💛💞መልካም ልቦች™💞💛


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


🥀♡ ማፍቀር ስትጀምር ከእምነት ጀምር ♡🥀
⚡️WELLCOM TO MELKAM LBOCH 💜
💚 በዚህ ቻናል ውስጥ ደስ የሚሉ የ ፍቅር ቃላቶች፣ግጥሞች፣የፍቅር ታሪኮች ያገኛሉ !
● ቻናላችንን SHARE ያድርጉ 🙏
➤ For any promotion and Advertising 📩
👉 @Z_afro ያነጋግሩ::

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


✅አትሂጂብኝ ❤️❤️❤️


❤️በአጭር ክፍል የሚጠናቀቅ ግሩም የፍቅር ትረካ  🌺

ሁላችሁም አንብቡት
❤️

ሙሉውን ለማንበብ ከፈለጉ
👇👇👇

✈️https://t.me/Enmare1988/5453
✈️https://t.me/Enmare1988/5453
✈️https://t.me/Enmare1988/5453


የፍቅር ጥግ


             ክፍል 1


እነሆ የመጀመሪያ ክፍል 👇👇👇

በጠዋቱ ከእንቅልፌ ተነስቼ  እየተጣደፍኩ  መለባበስ ጀመርኩ እማዬ ከስር ከስሬ እየተከተለች ታጎርሰኛለች እኔ አንዱን እቃ ሳነሳ አንዱን  ስጥል እንደልማዴ እየተርበተበትኩ እማዬ ያጎረሰችኝ አጣጥሜ በልቼ ወጣሁ።

ገና ትንሽ ከመራመዴ ከኋላ ከኋላዬ እማዬ እየጠራች ትከተለኛለች ድምጿን ስሰማው ወደኋላ ዞርኩኝና ደንግጬ ወደሷ ተመለስኩ
ልጄ ምን ሆነህ ነው ምሳህን እረስተህ ምትወጣው በል እንካ ብላ ትንሿን ቦርሳዬን አቀበለችኝ።
እኔም አመስግኛት መልሼ ወደቤት አስገብቻት ስሚያት ወደስራ ቦታዬ ሄድኩ።

ትናት ጀምሬ የተውኩትን መኪና ወደመጠጋገኑ ገባሁ  ።
ወዲያው አለቃዬ ከውስጥ ወጣና አንተ ወመኔ በቃ ይሄ ማርፈድህን እንቢ አልክ አደል አለኝና ተሳስቀን አብረን መስራት ጀመርን።

ወዲያው እማዬ ደወለችና እንደለመደችው አለቃህ ምን አለህ እረፈደብህ ስንት ሰአት ደረስክ ብላ ጠየቀችኝ ሁሉንም ነገርኳትና ከአልጋ እንዳትወርድ ምግቧን ብቻ በልታ እንድትተኛ ቃል አስገብቻት ስልኩ ተቋረጠ።

ምሳ ሰአት ላይ ሁሉም ምግብ አዞ ሲበላ እኔ የራሴን ምሳ በላሁ።
ትኩስ ነገር ለመጠጣት ወጣንና ጠጥተን እየተመለስን ገራጁ በርጋ አንዲት ልጅ መጥታ ገጨችኝና እራሷ መሬት ላይ ወደቀች ትኩር ብዬ አየኋትና ያምሻል እንዴ የተገጨሁት እኔ የወደቅሽው አንቺ ምን ሆነሻል ብዬ እዛው በወደቀችበት አልፊያት ወደገራጁ ገባሁ።

ይኸው ከዛን ቀን አንስቶ ለድፍን አንድ ወር ያህል ያለምንም ማቋረጥ ጠዋት ስራ ከመግባቴ በፊት ከስራ ቦታዬ አጠገብ ቆማ ጠብቃ አይታኝ በፍጥነት ከዛ አካባቢ ትሰወራለች።

አንዳንዴ ማናስታውላቸው ግን ውስጣችን ተላምደው ሚቆዩ ነገሮች አሉ አደል ብቻ ሳላስበው ሁሌ ጠዋት ጠዋት እሷን ማዬቴን ተላምጄው ነበር።
ልክ ድፍን አንድ ወር ሲሞላት የመጀመሪያ የተገናኘን ቀን እንደተጋጨነው ምሳ ሰአት ላይ መጣችና አውቃ ገጭታኝ እራሷ ወደቀች ሳያት አላስቻለኝም አይቻት ፈገግ አልኩ ...ከኔ በላይ ከት ብላ ሳቀችና ወይኔ ጉዴ አንተ ስቀህ ታቃለህ እንዴ ልክ በወሩ ታምር አየሁ ማለት ነው ፈገግ ስትል ነው ያየሁህ አደል አለችኝ።

አንቺ ጤነኛ አትመስይኝም እብድ ብያት አሁንም ትቻት ገባሁ።

ወደውስጥ ገብቼ ዞር ብዬ ሳያት ብቻዋን እየሳቀች እንደ እብድ እየሮጠች ሄደች።

ምኗን ነው የጣለብኝ እንዴ ምን ሆና ነው ብዬ ከጓደኞዬጋ ተሳስቄ ወደስራ ገባሁ።
እማዬ ህመሟ ትንሽ እየባሰባት ስለነበር በየደቂቃው ነው ስልክ ምደውልላት

በነጋታው ደገመችና ጠዋት በር ላይ ጠበቀችኝ ስተየኝ ብቻዋን ሳቀችና ተመልሳ ሄደች።
ያ ነገር ያለማቋረጥ ድጋሜ ለ15 ቀን ቀጠለ።


የሆነ ቀን ጠዋት ላይ እማዬ በጣም ስላመማት ከስራ ቀረሁ።
ጓደኞዬ ደጋግመው እየደወሉ ሲጨቀጭቁኝ ስልኬን አጠፋሁት።
ለእናት ቡና አፈላልቼ ምግብ ሰርቼላት አበላኋትና አለባብሻት ወደሀኪም ቤት ይዣት ሄድኩ እንደተለመደው ምንም በሽታ የለባትም።
እረፍት ታድርግ እራሷን እንዳታስጨነቅ ብለው መለሱን።
ሁኔታው ሰላም ስለነሳኝ ቁጭ አድርጌ አወራኋት ምንሽን ነው ሚያምሽ ምንሽጋ ነው የሚሰማሽ ብዬ ጠየኳት እናቴ ነገሩን ቀለል አድርጋው አረ ልጄ እኔ በሽታዬ ይሄ ነው አልልህም በቃ እዚህጋ ነው ስል ሌላጋ ያመኛል ልቤን ስል ኩላሊቴን ኩላሊቴን ስል ጨጓራዬን ጨጓራ ስል እራሴን በቃ ግራ ነው ሚገባኝኮ አለችኝ።

በቃ ዛሬ ቤት ውለን እረፍታችንን እናጣጥም ብያት ስልካችንን ዘጋግተን ከእናቴጋ ፈታ ስንል ዋልን ማታ ላይ ተያይዘን ቤተክርስቲያን ሄድን ስንመለስ እማዬ በዛው ጎረቤት ገብታ ወሬ ስትጀምር እኔ ትቻት ወደቤት ገባሁና ስልኬን ከፈትኩት ብዙ ያልተሳካ ጥሪ ገባልኝ ከፍቼው ደቂቃ ሳልቆይ ማላቀው ቁጥር ተደወለልኝ አነሳሁት።
ሄሎ!
ሄሎ አንተ በሰላም ነው ዛሬ ከስራ የቀረኸው አለችኝ።
ማን ልበል አልኳት።

ውይ እራሴን ሳላስተዋውቅ ፋኖስ ነኝ አለችኝ።
እሺ እኔ ደሞ ጨለማ ነኝ እንዴ... ፋኖስ ማነሽ አቅሻለሁ አልኳት
አዎ ታቀኛለህ ጠዋት ጠዋት አንተን ጥበቃ ብርድ እየጠጣሁ እየጠበኩህ እንዴት አታቀኝም ዛሬኮ ጠዋት ስትቀር ጓደኞችህን አልቅሼ ለምኜ ነው ስልክህን የሰጡኝ አለችኝ።
ማን እንደሆነች ሳውቅ እሺ ፋኖስ አሁን አወኩሽ ምን ፈልገሽ እንደደወልሽ ንገሪኝ ሰአት የለኝም አልኳት።

እእ ያው ዛሬ በሰላም ነወይ የቀረኸው ልልህና ድምፅህን ልሰማው ነው አለችኝ።

ስትሟዘዝ ነገረ ስራዋ አስጠላኝ
እንደውም ከቻልሽ ካሁን ቡሀላ ጠዋት ጠዋት እንዳላይሽ እያጨናነቅሽኝ ነው እኔ ሰላሜን ሚነሳኝ ሰው አልወድም አትከታተይኝ ስልኬ ላይም ደግመሽ እንዳትደውይ ብዬ ዘጋሁባት
ስልኳንም ብሎክ አደረኩት።


በነጋታው እንደለመደችው ከበሩ ፊት ለፊት ቆማለች እንደሌላ ጊዜው ፈገግ አላለችም አኩርፋ ነበር ባላየ አልፊያት ገባሁ።
የእማዬም ህመም ግራ እያጋባኝ ስራውም ትንሽ ቀዝቅዞ ስለነበር አንዳንድ ቀን ስራ እየገባሁ አንዳንድ ቀን ደሞ እየቀረሁ ሶስት ወራቶች ቆየን።

ሶስት ወር ሙሉ ፋኖስ አንድም ቀን ከመምጣት ተቆጥባ አታቅም ታየኝና እየሮጠች ትሄዳለች።
የቀረሁ ቀን በማይታወቅ ስልክ ትደዎልና ድምፅህን ልስማው ብዬኮ ነው በቃ ቻው ብላ ስልኩን ትዘጋዋለች እኔም የደወለችበትን ስልክ ብሎክ ማድረግ ሳይደክመኝ እሷም ስልክ እየቀያየረች መደወል ሳይደክማት ነው የቆየነው።

ጠዋት እንደተለመደው የስራ ቦታዬ በር ላይ ስደርስ ከሩቅ አንዴ አንዴ ጠብቀኝ እያለች እየሮጠች መጣች ።
ተኮሳትሬ ቆሜ ጠበቋት
ጥቁር ፌስታል አንጠልጥላለች እንካ ስጦታ ገዝቼልህ ነው እያለፍኩ ሳየው በጣም ስለወደድኩት ላንተ ገዛሁልህ እንካ አለችኝ።
አልፈልግም ሲጀመር አንድ ነገር ልንገርሽ ሴት ልጅ እራሷን ስታከብር ነው ደስ የሚለው በዚህ ልክ እራስሽን አታውርጅ እኔ ደሞ እንዳንቺ አይነት ሰው ምርጫዬ አደለም አትከታተይኝ ድጋሜ እዚህ ቦታ ቆመሽ እያየሽኝ ካገኘሁሽ አስቀይምሻለሁ ስጦታውን ደሞ ሂጅና ለሚፈልግ ሰው ስጭው ብያት ገፍትሬ ጥያት ገባሁ።
ንግግሬ ልኮ እንዳልሆነ ውስጤ ቢነግረኝም ግን ስላደረኩት አልፀፀተኝም ነበር።

ይቀጥላል....


✎ክፍል 2 ነገ ማታ 2:30 ይቀጥላል♥️    ቶሎ እንዲ🀄️ጥል LIKE♥️ እና Share አድርጉ።


  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

3.6k 0 29 12 233

"Arguing with a fool proves there are two."


ከሞኝ ጋር መጨቃጨቅ ሁለት መሆናችንን ያረጋግጣል
🔻


ውድ የመልካም ልቦች ቤተሰቦች ፈጣሪ ካለ ከነገ ማታ 2:30 ጀምሮ አዲስ ታሪክ እጀምርላቹሃለው ዝግጁ ናችሃ ?

5.5k 0 0 22 189

እኔን ነው የምቶደኝ እሱን አገባች እንጂ !

ጠይም ፍልቅልቆ ኤዱ ተሰፍሮ ከተሰጠን ብዙ ሽራፊ ጊዛያትን አብረን ሸርፈናል ብዙ ትዝታዎችን ተጋርተናል  ። ጥቁር ብዙ  ፀጉሯን በእጅ ጣቶቼ  እያርመሰመስኩ ፍቅሬን ገልጬላታለሁ

ተቀንድባ ያልቀነሰቻቸውን ብዙ  የቅንድቦቾን ፀጉር  በሌባ ጣቴ  እየዘበራረኩ አበሳጭቻታለሁ ። 

እወዳታለሁ፤ ትወደኛለች ፤ እንዋደዳለን ።

አብረን ስንሆን ሳቅ ይኖራል።  ነፃነት ይረበርባል ። ካለ አጀንዳ የመጣልን  ወሬ ላይ እንረባረባለን ።

እየተጨቃጨቅን ጭቅጭቃችን መሃል ላይ ሳቃችን ታግሎን እንደሚያውቅ ጭቅጭቁ በርዶ በሌላ ቀን  ሁለታችንም እየሳቅን ያሳቀንን አገላለፅ እየመዘዝን ስቀንበታል  ። 

በየቀኑ እየተገናኘን መሰልቸት የሚባል  Concept ውል ብሎን አያውቅም።

አንዳንድ   እንቅስቃስዬ በጥሞና ግዜ እንደሚጎረብጣት ትነግረኛለች።  ልቦናዬ ታውሮ ስለነበር  እሷን እንሚያሳጣኝ አልተገለፀልኝም ነበር።

ፍቅሯ በነፍሷ ስርቻ ውስጥ አለ ።  ዳስሸዋለሁ የማይዳሰስ ፍቅር ምላስ ላይ ብቻ  ያለ እንቶፈንቶ ነው ።

ለንቦጯን ጥላ ፤አኩርፋ ፤ተማራ እያጉመተመተች ስታገኘኝ ። የቆጥ የባጡን ለማሳቅ ዘብዝቤ ሳትስቅ የቀረችባቸው እለቶች አልነበሩም ።

እሱን አገባችው እንጂ እኔን ነው የምትወደው !

ስንት ቀን በግሬ ስኳትን ከባሏ ጋ በመኪና ቃል ሳይሰናዘሩ  ሲሄዱ አያቻቸዋለሁ።

ዘመናዊ ሆቴል ሲገቡ ጥግ አረቄ ቤት ተቀምጬ አይቻቸዋለሁ እጆን አልያዛትም ወይ ደሞ እሷ እጆን ጉያ ውስጥ አልወሸቀችም   ።

የኔ ኤዱ ከሁለት አንዱ አለማድረግ አይቻላትም ነበር ። እኛ መንገድ ላይ እንኳን ስናሽካካ እና ስንላፋ አፍረት አያግደንም

ከሱ ጋ ያጋመዳት ኑሮ ነው  ፍቅሯ እኔ ጋ ነው ያለው  ።

የፍቅር ታሪክ ብቻውን ለኑሮ አይሆንም ብላ ነው የወሰነችው ። ማሰላሰል የሌለው
ውስጣዊው ስሜት ብቻውን ረብ የለውም ብላ ነው አሰላስላ የተወቺኝ ።

አውጥታ አውርድ ስሜቷን አፍና ነው እሱን ያገባችው። ፍቅር ያረጃል ብሰለት ያሻግራል ብላ እንጂ  ቀልቧ እኔ ጋ ነው።  በግዜ ብዛት ልጅ ሲመጣ የኑሮ ቀንበር ሲጫናት  ከልቧ እወጣለሁ ። ከጓደኞቾ ጋ እንደዘበት ታነሳኛለች ።

ትክ ብላ ስታየኝ መወሰን እየታጋላታ እንደነበር ስታገባ ነው የገባኝ።  እንደቀልድ ስጋቷን ሹክ ስትለኝ ዋስትናዬን በተግባር አስደግፌ ማስዳስስ አልቻልኩም።

ኤዱ ዝም ብላ እንኳን ፊቷን አንብቤ ትገባኛለች። የንዴት መፍለቅያ ጠርዞቼን ታቃቸዋለች ። 

የኤዱን ገላ ከራሴም ገላ በላይ   እሷ የማታቃቸውን ገላዋ ላይ ያረፈ ጥቁር ጥንጥ ነጥብ ብዛት ሳይቀር አውቀዋለሁ።  ከኔ ጋ ነበር ማርጀት የነበረባት፤ ምን ያደርጋል  እኔን እየወደደችኝ እሱን  አገባችው እንጂ !

ይሄ ሁሉ አንብባችሁ ማ 👍👍 ተጫኑ

🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13

6.4k 0 27 2 267

ፍቅር ማለት❤️


ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም፡፡ወደም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍ አይዷለም፡፡በየጎዳናው ተቃቅፎ መታየትም ፍቅር ሊሆን አይችልም፡፡ፍቅር ማለት ማንም ሊያስዷስተን በማይችልበት መንገድ ላይ ደስታን የሚፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው፡፡

🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

6.3k 0 51 1 118

:–መንገድ ይወስዳል መንገድ ይመልሳል
የምኖዳቸውን ሰዎች የወሰደው መንገድ ግን _ ●  መመለሻ የለውም መሰለኝ




መመለሻው መንገድ ጠፍቷቸው ነው?

በህይወታችን ማለት እስከ አሁን በኖርንባቸው እድሜ ስናስበው ብዙ የምኖዳቸው ሰዎች እኮ በዙርያችን አልፈዋል

አይደል? እስኪ ስንት የምኖደውን ሰው እስከ ዛሬ አጣን? በዙርያችን በጭራሽ እማይጠፉ እኛን አጉል ልማድ አስለምደውን ከዙርያችን የጠፉ ስንት ሰዎች አሉ?

እኔ በበኩሌ ብዙ የምወዳቸው እና እነሱ ስላሉ ብቻ ህይወቴ በደስታ የተሞላበት ጊዜያቶች እንዳሉ አስታውሳለው።እና ከነሱ ሰዎች ጋር የማሳልፋቸው ጊዜያቶች መቼም ቢሆን አይቀየሩም ሁሌም እንደዚ እንቀጥላለን ብዬ ነበር የማምነው።ግን እነዛ ሰዎች አሁን ከጎኔ የሉም።ለምን ግን አላውቅም

እነዛ ሰዎች የሚለዩን እኮ በሞት ላይሆን ይችላል ምናልባት የህይወት መንገዳችን ተለያይቶም ይሆናል ምናልባት እነሱም ፍላጎት ሳይኖራቸው ቀርቶም ይሆናል እኮ ግን በድንገት ተስፋ የጣልንባቸው የምኖዳቸው ሰዎች ርኛ ሳናስበው ይሄዳሉ።መሄድ ይሂዱ ታድያ ለምን አየመለሱም?

እኔ ሁሌ መንገድ ይወስዳል መንገድ ይመልሳል የሚባል አባባል እሰማለው እነሱን የወሰደው መንገድ ከሄዱ ቧላ በመሀል በ ድልድይ ተዘግቶ ነው ወይስ እነዛ ሰዎች መንገዱ ጠፍቷቸው?®

ይሄን ካልን በስተመጨረሻ ግን ሰው ይሄዳል ሰው ይመጣል ግን እድሜያቹን የማይመጣ ሰው እየጠበቃቹ አጠገባቹ ያለውን ሰው አትዘንጉ

አንዳንዴ ለሄደ ሰው ብቻ ሳይሆን በዙርያችን ላለ ሰውም ጊዜ መስጠት ያስፈልጋል ይሄ ማለት ግን እነሱም ቢሆኑ ሰው ይሄዳል ሰው ይመጣል ናቸው እና ደስታቹንም ሆነ ሀዘናቹን ሰዎች ላይ አታድርጉ
አሁን ላይ በጣም የምቶዱት ሰው ይሄዳል።የናንተ የመውደዳቹና የመቀራረባቹም ብዛት አይወስነውም። ሁሌ አብሯቹ አይሆንም የሰዎች መሄድ ተፈጥሯዊ ነገር ነው ምክንያቱም ስነ ፈጥረቱንም ስናየው የሰው ልጅ እዚህ ምድር የመጣው ተመልሶ ሊሄድ ነው። እንደዚ ብላቹ ካመናቹ ለመጣው እና ለሄደው ሰው ሁሉ ልባቹ አይሰበርም ለማንኛውም ቸር ይግጠማችሁ

🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

9.5k 0 32 12 154

🔦ምክር_ቢጤ🔦


እውነታ ነገር ቢኖር ድሀ አግብታ በርሀብ የሞተች ሴት የለችም!!.....
🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
>>>

ሀብታም አግብታ ግን እንደፈለገ ከፍ ዝቅ ሲያደርጋት በብር የገዛት እስከሚመስለው የሚያመናጭቃት ለበሺታ የተዳረጉ ለሞት ስበብ ያደረጓቸው ሀብታሞች አሉ....

soምርጫውን አስተንትነው ለሚመርጡ ይሁን!? ድሀ ማለት የጭንቅላት የድን እንጅ የገንዘብ ምንም አይደለም…....!! ተሰርቶ የሚገኝ ነው ገንዘብ በአእምሮ ታስቦ በሰውነት ተሰርቶ የሚገኝ ነው!! በሀብት፣ በመልክ፣ በጤንነት፣ አትተማመኑ እነዚህ በድንገት ከእኛ የሚጠፋ ናቸው ።

🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔

9k 0 32 13 140

🔹10 ቀን ነው የቀረው አሁኑኑ ጀምሩት በሁአላ ታተርፉበታላችሁ 🔸


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል
| አጨዋወቱን በቪዲዮ በቅርብ ግዜ ዉስጥ እንለቅላችኋለን

ለመጀመር
http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref756016762


❤️አ😍ፈ😍ቅ😍ር😍ሻ😍ለ😍 ሁ❤️

አ🥰= አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈ🥰= ፈልጌው አደለም አላበዛም ሰበብ
ቅ🥰= ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ር🥰= ርሀብን ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻ🥰= ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለ🥰= ለማንም አልፈቅድም እንዲለዩሽ ከ
#እኔ👈
ሁ🥰  = ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እስከማይሽ በ
#አይኔ😢

13.5k 0 185 22 326

በሚወድህ ሰው ላይ ክፉ አትስራ
ለሚፈልግህ ሰው ቢዚ ነኝ አትበል

የሚያምንህን ሰው አታታል

ሁሌም የሚያስታውስህን ሰው አትርሳ!!
ቦታ ለሚሰጥህ ሰዉ ጊዜህን አትንፈገዉ!!👍👍👍

19.1k 0 119 2 347

⭐⭐ውድቀት የደበቀው ውበት

ሴተኛ አዳሪ ነች። ለብዙ ሰው የሽፍደት ማስታገሻ ናት። እሷን ከወሲብ ጋር ብቻ አጋምደው ነው የሚያስቧት ፤ የሚያዋሯት ፣ የሚደውሉላት የሚያገኟት።

በየቀደዳዎች ሽፍደት ፣አንሶላ ፣ቂጥ ፣ዳሌ ፣ስካር ዳንስ ዋነኛው አጀንዳቸው ያደርጉታል።

እኔ ራሴ...
ውበቷ ፤ቂጧ ፣ዳሌዋ ፣ ቅላቷ፣ ነፃነቷ ማርኮኝ ነበር የተዋወኳት ፣ለወሲብ ነበር የቀረብኳት እንዳገኘኋት ነበር ማንነቷ የጣፈጠኝ ፣ብዙ ሰው ጋር ያለየሁት ወፍራም መውደድ ፣አዛኝነት፣ሃቀኝነት ያየሁባት
እሷ ራሷ.....

አንዲት ጠዋት ቅዳሜ እለት እንዲ አለቺኝለምን ሴተኛ አዳሪነቴን ታስረሳኛለህ ፣ ለምን ካንተ ጋር ስገናኝ ሸርሙጣነቴን ታፈዘዋለህ ፣ለምን ታገዝፈኛለህ አለቺኝ

ምን ላድርግ ብለሽ ነው ተቃጥረን ስትመጪ የሚታየኝ ጨዋታሽ ፣ፍቅርሽ ፣የስብዕናሽ መዓዛ ነው ። እንደደረሽ
ደስስስ ይለኛል ያሻኝን ካለ ቀመር  እዘብካለሁ፤ እቀደዳለሁ። በቀደዳዬ ስትስቂልኝ ደስ ይለኛል ፤ በቀልዴ የመጬ እከየፍ እና ከልቤ እፈግጋለሁ ።

✔️ከዚ ደማቅ ሰው ወዳድነትሽ አልፌ ከዚ ጣፋጭ የወዳጅነትሽ ሳቅ ነጥቤ ከዚ ወዳጅነት ላይ የከተመች ልጅ ተሻግሬ
ከዚ የናፍቆት መጠማጠም ተሸጋግሬ በክፉ ገጠመኝ ተጠላልፈሽ ፣ በክፉ ሰዎች ተጎትጎተሽ የወደቅሽበት ግዚያዊ አንቺነትሽ እንዴት ይታየኝ አልኳት ቃል ሳትናገር
አቅፋኝ አንገት ውስጥ ተሸጉጣ አለቀሰች ።

ሳግ ብቻ ነው የተሰማኝ
የሳጓ ትርጉም ነጋሪ ቢኖር እንዲህ የሚል ይመስለኛል
ወለድከኝ ፤ቆንጆ ሴት፣ የተከበረች ፤ ለፍቅር እንደምመጥን አስዳሰስከኝ ከሚል አይዘልም አንገቴን የሚያርሰው እምባ ውስጥ ህይወት ፍቅር ተስፋ ሲረማመድ ይሰማኛል።

ወድጃታለሁ ሴተኛ አዳሪነቷ ለኔ አይሰማኝም
ታከብረኛለች፤ ሰው ትወዳለች፤ ጨዋታዬ ስጋቴ ህመሜ ሳቄ ይሰማታል።

እኔ ስቀጥራት ከፕሮፌሰሩ ፣ከባላሃብቱ ፤ ከባለስልጣኑ በላይ ሰፍፍፍ ትልልኛለች ፤ የምላትን ትሰማኛለች
ከማንም ጋር ስሆን ከሚሰማኝ ደስታ በላይ ከእሷ ጋር ስሆን እደሰታለሁ ።

እማወራው አያልቅብኝም እ ... እወዳታለሁ እንደወደድኳት ፤ ብዙ ወር መጥቶ ሄደ ፤ ፍቅራችን፣ አንዳችን ላንዳችን ያለን ነገር አልቀነሰም። የምግብ ዝግጅት ተምራ ጨረሰች ።ዘርፍ ቀየረች ። እቺን የመሰለች ልጅ እንዴት ብዬ በትላንቷ ምክንያት ልተዋት ?! በጭራሽ አልተዋትም !!

ሁሉም ግርር ብሎ ከሚያየው የሚታይ ነገር ጀርባ ብዙ ያልተስተዋለ ያፈጠጠ እውነት አለ

              
ይሄ ሁሉ አንብባችሁ ማ 👍👍 ተጫኑ

🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔


ብንቆይ ይሻላል

   ከመኖር አለመኖር ይሻላል እሚሉህን እንዳትሰማቸው። አለመኖር ተሽሎ አያውቅም…ሁሌም ፈጣሪን እንዲያቆይህ ለምነው…ለንሰሐ ሞት እንዲያበቃህ ፤ ቤተሰቦችህን ለመጦር እስኪያበቃህ ፤ አግብተህ ልጆች ወልደህ እስክትስም ድረስ እንዲያቆይህ ፀልይ።

   መረጋጋትን ከፈለግክ ደሞ ወደ ፈጣሪህ ቅረብ…የውስጥ ሰላምን ከፈለግክ ወደ ፈጣሪ አብዝተህ ቅረብ…ሁሉም ችግር ከሱ በታች ነው…እመነኝ ሁሉም ያልፋል…ከዚ በፊት እኮ ብዙ አልፈሀል…የሚያልፉ እማይመስሉ ቀናትንም ጨምሮ።

17.2k 0 70 14 339

🔸ቤተሰቦች በአል እንዴት እያለፈ ነው?

🔻እስኪ ኮሜንት ላይ አሳውቁን🔻


🔹
ፍለጋ
🔹


🔹ደስታን ስፈልግ ነው🔸

ደስታዬ የራቀኝ

🔹ፍቅርን ስሻ ነው🔸

ፍቅር የጠፋብኝ

🔹ሰላምን ሳስስ ነው🔸

ሰላሜን ያጣሁት

🔹ፍላጎቴን ስገድል🔸

ሁሉን አገኘሁት
🥺

🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀
 
💔 @MELKAM_LBOCH13 💔
💔  @MELKAM_LBOCH13 💔


🎄እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ !🎄

በቻናላችን ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ ልደት (ገና) በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ❤️

          
🎆መልካም በዓል 🎆💖

🔤🔤🌹🌹🔤 🔤🔤🌹🔤🔤🔤🔤🔤

18k 0 20 9 72

እማ.........!

ስለ እናቴ ልፅፍ ብዬ
ብዕሬን ያዝኩኝና

ቁሜም ቁጭ ብዬም
ትንሽ አሰብኩና

እማ ብዬ ተዉኩት
መላው ጠፋኝና

አሳምሮ ኸልቋት
ሁሉንም አሟልቶ

እንደት ትጠፋለች
እናት በስኪቢርቶ

እማ እንዲህ ናት ብዬ
ችዬ አልዘረዝርም ግን
እናት እናት ናት ሁሌ አትቀየርም

                    እማዬዋ


ፅጌሬዳ


      ክፍል 41

አባቴ ጠጋ አለና መተቃቀፉን ትደርሱበታላችሁ ለጊዜው እንግዶቻችሁን ብታስተናግዱ ምን ይመስላችኋል አለን።

ተላቀቅንና እጇን ይዤ ፊት ለፊቱ ወንበር ላይ ከጎኔ ቁጭ አደረኳትና እናቴን ሄጄ አቀፍኳት።

የባሰ እንባዋን ለቀቀችው አይ የኔ ልጅ ያ ሁሉ የእንባ ዘመኔ አልፎ ዛሬ አንተን እዚህ ቦታ ቆመህ ማየቴን ሳስበውኮ ህልም እየመሰለኝ ነው አለችኘ ።
እናቴ እኔምኮ እውነት አልመስልህ ብሎኛል ግን በቃ ዛሬ ደስታችን ፈጣሪ ቸር አደል የልባችንን ክፋት ሳያይ ለዚህ ቀን አበቃኝ እሱ የተመሰገነ ይሁን ቁጭ በይ በቃ አልኳትና ወዳባቴ ሄድኩ።

ያ ግርማ ሞገስ በተሞላ ድምፁ የሚያምር የአባትነት ፈገግታን እየለገሰኝ መቼስ አባት በአደባባይ አያለቅስም ብዬ ነው  እንባዬን ዋጥጥ ያደረኩት ልጄ አኮራኸኝ ክብሬን ደግመህ ደግመህ መለስክልኝ ፍሬያችሁን ለማየት ያብቃኝ ብሎ ጥብቅ አድርጎ አቀፈኝ።
ሁሉንም በየተራ አቅፌ ደስታዬን ከተጋሩኝ ቡሀላ ቁጭ አልን ።

በቃ አሁን ደሞ ወደ መዝናናቱ እንሂድ ደስታችንን እናክብር አለ አባቴ።

አይይይ ቆይ እሱን አንድ ላይ ነው ምናከብረው ገና የኔን ስጦታ መች አያችሁትና ነው አሉ አቶ ሳሙኤል።

ሁሉም ምን እንደሆነ ለማወቅ እንደጓጓ ግልፅ ነው።

ማሂ ግራ ገብቷት ምንድነው አባቴ እኔ ከዚህ በላይ ደስታን መቋቋም አልችልም በደስታ ብዛት እሞትብሀለሁ ያንተን ለሌላ ቀን አቆይልኝ አለችው።

አይ ኑ እኔን ተከተሉኝ ብለው ወደፊት ሄዱ እጇን ይዣት ተከተልናቸው ሌሎቹም ከኛ እኩል ምን እንደሆነ ለማየት ጓጉተው ተከተሉን።
ማሂ ወዴት እንዳልሄድ ፈርታ እንደሆነ አላቅም አጥንቴ እስኪሰባበር አጠብቃ ያዘችኝ ብል እራሱ ማጋነን አይሆንብኝም

እናንተ ሰዎች ሰው በደስታ ብዛት አይሞትም ብላችሁ ነው አደል ዛሬ በኔ ይጀመርና ጉድ እንዳትሆኑ ብላ ከት ብላ ሳቀች
ወዲያው አቶ ሳሙኤል ፊታቸውን ወደኛ አዞሩና  አሁን አይንሽን ጨፍኚ አሏት።

ጨፈነች የመኪና ቁልፍ ከኪሳቸው አወጡ ዙሪያዋን የተሞሸረች እንኳን ለመንዳት ለማየት የምታሳሳ መኪና ከፊት ለፊቷ ቆማለች ሁሉም ልክ መኪናውን ሲያዩ ማሂ አይኗን ከመግለጧ በፊት በጩኸትና ጭብጨባ አንባረቁት ደንግጣ አይኗን ገለጠች ።

ሰው ለካ ደስታ ሲበዛበት ሰውነቱን ማዘዝ ይከብደዋል ማሂ ለመጮኸም ለመደሰትም አቅም አጣች እንዲሁ በቆመችበት እንባዋን ዝርግፍ አደረገችው የአባቷ ደረት ላይ ልጥፍ አለችና አባቴ አመሰግናለሁ የኔ ጀግና በቃ ከዚህ ውጪ ደስታዋን በእንባ ነበር የገለፀችው።
እውነት ለመናገር ጉዳዩ ለኔም እንግዳ ነበር ከሷ እኩል ነው ሰርፕራይዝ የሆንኩት።

ማሂ ቃላት እንዳጠሯት ግልፅ ነበር የመኪና ቁልፉን ተቀበለችና ለመመረቅ ወደ ውስጥ ገባች መንዳት ግን አልቻለችም እጇ እየተንቀጠቀጠ አልታዘዝ አላት ተመልሳ ወረደችና በድጋሜ አባቷን ጥብቅ አድርጋ አቀፈቻቸው ።

ብቻ ምሽቱ የማሂ ነበር ።
ቁጭ ብለን አይኗን ከቀለበቱ ላይ ሳትነቅል እጇን አቅፋ እንደተቀመጠች መሸላት
ፕሮግራሙ ሲጠናቀቅ ሁላችንም ወደቤት አመራን ማሂም መኪናዋን እየነዳች ለሁለት መኪና ተከፍለን ወደ ቤት ሄድን።

ቤት ስንደርስ ዛሬማ ከዚህ ሁላ ደስታ በቀላሉ መውጣት አልፈልግም ሌሊት እያወራን እየተዝናናን ነው ማንጋት ያለብን አለ አባቴ።

ሁላችንም ተስማማን ቤቱን ሌላ ድባብ ውስጥ አስገባነው ሁላችንንም ደስታ አስክሮን ነበር ።

በመሀል አቶ ሳሙኤል ጨዋታ አነሱ በቃ ከዛሬ ጀምሮ እናንተ ባልና ሚስት ናችሁ መፈራረም ብቻ በቂ ነው እርግጠኛ ነኝ ልጄ በድጋሜ ሰርግ እንዲደገስ ምትፈልግ አይመስለኝም ባይሆን የመጀመሪያ ልጃችሁን ውለዱና ክርስታናውን እንደሰርግ አድርጋችሁ መደገስ ትችላላችሁ አይመስላችሁም አሉ።

አባቴ ቆጣ ብሎ ኦኦኦ እንደዚህማ አይሆንም እኔ ሀዋሳ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ሰርግ ነው ምደግስላቸው የመጀመሪያ ልጄማ እንዲሁ በቀለበት ማሰር ብቻ ጋብቻ አይመሰርትም ወዳጄ ሳሙኤል አንተንም እረዳሀለሁ ግን ሀዋሳ ላይ መሆን ይችላል ሰርጉ ትልቁ ግን የናንተ ውሳኔ ነው ልጆች እናንተ ምን እያሰባችሁ ነው አለን።

እኔ :- ሰርጉ ትንሽ ይቆያል አሁን አይደገስም እንጂ መደገሱን አልጠላም ግን አሁን እኔም አራሴን በስራ ማጠነክርበት አባቴ አንተም ወደቀድሞ ገቢህ ምትመለስበትን እድል ምታመቻችበት ሰአት ነው አልኩት።

ማሂ ቀበል አለችኝና እኔም በሱ ሀሳብ እስማማለሁ ልክ ነው የፎቶ ፕሮግራምና ቀለል ያለ ድግስ ቢኖረን ባይ ነኝ እሱ እንዳለው ትንሽ ቆየት ብሎ መሆን ይችላል አለች።

ሁሉም በሀሳባችን ተስማሙና ምሽቱ ያማረና የደመቀ ሆኖ አለፈ::

ከቀለበቱ ቡሀላ እኔ ከቤተሰቦቼጋ ወደ ሀዋሳ ተመለስኩና ለትምህርት ማስረጃነት የቀረኝን 1 file ይዤ መጣሁ።


ስራዬን አጣጡፌ መስራት ጀመርኩ ከአቶ ሳሙኤልጋ ስራ ቡታ ጅንን ያልኩ የስራ ባልደረባቸው ከስራ ውጪ ጓደኛቸው አማካሪያቸው  እቤት ውስጥ ደሞ ልጃቸውና የልጃቸው ባል ሆኜ ህይወታችን ቀጠለ ።
ከማሂጋ እኔና አባቴ እንተኛበት የነበረውን ክፍል ለራሳችን ወስደን የሁለታችን ክፍል አደረግነው።

ማሂም ከስራዋ ጎን ለጎን ስለጎዳና ልጆች የሚያጠነጥነውን መፅሀፏን ፅፋ አጠናቀቀች ።

እኔም ገና ትምህርቱን ተምሬ ሳልጨርስ የድርጅቱን ስራ ጥንቅቅ አድርጌ አወኩት ማለት እችላለሁ ነገሮችን የመያዝ የመረዳት ችግር ስለሌለብኝ ለኔ ከባድ አልነበረም።

እህቴም የራሷን ሽፎን ቤት ከፍታ መስራት ጀምራለች።
አባቴ ወደቀድሞ ስራው ገቢው ተመልሷል እንኳን ለቤተሰቡ ለሰውም መትረፍ ሚችለውን አባቴን መልሼ አግኝቼዋለሁ።

ሰርጋችን ከ2 ወር ቡሀላ ሀዋሳ ላይ ይደገሳል ምክንያቱም ማሂ እርጉዝ ናት።

ምዕራፍ 1
     ተ
      ፈ
    ፀ
       መ


በቀጣዩ ምእራፍ እንገናኛለን

  ይ🀄️ላ🀄️ሉን
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8
https://t.me/+4dGFaH_mUnExZjg8

💝የዩቲዩ ገፃችን💝
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333
https://www.youtube.com/@Kezerareaction333

16.2k 0 45 95 539

ውድ የመልካም ልቦች ቤተሰቦች ነገ የፅጌሬዳ የመጨረሻ ክፍል ነገ ማታ ይጠናቀቃል እስከዛሬ የለቀቅኩላችሁን እንዴት ነበር ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ 👇👇👇

Показано 20 последних публикаций.