አዳም ረታ : ኤግዚስቴንሻሊዝም እና አብዘርዲዝም
ክፍል አንድ
ይህ ኂሳዊ መጣጥፍ ኤግዚስቴንሻሊዝም ተብሎ በሚጠራው በዠን-ፖል ሳትረ እና አብዘርዲዝም ተብሎ በሚጠራው በአልበርት ካሙ ፍልስፍና መነፅር የአዳም ረታ የልብ ወለድ ድርሰቶችን የሚፈክር ነው፡፡ የአዳም ረታ የድርሰት ሥራዎችን ከኤግዚስቴንሻሊዝም ፍልስፍና አንጻር በመፈከር ረገድ ይህ የእኔ ሥራ የመጀመሪያ አይደለም፤ ሌሎች ሰዎችም በዉጭ ሀገር ቋንቋ ተመሳሳይ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ስማቸዉን ለመጥቀስ፡ ፀደይ ወንድሙ ዘ ኬዝ ኦፍ ኤግዚስተንስ ኢን ፍቅር እስከ መቃብር፣ ከአድማስ ባሻገር ኤንድ ግራጫ ቃጭሎች፡ ፍሮም ኤግዚስቴንሻሊስት ፐርስፔክቲቭ በሚል ርዕስ እ.አ.አ. 2007 ዓ.ም፣ አክሊሉ ደሳለኝ ኤግዚስቴንሻሊዝም ኢን ዘ ሴሌክትድ ክሬቲቭ ወርክስ ኦፍ አዳም ረታ በሚል ርዕስ እ.አ.አ. 2010 እና አዳም ረታ አዝ ኤ ሊትረሪ ኤግዚስቴንሻሊስት፡ ቴክስችዋል ኤንድ ዲስክሪፕቲቭ ክሪቲሲዝም በሚል ርዕስ እ.አ.አ. 2010 ዓ.ም፣ አረጋዊ ገ/ሚካኤል አን ኤግዚስቴንሻሊስት ሪዲንግ ኦፍ አዳም ረታስ ኖቭል መረቅ በሚል ርዕስ እ.አ.አ. 2017፡፡ ይህ ኂሳዊ መጣጥፍ ሙሉ በሙሉ ከላይ በጠቀስኳቸው አጥኝዎች ባልተዳሰሱ የአዳም ሥራዎች ላይ አትኩሮቱን ያደረገ ነዉ፡፡
አዳም ረታ ከሌሎች የሀገራችን ልብ ወለድ ደራሲያን በተለየ መልኩ የኤግዚስቴንሻሊዝም እና አብዘርዲዝም ፍልስፍና መሠረታዊ ሴማዎችን (themes) በጥልቀት የዳሰሰ ልብ ወለድ ደራሲ ነዉ፡፡ በመሆኑም፣ ደራሲዉን በልበ ሙሉነት ከኤግዚስቴንሻሊስት እና አብዘርዲሰት ልብ ወለድ ደራሲያን ጎራ መፈረጅ ይቻላል፡፡
አዳም ረታ በኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ የፈጠረ፣ በሕይወት ከሚገኙ የዓለማችን ታላላቅ ልብ ወለድ ደራሲያን መካከል አንዱ ሆኖ መጠራት የሚችል ደራሲ ነዉ፡፡ ደራሲዉ ለአራት አሥርት ዓመታት በዘለቀ የሥራ ዘመኑ በግሉ አራት ረጅም ልብ ወለዶችን ግራጫ ቃጭሎች (1997)፣ መረቅ (2007)፣ የስንብት ቀለማት (2008) እና አፍ (2010) እና ስድስት የአጫጭር ልብ ወለድ መድበሎችን ማሕሌት (1981)፣ አለንጋና ምስር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች (2001)፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ (2001)፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር እና ሌሎች አጫጭር ልብወለዶች (2002)፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ (2003)፣ ሕማማትና በገና እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች (2004) ለህትመት አብቅቷል፡፡ ከሌሎች እዉቅ ልብ ወለድ ጸሐፍት ጋር ደግሞ አባ ደፋር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች (1977)፣ ጭጋግና ጠል እና ሌሎች (1990)፣ አማሌሌ እና ሌሎችም (2009) እና አዲስ አበባ ኖይር (2012) የተሰኙ የአጫጭር ልብ ወለድ መድበሎችን ለህትመት አብቅቷል፡፡
አዳም ረታ በእኛ ሀገረ ልብ ወለድ ጠጠር ያለ ቁም ነገርና ፍልስፍናዊ ሐቲት በኪን ተኩሎ የሚቀርብበት ኪናዊ ድርሳን መሆኑን በገሀድ ካሳዩ የዘመናችን ጎምቱ ልብ ወለድ ደራሲያን መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ደራሲዉ በሀገሪቱ ሥነጽሑፍ እድገትም የአንበሳዉን ሚና ተጫዉቷል፡፡
ከላይ በመግቢያዬ እንደ ጠቀስኩት አዳም ረታ በፈጠራ ሥራዎቹ ዉስጥ በርካታ የኤግዚስቴንሻሊዝም እና አብዘርዲዝም ፍልስፍና ጽንሰ ዐሳቦችን በጥልቀት ዳስሷል፡፡ ደራሲዉ የኤግዚስቴንሻሊዝም እና የአብርዲዝም ፍልስፍና ዐቢይ ሴማዎችን የዳሰሰባቸዉ የልብ ወለድ ድርሰቶቹ አለንጋና ምስር እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ እና ከሰማይ የወረደ ፍርፍር እና ሌሎች አጫጭር ልብወለዶች ሲሆኑ በእነዚህ ሥራዎች ዉስጥ የተዳሰሱት ሴማዎች ደግሞ ፍፁማዊ አርነት (radical freedom)፣ ኃላፊነት (responsibility)፣ ጭንቀት (anguish)፣ ግብዝነት (bad faith)፣ ሐቀኝነት (authenticity)፣ ባይተዋርነት (abandonment) እና ወለፈንድ (absurdity) ናቸዉ፡፡ እነዚህ ሴማዎች በጥብቅ የተዛነቁ ናቸዉ፡፡
የኤግዚስቴንሻሊዝም እና የአብዘርዲዝም ሴማዎች በአዳም ረታ ድርሰቶች ዉስጥ
፩. ፍፁማዊ አርነት
ፍፁማዊ አርነት በሳትረ ኤግዚስቴንሻሊዝም ዉስጥ ትልቅ ሥፋራ የሚሰጠዉ ጽንሰ ዐሳብ ነዉ፡፡ ከሃያኛዉ ክፍለ ዘመን ታላላቅ የምዕራቡ ዓለም ፈላስፎች መካከል አንዱ የሆነዉ ሳትረም ከሁሉም የዓለማችን ፈላስፎች በላቀ ስለ ሰዉ ልጅ አርነት የተፈላሰፈ ፈላስፋ ነዉ፡፡ ለእሱ በሰዉ ልጅ ሕይወት ዉስጥ እጅግ የላቀ ዋጋ ያለዉ ነገር አርነት ነዉ (ሄርስችፊልድ፣ 1968)፡፡ በሳትረ ፍልስፍና ዉስጥ አፅንዖት የሚሰጠዉ የአርነት አይነት ተጨባጭ አርነት (practical freedom) ነዉ፡፡ ይህ አይነቱ አርነት ከሥነ ኑባሬያዊ አርነት (ontological freedom) የተለየና ገደብ (limit) ያለዉ ነዉ፡፡
አርነት የሳትረ የሥነ ኑባሬ ነባቢ አእምሮ (ontological theory) የማዕዘን ድንጋይ ነዉ፡፡ ይህ አርነት ፈፅሞ ሊሸሹት የማይችሉት የሰዉ ልጅ መገለጫ ባሕርይ (unescapable characteristics) ነዉ፡፡ ለሳትረ፣ ሰዉ መሆን ማለት ነፃ መሆን ማለት ነዉ፡፡ እንደ ሳትረ እሳቤ፣ አርነት የሚገደበዉ በራሱ በአርነት ብቻ ነዉ፡፡ በመሆኑም፣ የሰዉ ልጅ ከአርነት ቀንበር ነፃ መዉጣት አይችልም – ነፃ እንዲሆን ተረግሟልና፡፡
የሳትረ ሥነ ኑባሬ ነባቢ አእምሮ መነሻ ህልዉና (existence) የንጥረ ባሕርይ (essence) ወይም ማንነት ቀዳሚ ነዉ (existence precedes essence) የሚለዉ መፈክር ነዉ፡፡ ሳትረ የሰዉ ልጅ ህልዉና ከማንነቱ ቀዳሚ ነዉ የሚለዉን የሥነ ኑባሬ አስተምህሮቱን የገነባዉ ፈጣሪ በህልዉና የለም ብሎ ስለሚያምን ነዉ፡፡ እንደ እሱ እሳቤ፣ ፈጣሪ በህልዉና ባለመኖሩ ምክንያት፣ የሰዉ ልጅ እንደ ግዑዛን ፍጥረታት ቀድሞ የተሠራ ንጥረ ባሕርይ ወይም ተፈጥሮ የለዉም፡፡ የሰዉ ተፈጥሮ የሰዉ ልጅ ወደ መኖር ከመጣ በኋላ በራሱ ትልም መሠረት የሚሠራ ነዉ (ሳትረ፣ 2007)፡፡
እንደ ሳትረ (2007) እሳቤ፣ የሰዉ ልጅ ንጥረ ባሕርይ ወይም ማንነት ከህልዉናዉ ቀዳሚ ነዉ (essence precedes existence) የሚለዉ የኢማኑኤል ካንት እሳቤ የተሳሳተ አተያይ ነዉ፡፡ በመሆኑም፣ ይህን አተያይ አበክሮ ይቃረናል፡፡ የካንት እሳቤ የንጥረ ባሕርይን (essentialism) ዲበአካላዊ አስተምህሮ የሚሰብክ ነዉ፡፡ የንጥረ ባሕርይ አስተምህሮ ወሳኛዊነትን የሚሰብክ በመሆኑ ለአርነት ቦታ የለዉም፡፡ ሳትረ ከካንት በተቃራኒ፣ የሰዉ ልጅ ወደ ህልዉና ከተወረወረ በኋላ ማንነቱን እንደ አናጺ በትልሙ (projection) መሠረት የሚያንጽ ነፃ ፍጡር (subjectivity) እንጅ ልክ እንደ ዕደ ጥበባት እንደ ቢለዋ፣ ብዕር ወይም የእጅ ሰዓት ቋሚ ተፈጥሮን ይዞ ወደ ህልዉና የመጣ ፍጡር አይደለም ይለናል፡፡ ለሳትረ፣ የሰዉ ልጅ ወደ መኖር መጥቶ ማንነቱን ከመፍጠሩ በፊት ምንም (nothing/empity) ነበር፡፡