✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


መዝሙር 147:7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም
በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций






እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ።


♡ ወንድ ልጅ ተሰጠን ♡



ወንድ ልጅ ተሠጠን ሕፃን ተወለደ
በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ/2/


ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የተባለው አዳም
ይኸው ተወለደ ኪዳኑን አረሳም
በሞት ጥላ ላለን ጨለማን አራቀ
አማናዊው ፀሀይ ከድንግል ሠረቀ

ተመኝቶ ነበር ሙሴ ገፁን ሊያየው
አይተህኝ አትቆምም ብሎ ከለከለው
እርሱ ጀርባውን ሲያይ አዘልሽው በጀርባሽ
ከሁሉ መረጠሽ በልጁ ፊት በራሽ


ፊታቸውን ጋርደው መላእክት ሲቆሙ
እናቱ ነሽና ክንድሽ ላይ ነው ፍሙ
ይህ እሳት ወረደ ቤተልሔም ግርግም
በእጆችሽ ዳሰስነው አላቃጠለንም

በአባቱ እቅፍ ያለው እስከሚተርከው
አንድስ እንኳን የለም እግዚአብሔርን ያየው
ቢለንም ዮሐንስ በቃለ ወንጌሉ
አየነው በአንች እቅፍ በተለየ አካሉ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
     @Yemezmurgtm
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈




Репост из: ✟ ጋሜል- ዘ ኦርቶዶክስ ✟
​​​​​​

አጭር ግጥም
ርእስ ታላቅ ነው ልደቱ !!



በጉዞ ላይ ነበር ጌታችን ሲወለድ
ሊፈጽም ሲመጣ የአባቱን ፈቃድ
በቤተልሔም ዋሻ በዛች በግርግም
ከሰው ልጅ ተገኘ መድኃኔ ዓለም
የጌታ መወለድ መላእክት አይተው
አረኞች በሌሊት በስራ ላይ ሳሉ
በጌታ ብርሀን ዙሪያቸው ተሞሉ
መላእክት ከሰው ጋር በአድነት ዘመሩ
የጌታን መወለድ ለእረኞች ሲያበስሩ
ምስጋና ለእግዚአብሔር በላይ በአርያም
ለሰው ልጅ ይሁን በምድር ሰላም
ብለው ተቀኙለት ለሰራዊት ጌታ
ስጋን ለብሶልናል ሰይጣንን ሊረታ
ይህ ታላቅ ቀን ከመሆኑ በፊት
ተገልጾ ነበረ የክርስቶስ ልደት
ለሰብአ ሰገል እርሱን ላከበሩት
የጌታን መወለድ ባይናቸው ለማየት
እጅ መንሻ ይዘው በእጃቸው ይዘው
የልባቸውን ፍቅር ለመግለጽ ፈልገው
እውነተኛ ካህን አንተ ብቻ ነህ
ከሀያላን ሁሉ አቻ የሌለህ


🌷መልካም የገና በዓል ይሁንልን 🌷
💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox


♡ ይኸው (እሰይ) ተወለደ ♡

ይኸው ተወለደ የዓለም መድኀኒት/፫
እሰይ ተወለደ የዓለም መድኀኒት/፫

ትንቢት ተናገሩ ነቢያቱ ሁሉ/፫
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ/፫

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ/፫
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ/፫

ሰብአ ሰገል መጡ እጅ መንሻ ይዘው/፫
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ገበሩለት ሰግደው/፫

ምዕመናን እንሂድ ከልደቱ ቤት/፫
ውኃው ሆኗልና ማርና ወተት/፫

በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ/፫
ብሥራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ/፫
የአእላፋት ዝማሬ
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
     @Yemezmurgtm
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈




♡ በቤተልሔም ድንግ ወለደች ♡



በቤተልሄም ድንግል ወለደች
አማኑኤልን ታቅፋ ታየች
እረኞች ተቀኙ መላዕክት ዘመሩ
ስብሀት ለእግዚአብሔር በሠማይ በምድሩ

የያዕቆብ ኮከብ ከሩቁ ያየነው
በኤፍራታ ዋሻ በዱር አገኘነው
ድንቅ መካንሀያል ወንድ ልጅ ተሠጠን
በከብቶቹ ግርግም ተወልዷል ሊያነፃን      
ድንግል ያጠባችው
       ማርያም ያዘለችው
       ሁሉ በእርሱ የሆነ እግዚአብሔር ነው

ያረምና ሠባ የቴርሠሥ ነገስታት
ከሩቅ ምስራቅ መጡ ወድቀው ሊሰግዱለት
አንቺ ቤተልሄም የይሁዳ ምድር
እልልታሽ ተሰማ የዳዊት ሀገር
ድንግል ያጠባችው

ማርያምን ለመውሰድ ዮሴፍ ሆይ አትፍራ
ከመንፈስ ቅዱስ ነው ይሄ ድንቅ ስራ
ያለዘራ በዕሲ ጌታን የወለደች
የያቄም ልጅ ፅዮን እመብርሀን ነች
ድንግል ያጠባችው


በስጋና በደም ስለተካፈለ
ፍፁም አምላክና ፍፁም ሰው ተባለ
ወልደ-ማርያም ነው ወልደ-እግዚአብሔር
ለአለም የሠጠህ ሠላምና ፍቅር
ድንግል ያጠባችው

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


♡ የአማልክት አምላክ ተወለደ ♡


የአማልክት አምላክ ተወለደ
ተወለደ መድኃኔዓለም
የጌቶች ጌታ ተወለደ መድኃኔዓለም
ከድንግል ማርያም በቤተልሔም
ተወለደ አማኑኤል/2/


መጣ ወረደ          ተወለደ አማኑኤል
ክብሩን አዋርዶ     ተወለደ አማኑኤል
በበረት ተኛ           ተወለደ አማኑኤል
ትሕትናን ወዶ        ተወለደ አማኑኤል
ጌታ ተወልዷል      ተወለደ አማኑኤል
ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል
ጠብን አርቆ          ተወለደ አማኑኤል
ሊሰጠን ሰላም      ተወለደ አማኑኤል

የዲያብሎስን      ተወለደ አማኑኤል
ሥልጣን ሊሽር    ተወለደ አማኑኤል
እሱን ሊፈታ         ተወለደ አማኑኤል
በኃጢአት እስር    ተወለደ አማኑኤል
ይሄው ተወልዷል  ተወለደ አማኑኤል
በከብቶች በረት    ተወለደ አማኑኤል
አልፋ ዖሜጋ        ተወለደ አማኑኤል
አምላክ አማልክት ተወለደ አማኑኤል



እናመስግነው       ተወለደ አማኑኤል
እንደ መላእክት     ተወለደ አማኑኤል
ተወልዷልና          ተወለደ አማኑኤል
የዓለም መድኃኒት  ተወለደ አማኑኤል
ቃል ስጋ ሆነ         ተወለደ አማኑኤል
ከድንግል ማርያም ተወለደ አማኑኤል
የጌቶች ጌታ          ተወለደ አማኑኤል
መድኃኔዓለም        ተወለደ አማኑኤል

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር
@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm




♡ በበረት የተኛው ♡



በበረት የተኛው ቅዱሱ ሕፃን
ልብስም አልለበሰም ነበረ ዕርቃኑን /2/

በጨርቅ ጠቅልላ ስታቅፈው እናቱ
ትንፋሽ አለበሱት ከብበው እንስሳቱ /2/


እሰይ የምሥራች ሀሌ ሀሌ ሉያ
ጌታ ተወለደ ሊሆነን አርአያ /2/

የአእላፋት ዝማሬ

@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm


ከክርስቶስ ጋር ካልኖርክ በጭንቀት ትኖራለህ። በሀዘን, በጭንቀት, ውስጥ. ከመድኃኒቶች ሁሉ የሚበልጠው ራስን ለክርስቶስ በማደርግ ራስን ማቅረብ ነው። ሁሉም ነገር ይድናል. ሁሉም ነገር በትክክል ይሰራል. የእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን ይለውጣል፡ ይቀድሳል። ሁሉንም ነገር ያስተካክላል።



ቸሩ መድኃኔ ዓለም ፍቅሩን ያሳድርብን ☦️


♡ ቸሩ ሆይ ♡

ቸሩ ሆይ ቸሩ ሆይ ናና /2/
ቸሩ ሆይ አማኑኤል ናና
የእሥራኤል መና ቸሩ ሆይ ናና
ቸሩ ሆይ መድኃኔዓለም ናና



ቸሩ ሆይ     ለዓይነ ስውር መሪ 
ቸሩ ሆይ     ምርኩዝ መመኪያ ነህ    
ቸሩ ሆይ     አንተን የሚመስል 
ቸሩ ሆይ     ምንም ነገር የለም    
ቸሩ ሆይ     ምሕረትና ፍቅርህ  
ቸሩ ሆይ     ወሰን ወደር የለው    
ቸሩ ሆይ     ሳንወድህ ወደኽን    
ቸሩ ሆይ     ፈልገህ ጠራህን

ቸሩ ሆይ     ሰምተህ እዳልሰማህ 
ቸሩ ሆይ     አይተህ እንዳላየህ    
ቸሩ ሆይ     ሁሉን ታልፈዋለህ  
ቸሩ ሆይ     ፍቅራዊ አባት ነህ    
ቸሩ ሆይ     አማኑኤል ጌታ     
ቸሩ ሆይ     ቸሩ ፈጣሪያችን    
ቸሩ ሆይ     ውለታህ ብዙ ነው   
ቸሩ ሆይ     ለእኛ የዋልክልን



ቸሩ ሆይ     በከብቶች ማደሪያ 
ቸሩ ሆይ     በዚያች ትንሽ ግርግም    
ቸሩ ሆይ     ተወልዶ አዳነን   
ቸሩ ሆይ     ጌታ መድኃኔዓለም    
ቸሩ ሆይ     እልል በሉ ሰዎች  
ቸሩ ሆይ     አንድ ላይ ዘመሩ    
ቸሩ ሆይ     ስብሃት ለእግዚአብሔር 
ቸሩ ሆይ     በአርያም በሉ

የአእላፋት ዝማሬ
@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm


♡ አምላክ ሰው ሆነ ♡


አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ(፪)
በድንግል ማርያም ተከናወነ


የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ

ከሦስቱ አካል ወልድ አንዱ አካል
መጣ ወረደ በገባው ቃል
ተጸንሶ ሳለ ወልድ ከእናቱ
አልተነጠለም ከሦስትነቱ
ተአምራት አርጓል ድውይ ፈውሷል በአምላክነቱ

ይህንን ድንቅ ምስጢር በሉ ግሩም
ምስጋና አቅርቡ ለዘለዓለም
በስነ ፍጥረት ይታወቃል
የዓለም ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል
ደስ ይበላችሁ ደስ ይበለን በሉ እልል

የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ



ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm




♡ አማኑኤል ተወለደ ♡

አማኑኤል ተወለደ/2/
ዓለም ነፃ ወጣ ጠላት ተዋረደ
ምድር ነጻወጣች ጠላት ተዋረደ


ከራዲዮን ጌታ ስሙ ድንቅ መካር
በከብቶቹ ስፍራ ታይቶናል በፍቅር
ዓለምን ማረከ በበረት ተኝቶ
ድንገት በብርሃን የሰውን ልጅን ሞልቶ

በጨርቅ ተጠቅልሎ እንስሳት ሲያሞቁት
ተገኝቷል ኢየሱስ በከብቶቹ በረት
እንደ ተርሲስ ንጉሥ ይዘናል አምሃ
ስላየን ተወልዶ የህይወታችን ውሃ

ከዋክብትን የሚቆጥረው አማኑኤል ሊቆጠር
ወርዷል ቤተልሔም ከእናቱ ጋር ሊያድር
ያ ደገኛ ትንቢት ታይቶናል ማዳኑ
የመጎብኘት ዕለት መቶልናል ቀኑ


እስከ ቤተልሔም መርቶናል ኮከቡ
ዛሬም እንዲሰበር የፈውስ ርሀቡ
ታይዉስ ተገለጠ አዳኙ ማስያስ
በርስታችን ቆመን ልንል ሥሉስ ቅዱስ

ማያት አፍላጋቱን በእፍኙ የሰፈረ
የሰው ስጋ ለብሶ በማርያም አደረ
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሆነ
ሰላምም ለሰው ልጅ በምድር ተወሰነ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm


✞ አቡነ ሐብተማርያም ✞

ጽኑ ቃልኪዳን ነው ለሱ የተሰጠው
አቡነ ሐብተማርያም ለጽድቅ የመነነው
ክብሩ ታላቅ ነው ጸጋው ልዩ ነው

የጸሎቱ ዕጣን ድውዩን አድኗል
የታወረው በርቶ ሽባውን ተርትሯል
/ዛሬም ለአለማችን ጽኑ መዳኛ ነው
አባ ሐብተማርያም ኪዳኑ ልዩ ነው/(፪)

አዝ= = = = =
ረሃብ ቸነፈር ምድር ላይ ቢበዛ
የማዕጠንቱ ጸሎት ፈውሱን አበዛ
/በውስጥም በውጭም በጥላው ላላሉቱ
ዛሬም መድኃኒት ነው አቡነ እምነቱ/(፪)

አዝ= = = = =
ለሚያምን ይቻላል ተብሎ እንደተጻፈ
በሐብተማርያም ጸሎት ጽኑ ሞት አለፈ
/ከድቅድቅ ጨለማ መውጣት ከአማራችሁ
ሐብተማርያም በሉ ትፈወሳላችሁ/(፪)

አዝ= = = = =
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች
በስራዋ ብዙ ፈውስን ትሰጣለች
/ይደርብን በእኛ የቅዱሳን ጸጋ
ምልጃ ጥባቄአቸው እንዲሆን ከእኛጋ/

መዝሙር
ብርሃኑ ተረፈ


♡ እውነተኛ ስላም ♡

እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው
እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው
እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ{፪}

ሀጢያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል
ከአንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል
ወደ አንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለው
እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

ለቅዳሴ ፆሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ
በአደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ
ተሰነካክዬ ወድቄ አለሁና
እርዳኝ አማኑኤል በሀይማኖት ልፅና

አይኔ እንባን ያምንጭ ላልቅስ ስለ ሀጢያቴ
የንስሀ ትሁን ቀሪዋ ህይወቴ
በመዳኔ ሰአት በዛሬዋ ለት
ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት

ጌታ ሆይ ፀፀቴን እንባዬን ተቀበል
አባትሽ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል
ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መተህብኝ
በርህን በመዝጋት ከደጅ አታስቀረኝ


እያለፈ ነው ዘመኔ

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/ 
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/ 


በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/ 
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ 

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/ 
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/ 

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ 
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/ 

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ 
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/ 

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ 
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/ 

@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm


♡ በጎል በጎል ♡


በጎል በጎል ሰብአ ሰገል/፬/ 
በጎል ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቶ/፪/

ፀሐይ ፀሐይ ፀሐይ ሰረቀ/፪/  
ፀሐይ ሰረቀ ክርስቶስ ተጠምቀ /፪/


አንቺ ዮርዳኖስ ምንኛ ታደልሽ /፪/ 
የእግዚአብሔር መንፈስ ከላይ ወርዶልሽ 
የዓለም መድሐኒት ተጠመቀብሽ/፪/

ድንግል ማርያም ያስገኘሽው ፍሬ
ህዝቦቹን ለማዳን ተጠመቀ ዛሬ /፪/


ድንግል ማርያም ንፅህት ቅድስት /፪/ 
የጌታችን እናት ምስጋና ይገባሻል 
ከሴቶች ሁሉ አንቺ ተመርጠሻል/፪/
 
እልል እልል ደስ ይበለን/፪/ 
ወልድ ተወልዶ ነፃ አወጣን 
ዮሐንስ ሲያጠምቀው ድል አገኘን


አማን አማን አማን በአማን/፬/ 
በዓለም ተሰበከ የጌታችን ቃል 
በዓለም ተሰበከ የወንጌሉ ቃል

አዲሱ ሙሽራ ሲመጣ ያያችሁ/፪/ 
የዮርዳኖስ ሰዎች ስለምን ሸሻችሁ/፪/


አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ /፪/ 
በገሊላ መንደር ለሰርግ ተተጠራ/፪/

ሰርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ/፪/ 
የወይን ጠጅ ሆነ ውኃው ተለወጠ/፪/


እናንተ ተራሮች እግር ሳይኖራችሁ/፪/ 
እንዴት እንደጊደር ሽቅብ ዘለላችሁ/፪/ 

እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ስራ 
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሰራ/፪/ 


ጌታችን አንድ ቀን ያደረገው ተአምር 
ሲያስደንቅ ይኖራል ይህን ሁሉፍጡር/፪/

የግመል ደበሎ ለብሶ   ለብሶ ስላያቹ
መጥምቁ ዮሀንስ አውሬ መሰላችሁ /፪/


@Yemezmurgtm
@Yemezmurgtm

Показано 20 последних публикаций.