ብስራት ስፖርት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский


https://telega.io/c/BisratSportTm
Buy Ads 👆
የእግርኳስ መረጃዎችን ለመከታተል ወደ ትክክለኛው ቦታ መጥተዋል!
ትኩስ ትኩስ መረጃዎችን ፣ የዝውውር ዘገባዎች እንዲሁም የቀጥታ ስርጭት ከየስታዲየሞቹ እኛ ጋር በላቀ ጥራት እና ብቃት ያገኛሉ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


የቅዳሜ ጨዋታዎች ፕሮግራም

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 || በፕሪሚየር ሊግ

ብሬንትፎርድ ከ ብራይተን || 11:00

ክሪስታል ፓላስ ከ በርንማውዝ || 11:00

ኤቨርተን ከ ማንቸስተር ሲቲ || 11:00

ዌስትሃም ከ ሳውዝሃምፕተን || 11:00

አስቶንቪላ ከ ኒውካስል || 1:30

🇪🇸 || በስፔን ላሊጋ

ባርሴሎና ከ ሴልታ ቪጎ || 11:15

ላስፓልማስ ከ አትሌቲኮ ማድረግ || 4:00

@BisratsportTm


አሞሪም ስለ እሁዱ የወልቭስ ግጥሚያ !

"ልክ እንደ ማትየስ ኩኛ እና ሌሎች እወነተኛ ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች አሏቸው! ጨዋታው በጣም ከባድ ይሆናል"

@BisratsportTm


ስፖርቲንግ ሊዝበን አርብ ምሸት 3ለ1 ባሸነፉበት ጨዋታ ቪክቶር ዮኬሬሽ ሀትሪክ ሰርቷል!

ዮኬሬሽ በዘንድሮው የውድድር አመት በ46 ጨዋታ 47 ግቦችን ማስቆጠር ሲችል በአጠቃላይ 57 ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

@BisratsportTm


ፍሎሪያን ቨርትዝ የማንቸስተር ሲቲ ህልም ቢሆንም ጀርመናዊው የወደፊት ዕጣ ፈንታውን እስካሁን ድረስ አልወሰነም እናም በባየር ሙኒክ እና ሪያል ማድሪድ ይፈለጋል።

- ጃክ ጎውሀን

@BisratsportTm


🗣 አርቴታ ስለ ካላፊዮሪ

"ሁሉም ነገሮች በጥሩ መንገድ ከሄዱ ለፒኤስጂው ጨዋታ ይመለሳል ብዬ አስባለሁ ምናልባትም ከፒኤስጂው ጨዋታ በፊት ሊመለስ ይችላል"

"ካሁኑ ሜዳ ላይ ነው! የተለያዩ ልምምዶችን እየሰራ ነው! ሲመለስ በትክክለኛ መንገድ እና ያለምንም ችግር መመለስ መቻሉን እርግጠኛ መሆን መቻል አለብን"

@BisratsportTm


ሀቨርትዝ ለፒኤስጂው ጨዋታ ይመለሳል?

🗣 አርቴታ

"ከተጠበቀው ቀን በፊት ሊመለስ ይችል እንደሆነ ታሲዛለህ ብትለኝ አዎ አሲዛለው እልሃለው"

"በየቀኑ በሚሰራበት መንገድ እና እራሱን እንደሚገፋበት መንገድ ከሆነ ብዙ ይቆያል ብለህ አትጠብቅም"

@BisratsportTm


🗣 ኤንዞ ማሬስካ

"አሁንም ድረስ ከባለቤቶቹ እና ከስፖርቲንግ ዳይሬክተሮቹ የማይናወጥ ድጋፍ እንዳለኝ ይሰማኛል"

@BisratsportTm


ዲን ሂውሰን ላይ ፍላጎት ካላቸው ክለቦች ውስጥ አንዱ ማንቸስተር ዩናይትድ እንደሆነ የRelevo ዘገባ ያመላክታል።

@BisratsportTm


📊 || ካስሜሮ በትናንቱ የሊዮን ጨዋታ

-120 ደቂቃ ተጫወተ

- 4 የግብ ዕድል ፈጥሯል

- 1 ትልቅ የግብ ዕድል ፈጥሯል

- 2 አሲስት ማድረግ ችሏል

- 1 ፔናልቲ ለዩናይትድ አስገኝቷል

- ሜዳ ከነበረ ከየትኛውም ተጫዋች በበለጠ 9 የአንድ ለ አንድ ፍልሚያዎችን አሸንፏል

በ9.4 ሬቲንግ የጨዋታው ኮከብ! ⭐️

@BisratsportTm


አርሰናል በዚህ አመት እስካሁን ድረስ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የ117 ሚልዮን ዩሮ ለፋይናንስ የሚውል ሽልማትን ማግኘት ችሏል።

@BisratsportTm


የተረጋገጠ❗️

ማን ዩናይትድ ወይም ቶተንሃም የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮን የሚሆኑ ከሆነ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ 6 ክለቦች እንግሊዝን ወክለው ይሳተፋሉ።

@BisratsportTm


አሞሪም ከጨዋታው በኋላ !

"አሁን ትኩረታችንን የበለጠ የአውሮፓ ሊጉ ላይ ማድረግ አለብን! ወጣት ወጣት ተጫዋቾቻችንን በፕሪሚየር ሊግ ማሰለፍ አለብን"

@BisratsportTm


የአውሮፓ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ታውቋል !

ቶተንሀም Vs ቦዶ ግሊምት

ማንቸስተር ዩናይትድ Vs አትሌቲክ ቢልባኦ

@BisratsportTm


ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኦሎምፒክ ሊዮን ደጋፊዎች ለምሽቱ ጨዋታ ማንቸስተር ከተማ ገብተዋል !

@BisratsportTm


ላውታሮ ማርቲኔዝ በአምስት ተከታታይ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ጎል ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው የኢንተር ሚላን ተጫዋች መሆን ችሏል።

@BisratsportTm


🗣 ልዊስ ስኬሊ

"ከሪያል ማድሪድ ጋር መጫወት ማለት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር እንደመጫወት ነው! በማድሪዱ ጨዋታ ምንም አይነት ጫና አልተሰማኝም"

@BisratsportTm


ትናንት ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት አንድ የማድሪድ ደጋፊ የተናገረው !

"ከኮሎምቢያ እዚህ ድረስ መጥቻለሁ ምክንያቱም ማድሪድ ውጤቱን እንደሚገለብጠው አምናለሁ። በረራው 10 ሰዓታት ፈጅቶብኛል 1.300 ዩሮም ለትኬት አውጥቻለሁ ብሎ ነበር (በኛ ከ 200 ሺህ ብር በላይ)

The Rest Is History 🙂

@BisratsportTm


ከ19 አመት በኋላ ሳካ የሄነሪን ታሪክ በበርናባው ደግሞታል !

🤫

@BisratSportTM


ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ዴክለን ራይስ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተሸልሟል !

@BisratsportTm


አርሰናል ማድሪድን ደመሰሰው !

በሁለተኛ ዙር በሳንቲያጎ በርናባው በተደረገው የቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ አርሰናል 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

የአርሰናልን ጎሎች ሳካ እና ማርቲኔሊ ሲያስቆጥሩ የሪያል ማድሪድን ብቸኛ ጎል ቪኒሽየስ ማስቆጠር ችሏል።

አርሰናል በድምር ውጤት ሪያል ማድሪድን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

አርሰናል በቀጣይ በግማሽ ፍፃሜው ከፒኤስጂ ጋር ተገናኝቷል!

@BisratsportTm

Показано 20 последних публикаций.