እጮኛሞች ሆይ እናንተ ተፋቅራችሁ፣ተዋዳችሁ አላውቅበት ብላችሁ የምታበላሹት የነገ የትዳር ሕይወት ስንቶቹ የሚመኙት እና እግዚአብሔርን የሚማጸኑበት ሕይወት ነው፡፡ እናንተ ሳተውቁ የምታበ
ላሹ አጋጣሚ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ተጋብተው ወልደው ይከብሩበት ነበር፡፡ እናንተ ትዳር ሰልችቷች ስትለየዩ የሚበተኑት የሚንከራተቱት ልጆች ስንት መሐኖች እግዚአብሔርን ‹‹እባክህ የዓይኔ ማረፍያ አንድ ልጅ ስጠኝ›› ብለው የሚጸልዩት ነው፡፡
ባለ ትዳሮች ሆይ እናንተ መኖር መፋቀር አቅትዋችሁ ሕይወቱ ሰልችቷችሁ የምታፈርሱት ትዳር ስንቶቹ ለመኖር የሚጓጉት ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላ የሰጣችሁ እጮኛ እና ትዳር በዓይነ ጥላ ተንኮል የሚኮላሻው ስላላወቃችሁበት ነው፡፡ ግን ቁጭት ውስጥ የምትገቡት በእጃችሁ ያለውን እድል ስታጡት አሳልፋችሁ ለሌላ ስትሰጡት ነው፡፡ ዓይነ ጥላው እናንተን በመቆጨት ለማቃጠል ካለፈ በኃላ ‹‹ያኔ ምን ሆኜ ነው፣ለምን እንደዛ አደረኩ›› እያስበላ የጸጸት ዘመናትን እንድታሳልፉ ያደርጋችኃል፡፡ ታጋሹ ኢዮብ በሕይወቱ ላይ የደረሰበት ታላቅ ፈተናና መከራ በሥጋው ስልችት ስላለ ‹‹ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት›› በማለት ተናግሯል፡፡ /ኢዮ 10÷1/
ዓይነ ጥላ እጮኛሞችንና በላትዳሮችን በነገሮች ሁሉ እያሰለቻቸው ሌላ ሰውን እያስመኛቸው ለዝሙት ያጋልጣቸዋል፡፡ ወዳጆቼ የተጠናወተን ዓይነ ጥላ እንኳን ሥጋዊ የእጮኝነት እና የትዳር ሕይወትን ቀርቶ የነፍሳችንን መንፈሳዊ ሕይወት ያሰለቸናል፡፡ ጸሎት እንድንሰለች ያደርገን የለ? ጸሎት ስንሰለች እኮ መጨረሻችን ጸሎቱን መተው ነው፡፡ ልክ እንደ ጸሎቱ ፍቅር እና ትዳር ሲሰለቸን መጨረሻ መለያየት ነው፡፡ የዓይነ ጥላው አጋንንታዊ ግቡ የእኛን ሕይወት ማበላሸት እና ማኮላሸት ነው፡፡
ወዳጆቼ አንዳንዶች ‹‹መኖር ሰለቸኝ›› ሲሉ የምትሰሙት ዓይነ ጥላቸው መኖር ሲያሰለቻቸው ነው፡፡ ዓይነ ጥላ መኖር ሲያሰለቸን እረሳችንን እንድናጠፋ ነው የሚገፋፋን፡፡ መኖር መሰልቸት ለአጋንንቱ በቁም መሞት፡፡ በእጮኝነት መኖር መሰልቸት ለአጋንንቱ እጅ መስጠት ነው፡፡ በትዳር መኖር መሰልቸው በአጋንንቱ ተንኮል ስር መውደቅ ነው፡፡
ዛሬ ወጣቱን ዓይነ ጥላው ሕይወትን ስላሰለቻቸው በሱስ መጠመድ፣በስካር ሌሊቱን ሁሉ ማበድ ምንም አይመስላቸውም፡፡ ቀድሞ በማሰልቸት ስለገባባቸው መኖር የሚለው ነገር ለእነሱ ትርጉም የለውም፡፡
ዓይነ ጥላ እራሳችንን እንድንሰለች ያደርገናል፡፡ እራሳችንን ስንሰለች ለምን እንደምንኖር፣ለማን እንደምንኖር ስለማናውቅ የባዶነት ስሜት ውስጥ ይከተናል፡፡ ስለዚህ እጮኛሞች፣ባለትዳሮች የያዛችሁት ሕይወት የመሰልቸት ስሜት ከተሰማችሁ ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ በጸሎትም ወደ ፈጣሪ ጩኹ፡፡ ካልሆነ ግን በእጃችሁ ያለውን ሕይወት እያያችሁት ከእጃችሁ በማውጣት የሙሉ ጎዶሎ ያደርጋችኃል፡፡ ዓይነ ጥላው ሕይወታችንን በማሰልቸት ሳይቀማን ልንነቃበት እና ልናውቅበት ይገባል፡፡ ዛሬ የስንቱ የፍቅር እና የትዳር ሕይወት ባላታወቀ ግን በዓይነ ጥላ ስውድ ደባ ሕይወት አልባ ሆኗል፡፡ ላለፈ ክረምት ቤት ባይሰራም ዓይነ ጥላ በማሰልቸት ብዙ ነገራችንን ቢያበላሽም ካለፈ ሕይወት በመማር በአጋንት ሴራ የራሳችን የሆነ ነገርን እንዳንነጠቅ መጠንቅ አለብን፡፡
አንብበው ሲጨርሱ ለሌሎች ሼር በማድረግ ያቋድሱ፡፡
ክፍል ስድስት
በመጥፎ የሰውነት ጠረን እና ሽታ የሚመሰል ዓይነ ጥላ
/ወንዶች በተለይ ሴቶች የሚቸገሩበት/
ይቀጥላል …