ጥያቄ :- ጌታችን በወንጌል "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም።" ዮሐ. 3:5 ያለው ምሳሌያዊ እንጂ ጥምቀትን አይደለም የሚሉ አሉ፦
መልስ
👉 ውሃና ከመንፈስ መወለድ የተባለው በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ መሆንንና ለመዳን የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያመለክት ነው። እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሮአዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አንችልም።
ሐዋርያትና ከሐዋርያት የተማሩ ቅዱሳን ሊቃውንት ያስተማሩት በጥምቀት ዳግም ልደት መንግስቱን መወረስ የሚያስችል ምስጢር እንደሆነ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጥምቀት መንግስተ ሰማያት የሚያስወርስ ምስጢር እንደሆነ ሲገልጽ "ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማሕተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግስተ ሰማያት ውጪ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" ተብሏልና።" [ትርጓሜ ፊልጵስዩስ
ክፍለ ትምሕርት 3]
ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምም "ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም፣ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ያን ጊዜም ደምና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃ ይጠመቁ ዘንድ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።..."።[ በእንተ ጥምቀት ትምሕርት 3 ቁ.10] ብሏል።"
👉 ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይዘው ውኃው የተባለው ጥምቀት ሳይሆን በተቃዋሚዎች ዘንድ አንዳንዶቹ ውኃው ምልክት (symbolic) ነው ሌሎቹ የእምነት ማጽኛ ነው ሌሎቹም የእግዚአብሔር ቃል ነው የእምነት መመስከሪያ [አንዳንዶቹም ውኃ የተባለው ምሳሌያዊ ሲሆን መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል ይላሉ።] በማለት ይተረጉማሉ።
ማስረጃ 1:-ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ መጽሐፉ ይህን አስመልክቶ "በተቃዋሚዎች ዘንድ ርስ በርሳቸው እንኳ ይህ ሁሉ የአረዳድ ልዩነት የተፈጠረው ግን ሁሉም አንብቦ መተርጎም ይችላል በሚል የተሳሳተ ትምህርታቸው የተነሳ ነው። ይህን የጻፈልን የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረው የቅዱስ ፖሊካርፕስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ሄሬኔዎስ "እኛ በኃጢአት ምክንያት አካላችን የተቆማመጠብን እንደመሆናችን የእግዚአብሔርን ስም በመጥራትና በተቀደሰው ውኃ በመጠመቅ ከክፉ በደሎቻችን ሁሉ እንነጻለን፤ አዲስ እንደተወለዱ ሕጻናትም በመንፈሳዊ ልደት ዳግመኛ እንወለዳለን ራሱ ጌታችንም እንዲህ ብሎ እንደተናገረ፦ "እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3:5 (ቅሬታት፣ 34)
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ፖሊካርፕስን ያስተማረው እንደዚህ ነበር። ቅዱስ ሄሬኔዎስም ከመምህሩ ከቅዱስ ፖሊካርፕስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረው ይህንኑ ነበር፣ በተግባር ያየውም እንደዚህ ነበር። ስለዚህ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ሆነ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ሁሉ የተረዱት ጌታችን በውኃ መጠመቅ ለዳግመኛ ልደትና መንግሥተ ሰማያት አስፈላጊ ነው ያለ መሆኑን ነው።በኒቂያውና በቁስጥንጥንያው የእምነት መግለጫ አንቀጽ ላይም "ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።" ተብሎ የተገለጸው ከእነርሱ በፊት ከነበሩ አባቶችና እነዚያም ከሐዋርያት፣ ሐዋርያት ደግሞ ከጌታ የተቀበሉት አተረጓጎምና አረዳድ ነው። ከዚህ የቤተ ክርስቲያናዊ አረዳድ የወጡና መጽሐፍ ቅዱስን በራሳችን መንገድ እንተረጉመዋለን የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር ይዘው ብቅ በማለት አንዳቸው ትክክለኛው ይኸኛው ነው፣ ሌላቸው ደግሞ እርሱ ሳይሆን እንደዚህ ነው እያሉ ሁሉም የራሳቸውን ግምት በሰዎች ላይ ለመጫን ይደክማሉ። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2. ገጽ 99)
ይቀጥላል...
✍ ተክለ ማርያም