን፣በተሰጦአችን ዓይናቸው ደምየሚለብስ፣በቅናት የሚንከላወስ የቅርብ ሩቅ የሆኑ ሰዎች የእኛን ለምሳሌ ልብሳችንን፣ቁሳችንን በመስረቅ እና በሰው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡ እነዚህም ሰዎች ሁለት ገጽታ ነው ያላቸው፡፡ አንደኛው ቀርበውን ወዳጅ ሆነውን ጓዳ ጎድጓዳችን ካወቁ በኃላ በመጎራበት የእኛን ነገር በመስረቅ ወስደው ያስመትቱበታል፡፡ ሁለተኛው እኛን ሳይቀርቡን ለምሳሌ ያሰጣነውን ልብስ፣ያስቀመጥነውን ቁስ ወዘተ ከውጭ ሆነው በማሰረቅ ያስመትቱብናል፡፡

ወዳጆቼ ሆይ አንዳንዴ ከቤት ያስቀመጥነው ልብስ እና ቁሳቁስ እንዲሁም በውጭ ያሰጣነው ልብስ እንደ ዘበት የሚጠፋው ለመተት ተግባር ነው፡፡ እኛ ኢትዮጲያውያን ኑሮአችን፣ማህበራዊ መስተጋብራችን ለመጠላለፍ፣በመተት ለመጉዳዳት ይመቸናል፡፡ ምክንያቱም ጉርብትናችን እንደ ቤተሰብ፣አሰፋፈራችን እንደ ምላስ እና ጥርስ በአንድ ቦታ ስለሆነ ነው፡፡
እዚህ ላይ አጥርቼ ልለፍላችሁ፡፡ መቼም ‹‹እንዴት መተት በወዛችን ይመተትብናል?›› ማለታችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ አሁን በረቀቀው ዓለም አንድ ሰው አንድን ሰው በጨለማ እና ሰው በሌለበት ቦታ ቢገድለው ለገዳይ ምስክር ላይኖር ይችላል፡፡ ለሟች ግን እውነተኛ እና ሐቀኛ ምስክር አለ፡፡ ይህም አሻራ የምንለው ነው፡፡ አሻራ ደግሞ በሟች ሰውነት ወይም ሟች በሞተበት መሣሪያ ላይ የሚታተመው በወዝ ነው፡፡ ሟች የሞተበት ማንኛው ነገር ላይ የገዳይ አሻራ በራሱ ወዝ ምስክር
ይሆንበታል፡፡ ይህ ማለት ወዝ ማንነት ነው፡፡ ወዝ የአንድን ሰው ሁለንተና ሊገልጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወዳጅ ያልናቸው እና በቅናት በጠላትነት የሚነሱብን ሰዎች በልብሳችን እና በቁሳችን ሳይሆን እሱ ላይ ባለው ወዛችን መተት ያስመትቱብናል፡፡ ያኔ ከሕይወታችን የሚፈልጉትን መልካም እድላችንን ይነጥቁናል፡፡ በራሳችን ወዝ በመተት በማፍዘዝ በማደንዘዝ ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ፤ከመቃብር በላይ ከሕያዋን በታች ያደርጉናል፡፡

ያኔ ከእኛ ኃላ ያሉት ሰዎች በእኛ እድል ከእኛው ይቀድሙናል፡፡ ብንሮጥ አንደርስባቸውም፡፡ የእኛ የሆነ ነገር እነሱ ጋር ስላለ ምን ይዘን እንሮጣለን?  እኛ ውበት ከቁመናና እና ከመልካም ጠባይ ጋር ይዘን እነሱ ከእኛ በታች ሆነው በእኛው እድል ከእኛ በላይ ይሆናሉ፡፡ እነሱ ያገባሉ እኛ ቆመን እንቀራላን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ይወልዳሉ እኛ የወላድ መካን እንሆናለን፡፡ እነሱ በእኛ እድል ሠርተው ሐብታም ይሆናሉ እኛ መሥራት እየቻልን እድላችንን ተነጥቀን በቤታችን ታስረን እንኖራለን፡፡ እኛ ተምረው የት ይደርሳሉ ለሰው እና ለሀገር ይተርፋሉ ተብለን ተስፋ የተጣለብን ተስፋ ቢስ ሆነን እውቀታችንን ተነጥቀን ያለ አንዳች ሥራ እንቀመጣለን እነሱ በእኛ እድል እና እውቀት ተምረው እንጀራችን እየበሉ ይኖራሉ፡፡

ብዙዎቻችን እንደ ቀልድ በለጋነት እድሜያችን ነገሮችን በፍጹም በማናውቃቸው ጊዜያት እድላችንን በወዛችን ተነጥቀናል፡፡ ለምሳሌ በትምህርት ዓለም እያለን አንዱ የትምህርት እድላችን፣እውቀታችን የሚሰለበው በመተት ቢሆንም የሚደገመው በወዛችን ነው፡፡ ይህም ደብተራችን፣ብዕራችን፣ልብሳችንን ተውሰው በወዙ አስደግመውበት ይመልሱልናል፡፡ እኛም በአስደንጋጭ ሁኔታ የትምህርት አቅማችን እየወረደ፣ትምህርት እያስጠላን በሂደት እንፈዛለን እንደነዝዛለን፡፡ እነሱ እያየናቸው እየተገላበጡ እየተለወጡ ይሄዳሉ በእኛ እድል ተምረው ሰው ይሆናሉ፡፡

እኛ ለወዳጅ ባዋስነው እኛ በተሰረቀብን ልብስ፣ቁስ በወዙ መተት ተመትቶበት ዕድላችንን ይወስዳሉ፡፡ በተለይ የትዳር፣የልጅ፣የሥራ ወዘተ ዕድላችን በወዛችን ተደግሞበት ብዙ ነገራችንን እናጣበታለን፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ረቀቅ ያለበት ጊዜ ስለሆነ መተት የሚመትቱትም እንኳን በቁሳችን በእጃችን ወዝ የመስለብ ሥራን ይሠራሉ፡፡ አንድ የማውቀው ማህበርተኛዬ አለ፡፡ ይህ ልጅ አሜሪካ እንደ ነገ ሊሄድ እንደ ዛሬ የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቶ ጓደኞቹን ይጠራል፡፡ እሱ ይህንን ባዘጋጀ ጊዜ አንድ የሚያውቃቸው ትልቅ አባት ከሽሬ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ድረስ በመምጣት አግኝተውት ‹‹ልጄ እባክህ እንዲህ ዓይነት ሰው ጠበቅ አድርጎ እጅህን ጨብጦ ሰላም ይልሃል፡፡ ከቻልክ ጸሎተ ማርያምን እየጸለይክ አናግረው ግን ሰላም ባትለው ይሻላል›› ይሉታል፡፡ እሱም እንደ ቀልድ ለይስሙላ እሺ ይላቸዋል፡፡

ማታ ፕሮግራም ይጀመራል ወዳጅ የተባለ ሁሉ ይመጣል፡፡ ይበላል ይጠጣል፡፡ አንድ የሚያውቀው እና በነገሮች ሁሉ የሚቀናበት ስለ እሱ መልካም እድሎች በተደጋጋሚ ‹‹አንተማ ታድለህ፣አንተማ ያሰብከው ይሳካል›› እያለ የሚያሟርትበት ጓደኛ ተብዬው ግጥም አድርጉ ባልተለመደ ምልኩ ጨብጦ ሰላም ይለዋል፡፡ አጅሬም ከሆነ በኃላ የእኛ አባት ቃል ትዝ ይለውና በልቡ ‹‹ምናባቱ ምን ያመጣል›› ብሎ እንደ ዘበት አይቶ ያልፋል፡፡ ይሄ ልጅ አሜሪካ እንደ ገባ ከጥቂት ቀናት በኃላ እጄን ወጋኝ ጠዘጠዘን ማለት ጀመረ፡፡ እዛም በጥሩ ሁኔታ ታከመ ግን እየተሻለው ሳይሆን እየባሰበት ሄደ፡፡ በሚገርም ሁኔታ ቀኝ እጁ እንደ ለምጽ በመንደድ በሂደት እጁ ሰለለ፡፡ ዛሬ ቀኝ እጁ ምንም የማይሠራበት ሆኖ ከመስለሉ በተጨማሪ ሠርቶ አምድ አፋሽ ሆኗል፡፡ ጤናውን አጥቶ በመተት ተጎድቶ ይኖራል፡፡

ወዳጆቼ ከላይ በርዕሱ እንደነገርኳችሁ የመተት አንዱ ጦሱ ጤናችንን ማቃወሱ ነው፡፡ ስንቶች አሉ በልብሳቸው፣በቁሳቸው ወዝ መተት ተመትቶባቸው እድላቸውን ብቻ ሳይሆን ጤናቸውንም አጥተው የአልጋ ቁራኛ የደዌ ዳኛ ሆነው በየ ቤታቸው፣በየ ጸበሉ በየ ሐኪም ቤቱ ያሉ፡፡

እህት ወንድሞቼ ከቤታችሁ ያስቀመጣችሁት፣በውጭ ያሰጣችሁት የውስጥ ልብሶቻችሁ ለምሳሌ ፓንት፣ታይት፣ካልሲ፣የጡት ማስያዣ፣ጃፖኒ/ፓክ አውት/ በቀጥታ ከሰውነታች ጋር ስለሚገናኙ በወዝ ለሚመት መተት አንድ ግብአት ስለሆኑ ጠንቀቅ ብትሉባቸው አይከፋም፡፡ ‹‹ኢዲያ
ውሸት ነው እኔ ላይ አይሠራም›› ካላችሁ እዳው ገብስ ነውና ታገኙታላችሁ መልሳችሁ የማታገኙትን እድላችሁንም ታጣላችሁ፡፡

ወዳጆቼ ሆይ በልብሳችን ወዝ የሚመተተው መተት እድላችንን ከማኮላሸት በተጨማሪ መልካችንን ያበላሻል፡፡ አንዲት ሴት በወዝዋ ጓደኛዋ መተት ብታስመትትባት መልከኛዋ ለወንዶች መልከ ጥፉ ሆና ትታያለች፡፡ መልከ ቢስዋ ለወንዶች መልከኛ ሆና ትታያለች፡፡ በዚህም አስመታችዋ የመልከኛዋን የመልክ ወዝ ተላብሳ ቆንጆ መስላ ትታያለች፡፡ ለዚህም ነው መልከኞቹ ውበት ይዘው ሳያገዙ ይቀራሉ የእነሱ ጓደኛ መልከ ቢስ መተተኛዋ ቆንጆ ወንድ አግብታ ትኖራለች፡፡ ወዳጆቼ በወዝ የሚመተት መተት የመልክ ደም ግባታችንንም እንዲወሰድ ያደርግብናል፡፡ በብዛት በመልካቸው የወዝ ድግምት ተደግሞባቸው ያሉ ሰዎች ፊታቸው ባላወቁት ምክንያት ውበታችው ይጠፋል፣ፊታቸው በብጉር ይመታል፣ፊታቸው ይቆስላል፣ፊታቸው እየሻከረ እየወየበ ይሄዳል፣የማይጠፋ ጠባሳ መሰል ምልክት ይታይባቸዋል፡፡




〰️ ለዓይነ ጥላና ለገርጋሪ〰️
በስመ አብ በል ጸሎት በእንተ ዓይነ ጥላ ወገርጋሪ አስማተ እግዚእነ #ኢየሱስ_ክርስቶስ ራፎን ፫ ጊዜ ራኮን ፫ ጊዜ ጰስአፍሊስ ፫ ጊዜ መልዮስ ፫ ጊዜ አናኤል ፫ ጊዜ ጽራኤል ፯ ጊዜ ሕናኤል ፫ ጊዜ ናፎስ ናሮስ ኮሮስ ፫ ጊዜ ፌሎስ ፫ ጊዜ ቢናር ፫ ጊዜ ሊናስ ፫ ጊዜ ሊኖስ ፫ ጊዜ ሊፍሎራኖስ ፫ ፓፓሮስ ፫ ኢሮስ ፫ አኖሮስ ፫ ኢሮን ፫ ጊዜ ብርስባሔል ፫ ጊዜ ድማሄል ፫ ጊዜ በኃይለ ዝንቱ አስማቲከ አድኀነኒ እምኩሉ ዓይነ ጥላ ወዓይነ ባርያ ስድዶሙ ለአጋንንት ዕቀበኒ ወአድኀነኒ ሊተ ለገብርከ #የክርስትና_ሥም
#ገቢሩ የቀጠጥና አበባ የፅጌ ረዳ አበባ የቀጋ አበባ ዕፀ ሳቤቅ ሞይደር እነዚህን አንድ ላይ ቀምመህ ለ ፯ ቀን ማታ ማታ ታጠን የማያዳግም መፍትሔ ይሰጣል ።

         ❤️የሕዝብ_መስተፋቅር ❤️
ጸሎተ ተሳልሞ ወተፋቅሮ ነገሥት ወመኳንንት ዘኩሎሙ ፍጥረታቲከ አከለወጅ ፱ ጊዜ ሰማይጅጅ ወአርሞንሂ መጅጅ በሴቅምንጅ ከርወነጅጅ ከንጅጅ ሰያሜከራጅ በእሉ ቃላቲከ አስተፋቅረኒ ወአስተጻምረኒ ምስለ ኩሎሙ ወሉደ አዳም ወሔዋን ነች ምስለ ኩሎሙ ነችች ወረስየኒ ፍቁረ በኀበ ኩሉ እግዚእ ወአጋዕዝት ኦ #እግዚአብሔር መፍቅሬ ሰብእ ጸግወኒ ፍቅረ ወሰላመ በከንቱ የሀቡኒ ወርቀ ወብሩረ ኦሆ ኦሆ ኦሆ ይብሉኒ ኩሎሙ ሰብእ ወይፌጽሙ ፈቃደ ልብየ ሊተ ለገብርከ ዕገሌ #የክርስትና_ሥም
#ገቢሩ በ፯ ኮረሪማና እፍኝ ስንዴ አንድነት ፈጭተህ ጋግረህ ፵፱ ጊዜ ደግመህበት ብላ ወለፍቅር ይከውነከ ።

                〰️ለመንሥኤ_እስኪት〰️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ጸሎት በእንተ ንአጽዖተ እስኪት ጢፍራን ፯ ጊዜ ወዱን አንቅዕ እስኪቶ ያንቅሖ ያንቅሕ ፯ ጊዜ ለገብረ ዕገሌ ዶር ፯ አኽያ ፯ ሽራኽያ መሸያ ፍታህ ዮፍታሔ ብሂል  ፍታሕ ተፈታሕ አንቀሕ አንቀሕ ወእለ ነቅሐ ያንቅሐ እስኪቶ ለከብርከ ዕገሌ: ፍርኑ ፍርናኤል ሱሱራኤል ሲሲሳኤል አጽንዕ እስኪቶ ከመሐጺን ማዕሠረ እስኪቱ ለገብርከ ዕገሌ ገቢር በአሞሌ ጨው በ፵፱ ቁንዶ በርበሬ ደግመህ ብላ ።

          〰️ለፈተና_የሚሆን〰️
ዋይ ዘጭላት ቁርአን ቁርአንከ በይንከ በይነጁና ሰረተኪላሂ መስተሐቢረ ወቀውዝረ ቀሊናታም በእሉ አስማተ ፍታሕ ማእሰረ ሥራዮሙ ለኩሎሙ መሠርያን እምላእለ ገብርከ ዕገሌ#የክርስትና_ስም
#ገቢር የቧጮ ተቀጽላ የሎሚ ተቀፅላ የዋርካ ተቀፅላ በእለት ውሀ አስማቱን ፯ ጊዜ ደግመህ ለ ፯ ቀን ታጠን ።




፵፪ #ለአስም የቀጠጥናውን ስር ከዕፀ መናሂ ከስረ ብዙ ከእንጭብር ከአሜራ ከጥቁር የደጋ እንጆሪ ጋር አልመህ ስራቸውን በጠጅ ጥለህ ጠጣ ።
፵፫ #ሰውነቱ_ለሚመነምን ህፃንና ለማንኛውም ሰው የቀጠጥናውን ስር የምድር እንቧይ ስር የብሳና ቅርፊት የጤና አዳም ፍሬ በአንድነት ደቁሰህ ለህፃን ልጅ በወተት አጠጣ ለአዋቂ ሰው በቡና በሸክላ ስኒ አጠጣ
፵፬ #ለህገ_ጠብቅ  የቀጠጥናውን ስርና የወይን የምድር እንቧይ የሴት ቀስት ስራቸውን ደቁሰህ በአዲስ ጠላ አቀላቅለህ ጠጥተህ ተራከብ ምስለ ብእሲትከ ኢይክል አውስቦታ ካልዕ ብእሲ
፵፭ #ለጀርባ_ህመም የቀጠጥናውን ስርና የአቱች ስሩንም ቅጠሉንም አድቀህ በአንድነት በአጓት ዘፍዝፈህ ጠጣ ።
፵፮ #ለቡዳ የቀጠጥና ስሩንና ጊዜዋ አልቴት ጤና አዳም ጭቁኝ ነጭ ሽንኩርት የአስተናግርት ፍሬ መሬንዝ ዕፅ ፋርስ የጅብ አርና ገበት ቀምሞ ማጠን ነው ፡ በግራ እጅህም ይዘህ ካለበት ቤት ወይም ቦታ ስትገባ ይለፈልፋል ።
፵፯ #ለሾተላይ የቀጠጥና ስር የምድር እንቧይ ስር የቀበርቾ የአቱች የፍየል ፈጅ የዝግጣ የአጋም ስራቸውን የባህር ጤፍ ፍሬውን ከሰሊጥ ጋር አልሞ ወቅጦ በማር መዋጥ አሰራሩ ከአስር ላይ አድበልብሎ በመጀመሪያ ባልየው ፩ዱን ይዋጥ ሚስትየዋ ፱ን ከ፪ ላይ ከፍላ ፫ ቀን ፫ ፫ እየዋጠች ትጨርስ ።
፵፰ #ለደም_ብዛት የቀጠጥናውን ስር በወይራ አንካሴ ምሰህ በትንሽ ጣትህ እየለካህ ስጥ ይቆርጥም ነገር ግን ደሙ እንዳያልቅ ደሙን እየተለካ ነው በመጠኑ ካልሆነ ደም ይጨርሳል


🌿🌿🌿 ቀጠጥና(ዕፀ ደብተራ)🌿🌿🌿
             #የቀጠጥና_ገቢር

፩ #ለጨብጥ  ከ ፫ ላይ በወይራ አንካሴ ምሶ በትክል ድንጋይ ላይ ቀጥቅጦ ፫ ቀን በውሀ አፍልቶ ማጠጣት
፪ #በምጥ_ለታመመች_ሴት የቀጠጥናውን ስር በወይራ ፍም ማህፀንን ማጠን ነው ።
፫ #ለሁሉ_መስተፋቅር ስሩን አልሞ ደቁሶ በቅቤ ለውሶ መዝሙረ ዳዊት ከመያፈቅርን ፯ ጊዜ ደግሞ እራሱን ቀብቶ ወደ አደባባይ ቢወጣ ኩሉ ያፈቅሮ ።
፬ #በድንገት_ሆነ_በተለያየ_ምክንያት_እግሩ_ላበጠ
በቀጠጥናው ቅጠል በእሳት ሞቅ እያደረጉ መተኮስ ነው ።
፭ #የጠላት_ሙግት_በተነሳብህ_ግዜ በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ልሄም አመድ ከቀጠጥናው እንጨት ጋር የጊዮርጊስን መልከአ ደግመህ አመዱን በ፬ቱ ማዕዘን ለነፋስ ስጥ ዕፁን መፋቂያ አድርገህ እየፋቅህ ወደ ችሎቱ ሂድ ።
፮ #ጉሮሮው_ላበጠ_ሰው የቀጠጥናውን ስር በትክል ድንጋይ አልሞ በማር ህፃን ልጅ እንዲያዋህድላችሁ በማድረግ የታመመውን ሰው እህል ሳይቀምስ ጧት ጧት ለ፭ ቀን አቅምስ ።
፯ #ዘኢያወርድ #ለስንፈተ_ወሲብ የቀጠጥናና የጠንበለል የቀጋ አበባቸውን አልሞ በማር ለውሶ በ፫ በ፫ ቀን ፫ ጊዜ ይዋጥ
፰ #ለችፌ የቀጠጥናውን ስር ከጥፍሬና ከምድር እንቧይ ስር ጋር ህፃን ልጅ ደቁሶ በማር ለውሶ ከበሽተኛው ቁስል ለይ ማሰር እስከሚድን ድርስ አይፈታም ።
፱ #ተስቦ_ከቤት_እንዳይገባ የቀጠጥናው ስሩንም ቅጠሉንም እየዘፈዘፉ ጧት ጧት ቤቱን የቤቱን ቅፅረ ግቢ እርጭ ።
፲ #ብልቱ_ለደከመ ከጅብራ ስር ጋራ የቀጠጥናውን ስር ህፃን ልጅ ደቁሶ መዝሙረ ዳዊት እግዚአብሔርን ቆመን ፯ ጊዜ ደግመህ በጉሽ ጠላ ጠጣ ።
፲፩ #ትክሻው_ላበጠ_በሬ የቀጠጥናውን ስር ከእሬት ስር ጋር በእሳት አቃጥለህ በቅቤ ለውሰህ ቅባ ።
፲፪ #ለስራይ የቀጠጥናውን ስር ከቁንዶ በርበሬ ከ፯ ዘቢብ ጋር የአሞሌ ጨው ቀላቅለህ አብላው
፲፫ #ቅንቅን_በጆሮው_ለገባበት_ሰው የቀጠጥናውን ስር እየጨመቅህ ከጆሮው ጨምርበት ።
፲፬ #ለነስር የቀጠጥናውን ስር ከምድር እንቧይ ስር ጋር ህፃን ልጅ ደቁሶ በአዲስ ጨርቅ ቋጥሮ በግራ አፍንጫው ወትፍ ።
፲፭ #ትዳር_ላጣች_ሴት የቀጠጥናውን ስር ከምስረች ስር ጋራ ርእሰ አሌፋትን (ታውን) በነጭ ወረቀት ጽፈህ አሳርረህ ስሩንም ገበያ አዙራ በልህኩት ትጠጣው ።
፲፮ #ለሳል የቀጠጥናውን ስር ከጉመሮ ስር ጋር ቀቅሎ ጧት ጧት ፩  ፩ ፍንጃል ስተይ ።
፲፯ #ለራስ_ነቀርሳ ለቆሰለበት የቀጠጥናውን አበባ ከጽጌ ረዳ አበባ ጋር በፍየል ቅቤ አንጥሮ በአፍንጫው ግበር ።
፲፰ #ሆዱ_ለሚጮህ_እና_ለሚያቃጥለው የቀጠጥናውን ስርና የቄስ በደጄ ስሩን ቀቅሎ አልሞ ደቁሶ በማር ማብላት ነው
፲፱ #ሲበላ_ወደላይ_ለሚለውና_ለሚያቅለሸልሸው
በዕለት ውሀ ዘቢቡን ጨምቶ የቀጠጥናውን ቅጠል አልሞ ደቁሶ ከዘቢቡ ውሀ ጋር አዋህዶ በዋንጫ ይጠጣ ።
፳ #ለጥላ_ወጊ መከላከያ የቀጠጥናውን ስር በወይራ አንካሴ ምሶ እፀ አንግስን እየደገሙ ፫ ጊዜ ደግሞ መሄድ ነው ።
፳፩ #እንስሶችህን_አውሬ_እንዳይበላቸው የቀጠጥና ስሩንና ቅጠሉን በዕለት ውሀ ጨምቀህ ዘየሀድርን ፯ ጊዜ ደግሞ በየወሩ በረቱን እርጭ
፳፪ #በመብልና_በመጠጥ_ስራይ_ለተደረገበት የቀጠጥና ቅጠሉን ከምድር እንቧይና ከእንጭብር ቅጠል ጋራ አልሞ ደቁሶ በማር ለውሶ ጧት ጧት በልክ በልኩ መብላት ነው ።
፳፫ #ለስራይ_መከላከያ በመንፈቀ ሌሊት ፵ ክንድ ርቆ ልብስን አውልቆ በወይራ አንካሴ ቆፍሮ መቃብያንን ደግሞ የቀጠጥናውን ስር ነቅሎ ከአቱች ጋራ ሰፍቶ ቢይዙት የአቅብ ኩለሄ ።
፳፬ #መስተፍቅር  ለተደረገበት ሰው የቀጠጥና ስሩን አልሞ ደቁሶ ከዝንጀሮ ኩስ ጋራ ፍትሀ ዘወልድን ደግሞ በጠላ ማጠጣት ነው ።
፳፭ #ለገበያ የቀጠጥና ስሩን ከነጭ ዕጣን ጋር አምጽኡን ደግመህ ታጠን ።
፳፮ #ቁስሉ_አልድንም ሲልና መግሉን ለማድረቅ የቀጠጥና ቅጠሉን አልሞ መነስነስ ነው ።
፳፮ #ከብትና_በግ_ፍየል_ሲከሱ የቀጠጥና ስርና ቅጠሉን አድርቆ  በጨው አብላ ።
፳፯ #መስተባርር ለተደረገበት ሰው ቀጠጥናውን ረቡዕ ቀን ቆፍሮ በስሩ ላይ ፯ ቀን በትክል ዕብን ላይ ቀሞ ፍትሀ ዘወልድንና ጠቢበ ጠቢባንን ደግሞ በጣዝማ ማር ለውሶ መብላት ነው ።
፳፰ #ለሙግት የቀጠጥና ስሩን ነቅለህ ከቤትህ ደጃፍ አኑረህ ሌሊት ከመኝታህ ተነስተህ ጧፍ አብርተህ ስሩን በግራ እግርህ እረግጠህ ፍካሬን ትጠፍዕ ላይ እያጠፋህ ፯ ጊዜ ደግመህ በነጋታው ይዘህ ወደ ችሎት ሂድ ።
፳፱ #ለልጅ_አገረድ_መፍትሄ_ሀብት ባል ላጣች ሴት
የቀጠጥና ስሩን 3 ቦታ በወይራ አንካሴ ቆፍረህ ወፍ ባልቀመሰው ውሀ ዘፍዝፈህ እግዚኦ ሚበዝሀኑ ፯ ጊዜ ደግመህ ፫ ቀን የደጅ ማይ ትውጣበት ገላዋንም ትታጠብበት ግማሹን ትታጠብ፡ ዓዲ ለዘፀልኣ ምታ የቀጠጥና ስሩን በእሳት አቃጥሎ ዓይኗን ትኳል ።
#፴ #ለማንኛውም_አስፈላጊ_ነገር የቀጠጥና ስሩን ከ፫ ቦታ በወይራ አንካሴ ቆፍረህ ከትክል ድንጋይ ላይ ቀጥቅጠህ ከጽጌ ረዳ ጋር አዋህደህ ታጥነህ ተኛ
፴፩ #ለትምህርት የቀጠጥና አበባውን ከጠንበለልና ከጽጌ ረዳ አበባ ጋር በትክል ድንጋይ ደቁሰህ በብርጭቆ ከ፫ ዕብን ላይ ከፀሀይ ላይ አድርገህ መልክአ ኢየሱስን እየደገምክ አፍልተህ ስተይ ።
፴፪ #ማንኛውም_ክፉ_ነገር_እንዳይደስስብህ የቀጠጥናውን ከ፫ ቦታ ለይ በቀንድ ቢለዋ ምሰህ ስሩን ቆርጠህ የጥቁር ጤፍ ቂጣ ብር የምታህል ጋግረህ ቂጣውን ከተማሰው ጉድጓድ ውስጥ አድርገህ አፈሩን መልስበት የቀጠጥናውን ስር ቀጥቅጠህ አድርቀህ በብረት ምጣድ አሳርረህ ተነቀስ ዕድሜህ ድረስ ክፉ መከራ አያገኝህም ፡ ነገር ግን ስትቆርጥ ጥላህ እንዳያገኘው ተጠንቀቅ
፴፫ #ለመስተሀምምና_ለዛር_ውላጅ_ለጥላ_ወጊ
መጠበቂ የቀጠጥና ስሩን ከአንድ ቦታ ቆፍረህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ዋጥ ።
፴፬ #ለሌባ የቀጠጥና ስር ከ፫ ቦታ በወይራ አንካሴ ምሰህ በግራ ፈትል ወስላታ መስክ ሰላቢ ከመቅብዕ ይቅለፁ ወከመ ሰም ይብረዱ በሎ ወቅትሎ ጥናክኤል ፯ ጊዜ አድራኤል ፯ ቃምናኤል ፯ በዝ ቃል ስትዞር እደር ተያዝ ዕደር አለህ ቃለ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወቃለ እግዚአብሔር ይህን በዕፁ ላይ ፯ ጊዜ ደግመህ ፫ ጊዜ ቤቱን አዙረህ ከቤትህ ውስጥ ቅበር ።
፴፭ #ለመድፍነ_ፀር ቢስሚላሂ፡ሮሂማን፡ሮሂም፡ወሱሬቹ፡በሸናኤል፡ፈቸቸኤል፡ህያው፡ሆር፡ማሹ፡አሴር፡ሴኮ፡ጀመጀረ፡ሴሬ፡ጉሬ፡ወሬን፡በሬን፡ሀናቁፎ፡ጭጭኤል፡ናችር፡አልማችር፡በከመ፡ደፈንክ፡ልቦ፡ለዲያብሎስ፡ከማሁ፡ድፍን፡ልቦሙ፡ለፀርየ፡ወለጸላእትየ ... ብለህ ስርና ቅጠሉን ደቁሰህ አስማቱን በቀይ ቀለም ጽፈህ ከ፫ ላይ በእሳት አቃጥለህ በጥቁር ጤፍ ቂጣ ጋግረህ ለጸሊም ከልብ አብላ ።
፴፮ #ለወገብ_እና_ለጀርባ_ህመም የቀጠጥና ስርና ቅጠል ከአቱች ስር ጋራ ደቁሰህ አልመህ በአጓት ጠጣ
፴፯ #ለዓቃቤ_ርእስ የቀጠጥናውን አበባ ከትክል ዕብን ላይ ሰልቀህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ለውሰህ ገጽህን ተቀባ እስከ ዓመት ከፀር የአቅበከ ።
፴፰ #ለመፍትሔ_ሀብት የቀጠጥናውን አበባ (አሉማ) የአመራሮ ፍሬ አደይ አበባ አንድነት ቀምመህ አምጽኡን ወይከስት አእዋመ ድረስ ፵፱  ጊዜ ደግመህ በአምሳያ ቅቤ ለውሰህ ራስህን ተቀባ ለሹመትም ይከውን ።
፴፱ #አልሸጥ_ላለ_ከብትና_ለማንኛውም_ንብረት የቀጠጥናውን ስር ነቅለህ በግራ እጅህ ይዘህ ሂድ ይሸጣል ።
፵ #ለገበያ የቀጠጥናውን ስርና የዘረጭ እንባይ የጭቁኝና የአስተናግር ስራቸውን ታጠን ።
፵፩ #ጆሮው_ለደነቆረ የቀጠጥና ፍሬውን ደቁሶ ከሰሊጥ ጋር አንጥሮ በትንሽ በትንሹ በጀሮው ይክተት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🌿🌿 አሰርኩሽ በበረሃ የሚገኘው እፅ ህይወት ይባላል ።
ስሩ ድንች የመሰለ አለው በቆላ የሚገኘው ሴቴው ነው በደጋ የአለው ወንዴው ይባላል ።

#አሰርኩሽ /ወንዴ ሴቴ አለው / እፀ_ማእሱር

፩ #ያበደ ውሻ ለለከፈው ስሩን በወተት አጠጣው ።
፪ #እባብ ለነደፈው በማር አብላ ።
፫ #ለመስተፋቅር የሴቴ አሰርኩሽን ስር በጣዝማ ማር ብልት ቀብቶ መገናኘት ነው ።
በውሀ ሽንት ለውሶ ከተልባ ጋር ጨምሮ ቢበሉ የነገሩትን የነገሩዋትን ለማንም አይናገሩም ።
፬ #ለሀብት #ለፍቅር #ለንግድ የምትፈልገውን ነገር ተናግሮ ለዚህ ሁነኝ ብሎ እፀ አንግስ ደግሞ መቁረጥ ነው ። #ባልዋ_ለጠላት_ሴት_ወይም_ሚስቱ_ለናቀችው_ወንድ
ስሩን ከአለብላቢት ስር ጋር ወቅጦ በሻሽ ሸፍኖ በጉያ ውስጥ ማዋልና ማሳደር፡ከዚህ በጧት የውሀ ጨምቆ በሚበላ በሚጠጣ ቢሰጡት ይስማማሉ ይታረቃሉ፡የሌላ ሰው ወሬ አይሰሙም ።
፮ #ለሀብት ለከብት እርባታ ስሩን ወቅጠህ በወተት በጥብጦ መርጨት ነው፡ለንብ በማር በጥብጦ መርጨት ነው ።
፯ #ለቁስል ቅጠሉን ከፈላጹት ቅጠል ጋር ወቅጦ መደምደም ነው ።
ለኪንታሮት ለነቀርሳ እንደዚሁ ማድረግ ነው
፰ #ለመስተፍቅር ፍሬውን ከአስተናግር ከትንባሆ ከእፀ ሳቤቅ (አረግ እሬሳ) ፍሬ ጋር ወቅጦ በማር ወይም በጣዝማ ማር ለውሶ ቀብቶ መገናኘት ነው ።
፱ #ለሴት_ወንድ_እንዲወዳት ስሩን አክስሎ በግራ ጭን መቅበር ነው ።


🌿🌿መክስት_እፀ አንግስ🌿🌿
#ጸሎተ_በእንተ_እፀዋት

ድፍናኤል ፫ ለቆፎን አቅላጥፎን ገረፎን አግራፎን አቅናፊአን መልአከሰላም ጌቴሬ መልክዮን መላክዮን በእሉ አስማት ክስት ሀይሎ ለእፅ እገሌ ለገብእከ
ለአርእዮ ሀይሎሙ ለእፀዋት በገዳም ወበሀቅል እለ ሀለው ለሰናያን ወለእኩያን አቅላፎን ፫ ሄልሜሎን ሜልዮን አገልዮን አንተ ከሳቴ ዕፅ ክስት ልብየ ወአብርህ አእይንትየ ለነጽሮ ዕፅው ወለገቢረ ሆሳእና ክርስትናኤል ፯ አጥላሹም በጠሹም በሀይለ ዝንቱ አስማቲከ ክስት ለኩሎን ዕፀዋት ለመፍትሔ ሀብት ወስርያት ክርስትናኤል ፯ ሙጥአኤል መጥናኤል ሰልዋንዮን አናንዮን ጸጸጸ በስምኤል ንመውኦ በድፍራኤል ንመውኦ በብክዮስ ንመውኦ ነዓ ነዓ እንተ ከሳቴ እፅ ጥጥያፎን ሰሀቦሙ ወአቅረቦሙ ለኩሎሙ እፀዋት ፍታህ ምስዋሮሙ መሰአር ምረሪሆሙ ወአርህቅ ለዘይሴውሮሙ አጋንንት እኩያን ወቀጥቅጥ ሀይሎሙ ለሰይጣናት ለዘይትቃረኖሙ ለእፀዋት መሀቅል መስተሀቅል መግዱር መሀድር መኢለዮን መቱ ክልዮን መክልዮን መካክልዮን አቅጽላፌድ ትክላፊድ ግምላትዮን ንዑ ንዑ እፅዋት እለሀለውክሙ በገዳም ወበሀቅል ክስቱ ሀይልክሙ ለገቢረ ኩሉ ሰናይ በእደ ካህን እገሌ ፵፱
ገቢር ..... በጠንበለል በቀንጣፋ ተቀጽላ ደግሞ በነጭ ማር መብለት ወይም ዘፍዝፎ ሰባት ቀን መጠመቅ እጁን በእፁ ማሸት ዓይንንም መኳል ነው ።

እፅ ብሩክ ይእቲ እፀህይወት ዘውስተ ነገት በእፀ መድሀኒት በዲበ ምድር !!!


🌿🌿ዕፀ ደብዳቤ🌿🌿
▶️ #ለደከመ_አይን ፦ የእንስላል ቅጠል ጨቅጭቀህ ውሃውን አጥለህ አይንህን ብታጥብ ጥሩ አድርጎ ያሳይሃል ።
▶️#ለነስር ፦ የልት ስር በክርስትና ስምህ ቆርጠህ በ 3 አጽቅ ከርክመህ በግራ ፈትል ከግንባሩ ከግራና ከቀኝ ጆሮ ግንዱ ስር እሰር ወዲያው ይድናል ።
▶️#ለችፌ_ለቆዳ_በሽታ_ለማድያት _ለቋቁቻ ፦የተነጠረ ድኝ ከብርብራ ፍሬ ጋር አገናኝተህ በጣም ሰልቀህ በቅቤ ለውሰህ ብትቀባው ይድናል
▶️#ለሳንባና_ለጉበት ፦ በሶብላ ፣ ዘቃቅቤ በወተት ዘፍዝፈህ ወይም በብርዝ ውሀ በባዶ ሆድ ቢጠጡት በሆድ አንጀት ያለውን ትል በሙሉ ያስወግዳል ።
▶️#ለምቀኛ ፦ የቀጠጥና ስር በወይራ አንካሴ ቆፍረህ የዕገሌን ቁመኛ በስሙ እንዲህ ቁረጥ ብሎ ልጡን ጥሎ በጥሬ ጨው አብሮ ጎርሶ እንደመሟጫ መምጠጥ ነው ። የሚቆረጠው ዓርብና ረዕቡ ነው ።
▶️#ለምች_ለወስፋት_ለሳል_ለልብ_ደዌ_እንደ_ሀሞት_ለሚመረው_ለሚአዞረው_ለሚያንቀጠቅጠው_ለስራይ ፦ ጣዝማ ማር ፣ ንጥር ቅቤ ፣ተልባና ኑግ ፣ ሴቴ ሬት ቡጡን 7 ቀን በማሰሮ አዋህዶ የረጋውን ቢበላ ቅራሬውን ቢጠጣ ይድናል ።
▶️#አንድ_ሰው_ቡዳ_መሆኑን_ለማወቅ ፦ ቅንጭብና ዋጊኖስ ከቤት በጎዘጉዙ ቡዳው ከቤት አይቀመጥም ።
▶️#ለድምፅ ፦ እፀ ተከዜ ፣ መሬንዝ ፣ ጊዜዋ ስራቸው በቅቤ አንጥረህ 7 ዕለት ቀብረህ የምድር እንቧይ 14 ፍሬ ከንጥሩ አግባ ውሃውን እንዘረዘይና አቱች ደምሮ በቶፋ በጣዝማ ማር ጠጣ ፍቱን ልብ ያበራል ይከፍታል ።
▶️#ጆሮው_ለደነቆረ ፦ የቀጠጥና ፣ የሰሌን ፍሬ በአንድነት አዋህዶ ደቁሶ አንጥሮ በጆሮው መጨመር ነው 7 ቀን በ7ኛው ቀን ይሰማኛል ።
▶️#ሌሊት_አልጋ_ላይ_ለሚሸና ፦ የፍልፈል አፈር አንተርሰኸው ካሳደርከው በሃላ ጧት ሳይሸና ሳይፀዳዳ ሳይነጋገር የፍልፈል አፈሩን በኩበት አድርገህ ቢሸናበት ወዲያውኑ ይድናል  ።
▶️#ለአስም ፦ እንጭብር ስርና ቅጠሉን ልምጭ ቅጠሉን የሁለገብ ስርና ቅጠል ጦስኝ ኮሽም ስር በአንድ ለይ ቀቅለህ በጠርሙስ አጥለህ ጠዋት ጠዋት በባዶ ሆድ አንዳንድ ብርጭቆ እስከ 7 ቀን ብትጠጣ ትድናለህ ።
▶️#ለነቀርሳ፦ የፍህሶ ስሩን አድርቀህ አልመህ ሰልቀህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ለውሰህ ብትቀባ ትድናለህ ።
▶️#ዓይኑን_ለሚበላው ፦ የሜዳ እንስላል ስር አክስሎ አልሞ 7 ቀን አይኑን ይኳል ይድናል ።
▶️#ለሰላቢ ፦ የምድር እንቧይ ስር የጊዜዋ ስር በወይራ አንካሴ ምሶ በቀንድ ቢለዋ ቆርጦ ከቤት በራፍ ቢሰቅሉት ሀብትን አያስነካም ።
▶️#ሀብቷ_ላልቀና_ልጅ_አገረድ ፦ የቀጋና የእንጆሪ ቅጠል ዘፍዝፎ በአዲስ ሸክላ 3 ቀን ትታጠብ ስሩንም ትታጠነው ታገባለች ሀብቷም ይቀናል ።
▶️#ከማንኛውም_ሰው_ወይም_ከሴት_ሚስጢር_እንዳይሰወርብህ ፦ ዕፀ ፋሪስ የረኛ ቆሎ አብሾ ፍሬአቸውን አድርቆ ደቁሶ በጉራይማሌ ወፍ ደም ለውሶ ያሮጊት ፈስ የጠለንጂ ስር የአስተናግር ፍሬ የእንቁራሪት ምላስ ጨምረህ በቀይ ከፋይ ጨርቅ ጠቅልለህ በቀይ ሀር ተብትበህ ብትይዝ አይደብቁህም ።
▶️#ኮሶ_የሚያጠፋ ፦ የጠንበለል ቅጠል የወገርት የመጭ የገብር እንቧይ የጫቅማ ወይም የጉሎ የቀጠጥና የነዚህን ስራቸውን ወቅጠህ በሱፍ ውሀ ብትጠጣ ትድናለህ ።
▶️#እብድ_ውሻ_ለነከሰው ፦ የምድር እንቧይ ስር ማክሰኞ በወይራ አንካሴ ምሰህ በቀንድ ቢለዋ ቆርጠህ በጣትህ ክርክር ልክ አድርገህ ከለከፈው ከ 10 ቀን ወይም 5 ቀን ቢሆን ጀምሮ ደቁሰህ በውሀ 3 ወይም 4 ቀን ማቅመስ ነው ።
▶️#አፍንጫው_ለሚገማ_ጆሮው_ለሚመግል ፦ ዕፀ ዘዌ ስሩን ደቁሶ በቅቤ ለውሶ አውሎ አሳድሮ በፀሀይ አቅልጦ አጥሎ መጨመር ነው ይድናል ።
▶️#የደረት_ሳል_መድሀኒት ፦ አብሽ ቀቅሎ አጠንፍፎ አድርቆ ፈጭቶ ማር ጨምሮ በወተት አገንፍሎ በባዶ ሆድ ቢበላ ይነቅልለታል ።
▶️#ግማሽ_እራሱን_እየከፈለ_ለሚያመው ፦ ቀይ ሽንኩርት ይብላ ይድናል ።
▶️#ለሆድ_በሽታ_ሁለ ፦ የሮማን ቅርፊት ከዝንጅብል ጋር 7 ቀን ቢያውጡት ባፉ መግል ያወጣለታል ።
▶️#ለተመለጠ_ፀጉር ፦ የኑግ እና የዋጊኖስ ቅጠል ወቅጦ ጨምቆ ቢቀቡት መልሶ ይበቅላል ።
▶️#እግሩን_እስከ_ባቱ_እስከ_ጭኑ_እከክ_ቢወርሰው_ ፦ የሴት በግ ሀሞት ብትቀባው ይድናል 
▶️#ደምና_መግል_ለሚያስቀምጠው ፦ የፍየል ወተት አንፍረህ አብርደህ ተልባ ጨምረህ ብታጠጣው ይድናል
▶️  #ዛር_ዉላጅ_ሌሊት_በሴት_እየተመሰለች_ለሚገናኘው_ወንድ_በወንድ_እየተመሰለ_ለሚገናኛት_ሴት
የሎል ቅርፊት ወደ ምስራቅ በኩል ቀርፍተህ ማታ እሳት ላይ አድርገህ ታጠነህ ተኛ ከምኝታህ ስትነሳ ያደረ ሽትህን ብትሸናበት ይለቃል ።
▶️    #ሰው_መድሀኒት_ቢያበላህ_እንዲያስታውክህ ፦የግራዋ የሰሌን ስራቸውን በአንድነት ሰፍተህ ያዝ
▶️#ለድምፅ ፦ ዕፀ መናሂ በጥሩ ጠጅ ዘፍዝፈህ 7 ቀን ጠጣ
▶️#ለመሰወር_ለግርማ_ሞገስ ፦ የላንቁሶ ተቀጽላ በበግ ሀሞት ለውሰህ ሰፍተህ ያዝ
▶️#ልቡ_ለሚፈራና_ለሚያበሳጨው_
ዕፀ ልቡና ሁለመናዋን አልመህ በማር ለውሰህ ማቅመስ ነው ።
▶️#ለአቃቤ_ርእስ ፦ የቀጠጥናውን አበባ ከትክል ዕብን ላይ ሰልቀህ ውሀ ባልነካው ቅቤ ለውሰህ ገፅህን ተቀባ እስከ አመት ከጥይት ከዱላ ከፀር የአቅበከ ።
▶️#አልሸጥ_እንስሳ_እና_ለማንኛውም_ንብረት
የቀጠጥና ስር ነቅለህ በግራ እጅህ ይዘህ ሂድ ይሸጣል
▶️#ለገበያ ፦ የቀጠጥናውን ስር የዘረጭ እንቧይ የጭቁኝና የአስተናግር ስራቸውን ታጠን ።
▶️#ለመፍትሄ_ሀብት ፦ የቀጠጥናውን አበባ የአመራሮ ፍሮ የአደይ አበባ አንድነት ቀምመህ አምጽኡን ወይከስት አእዋመ ድረስ 49 ጊዜ ደግመህ አምሳያ እላም ወተት ቅቤ ለውሰህ እራስህን ተቀባ ለሹመትም ይከውናል ።




❤ 2ኛ/ መተት ፦

አንድ ሰው በአንድ ሰው በመቅናት የሚያደርገው የምቀኝነት የአጋንንት ሥራ ነው፡፡ መተት በትዳር ዕድል በልጅ በባል/በሚስት በመቅናት የሚደረግ ክፉ አሠራር ነው፡፡ በትዳር ላይ መተት ከተደረገ ፈጣን የባሕርይ ለውጥ ማምጣትና ሰላም ማጣት ከዛም እስከ መለያየት የሚደርስ መጠላላት በመሃላቸው ሊፈጥር ይችላል፡፡ ታዲያ ሁለቱም በተለይም የተጋቢዎች ወገን የአጋንንቱን አሠራር ባለመረዳት ፍቺን እንደ አማራጭ በማየት በችኮላ፣ ትዕግሥት በማጣት አጋንንቱን ይተባበራሉ፡፡

የቤተሰብ ጣልቃ መግባት ለአጋንንቱ ጥሩ ከለላ ስለሚሆንና ቤተሰብን በጐ በመሰለ ሐሳብ በመደገፍ ይገባባቸውና በእነርሱ አድሮ የመለያየትን ሥራ ይሠራል፡፡ የሚያሳዝነው ሁለቱ ተፋቺዎች ምክንያት ያለው በሚመስል ባልታወቀ ምክንያት ተለያይተው ሌላ ቢያገቡ ትዳራቸው ከድጡ ወደ ማጡ ነው የሚሆንባቸው፡፡ ቀድሞ አጋንንት ስላፋታቸው ሁለተኛው ትዳር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ማበጣበጥ ሰላም መንሳት ይጀምርና ያለያያል፡፡

በዚህም ተፋቺው ‹ትዳር› የሚባለው ነገር ሲነሳ ግፍግፍ በማለት ለልጆቻቸውና ለወዳጆቻቸው የትዳርን መጥፎ ገጽታ ብቻ በመናገር ቤተሰብን ተጽዕኖ ውስጥ በመክተት ታናናሾችንና ልጆችን ‹ትዳር ከእርሷ ወዲያ ላሳር› በማለት ትዳርን እንዲፈሩ ፈርተውም እንዳያገቡ በማድረግ ቆሞ ያስቀራል፡፡

ለዚህ መፍትሔው በትዳር ያልተጠበቀ ክሥተት ሲፈጠር መጸለይና አባቶችን በጸሎት እንዲረዱ ማድረግ፣ በተቻለ አቅም ጠበል መጠመቅ፣ ችግሩን ማወቅና ለችግሩ መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡

ወዳጆቼ በትዳር በመቅናት የሚመተት መተት ልክ እንደ ዛር እና ዓይነ ጥላ ፅንስ ሊያጨናግፍ እና ፅንስን በማኅፀን ውስጥ ሊያጠፋ ይችላል፡፡ በተለይ እርጉዝ ሴት ሆና የመተት አጋንንት ከተላከባት በማሕፀኗ ውስጥ ያለውን ፅንስ ስለሚመታውና ስለሚያድርበት ፅንሱ ሊጨናገፍ እና ሊጠፋ ይችላል፡፡
አንዳንዴ ሊወልዱ ጥቂት ወራት እና ጥቂት ቀናት ብሎም ዕለቱን ለፅንስ ክትትል ምርመራና ለመውለድ ሆስፒታል ሲሄዱ በሐኪሞች ‹‹ፅንሱ ልክ አይደለም፣ ጠፍቷል›› ተብሎ ጆሮ ጭው፣ ልብ ክው የሚያደርግ መርዶ የሚሰሙት በዛር፣ በዓይነ ጥላና በመተት ድግምት በሚፈጠር አሳዛኝ ክሥተት ነው፡፡

ልብ ካላችሁ እህቶቼ ብዙ ፅንሱ ከመጨናገፉ በፊት አንዳንዶች ሕልም ያያሉ፡፡ የሆነ ጥቁር ሰው ሲታገላችሁ፣ ማኅፀናችሁን ሲረግጣችሁ፣ ሲመታችሁ፣ የምትወዱትን ነገር ታግሎ ሲነጥቃችሁ፣ የሆነ ሰው እላያችሁ ላይ ሲከመርባችሁ፣ ሲያንቃችሁ እና ሲተናነቃችሁ ወዘተ ታልማላችሁ፡፡

ይህ የሚሆነው ከእርግዝናችሁ የቀና የቤተሰብ ዛር፣ ዓይነ ጥላ እና በተለይ በትዳራችሁ፣ በእርግዝናችሁ የሚቀናባችሁ ሰው የመተት አጋንንት ሲያስልክባችሁ እና ክፉ መናፍስቱ ሲዋጋችሁ ነው፡፡ ይህን ሕልም ስታዩ የዛኑ ቀን አልያም በጥቂት ቀናት ውስጥ ምንም ሳትሆኑ በድንገት ደም ይፈሳቹኃል ከዛም ፅንሱ ይቋረጣል፡፡
መፍትሔው ???????


❤ 1ኛ/ ዓይነ ጥላ

ዓይነ ጥላ ገርጋሪ ምቀኛ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ይህ ክፉ መንፈስ አድብቶ በመተናኮል ዕድላችንን በመዝጋት እጃችን ገባ ያልነውን ነገር በማሳጣት ይተናኮላል፡፡ ዓይነ ጥላ አብረውን ከሚወለዱና ተወልደን ከጊዜ በኋላ ከሚጠናወቱን ክፉ መንፈስ አንዱ ነው፡፡

ዓይነ ጥላ ያለባቸው ባል ወይም ሚስት በትዳራቸው ሰላም፣ ፍቅር፣ መግባባት በመሃላቸው በፍጹም አይኖርም፡፡ በተለይ በሩካቤ ሥጋ አይስማሙም፣ አይጣጣሙም፣ አይግባቡም፡፡

የዓይነ ጥላ መንፈስ ተጠቂ ከሆኑ እንኳን ሩካቤ ሥጋን በመፈቃቀድ ሊፈጽሙ ቀርቶ አብሮ መተኛት መተቃቀፍ አይወዱም፡፡ መንፈሱ የባልን ሰውነት ወይም የሚስትን ሰውነት እንደ ባዕድ አካል በማሳየት እንዲቀፈው/እንዲቀፋት በማድረግ ምክንያት የሌለውን ጥላቻ በመሃላቸው ይዘራል፡፡ በሩካቤ ሥጋም ደስታ የሚባል ያሳጣቸዋል፡፡ ሩካቤ ሥጋን የሚፈጽሙት ስለተጋቡ ብቻ እንጂ ወደውና ፈቅደው አይደለም፡፡ ደመ ቀዝቃዛ ያደርጋቸዋል፡፡

ከትዳር በፊት ወደ ሕይወታቸው ሰተት ብሎ የገባው መንፈስ በትዳራቸው ውስጥ ራሱን በተለያየ ጠባይና መልክ በመግለጥ፣ ለትዳራቸው መበጣበጥ እና መናወጥ ምክንያት ይሆናል፡፡ በማግባታቸው የተበሳጨው ዓይነ ጥላ በትዳር ኑሮአቸው ውስጥ የበቀል መርዙን እየረጨ፣ ትዳሩን እያቀጨጨ ለፍቺ ይዳርጋል፡፡

ዓይነ ጥላ በትዳር ሕይወት ሰላም በመንሳት እና በሩካቤ ሥጋ ጊዜ ስሜት በማጥፋት፣ የሩካቤ ሥጋ ደስታን በማበላሸት የተካነ ስለሆነ የመንፈሱን ጠባይ አውቃችሁ ልትነቁበት እና በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ልትዋጉት እንዲሁም በቅዱስ ቁርባን ጸጋ ከሕይወታችሁ ልታርቁት ይገባል፡፡ ምክንያቱም መንፈሱ ሸፍጠኛና ከጠባይ ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ የብዙዎችን ትዳር ለፍቺ አብቅቷል፡፡
መፍትሔው ???????




የዳዊት ገቢር
#ለአቃቤ_ዕርስ
❤️መዝሙር፭ #ቃልየ፧አጽምዕ፧እግዚኦ፧ወለቡ፧ጽራሕየ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ..በየብስም,ባሕርም,በመንገድም እህል ሳትቀምስ በቅባ ቅዱስ ,በሜሮን,ውሀ ባልነካው ቅቤ ..በማንኛውም ቅባት ላይ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ #ከሞት ይጠብቅሀል
እንዲሁ #ለራስ_ምታት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ተቀባ ።
#አይኑን_ለታመመ
❤️መዝሙር ፮
#እግዚኦ፣በመዓትከ፣ኢትቅሥፈኒ፣ወበቅሠፍትከ፣ኢትገሥጸኒ.... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም
#ገቢሩ .. መዝሙሩን ፯ ጊዜ ደግሞ ፅፎ መያዝ እንዲሁ በቅቤ ፯ ጊዜ ደግሞ የታመመውን አይን መቀባት ያድናል ።
#ደግሞም ለምትፈራው ነገር ሁሉ ከቤት ሳትወጣ ማንኛውንም ሽት ቤት ሳትጠቀም ከሰው ሳትነጋገር የምትፈራውን ሰው ስም ከነእናቱ  ስም እየጠራህ ፯ ጊዜ ድገም ከእሱ ትድናለህ ።

#አስማት_ለተዋለበት_የአጋንንት_ቁራኛ_ለያዘው_ሰው
❤️መዝሙር ፯
#እግዚኦ፣አምላኪየ፣ብከ፣ተወከልኩ፣ኢትግድፈኒ....ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ .. ፀሀይ ከማታየው ጉድጓድ ውሀ ቀድተህ ከዕለቱ ከዕለቱ ሐፁረ መስቀል ፣ አርድእት ፣ ባርቶስ ጋር ፰ ቀን ፯ ፯ጊዜ ደግመህ አጥምቀው በእግዚአብሔር ቸርነት ይድናል ።  ይህንንም ስታደርግ ደርግ ልጅና ከብት ማንኛውንም ሰው ከሌለበት ሜዳ ነው ።  ከቤትም ከመንገድም አትድገም
#እንደዚሁ ባሏ ለጠላት ሴት በቅቤ ፯ ጊዜ ደግመህ ሰውነቷን ትቀባ ባሏ ይወዳታል ።

#ለታመሙ_ሕፃናት
❤️መዝሙር ፰
#እግዚኦ፣እግዚእነ፣ጥቀ፣ተሰብሐ፣ስምከ፣በኩሉ፣ምድር..ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ መዝሙሩን ጽፈህ አሲዘው ይፈወሳል ።
#እንዲሁ ለታሰረ ሰውም በኅብስት ላይ ጽፈህ ስጠው በእግዚአብሔር ቸርነት ይፈታል
#እንዲሁ በዝርግ ሳህን ላይ ጽፈህ በዓሣ መረብ ከተህ ከባህር ብትጥለው ብዙ አሳ ይያዝልሃል ። 
#እንዲሁ ለገበያ በእንቧጮ አርጩሜ ፯ ጊዜ ደግመህ የምትሸጠውን  እቃ ፯ ጊዜ ብትመታው ይሸጣል
#እንዲሁ ጥሬ ጨው በማር ለውሰህ ፯ ጊዜ ደግመህ ብትበላ ከሰው ጋር በፍቅር እና በሰላም ለመኖር ያስችልሃል ።

#ጠላት_በበረታብህ_ጊዜ
❤️መዝሙር ፱
#እገኒ፣ለከ፣እግዚኦ፣በኩሉ፣ልብየ ... ከሚለው ጀምሮ ሙሉውን መድገም ።
#ገቢሩ .. የራሱን የእናቱን ስም እየጠራህ ፫ ፫ ጊዜ ብትደግም ይታገስሃል ።
#እንዲሁ ሀገር ቢጠላህ ፯ ጊዜ በሊት ውሀ ደግመህ በ፬ቱ ማዕዘን እርጭ ሰው ሁሉ ይወድሃል።
እንዲህ እያለ እስከ መዝሙር ፻፳፭ ድረስ ይቀጥላል ለዛሬ ምሽት እነዚህን ፃፍኩላችሁ !!!
የዳዊቱን ሙሉ ገቢር የምትፈልጉ ሰዎች ካላችሁ ከታች pdf የምለቅላችሁ ይሆናል ።




አንዳንዴ ሊወልዱ ጥቂት ወራት እና ጥቂት ቀናት ብሎም ዕለቱን ለፅንስ ክትትል ምርመራና ለመውለድ ሆስፒታል ሲሄዱ በሐኪሞች ‹‹ፅንሱ ልክ አይደለም፣ ጠፍቷል›› ተብሎ ጆሮ ጭው፣ ልብ ክው የሚያደርግ መርዶ የሚሰሙት በዛር፣ በዓይነ ጥላና በመተት ድግምት በሚፈጠር አሳዛኝ ክሥተት ነው፡፡

ልብ ካላችሁ እህቶቼ ብዙ ፅንሱ ከመጨናገፉ በፊት አንዳንዶች ሕልም ያያሉ፡፡ የሆነ ጥቁር ሰው ሲታገላችሁ፣ ማኅፀናችሁን ሲረግጣችሁ፣ ሲመታችሁ፣ የምትወዱትን ነገር ታግሎ ሲነጥቃችሁ፣ የሆነ ሰው እላያችሁ ላይ ሲከመርባችሁ፣ ሲያንቃችሁ እና ሲተናነቃችሁ ወዘተ ታልማላችሁ፡፡

ይህ የሚሆነው ከእርግዝናችሁ የቀና የቤተሰብ ዛር፣ ዓይነ ጥላ እና በተለይ በትዳራችሁ፣ በእርግዝናችሁ የሚቀናባችሁ ሰው የመተት አጋንንት ሲያስልክባችሁ እና ክፉ መናፍስቱ ሲዋጋችሁ ነው፡፡ ይህን ሕልም ስታዩ የዛኑ ቀን አልያም በጥቂት ቀናት ውስጥ ምንም ሳትሆኑ በድንገት ደም ይፈሳቹኃል ከዛም ፅንሱ ይቋረጣል፡፡

❤ 5ኛ/ መስተፋቅር ፦

መስተፋቅር ማለት አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ያለ ፍላጐትዋ በአጋንንት ጥበብ እንድትወደው ማድረግ ነው፡፡ መስተፋቅር የተደረገበት ሰው ከፍተኛ ፍቅር ውስጥ በመግባት በቤተሰብ እንኳን ተው/ተይ ቢባሉ ከቤተሰብ እስከ መለያየት ተወራርደው እንቢኝ ይላሉ፡፡

በመስተፋቅር የተጀመረ ትዳር ትልቁ ችግር እግዚአብሔር የመሠረተው ሳይሆን በሰይጣን ጥበብ የተመሠረተ ስለሆነ አይጸናም፡፡ በጊዜ ሂደት ምስጢሩ ይወጣል አልያም መስተፋቀሩ ይከሽፋል፡፡ ያኔ በመናፍስት ጥበብ ያዋረሱት ፍቅር እንደ ጉም ይተንና የተደረገበት ሰው እንደ ሰመመን መርፌ ከነቃ ሁሉም ነገር ይበላሻል፡፡

በመስተፋቅር በተመሠረተ ትዳር የሚወለዱትም ልጆች የመናፍስቱ ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ጤና ከማጣት እስከ መደንዘዝ ይደርሳሉ፡፡ በመስተፋቅር በተመሠረተ ትዳር የሚወለዱት ልጆች የአጋንንቱ ግብር ናቸው፡፡

ትዳሩ የተመሠረተው እና ልጆቹም የሚመጡበት መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለማይወደድና ብሎም ስለማይባረኩ የእናት ወይም የአባታቸው አጋንንት እየተጠናወታቸው ለሀገር እና ለወገን በተለይም ለቤተ ክርስቲያን የማይጠቅሙ፣ ከጥቅማቸው ጥፋታቸው ያመዘነ ልጆች ይሆናሉ፡፡

❤ 6ኛ/ ቡዳ ፦

ወዳጆቼ እንደ ቀልድ የምንሰማውና የምናየው የቡዳ መንፈስ ጣጣው ብዙ ነው፡፡ አንዲት ሴት በውበቷ፣ በጸጉሯ፣ በቁመናዋ የአጋንንት ጥርስ ውስጥ ገብታ፤ በቡዳ መንፈስ ተበልታ ከሆነ በትዳር ሕይወቷ እጅጉን ልትቸገር ትችላለች፡፡

በተለይ በጸባይ እና በልጅ ማጣት ትቸገራለች፡፡ የቡዳ መንፈስ ያለባት ሴት አመሏ ንጭንጭ ይላል፣ ሆድ የሚብሳት እና ለቅሶ የሚቀድማት ናት፡፡ በተለይ መልከኛ ከሆነች ራስዋን የምትጥል፣ ለውበቷ ግድ የሌላት ዝርክርክ ትሆናለች፡፡

እንዲሁም የቡዳ መንፈሱ በማኅፀኗ ውስጥ አሸምቆ በመደበቅ ፅንስ ሊያጨናግፍባት እና ሊያጠፋባት ይችላል፡፡ በቡዳ ዓይኗን ከተበላች ዓይኗን ያቃጥላታል፣ አጥርቶ የማየት ችግር ይገጥማታል፣ ውበቷ ይበላሻል ለምሳሌ ፊቷ እንደ ማድያት ባለ ሁኔታ ይበልዛል፣ በወጣትነቷ ፊቷ የአሮጊት ፊት ይመስላል፣ ያለ እድሜዋ ፊቷ ይሸበሸባል፡፡ ማኅፀኗን ይቆርጣታል የሚገላበጥ እና ውስጡ የሆነ ነገር ያለ መስሎ ይሰማታል፡፡

ወዳጆቼ ስለ ቡዳ ካነሳን እንደው እርግዝና በቡዳ እንደሚበላ ታውቃላችሁ? ብዙዎቻችን የቡዳ መንፈስ በውበት በደም ግባት ወዘተ የሚገባ ብቻ ይመስለናል፡፡ ግን እርግዝናም በቡዳ ይበላል፡፡ እናቶቻችን ሲያረግዙ ማርገዛቸውን ለሰው የማያሳውቁት፣ እርግዝናቸውን በልብስ ደረብረብ አድርገው የሚሸፍኑት ከዓይነ ወግ ቡዳ ራሳቸውን ለመጠበቅ ብለው ነው፡፡ ልብ ካላችሁ አንዳንድ ሴቶች እርግዝናቸው ያምራል፡፡ ከቁመናቸው ጀምሮ እስከ ፅንሱ አቀማመጥ ላያቸው ለዓይን ደስ ይላሉ፡፡

የቡዳ መንፈስ ደግሞ ከዓይን ተነስቶ ወደ ሰው የሚገባ መንፈስ ስለሆነ እርግዝናቸውን በቡዳ ይበላል፡፡ ከዛማ ብዙም ሳይቆዩ አቅለሸለሸኝ፣ አመመኝ፣ ማኅፀኔን ቆረጠኝ ወዘተ በማለት ደም ሊመታቸውና ፅንሱ ሊጨናገፍ ብሎም ሊጠፋ ይችላል፡፡

ስለዚህ እባካችሁ እርጉዝ ስትሆኑ ፅንሱን ሰው ይይልኝ፣ ማርገዜን ምቀኞቼ ይወቁልኝ፣ ዓይናቸው ደም ይልበስ እያላችሁ ስስ ልብስ በመልበስ አትታዩ፡፡ በተለይ የመውለጃ ጊዜያችሁ ሲደርስ ሰው የሚበዛበት ቦታ በመታየት እና በመዝናናት ስም ዞር ዞር ከማለት ታቀቡ፡፡

ቤቢ ሻወር እያላችሁ እርግዝናችሁን በቡዳ አታስበሉ፡፡ ቤቢ ሻወር ብላችሁ እዩልኝ እንዳላችሁ በቡዳ የተበላ፣ ጤና ያጣ ልጅ ወልዳችሁ ልጄን አትዩብኝ፣ ደብቁልኝ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፡፡

ወዳጆቼ ከላይ ያየናቸው ርኩሳን መናፍስት፣ በትዳራችን ላይ ጣልቃ በመግባት፣ ካለመግባባት እስከ መለያየት ሊያደርሱን ስለሚችሉ በትዳራችን ውስጥ የሚፈጠሩትን ነገሮች ረጋ ብሎ፣ አስተውሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡

በተረፈ ትዳራችሁ በክፉ መናፍስትም ይሁን በሰው ተንኮል ችግር ውስጥ ከገባ፣ የወለድናቸውም ልጆች እክል ከገጠማቸው ንስሐ ገብተን፣ በጸሎት በርትተን በአምልኮት ሕይወት ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር ከመለስን ምህረቱን፣ ቸርነቱን ወደ እኛ ይመልሳል፣ መፍትሔም ይሰጠናል፡፡

ቀናችሁን በጸሎት ጀምሩ፣ ማታ በጸሎት እደሩ!

መርጌታ አምደብርሃን ይትባረክ !!!

Показано 20 последних публикаций.