ዱኒያ………………….
ዱኒያ ማለት ፈተና የበዛባት የውሸት አለም ነች! ዛሬ ተደስተህ
ነገ ታለቅሳለህ ....ዛሬ አግኝተህ ነገ ታጣለህ! ፈተናውን ሁሉ
አልፌ ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሻለሁ ብለህ ኡፎይ ስትልና የእረፍት
ኑሮ መኖር ስትጀምር ድንገት ሳታስበውየሰበሰብከው ሁሉ
ይበተናል። በሌላ በኩል ደግሞ....በቃ ከዚህ በኋላ ሁሉንም ነገር አላገኘውም ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ስትቀመጥ..ጀሊሉ ያላሰብከውን ነገር አምጥቶ ይሰጥህና ጨለማ የሆነው ኑሮህ በብርሀን ይደምቅና የቀዘቀዘው ቤትህ ይሞቅና በደስታ ያስፈነድቅሀል።
ብቻ ምን ልበልህ ዱኒያ ጤዛ ነች" ስታስከፋህም ሆነ ስታስደስትህ አልሃምዱሊላህ ብለህ ለጌታህ ምስጋና አቅርብ። ለዚች ብልጭልጭ አለም ቅንጣት ታክል ሳትጨነቅ የነገ የአኼራ ሂወትህ እንዲያምርልህ ወደ ጌታህ አልቅስ! ዱኒያ ጊዜያዊ መኖሪያ እንጂ ዘላለማዊ መኖሪያ አይደለችም። ብዙ አትድከምላት፣ ብዙ አታስብላት! ..ይልቅ ለአኼራህ
ድከም፣ ለአኼራህ አስብ፣ ለአኼራህ ተጨነቅ፣ ለአኼራህ
ስራ" እመነኝ!...ጭንቀትህ ለዱኒያ ሳይሆን ለአኼራ መሆን
ሲጀምር የውስጥ ሰላምና መረጋጋት ታገኛለህ።
[ማሊክ ኢብኑ ዲናር እንዲህ ይሉናል]
ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኼራ ያለህ
ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል! ለአኼራ ባለህ ሀሳብና
ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል!
ጭንቀትህና ሀሳብህ ለአኼራ ይሁን ዱኒያ ጠፊ ነች
አስተዉል በሰዉ ዘንድ መልካም ሆነህ ብትታይ ዘላቂ እንዳልሆነ እወቅ::
ነገር ግን የእዉነት መልካም ሁን ያኔ የእዉነት በሰዎች ዘንድ መልካም ነገር ይኖረኛርካል
ነገር ግን ለሰጡህ እይታ ወይም መልካም አስተሳሰብ ደንታ አይኑርህ ከሰዉ ክብርን አትጠብቅ:: ስራ ለሰሪዉ እሾህ ላጣሪዉ ይባል የለ ☺️
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·.
https://t.me/joinchat/AAAAAE6HtHNiEljTsdd57w •════•••🍃🌺🍃•••════•