Addis Admass


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций




የአሜሪካ ትምህርት ዲፓርትመንት 1 ሺ 300 ሰራተኞችን አባረረ

• 60 ዩኒቨርስቲዎች በመብት ጥሰት ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው



የአሜሪካ የትምህርት ዲፓርትመንት 1ሺ 300 ሰራተኞቹን በማባረር የሰው ሃይሉን በ50 በመቶ ገደማ መቀነሱን አስታወቀ፡፡ የትራምፕ አስተዳደር አዲሷ የትምህርት ዲፓርትመንት ሃላፊ ሊንዳ ማክማዎን፣ "የአሜሪካን የትምህርት ሥርዓት ወደ ታላቅነቱ ለመመለስ ጉልህ እርምጃ ነው" ብለውታል፤ የሰው ሃይል ቅነሳውን፡፡

የትምህርት ዲፓርትመንት ሃላፊዋ ስለጉዳዩ በx ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ "የሰው ሃይል ቅነሳው ለውጤታማነት፣ ለተጠያቂነትና ሃብቶች እጅጉን አስፈላጊ ወደሆኑበት ቦታ መመራታቸውን ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል፡- ለተማሪዎች፣ ለወላጆችና ለአስተማሪዎች።" ብለዋል፡፡

አክለውም፤ "የትጉህ የመንግሥት ሰራተኞችን ሥራና ለዲፓርትመንቱ ያበረከቱትን አስተዋፅዖ አደንቃለሁ። እርምጃው የአሜሪካ የትምህርት ሥርዓት ታላቅነትን ለመመለስ ጉልህ እርምጃ ነው።" ብለዋል፡፡


ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው፤ የትምህርት ዲፓርትንቱ በቅርቡ ካደረገው የሠራተኛ ቅነሳ በኋላ፣ የሰው ሃይሉ ከቀድሞው 4ሺ100 ሰራተኞች ወደ 50 በመቶ ገደማ የሚቀንስ ይሆናል፡፡ የዲፓርትመንቱ መረጃ እንደሚጠቁመው፤ ባለፉት 7 ሳምንታት ተጨማሪ 572 ሰራተኞች 'በፈቃደኝነት የመልቀቂያ እድሎችንና ጡረታን' ተቀብለዋል፡፡.


ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአሜሪካ ትምህርት ዲፓርትመንት፣ 60 የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች. የሲቪል መብት ጥሰት ወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው ስለመሆኑ ከትላንት በስቲያ ሰኞ አስታውቋል።


የትራምፕ አስተዳደር እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጦርነት በመቃወም የሚካሄዱ ሰልፎችን በአይሁድ ተማሪዎች ላይ ያነጣጠረ “ፀረ-ሴማዊ ትንኮሳና መድልዎ” ሲል ፈርጇል።


ትራምፕ 80ሺ ዶላር የሚያወጣ አዲስ ቴስላ ገዙ

ለኤለን መስክ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት ነው ተብሏል

በቴስላ ላይ አድማና ተቃውሞ የሚያደርጉትን ነቅፈዋል



የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ኩባንያ (ቴስላ) መሥራች ለሆነው ኢለን መስክ ድጋፋቸውን ለማሳየት፣ አዲስ ብራንድ ቴስላ እንደሚገዙ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ቃል ገብተው ነበር፡፡ በቃላቸው መሰረትም በትላንትናው ዕለት 80 ሺ ዶላር የሚያወጣ (10 ሚ. ብር ገደማ) አዲስ ቀይ ቴስላ ሸምተዋል፡፡

ትራምፕ በዋይት ሃውስ በርካታ ቴስላ መኪኖች ቀርበውላቸው ከመስክ ጋር ሆነው ሲያማርጡና መኪና ውስጥ እየገቡ ሲሞክሩ የታዩ ሲሆን፤ "ቴስላ ቆንጆ መኪና ነው" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

መስክ በትራምፕ አስተዳደር አዲስ የተቋቋመውን የመንግስት ውጤታማነት ዲፓርትመንት (DOGE) ለመምራት በፕሬዚዳንቱ መሾሙ የሚታወቅ ሲሆን፤ የመንግስት መ/ቤቶችን ወጪና ብክነት በመቀነስ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ሠራተኞችን መቀነስን ጨምሮ ሌሎች እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በርካታ "ግራ ዘመም" ዲሞክራቶች ግን በፕሬዚዳንት ትራምፕና በመስክ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ክፉኛ ይቃወሙታል፡፡


ትራምፕ የመስክ ኩባንያ የሚያመርተውን ቴስላ መኪና የገዙትም በአሜሪካ በቴስላ ተሽከርካሪዎች ላይ ተቃውሞ መነሳቱንና የኩባንያው የአክስዮን ዋጋ መቀነሱን ተከትሎ ነው።

ባለፈው ሳምንት ቁጥራቸው 350 ገደማ የሚሆኑ ተቃዋሚዎች፣ በኦሪጎን ፖርትላንድ በሚገኘው የቴስላ የኤሌክትሪክ መኪና መሸጫ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን፤ በተያዘው መጋቢት ወር መጀመሪያ ደግሞ ኒውዮርክ በሚገኘው የቴስላ መሸጫ ቢሮ ደጃፍ ላይ በተከሰተው አመጽ የተሞላበት ተቃውሞ ዘጠኝ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፡፡


የቢሊየነሩን ቴስላ ኩባንያ ለማክሰርና ለመጉዳት በአክራሪ ግራ ዘመም ፖለቲከኞች የሚደረገውን የአድማ ዘመቻ "ህገ ወጥ" ሲሉ ትራምፕ ነቅፈውታል፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ለመቀልበስና ለመስክ ድጋፋቸውን ለማሳየትም ነው 80 ሺ ዶላር አውጥተው "ብራንድ ኒው" ቴስላ የገዙት፡፡

አዲስ ለገዙት ቴስላ አውቶሞቢል ቼክ እንደሚጽፉ ለጋዜጠኞች የተናገሩት ትራምፕ፤ ምንም ዓይነት የዋጋ ቅናሽ እንዲደረግላቸው እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ መኪና እንዳያሽከረክሩ በመከልከላቸው የገዙትን ቴስላ ራሳቸው እንደማይነዱት የጠቆሙት ትራምፕ፤ ሠራተኞቻቸው እንዲጠቀሙበት በኋይት ሃውስ ውስጥ እንደሚተዉት ጠቁመዋል፡፡

እርሳቸው የቴስላን ምርት መግዛታቸው፣ የቴስላ መኪናን ሽያጭና የአክስዮን ዋጋውን እንደሚያሳድገውም ትራምፕ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

አሜሪካውያን ደጋፊዎቻቸውም፣ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና የሆነውን ቴስላን በመግዛት ለቢሊየነሩ ኤለን መስክ ድጋፋቸውን እንዲያሳዩ ፕሬዚዳንቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትራምፕ አዲስ ቴስላ እንደሚገዙ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ፣ ወደ ሥልጣን ከመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ የቴስላ የአክስዮን ዋጋ ትላንት ማክሰኞ፣ በ4 በመቶ ገደማ መጨመሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

"መስክ አሜሪካን ዳግም ታላቅ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት በዕውቀቱና ክህሎቱ በማገዙ ምክንያት ለምንድን ነው የሚቀጣው?" ሲሉ የሞገቱት ትራምፕ፤ "መስክ ለሀገሪቱ ድንቅ ሥራ እየሰራ ነው" ሲሉ አሞግሰውታል፡፡


ትራምፕ 80ሺ ዶላር የሚያወጣ አዲስ ቴስላ ገዙ


ፕሬዚዳንቱ በትላንትናው ዕለት ሰኞ በካሙኩንጂ የምርጫ ክልል ለነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር፤ "ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በናይሮቢ ወንዝ ማደስ ፕሮግራም ሥር ትልቅ ፕሮጀክት እየጀመርን ነው፡፡ የናይሮቢን ወንዝ ጽዱ ለማድረግ 60 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እንገነባለን" ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የከተማዋን ጽዳትና ንጽህና ብቻ አይደለም የሚያሻሻሽለው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ይልቁንም ከ30ሺ ለማያንሱ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡

"ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የናይሮቢን ወንዝ ወደ መዝናኛ ስፍራ እንደምንቀይር ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።" ብለዋል፤ ሩቶ በንግግራቸው፡፡


ፕሮጀክቱ የማህበረሰብ ፓርኮችን፣ የህዝብ አዳራሾችንና የመጸዳጃ ቤቶችን ልማት እንደሚያካትት የተገለጸ ሲሆን፤ በተጨማሪም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ግንኙነት ለማስተሳሰርና ለማቀላጠፍ 44 የእግረኛና የተሽከርካሪ ድልድዮች ይገነባሉ ተብሏል፡፡

የናይሮቢ ወንዝ እድሳት ፕሮግራም፤ የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል፣ ኢኮኖሚያዊ እድሎችን ለማጎልበትና የናይሮቢን ተፈጥሯዊ ከባቢ ለመመለስ ያለመ የመንግሥት ሰፊ የከተማ እድሳት ስትራቴጂ አካል መሆኑ ታውቋል፡፡


የወንዝ ዳርቻ ልማት በኬንያ ናይሮቢ?!



የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ የናይሮቢ የወንዝ ልማት ፕሮጀክትን በይፋ ማስጀመራቸው ተዘግቧል - የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ዓይነት ይመስላል፡፡ በዚህም የተነሳ ይመስላል አንዳንዶች ፕሬዚዳንቱ ከኢትዮጵያ አይተው ነው ፕሮጀክቱን የጀመሩት ለማለት ሰበብ የሆናቸው፡፡ ለዚህ ግን በቂ ማረጋገጫ ያለ አይመስልም፡፡ ቢያንስ ለጊዜው፡፡ ለነገሩ ከእኛም አይተው ወይም ቀድተው ቢሆን እሰየው ነው፡፡ ለአርአያነት በመብቃታችን ልንኮራ ነው የሚገባው፡፡


ወደ ዘገባው ስንመለስ፣ ግዙፉ የናይሮቢ የወንዝ ልማት ፕሮጀክት የ60 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ መስመር ዝርጋታና የ50 ሺ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን ያካትታል፡፡

ፕሬዚዳንት ሩቶ በትላንትናው ዕለት የናይሮቢ ወንዞች ልማት የኢንጂነሪንግ ሥራን ያስጀመሩ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ በእጅጉ የተበከሉትን የናይሮቢ ወንዞች ለማጽዳትና የከተማዋን ከባቢያዊ ሁኔታ ለማደስ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በናይሮቢ ወንዝ ዳርቻዎች በ388 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የማህበራዊ መኖሪያ ቤቶች እንደሚከናወንም ተጠቁሟል፡፡


"በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል"


በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል "በማንኛውም ቅፅበት ጦርነት ሊነሳ ይችላል" ሲሉ ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳይ አስጠነቀቁ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳም፤ "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በግልጽ የሚታይ መቃቃር አለ። የእኔ ስጋት ይህ ከቃላት አልፎ ወደ ጦርነት እንዳያድግ ነው" ብለዋል።

ጦርነቱ ለቀጠናውም ዳፋ እንደሚሆንም ጄኔራል ፃድቃን በእንግሊዝኛ ባስነበቡት ጽሑፍ አስታውቀዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል የሚደረግ ጦርነት በሁለቱም ወገኖች እንደሚባለው "አጭርና ወሳኝ" እንደማይሆን የገለጹት ጄኔራል ፃድቃን፤ ለቀጠናው አውዳሚ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።

"ጦርነቱ ሲያከትም አሁን የምናውቀው የአገራቱ ጂኦግራፊ ይለወጣል። በአፍሪካ ቀንድና ከቀይ ባሕር አሻግሮም ጉልህ የፖለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ያስከትላል" ብለዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደርና ዴሞክራታይዜሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ፣ ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳይ፣ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚቀሰቀሰው ጦርነት "የሱዳንና የቀይ ባሕር ደኅንነት ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ያሳድራል" ብለዋል።

"በጦርነቱ ማዕከላዊ የምትሆነው በደንብ የሠለጠነና ልምድ ያካበተ ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላት ትግራይ ናት" ሲሉም አክለዋል፡፡ (ቢቢሲ እንደዘገበው።)




የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዛሬ የሰጠው መግለጫ

" ... አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጸያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታይተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡

ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች፤ የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡

በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሰጡና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡

ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው፣ ከድርጊታቸው በመታረም፣ የሕግ የበላይነትን እንዲያስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡

በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት የሌላቸው ብቻ ሳይሆን፣ የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ፣ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝኃ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። "⬇️⬇️


የፊልሙ ቀረጻ እዚሁ አዲስ አበባ የተከናወነ ሲሆን፤ ከ65 በመቶ በላይ በሪፌንቲ ሞል ህንጻ ላይ መቀረጹ ተነግሯል፡፡

እንግዱ የተባለው ገጸባህርይ 7 ዓይነት ማንነቶችን ወይም ሰብዕናዎችን የያዘ መሆኑ ፊልሙን ለየት ያደርገዋል ያለው ደራሲና ዳይሬክተሩ ሳዳም ነጌሶ፤ የዚህን መነሻ ሃሳብ የወሰደው እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም ከተሰራው Split የተሰኘ የሆሊውድ አስፈሪ ትሪለር ፊልም መሆኑን ጠቁሟል፡፡

በፊልሙ ላይ እንግዱን ሆኖ የተወነው ጌዲዮን ፍቃዱ በሰጠው አስተያየት፤ "ስክሪፕቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳነበው ልሰራው የማልችለው ነበር የመሰለኝ፡፡ በአንደ ሰው ላይ ሰባትና ከዚያ በላይ ማንነቶችን ማሳየት ፈታኝ ነበር፡፡ እንደምንም ግን ተወጥቼዋለሁ" ብሏል፡፡

"እንግዱ" ፊልም በትላንትናው ዕለት በዓለም ሲኒማ ለአርቲስቶችና ለፊልሙ ቤተሰቦች ለዕይታ የበቃ ሲሆን፤ መጋቢት 5, 6 እና 7 እንዲሁም መጋቢት 12, 13 እና 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሁሉም ሲኒማ ቤቶች በይፋ እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡


"እንግዱ" የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ትሪለር ፊልም ሊመረቅ ነው

• 2.5 ሚሊዮን ብር ፈጅቷል ተብሏል

በአጠቃላይ 2.5 ሚሊዮን ብር እንደፈጀ የተነገረለት "እንግዱ" የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ትሪለር ይዘት ያለው አዲስ ፊልም፣ ከመጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡

በሳዳም ነጌሶ ተደርሶ ዳይሬክት የተደረገው ፊልሙ፤ በልባም ፒክቸርስ ተዘጋጅቶ በሳዳም ፊልም ፕሮዳክሽንና በሶሎዳ ስቱዲዮ መቅረቡ የተነገረ ሲሆን፤ የ1 ሰዓት ከ32 ደቂቃ እርዝማኔ ያለው ነው ተብሏል፡፡

ዛሬ ጠዋት ረፋዱ ላይ በፊልሙ ዙሪያ ፕሮዲዩሰሮቹና ተዋናዮቹ በሪፌንቲ ሞል (ቦሌ ቡልቡላ) ለሚዲያ ባለሙያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በጋራ ሰጥተዋል፡፡

"እንግዱ" የተሰኘውን ፊልም ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ8 ወር በላይ እንደፈጀ የተገለጸ ሲሆን፤ በፊልሙ ላይ ከ35 በላይ ታዋቂና አጃቢ ተዋናዮች እንደተሳተፉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከፊልሙ መሪ ተዋናዮች መካከል፡- አንጋፋው ተዋናይ ሰለሞን ሙሄ፣ ኤደን ገነት፣ ታዋቂው ኮሜዲያን ደረጄ ሀይሌ፣ ጌዲዮን ፍቃዱና አሰፋ ገ/ሚካኤል ይገኙበታል፡፡

⬇️⬇️


ታዋቂው ሙዚቀኛ አቶ አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡


ዩክሬን በሞስኮ ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ማድረሷን ሩሲያ አስታወቀች


አሜሪካ እና ዩክሬን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚያደርጉት የሰላም ንግግር በሚጠበቅበት ሰዓትምሽቱን ዩክሬን የድሮን ጥቃት በሞስኮ ላይ መፈፀሟን ሩሲያ ገልፃለች፡፡

ዩክሬን ወደ ሞስኮ ከሰነዘረቻቸው ድሮኖች መካከል 73 ድሮኖችን ሩሲያ መታ መጣሏን የሞስኮው ከንቲባ ሰርጌይ ሶቢያኒን ገልፀዋል፡፡

የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎም አራት በሞስኮ ከተማ የሚገኙ አየር መንገዶች በረራዎችን ሰርዘዋል፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ማምሻውን ዩክሬን የከፈተችው ጥቃት ከእስካሁኑ የከፋ ሲሆን በጥቃቱ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡






ሻል ሲል በታተመበት ቀን 4 ኪሎ ጆሊ ባር ለተወሰነ ደቂቃ ተከራይቼ ማንበብ ጀመርኩ። አከራዬ ሰውዬ ቦቸራ ይባል ነበር፣ ባለውለታዬ ነው፤ አንዳንዴ ሌላ ጊዜ ትከፍላለህ ይለኝና ያልፈኝ ነበር።

በጣም ሻል ሲል አዲስ አድማስን እየገዛሁ ማንበብ ጀመርኩ። አዲስ አድማስን ማንበብ ሌሎች የህይወት ድርጊቶቼን ደማቅ አድርጎልኛል።

ለምሳሌ፡- አንድ ቦታ፣ ቤት ወይም ከቤት ውጪ ለረጅም ሰዓት መቆየት አሰልቺ ነው። የሳምንቱን አዲስ አድማስ ይዤ በነበርኩበት ሁሉ ግን አስደሳች ጊዜ አሳልፍ ነበር።

የሳምንቱን መረጃ ይዤ ከሰዎች ጋር አፌን ሞልቼም እከራከር ነበር። ማሳረጊያ ማጣቀሻዬ "አዲስ አድማስ ላይ ተፅፏል" የሚል ነበር። አዲስ አድማስ፤ መፎከሪያችን ነበረች።

በጣም በጣም ሻል ሲል፣ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሰብሳቢ (Collector) ለመሆንም ታድዬ ነበር።

በኋላም ፅሁፍ መላክ ጀምሬ ተለማማጅ ዓምደኛ ለመሆንም ችዬአለሁ። እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ 3 ፅሁፎቼ በአዲስ አድማስ ታትመዋል። የበለጠ ፍቅር ያሳድራል።

ዛሬ ጊዜው ተቀይሮ ስልካችን ውስጥ ብንደበቅም፣ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የሁልጊዜ የልብ ወዳጃችን ናት።
እናመሰግናለን። መልካም 25ኛ ዓመት!

ብርሃኑ /Abt/


አዲስ አድማስ የዛሬ 25 ዓመት ስትጀመር---

አዲስ አድማስ የዛሬ 25 ዓመት ስትጀመር፣ እኔና እኩዮቼ ለዓቅመ ጋዜጣ ልንደርስ አካባቢ ነበር፡፡ እናም በሠርቶ አደር ጋዜጣ በተለጠፈ ግርግዳ የንባብ ክህሎትን ያዳበርን እኛ፣ እንዲሁም ቅዳሜን ከእኛ ጋር፣ እሁድን ላንድ አፍታ፣ ለወጣቶችና፡ የመሳሰሉትን የለገዳዲና የኢትዮጵያ ሬድዮ ፕሮግራሞች እየሰማን ላደግን እኛ፣ ከግል ጋዜጣና ሬድዮ ጋር በጥሩ የወጣትነት ዘመናችን ላይ ተገናኝተናል፤ 1990ዎቹ መጀመርያና አጋማሽ አካባቢ።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ኤፍ ኤም 97.1፣ በኋላም ሸገር ሬድዮ በተሻለ የመዝናኛና የዕውቀት ይዘት ወጣትነታችንን ያደመቁ የዘመን ቅርሶች ናቸው።

በግሌ አዲስ አድማስን ማንበብ የጀመርኩት 1996 ዓ.ም. ላይ ነው። ችስታ ስለነበርኩ ከታተመ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ያለፈው፣ ሌሎች ሰዎች ገዝተው አንብበው ሲጨርሱ በተውሶ አንብቤ በክብር እመልሳለሁ።

⬇️⬇️


በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈጠረው ልዩነት በእርቅ መፈታቱን ያደነቁ የተለያዩ ማህበራት ተወካዮች፤ ሌሎችም በክስ ሂደት ላይ ያሉ ማህበራት ችግራቸውን በእርቅ የሚፈቱበት ሁኔታ ይመቻች ዘንድ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡

ከኦክሎክ ሞተርስ ጋር የእርቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው የተገለጸው ከ60 ማህበራት ውስጥ 16 ያህሉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከ20 ዓመት በፊት የተመሰረተውና በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማራው ኦክሎክ ሞተርስ፤ በትግራይ መቀሌ ከተማና በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ ባስገነባቸው የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ ከ16 በላይ የተለያዩ ሞዴል ተገጣጣሚ ተሽከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት እየገጣጠመ ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡


በእርቅ ስምምነት ላይ የደረሱት የማህበራት ተወካዮች በሰጡት አስተያየት፤ "ወደ ህግ መሄድ ጊዜ የሚፈጅና አላስፈላጊ ወጪ የሚያስከትል በመሆኑ ችግራችንን በእርቅ ለመፍታት ተስማምተናል" ብለዋል፡፡

በኦክሎክና ማህበራቱ መካከል እርቅ ለማድረግ ተነሳሽነቱን የወሰዱት የሽማግሌዎቹ ተወካይ እንደገለጹት፤ መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት አላገኙም ነበር፡፡ "በተለይ ማህበራቱ ከኦክሎክ የተላክን መስሏቸው ዕርቁን አሻፈረን ብለው ነበር፤ ዓላማችን በሁለቱ መካከል ሰላምና እርቅ መፍጠር መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ነው የተስማሙት" ብለዋል፤ በሰጡት መግለጫ፡፡

የኦክሎክ ሞተርስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሣሁን በበኩላቸው፣ መጀመሪያ ላይ በማህበራቱ በኩል ስለድርጅቱ የተሳሳተ መረጃ ይሰራጭ እንደነበር አንስተዋል፡፡ ለአብነት ያህልም፡- ኦክሎክ ከማህበራቱ አባላት 1.2 ቢሊዮን ብር ሰብስቦ አንድም መኪና አላስመጣም የሚለው ነው ብለዋል፡፡ ሌላው ደግሞ በራሱ በድርጅቱ የተመዘገበ የመኪና መገጣጠሚያ ፈቃድ የለውም የሚል እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

"እውነቱ ግን ኦክሎክ ሞተርስ በመቀሌና በአዲስ አበባ በስሙ የተመዘገበ የመኪና መገጣጠሚያ ያለው ሲሆን፤ ከመኪና ፈላጊዎች የማህበራት አባላት የተሰበሰበው ገንዘብ 1.2 ቢሊዮን ብር ሳይሆን 41 ሚሊየን ብር ነው፡፡" ብለዋል፤ ሥራ አስኪያጁ፡፡

ኦክሎክ ከአባላቱ ገንዘብ ሰብስቦ ምንም መኪና አላመጣም የሚለውም ትክክል አይደለም ያሉት አቶ ታመነ ካሣሁን፤ የማህበሩ አባላት እስካሁን 800 ተሽከርካሪዎችን በካሽና በብድር ወስደዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሽማግሌዎቹ ቡድንም እኒህን የተሳሳቱ መረጃዎች በራሳቸው መንገድ አጣርተው፣ እውነታው ላይ መድረሳቸውን በራሳቸው አንደበት ያረጋገጡ ሲሆን፤ እርቅ ላይ የተደረሰውም ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡


ኦክሎክ ሞተርስና ማህበራቱ ችግራቸውን በእርቅ መፍታታቸውን አስታወቁ

ኦክሎክ ሞተርስና አንዳንድ ማህበራት በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት በእርቅ መፍታታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይሄ ይፋ የተደረገው ዛሬ ጠዋት ረፋድ ላይ የኦክሎክ ሞተርስ ሥራ አስኪያጅ፣ እንዲሁም የሽማግሌና የማህበራቱ ተወካዮች በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ባሰራጨው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ከጥቂት ወራት በፊት በተሳሳተ መረጃና ጉዳዩን በጥልቀት ካለመረዳት የተነሳ ከድርጅታችን ጋር የሽያጭ ውል በመግባት ተሽከርካሪዎችን ለመግዛት ተስማምተን በጋራ እየሰራን ካሉ በርካታ ማህበራት ውስጥ በተወሰኑ ማህበራትና ግለሰቦች አማካኝነት በድርጅቱ ላይ የስም ማጥፋት ተግባር ተፈፅሞ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ማህበራቱና አባላቱ ጉዳዩን በጥልቀት ከመረመሩና በጊዜው የተነገራቸውን መረጃዎች መለስ ብለው በማጣራትና ከድርጅታችን ጋር በመነጋገር፣ በሀገራችን ባህል ወግ መሰረት፣ ችግሩን በእርቅ ፈተን በመስማማት ወደ ትግበራ ስራ ገብተናል ብሏል፤ ድርጅቱ በመግለጫው።

ኦክሎክ ሞተርስና ማህበራቱን በሽምግልና ለማስታረቅ እልህ አስጨራሽ ጥረት መደረጉ የተገለጸ ሲሆን፤ የማታ ማታ ስምምነት ላይ መደረሱ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት ገንዘብ የሚፈልጉ ገንዘብ፣ መኪና የሚፈልጉ ገንዘብ እንዲወስዱ የተስማሙ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት 20 ያህል አባላት መኪና እንደሚረከቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ገንዘብ የሚፈልጉ ደግሞ በ45 ቀናት ውስጥ ገንዘባቸውን እንደሚወስዱ ተነግሯል፡፡

Показано 20 последних публикаций.