ይህንን ፀሎት ከአንድ መፀሀፍ ላይ አገኘውት ( የመፀሀፉ ርዕስ አሁን ትዝ አይለኝም)
በጊዜው በጣም አስደንቆኝ ማስታወሻዬ ላይ ፅፌው ነበር፡፡ ምንአልባት አንድ ሰው ከጠቀመ ብዬ ላጋራችሁ አሰብኩ፡፡
ፀሎት
🧎ኦ ልበ ትሁትና የዋህ የሆንህ ኢየሱስ ሆይ ስማኝ አጥብቄ መወደድን ከመፈለግ አድነኝ፡፡
ከፍ ከፍ ማለትን ወይም መወደስን ከመፈለግና አድነኝ፡፡
ክብርን ከመፈለግ ምስጋናን ከመፈለግ አድነኝ ከሌሎች ይልቅ ቅድሚያ እንዳልፈልግ ጠብቀኝ ከሌሎች ይልቅ አዋቂ ሆኖ መገኘትን ከመሻት አድነኝ
የሰዎችን ይሁንታና አዎንታን ከመፈለግ አድነኝ፡፡
🧎ኦ ኢየሱስ ሆይ ዝቅ ዝቅ ማለትን ከመፍራት
መናቅና መጠላትን ከመፍራት
ተግሳፅን ለመቀበል ከመፍራት
እንዳይበድሉኝ ከመፍራት
ሰዎቸ እንዳይጠረጥሩኝ ከመፍራት ታደገኝ
ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሌሎች ከእኔ ይልቅ እንዲወደዱ
ሌሎች ከእኔ ይልቅ ከብረው እንዲታዩ የመፈለግ ፀጋን ስጠኝ
በዓለም ዓይን ሌሎች ከእኔ ይልቅ ልቀው ይታዩ እኔ ግን አንሼ ልገኝ
ሌሎች ሲመሰገኑ ኔ ግን አንሼ ልገኝ
አስታዋሽ ማጣትን እንድቀበል አስችለኝ
መሆን የሚገባኝን ያህል በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኜ ከተገኘው ከእኔ ይልቅ ሌሎች ቅዱሳን እንዲባሉ መፈለግን ስጠኝ አሜን🙏
Lemamaker agelglot
@chere85@chere85 ytekemu behulum zuriya enamakralen