የወላጅ-መምህር ግንኙነት
የወላጅ - መምህር ግንኙነት ልጆች በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡የወላጅ-መምህር ግንኙነት የተማሪን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሁለት ወሳኝ ባለድርሻ አካላት መካከል የሚኖረውን ትብብር ለማጠናከር ከሚረዱ እስትራቴጂዎች አንዱ ወሳኙ ነው፡፡
ወላጆች ከልጆቻቸው መምህራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ስለሚኖረው ፋይዳ በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡ ከጥናቶቹ መረዳት እንደሚቻለው በልጆቻቸው ትምህርት ዙሪያ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉ ወላጆች በዚያው መጠን የልጆቻቸው ውጤትም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚሻሻል ነው፡፡
ውጤታማ የወላጅ - መምህርን ግንኙነት እንዲኖር መጀመሪያ መሆን ያለበት ከልጅዎ መምህር ጋር የሚኖርዎት ውይይት መረጃ መሰብሰብ ላይ ብቻ የሚገደብ አለመሆኑን ጠንቅቆ መረዳት ነው፡፡ የወላጅ-መምህር ግንኙነት ፋይዳው ልጅዎን በትምህርት ቤት ዙሪያ ሳለ የሚታይበትን የባህሪ ሁኔታ በሚመለከት መረጃ ከመሰብሰብም በላይ ነው፡፡
የወላጅ መምህር ግንኙነት ወላጆችና መምህራን አንድን ተማሪ አስመልክተው በት/ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ ምን ዓይነት የትምህርት ብቃት(capacity) እንዲሁም ባህሪ(behavior) እንዳለው ጠቅላላ መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው፡፡ አንድ ተማሪ በትምህርት ቤትም ሆነ በቤት ውስጥ ያለውን ጠንካራ ጎን እንዲሁም መስተካከል ያለበትን ድክመት በግልጽ ተወያይተው የጋራ መፍትሄ የሚያበጁበት ነው፡፡የወላጅ -መምህር ግንኙነት (parent-teacher communication):: ወላጆች ልጆቻቸው ቤት ውስጥ እንዴት ለትምህርታቸው ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ተገቢውን ምክርና ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የወላጅ-መምህር ግንኙነት የሚያበረክተው አስተዋፆም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡
ሆኖም ግን በርካታ ወላጆች ይህን ሁሉ በሚገባ የተረዱት አይመስልም፡፡ እነሱ መስራት የሚገባቸውን ተግባራት ሁሉ የትምህርት ቤት መምህራን ብቻቸውን እንዲወጧቸው ሲጠብቁ በተደጋጋሚ ይስተዋላል፡፡ ልጆች ቤት ውስጥ የሚደረግላቸው የቤተሰብ ድጋፍ እና ክትትል እጅግ ከፍ ያለ ሚና ሲዘነጉ ይስተዋላል፡፡
ስለ ልጆች አጠቃላይ ሁኔታ ከሌላው ሰው ቀድመው የሚረዱት ወላጆቻቸው ናቸው፡፡የልጆችን ባህሪ፣ የትምህርት አቀባበላቸውን እንዲሁም ያላቸውን ዝንባሌ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ጭምር ከመምህራን በፊት የሚያውቁት ወላጆች ናቸው፡፡ መምህራን የዚህን ያህል ርቀት ተጉዘው የተማሪውን የልብ ትርታ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
አንድ መምህር የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች ሁሉ በሚገባ ተረድቶ ተገቢ መፍትሄ ማበጀት እንዲህ ቀላል ስለማይሆን ወላጆች የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን (means of communication) በማመቻቸት የልጆቻቸውን ባህሪ፣ጠንካራ እና ደካማ ጎን ከልጆቻቸው መምህራን ጋር በመወያየት መምህሩ/ሯ ተማሪውን በሚገባ ተረድቶ የተሻለ ድጋፍ ያደርግለት ዘንድ ከነሱ የሚጠበቀውን ካደረጉ በርግጥም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ጥረት አድርገዋል ማለት ይቻላል፡፡
የወላጅ-መምህር የቅርብ ግንኙነት ልጆች በትምህርት ቤትም ሆነ ከዚያ ውጭ ባለ ህይወታቸው ስኬታማነትን ይጎናፀፉ ዘንድ በጣም እስፈላጊ ግብዓት መሆን ይችላል፡፡በወላጅ እና መምህራን መካከል በተማሪው ዙሪያ የሚመክር የግንኙነት መስመር ሲኖር ተማሪውም እሱን የላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ የሚንቀሳቀስ ጠንካራ የትብብር መድረክ መኖሩን እንዲረዳ ያስችለዋል፡፡
በተመሳሳይ ወላጆችና መምህራን በቅርብ እነደሚገናኙና እነደሚወያዩ የተረዱ ልጆች ብዙውን ጊዜ ከሌሎቹ የተሻለ ከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ በውጤታቸውም ብልጫ ይኖራቸዋል፡፡ከዚህም ባሻገር በትምርት ቤት ውስጥም በባህሪያቸው የተመሰገኑ ጎበዝ ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡
የወላጅ- መምህር ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ የተወሰኑትን እንመልከት፡-
1. በወላጆችና መምህራን መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች ዓላማቸው የልጅዎን የትምህርት ውጤት ማሻሻል መሆኑኑን ይረዱ፡፡ልጅዎ ነገ የተሻለ ዜጋ ሆኖ ይቀረጽ ዘንድ ዛሬ እየተደረገ ያለ ጥረት መሆኑን ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም፡፡
2. ስለ ልጅዎ የትምህርት ውጤት ሲነሳ ጠንካራ ጎን ላይ ብቻ ትኩረቶን ከማድረግ ተቆጥበው መሻሻል የሚገባውንም በመለየት መወያየት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡
3. ስለ ልጅዎ ለመወያየት ሁል ጊዜ ኮንፍረንስ ብቻ አይጠብቁ፡፡ከልጅዎ መምህር ጋር መገናኘትና መወያየት መደበኛ(regular) ተግባርዎ ያድርጉ፡፡ በዚህም ልጅዎ ላይ ጤናማ ያልሆነ ክስተት ቢፈጠርኳ በጊዜ ተረድተው አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
እነዚህን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ከልጅዎ መምህር ጋር ያልዎት ግንኙነት እየተጠናከረ ይመጣል፤ሁሌም የሚያልሙት የልጅዎ ስነምግባርም ሆነ የትምህርት ውጤት ከፍታም እውን መሆን ይችላል፡፡
ጠንካራ የወላጅ መመምህር ግንኙነት ለተማሪዎች ውጤታማነት