፩
#የንጉሥ_ተክለ_ሃይማኖት አያት የሆኑት የጎጃም ነጋሽ የደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ ወታደር የነበረው ፈረንሳዊው አርኖ ሚሼል ዳባዲ፤ የደጃዝማች ጎሹን ጀግንነትና አስተዋይነት፤ ሃይማኖት ጠበቃነታቸውን...፤ አማረኛ ቋንቋን ተምሮ በራሳቸው ቋንቋ እንስከሚያጠናቸውና እስከሚያወራቸው ድረስ ፍቅር፤ ወዳጅነትና ወንድምነት አሳይተውታል፡፡ #ከሰለጠነችዋ_ፈረንሳይ መጥቶ ከጎጃም ብዙ የተማረ መሆኑን ይነግረናል፡፡
፪
“የደጃች ጎሹ ቤት ቆይታዩ ለኔ ጠቅሞኛል፡፡ ብዙ የማላውቀው ነገር አውቂያለሁ፡፡ ብዙ ነገር ግልፅ ሆኖልኛል፡፡ በግቢያቸው የነገሠው ይህ ጥልቅ ክርስቲያናዊ ስሜት፣ ከየትኛው ጥንታዊ ሐረግ እንደሚመዘዙ በቅጡ ያልተረዳሁት #ሞት_አይፈሬነታቸውና ያ ግድየለሽነት የተላበሰ #ጀግንነታቸው ይገርመኝ ነበር፡፡ በሠፈር በአደባባያቸው የተነዛው የወንድነት ወኔና ጀግንነታቸው የበለጠ እንዳውቃቸው ጥረት እንዳደርግ ግድ አለኝ፡፡ በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የአገራቸውን ባህልና ወጋቸውን የበለጠ የማወቅ ጉጉቴ ጠነከረና የበለጠ እንድረዳቸው #የአማረኛ_ቋንቋ_መማር_ጀመርሁ፡፡
፫
#ከዚህ_ጀግና_የጎጃሜ_ጦር_ጎን_ተሰልፌ_የተካፈልሁበት ዘመቻ የእውቀት አድማሴን በማስፋት አዲስ የምርምርና የጥናት አቅጣጫ እንድይዝ አድርጎኛል፡፡..." ሲል ይጽፋል።
፬
ዳባዲ ከብዙ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአማረኛ ቋንቋን ትምህርቱን አጠናቆ፤ በአማረኛ መግባባት ጀምሯል፡፡
...ለእኒህ መስፍን ያለኝ ፍቅር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ #አሁንማ_አማረኛ_በደንብ_ስለምናገር የምጠራቸውም እንደ አገሩ ልማድ #ጌቶች› እያልሁ ነው፡፡...እኒህ ሉል አስተሳሰባቸው የደረጀና የውጭውንም ዓለም የማወቅና የመረዳት ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም እድሌን ከእድላቸው አስተሳስሬ አብሬአቸው ለመሆን ወሰንኩ፡፡...”
ሲል ዳባዲ ዕድሉን ከደጃዝማች ጎሹ ጋር ኑሮውን ከጎጃም አስተሳስሮ መኖሩን ቀጠለ።
የማወጋችሁም እንዲሁ ይቀጥልና
፭
አበረ አ. አዳሙ